Logo
Getu Temesgen
ዜና እረፍት
#ethiopia | በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፖሊስና ኅብረተሰብ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢነት፣ በፕሮግራም መሪነት እና በመድረክ አስተዋዋቂነት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ለበርካታ ዓመታት በታታሪነት፣ በታማኝነትና በቅንነት ስታገለግል የነበረችው ኢንስፔክተር ኪያ ንጉሴ ቱሉ ባጋጠማት ህመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በ40 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

በመሆኑም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ዊንጌት ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት በመኮንኗ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቿ መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.