4 days ago
ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
· አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፦ የሰዎች ህመም የሚሰማቸው፣ ተስፋን በተግባር የሚተረጉሙት ስራ ፈጣሪ
“Life’s most persistent and urgent question is, 'What are you doing for others?'”
(የህይወት ዘወተር እና አጣዳፊው ጥያቄ፦ ‘ለሌሎች ሰዎች ምን እያደረግክ ነው?’ የሚለው ነው።)
— ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር
በማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን አይቶ ከመቆጨት ይልቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን መነሳት የትልልቅ ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው። በትውልደ ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ዘንድም የሚታየው ይህ ህያው እውነት ነው፤ ጥበብን፣ የበጎ አድራጎት መንፈስን እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን በማስተሳሰር በሀገራችን ልዩ የለውጥ አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
የተድላ አምቡላንስ መወለድ፦
የህይወት አድን አገልግሎት ራዕይ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በሀገራችን በህክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትልቅ ክፍተት በጥናት በመረዳት ነው "ተድላ አምቡላንስን" ወደ ስራ ያስገቡት። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት (ኦቲዝም) ያለባቸው፣ የዳያሊሲስ ህመምተኞች እና አረጋውያን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጋጥማቸውን የእንቅስቃሴ እና የትራንስፖርት እንግልት በመመልከት፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የድንገተኛ እና ድንገተኛ ያልሆነ የህክምና መጓጓዣ አገልግሎት እንዲመሰረት አድርገዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራ በላይ የማህበረሰብ አለኝታነትን መርሁ በማድረግ፦
· ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ፣
· በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ደረጃ አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ የተጋ፣
· ለሁሉ አቀፍ ተደራሽነትና ለዜጎች ክብር የቆመ ተቋም ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
“The best way to find yourself is to lose yourself in the service of others.”
(ራስህን ለማግኘት የሚቻለው የተሻለው መንገድ በሌሎች አገልግሎት ውስጥ ራስህን ስትሰጥ ነው።)
— ማሃትማ ጋንዲ
“ማንም የላት”፦
ጥበብ ለሰብአዊነት እና ለማህበራዊ ንቅናቄ
አቶ ሳሚ ከስራ ፈጣሪነታቸው ባሻገር፣ ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያላትን ትልቅ ሀይል በመረዳት ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ “ማንም የላት” የተሰኘውን ታሪካዊ የኅብረት ዜማ ፕሮዲዩስ አድርገዋል።
ይህ ስራ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ በቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) እንዲሁም በዳይሬክቲንግ ነፃዓለም አብዲ የተቃኘ ሲሆን፤ ድምፃውያን ማስተዋል እያዩ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሀና ግርማ እና አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) ድምፃቸውን ሰጥተውበታል። ከ50 በላይ የሙያ አጋሮች የተሳተፉበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ህብረተሰቡን ስሜታዊ ጉዳት ውስጥ ሳይከት በደማቅ ቅንብር የችግሩን አሳሳቢነትና የለውጥ አስፈላጊነት ያሳያል።
አካል ጉዳተኝነት የችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እና የትራንስፖርት እጥረት ዋናው ክፍተት መሆኑን ማሳወቅ ነው። “ማንም የላት” የሚለውን ስሜት “እኛ አለንላት!”በሚል አዎንታዊ ምላሽ ለመተካት ያለመ ማህበራዊ ንቅናቄ ነው።
አቶ ሳሚ ካህሳይ እና ድርጅታቸው ተድላ አምቡላንስ ቃላቸውን በተግባር በማስመስከር፤ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በተደረገ ስነ-ስርዓት፦የሙዚቃ ቪዲዮውን ገቢ፦ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የዩቲዩብ ቻናል ተለቆ የሚሰበሰበው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንዲሆን አስረክበው ነበር።
በርካታ ዊልቸሮች፣ ዘይት፣ ላርጎ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመቄዶንያ መስራች ለዶ/ር ቢንያም በለጠ በአካል አስረክበዋል።
ተድላ አምቡላንስ ለማንኛውም ሰዓት ለመቄዶንያ ማዕከል ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት በይፋ ቃል ገብተዋል።
የአቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ህልም በዋና ከተማው አዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በክልሎች፣ በገጠራማ አካባቢዎች እና ክፍለ ሀገራት የሚኖሩ፣ አማራጭ ያጡ ዜጎች ዘንድ ይሄው ዘመናዊና የተከበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲደርስ ከመንግስት እና ከተለያዩ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት አቅደዋል።
“No one has ever become poor by giving.”
(መስጠት ማንም ሰው ደሃ አያደርግም።)
— አን ፍራንክ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ በስራ ፈጠራቸው ሀገራዊ ክፍተትን የደፈኑ፣ በጥበብ ስራቸው የማህበረሰብ ህሊናን ያነቁ፣ በበጎ አድራጎታቸው ደግሞ የብዙዎችን እምባ ያበሱ የዘመናችን አርአያ ናቸው።
ተድላ አምቡላንስ “ሕይወትን ለማስቀጠል እየመጣን ነው!” በሚለው መሪ ቃሉ፣ የብዙዎችን ህይወት የመታደግ እና ተስፋ የመንዛት ታላቅ ሀገራዊ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ከ 27 ዓመታት ሰድት በኋላ አገር ቤት መጥተዋል። የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው "እናቴ፤ ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
የሀገር ጥሪን የመለሰ የዲያስፖራ ተሳትፎ፦ ህልምን በሀገር ላይ መተርጎም እንደነሳሚ ነው።
“Ask not what your country can do for you — ask what you can do for your country.”*
(ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን፣ እኔ ለሀገሬ ምን አደረግሁ ብለህ ጠይቅ።)
— ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካ) ያካበቱትን የሙያ ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ይዘው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በህክምናና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩት በምክንያት ነው። መንግስትና የሀገር ጥሪ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያቀረቡትን ጥሪ መሰረት በማድረግ፣ በውጭ ሀገር ያዩትን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥና ህልማቸውን በሀገራቸው ምድር ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።
ይህ እርምጃቸው ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፤ ሌሎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መጥተው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ትልቅ ማነቃቂያና መንገድ ጠራጊ አርአያ የሚሆን ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ ጀግንነት ነው!
ለሥራቸው፤ ለሰበአዊነታቸው እጅ እንነሳለን!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
"ሕይወትን ማዳን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያችን!"
– ተድላ አንቡላንስ
📞 ለአስቸኳይ ጥሪዎች 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት ዝግጁ
☎️ +251 985 585 888
📞 8558
የማኅበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ናቸው - ይከተሉን፦
Facebook: fb.com/Tedlaambulance
Instagram: instagram.com/tedlaambulance
Telegram: t.me/tedlaambulanceservice
TikTok: tiktok.com/tedlaambulance

1 month ago
«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው
• በእናት የተጻፈ በአይነቱ የመጀመሪያው እውነተኛ የህይወት ታሪክ ነው
#ethiopia | አዲስ አበባ — ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል ጋር ያሳለፈችውን ውጣ ውረድ፣ ጽናት፣ ተስፋ፣ እምነት፣ የእናትነት ፍቅርና ለልጅ የተከፈለ መስዋዕትነት ያጋራችበት «የማይናገረው ልዑል » የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ይመረቃል።
መጽሃፉ በኦቲዝም ዙሪያ በአንድ ወላጅ እናት ተጽፎ ለንባብ የበቃ በሀገራችን የመጀመሪያው መጽሐፍ ነው።
ይህን ልብ ሰቃይ እውነተኛ የህይወት ታሪክ በከፍተኛ ጥራት ለአንባብያን እንዲመች አድርጎ የአርትኦትና ቅንብር ስራውን የሰራው ታዋቂው ጋዜጠኛና አርታኢ መላኩ ብርሃኑ ነው። ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ ከመደበኛ የኮሚዩኒኬሽን ስራው ባሻገር በበጎ ፍቃድ በኦቲዝም ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እና ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆችና ወላጆቻቸው መብቶች በመታገል የሚታወቅ የኦቲዝም አድቮኬት ነው።ከዚህ ቀደምም ከህጻናት ክህምናና ኦቲዝም ስፔሻሊስት ዶክተር ሃዲያ ይማም ጋር “የኦቲዝም ምስጢሮች” በሚል ርዕስ የተሰናዳ መጽሃፍ በትብብር አዘጋጅቶ ለንባብ ያበቃ ባለሙያም ነው።
“የማይናገረው ልዑል” መጽሃፍ ባለታሪኳና ደራሲዋ መሰረት ክንፈ ሃይሌ ልጇ ልዑል ኦቲዝም እንዳለበት ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በሃገረ አሜሪካ የልጇን የመማርና በእንክብካቤ የመያዝ መብት ለማስከበር ያደረገችውን እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ፣ እንዲሁም እንደእናት ልጇን ለመርዳት የከፈለችውን መስዋዕትነትና የገጠሟትን ተስፋ አስቆራጭ የህይወት ምስቅልቅሎች የተወጣችበትን ጥንካሬ በልብ አንጠልጣይ ትረካ ያካፈለችበት መጽሃፍ ነው።
ባለፈው ጁን 6 ቀን 20206 በአሜሪካ ሲያትል ከተማ በታላቅ ድምቀት የተመረቀው ይህ መጽሃፍ ብዙዎች እንደመሰከሩት በመላው አለም ላሉና ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ለሚያሳድጉ ሚሊዮኖች እናቶች የሚያሳልፉትን ውጣውረድ የሞላበት ህይወት የሚያሳይ መስተዋት ነው።
የህ “የማይናገረው ልዑል” መጽሐፍ፤ በቅርቡ በቀረቡ የሚዲያ ዘገባዎች የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ በኦቲዝምና በወላጅነት ዙሪያ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል።
በመጪው ቅዳሜ በሚካሄደው በዚህ ልዩ የመጽሃፍ ምረቃ መድረክ ላይ በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ ታዋቂ የልዩ ፍላጎት ምሁራን፣ ወላጆች፣ በኢትዮጵያ በኦቲዝም ላይ የሚሰሩ ተቋማት መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የጥበብ ሰዎችና ሚዲያዎች እንደሚታደሙበትም ታውቋል ።
በዕለቱ በልዩ ፍላጎትና በኦቲዝም ምልከታዎች፣ በወላጅነት ስነልቡና፣ በመጽሃፉ ፋይዳ፣ በአመለካከት ለውጥ እና ኦቲዝምን በመቀበል በኩል ያሉ ክፍተቶችን ጨምሮ የመጽሐፉን ልብ ሰቃይ አንቀጾችና ዲስኩሮች የማንበብ ስነ-ስርዓት እንዲሁም ጥልቅ የመጽሐፍ ምልከታ (Review) የሚቀርብበት ልዩ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል።
የዕለቱ የመድረኩ ንጉስ ታዬ ወርቁ መርሃ ግብሩን በሙያዊ ብቃቱ ያሰናስለዋል።
ይህንን መርሃግብር ለመታደም ፍላጎቱ ላለው ማንኛውም ሰው መድረኩ ነጻና ክፍት መሆኑንም ደራሲዋና አርታኢው ተናግረዋል።
ለንባብ በሚጋብዝ ውበት የመጽሃፉን የውስጥ ገጽ አቀማመጥና አጠቃላይ የዲዛይን ስራውን ወጣት ዲዛይነር አክሊሉ ድልነሳ በጥበባዊ ብቃት ሰርቶታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ፣ ድሬ ቲዩብ፣ አርትስ ቲቪ፣ ፋና ቴሌቪዠን፣ አራዳ ኤፍኤም እና በርካታ ሚዲያዎች የመርሃግብሩ የሚዲያ አጋሮች ሲሆኑ የኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል በዚህ መጽሃፍ ምረቃ መርሃግብር ላይ የክብር አባል ሆኖ እንደሚታደምም ታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) በየዓመቱ የሚያዘጋጀው እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን የሚያገናኘው 43ኛው የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚኒሶታ ስቴት በከፍተኛ ድምቀት ተከፍቷል። የዘንድሮው ዝግጅት የባህል እና የስፖርት ትዕይንቶች ጎልተው የወጡበት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራዊ አንድነት እና የወገን ደራሽነት በጉልህ የታየበት ሆኖ ተገኝቷል።
እጅግ ማራኪ እና ደማቅ በነበረው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፣ የፌስቲቫሉ ዋነኛ ድምቀት የሆኑት 34ቱ የስፖርት ክለቦች በህዝቡ ፊት የክብር ሰልፍ በማድረግ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል። በተለይም ህጻናት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቀው ያቀረቡት ልዩ ትዕይንት የመድረኩን ድምቀት ከመጨመሩም በላይ የተመልካችን ስሜት የነካ ነበር። በዚሁ ደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የሚኒሶታ ስቴት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ምንም እንኳን የፌስቲቫሉ መንፈስ የደስታ እና የትውውቅ ቢሆንም፣ ታዳሚው በሀገር ቤት ያለውን ሀዘን አልዘነጋም። በቅርቡ በአርሲ ዞን ንጹሀን ወገኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ግድያ እና ጥቃት በማሰብ በስታዲየሙ የህሊና ጸሎት ተደርጓል። በስታዲየሙ ግዙፍ ስክሪን ላይም የተጎጂዎችን መታሰቢያ እና የአጋርነት መልዕክት የሚያንጸባርቁ ጽሁፎች ተላልፈዋል። የፌዴሬሽኑ አመራር ባደረገው ይፋዊ ንግግር፣ እነዚህን ጥቃት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም እና ለመርዳት ቃል የገባ ሲሆን፣ ፌዴሬሽኑ ሁልጊዜም ከወገኑ ጎን እንደሚቆም አረጋግጧል።
ለዘ-ሐበሻ አስተያየታቸውን የሰጡ የተለያዩ የፌስቲቫሉ ታዳሚዎች፣ ይህ ታላቅ ዝግጅት ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊ በሚገኝባት ሚኒሶታ መደረጉ እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ፌስቲቫሉ ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር በውጭ ሀገር ተወልደው ላደጉ ልጆቻቸው ትልቅ የባህል ትምህርት ቤት መሆኑን አስረድተዋል።
"ይህ ዝግጅት ልጆቻችን ማህበራዊ እሴቶቻቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ባህላዊ አለባበሳቸውን እና አጠቃላይ ማንነታቸውን በአካል አይተው እንዲማሩ ትልቅ በር የከፈተ ነው፤ የሀገር እና የወገን ናፍቆታችንንም የምንወጣበት ብቸኛው መድረካችን ነው" ሲሉ አንድ አስተያየት ሰጪ ስሜታቸውን አጋርተዋል። የፌስቲቫሉ ድባብ አዳዲስ ትውውቆች የሚፈጠሩበት እና ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት የሚንጸባረቅበት መሆኑንም ብዙዎች መስክረዋል።
የዘንድሮው ፌስቲቫል የስፖርት እና የባህል መድረክ ብቻ ሳይሆን እንደተለመደው የሰብዓዊነት እና የንግድ ልውውጥ ማዕከልም ሆኗል። በስታዲየሙ ዙሪያ በተዘጋጁት ድንኳኖች ውስጥ ከሀገር ቤት እና ከውጭ የመጡ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሰፊ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከላት፣ የኦቲዝም ድጋፍ ሰጪ ተቋማት፣ እና የአረጋውያን መጦሪያ ማዕከላት ይገኙበታል። እነዚህ ተቋማት ስራቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ አዳዲስ አባላትን እና ደጋፊዎችን በመመዝገብ ላይ ናቸው። በተጨማሪም ባህላዊ አልባሳት፣ የሀገር ባህል ምግቦች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ እና የተለያዩ ሸቀጦችን የሚያቀርቡ ነጋዴዎች (Vendors) ቦታውን ሞልተውታል።
እስከ መጪው ቅዳሜ ጁላይ 4 ድረስ በሚቆየው በዚህ ፌስቲቫል የፊታችን አርብ ልዩ "የኢትዮጵያ ቀን" (ሆኖ እንደሚከበር አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። በዚህ ዕለት የተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች በሚያቀርቡት የሙዚቃ እና የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ፌስቲቫሉ ይበልጥ ደምቆ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

2 months ago
እባካችሁ በኦቲዝም ስም አትነግዱ!
"ከወላጆች አይን እንባ በዝታለች፣ እግዚአብሄርም ያያል !"
( መላኩ ብርሃኑ)
ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም "እጅግ በጣም ውድ" ችግር ነው፡፡ ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ የወላጅን ሸክም ለማቅለል የተዘረጋ ምንም አይነት ስርዓት ስለሌለ ኦቲዝም ወደአንድ ቤት ሲመጣ የዚያ ቤት ህይወት ከመሰረቱ ይናጋል።
ልጆቹ የሙሉ ጊዜ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው ወላጅ እየሰራ ከሆነ ስራውን፣ እየተማረ ከሆነም ትምህርቱን ለመተው ይገደዳል። ይህ ደግሞ ለኦኮኖሚ ጫና፣ ለስነልቡና ቀውስ፣ ለማህበራዊ ግንኙነት መዳከምና አልፎ ተርፎም ለከባድ የጤና ቀውስ ይዳርጋል።
እስኪ አስቡት !
ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ልጅ ኦቲዝም እንዳለበት ለመመርመር (Diagnose) ለማድረግ የላብሯቶሪ ወጪውን ሳይጨምር ለህክምና ባለሙያው ብቻ የሚከፈል እስከ 20 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ይደርሳል።
እስከ 25 ሺህ ብር የሚደርስ የሃገር ውስጥ ምርመራን እንተወውና እንደ yeast overgrowth, heavy metal test, OAT test, FRAT test ውጪ ልኮ ለማሰራት ከ100 -200 ሺህ ብር በላይ ይጠየቃል።
ኦቲዝም ያላቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ ከአንጀታቸው ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አለባቸው ተብሎ ስለሚታመን 'ግሉቲን እና ኬዚን' የሚባሉ ንጥረነገሮች ካሏቸው ምግቦች ነጻ መሆን አለባቸው። እኛ ሃገር ደግሞ “ግሉቲን ፍሪ፣ ኬዚን ፍሪ” የሚባሉት የምግብ አይነቶች በአቅርቦት ደረጃ ውስንና በጣም ውድ ናቸው።ከሰንዴ ዘርና ከወተት መራቅ አለባቸው።
ለነሱ የሚሆን ወተት ለመስራት የሚጠቅም አንድ ኪሎ 'አልመንድ' የሚባል ፍሬ በትንሹ እስከ 5 ሺህ ብር ያስወጣል። ምግባቸው ውድ በሆነው የንጹህ የወይራ ዘይት ካልሆነ በቀር በሌላ መሰራት አይችልም። ስኳርና ሰውሰራሽ ማጣፈጫ ስለማይጠቀሙ በምትኩ ቴምር ለመግዛት በኪሎ ከ1500-3500 ብር ድረስ ይጠይቃል።
በዚህ ሳቢያ ልጆቹ የሚወስዱት ምግብ አይነት ስለሚያንስ እንዳይጎዱ ሲባል 'ሰፕሊመንት' ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ለነሱ የሚሆን የአሳ ዘይት ዋጋው ከ 12 ሺህ እስከ 35ሺህ ብር ይሸጣል። ለጥቂት ቀን ብቻ የሚሆን ቫይታሚን ዲ ደግሞ እስከ 5 ሺህ ብር ይሸጣል። አቅም ላለው ወላጅ እንኳን ሌሎች ሌሎች ተጨምረው የሰፕሊመንት ዋጋ ብቻ በወር ከ50 ሺህ ብር በላይ ያስወጣዋል።
በአጠቃላይ ለአንድ ኦቲዝም ላለበት ልጅ የሚወጣው የአንድ ወር የምግብ ወጪ አንድ ቤት ውስጥ ለሙሉ ቤተሰብ ከሚወጣው የቀለብ ወጪ ይበልጣል።
ኦቲዝም በሽታ ስላልሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ ለኦቲዝም የሚደረገው ድጋፍ በአብዛኛው የንግግር፣ የባህሪና የአካልና ሰውነት ቅንጅት ቴራፒ ነው፡፡ እዚህ ጋር ደግሞ ነጋዴዎቹ ተሰብስበዋል።
የሚችሉትም የማይችሉትም የሆነች ዛኒጋባ ተከራይተው እንሰጣለን ለሚሉት ተራፒ የሚያስከፍሉት ዋጋ በጣም ውድ ነው። ለአንድ ልጅ በወር 30 ሰዓት ቴራፒ ለመስጠት የሚከፈለው ገንዘብ የአንድ ልጅን የ6 ወር የግል ትምህርት ቤት ክፍያ ይበልጣል።
በቁጥር ጥቂት የሆኑት 'የልዩ ፍላጎት አካቶ' ያላቸው ትምህርት ቤቶች ክፍያ ዋጋ ደግሞ አይወራ። ታዋቂ ነን የሚሉት አንዳንዶቹ ትምህርት ቤቶች በወር እስከ 100 ሺህ ብር ያስከፍላሉ። በጨበጣ ያለምንም እውቀት ኦቲዝምን ቢዝነስ ያደረጉ አንዳንድ ነጋዴ ግለሰቦች የከፈቱት ትምህርት ቤት ደሞ አለ። አዳሪ ብለው እስከ 300ሺህ ብር በወር ያስከፍላሉ።
ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች እንኳን የማያስከፍሉትን አይነት ገንዘብ የሚያስከፍሉ አካቶ ት/ቤቶችና በኦቲዝም ስም የተቋቋሙ ተቋማት በጣም ብዙ ናቸው፡፡
በዚህ ላይ ልጁ ትምህርት ቤት ሲሄድም ሆነ ሲመለስ ሰርቪስ የሚጠቀም ከሆነ ወላጆች ለመጓጓዣው ከመደበኞቹ ህጻናት በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ፡፡
ይህን ይህን ሳይ በሃገሬ ተስፋ እቆርጣለሁ። ስርዓት ያልተዘረጋለት፣ ደንብና ህግ ያልወጣለት፣ በሙስና ሰንሰለት የተጨማለቀ ፣ ከኤንጂኦ እስከ ግለሰቦች ድረስ በኦቲዝም ስም የጦፈ ንግድ ሲካሄድ ሃይ ባይ የታጣበት ሃገር ላይ ነን ያለነው።
እንደኔ ጠለቅ ብሎ ለሚያየው እዚህ ዘርፍ ላይ ያለው መጨመላለቅና ብዝበዛ በጣም ይሰቀጥጣል፡፡
መቼም በጥቂቱ ካነሳሁት እውነት አንጻር በዚህ ዘመን የኑሮ ውድነት አንድ ወላጅ ቤት ኦቲዝም ሲደረብበት በስነልቡናም፣ በገንዘብም ምን ያህል ከባድ የህይወት መርግ እንደሚፈጥር ካሰባችሁት ይበቃል፡፡
እናንት 'ሞራል አልባ' ነጋዴዎች! እንዲህ ባለ 'ውድ' ችግር ላይ አይናችሁን አጥባችሁ ገንዘብ ለማጋበስና መሄጃ አጥቶ የተቸገረውን ወላጅ ለመበዝበዝ እንዴት ህሊናችሁ እሺ አላችሁ ግን? (በርግጥ ህሊና የላችሁም!)
በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡ይህ'ኮ ኢሰብአዊነት ነው። ወንጀል ነው። የሞራል ዝቅጠት ነው። ዛሬ ከኔ ባልተሻለ ጥቂት ንባብ ብቻ ተነስታችሁ ቤት ተከራይታችሁና ማዕከል ከፍታችሁ ‘ባለሙያ ነን’ እያላችሁ 'ቢዝነስ' የምትሰሩ ፣ ቲክቶኩንና ሶሻል ሚዲያውን ያጣበባችሁ ሰዎች ... ምናችሁን ነው የሚያማችሁ? ነገ'ኮ ይህ በህጋዊነት ሽፋን ያለቁጥጥር በተለቀቀ ሜዳ ላይ ስትፋንኑ የበደላችሁት ወላጅ እንባ ቤታችሁ ድረስ ይመጣል።
ኦቲዝም ላይ እንሰራለን ብላችሁ የምትደሰኩሩ ሃኪሞችምም፣ ሳይኮሎጂስቶችም፣ ቴራፒስቶችም፣ አካቶ ትምህርት ቤቶችም፣ማዕከላትም ቆም ብላችሁ ብታስቡ ይበጃችኋል!
ይህ ምርጫ ያጣ… ተመልካች ያጣ፣ ልጄ ቢሻሻልልኝ ብሎ እዚህም እዚያም መፍትሄ ፍለጋ የሚኳትን ወላጅ በኦቲዝም ምክንያት ጥሪቱን አሟጦ ሌሎች ልጆቹን የሚያሳድግበትና ቤቱን የሚመራበት ገንዘብ እስኪያጣ ድረስ ሲቸገር እናንተ አላግባብ በዘረፋችሁት ገንዘብ ሰላም፣ ጤናና የሰላም እንጀራ አይኖራችሁም ።
አያሳዝናችሁም ግን ? በናንተ የዋጋ ውድነትና ሳቢያ አቅም አጥቶ ዕድሜውን ሙሉ ‘ለልጄ ይህንን ሳላደርግለት’ ብሎ በጸጸት እንባ የሚታጠብ ወላጅ ግን አያሳዝናችሁም?
በዚህ ወላጅ ላይ ህይወት ላይ እየተጫወታችሁ እስከመቼ ራሳችሁን ታበለጽጋላችሁ ?
አንድ ቀን ግን ይመጣል! አላግባብ ለምትሰበስቡት ትርፍ አንድ ቀን እግዚአብሄር ይፈርድባችኋል ! የወላጅ እንባ በቤታችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይመጣል። ያኔ እናንተም ቁጭ ብላችሁ ታለቅሳላችሁ !
(ማሳሰቢያ ፤ ይህ ጽሁፍ በሃቅ የሚሰሩ፣ ልጆቹንና ወላጆችን ለመርዳት የሚለፉትን ባለሙያዎች አይመለከትም)
ሜርድ!!

3 months ago
በኢትዮጵያ የዲጂታል ኦቲዝም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ
#ethiopia | ልጆች ረጅም ሰዓት በስልክና በቪዲዮ ጌሞች ላይ ማሳለፋቸው፣ መናገር የሚችሉ ሆነው ከተወለዱ በኋላ አንደበታቸው እንዲያዝ እያደረገ መምጣቱ ተገልጿል።
ይህም በተፈጥሮ ከሚመጣ ኦቲዝም ባልተናነሰ ለዲጂታል ኦቲዝም እያጋለጣቸው መሆኑን ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሸዋጌጥ ክብረት ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ወላጆች ልጆቻቸው ሲያለቅሱ ወይም ሲያስቸግሩ ስልካቸውን ሰጥተው ዝም ማሰኘትን እንደ ዋነኛ አማራጭ መውሰዳቸው በትውልዱ ላይ ትልቅ አደጋ እየጋረጠ ይገኛልም ብለዋል።
ዲጂታል ኦቲዝም የሚባለው ስያሜ ልጆች ከስክሪን ጋር ረጅም ጊዜ በማጥፋታቸው ሳቢያ የሚፈጠር የተግባቦትና የማህበራዊ ግንኙነት ክፍተት መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ሸዋጌጥ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቷ ላይ እየተስተዋለ የመጣው የህፃናት ስልክ አጠቃቀም ጤነኛ ሆነው የተወለዱ ህፃናትን ሳይቀር መናገር አቅቷቸው ወደ ማህበራቸው እንዲመጡ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ስራ አስኪያጇ ልጆች ዝም ብለው ስልክ ላይ ጊዜ ካጠፉ አያወሩም፤ ቃላት ማውጣት ያለበት ላንቃቸውም ዝም እያለ ነው የሚሄደው ያሉ ሲሆን ፣ በሕክምና ሲረጋገጥም "ዲጂታል ኦቲዝም" ሆኖባቸው የተገኙ የብዙ ህፃናት ቁጥር በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍም ትልቁ ሥራ ወላጆች ላይ እንደሚጣልና በተለይም ህፃናት ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ባለው ከ1 እስከ 4 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

ልጆች ረጅም ሰዓት በስልክና በቪዲዮ ጌሞች ላይ ማሳለፋቸው፣ መናገር የሚችሉ ሆነው ከተወለዱ በኋላ አንደበታቸው እንዲያዝ እያደረገ መምጣቱ ተገልጿል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም ትልቁ ሥራ ወላጆች ላይ እንደሚጣልና በተለይም ህፃናት ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ባለው ከ1 እስከ 4 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
seledadotio

ሀና ሰይፉ

በዚህ መንገድ ተነግሯችሁ ፣ተረድታችሁትስ ታውቃላችሁ ?
(መላኩ ብርሃኑ)
ኦቲዝም ሰዎች እንደሚያስቡት ዝም ብሎ "ልዩ" መሆን ብቻ አይደለም! ዝም ብሎ ያልተለመደ "እንግዳ ፀባይ" ማሳየትም ብቻም አይደለም።
አንዳንዴ Autism ከዛም በላይ እጅግ የጠለቀ ነው:: ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ውስጣቸው እጅግ ጩኸት የበዛበት ነው። ያ ጩኸት አቅምን የሚፈታተንና መቼ ምን እንደሚፈጠር የማይታወቅበት፥ ስሜትን የሚያጥለቀልቅ ከባድ ማዕበል ነው።
እኛ በቀላሉ የምናልፋቸው ቀላል ነገሮች ነገሮች ለእነሱ የዕለት ተዕለት አድካሚ የትግል ሜዳዎች ናቸው።
ድምፆች ልክ እንደ አካላዊ ህመም ሲሰሟችሁ አስቡት። ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ ስትሰሙ ከምትሆኑት ነገር ጋር አነጻጽሩት።
እኛ ቸል የምንለው ‘ቲክ ቲክ’ የሚለው የሰዓት ድምጽ ፥ የመኪና ጡሩምባ፥ ወይም የሰዎች ጫጫታ ለእነሱ ልክ ጆሮ ላይ እንደሚጮህ ስፒከር አእምሮን ሲበጠብጠው ይታያችሁ። እንዲያ ነው የሚሰማቸው። የሚጮኸው የጁስ መፍጫ፣ የሚንጫጩ ሰዎች በነሱ አዕምሮ ውስጥ ሲደርሱ በብዙ መቶ እጥፍ ጨምረው ማብቂያ የሌለው ረብሻ ይፈጥራሉ። ከዚያ ለመሸሽ የሚገቡበት ሲጠፋቸው፣ ጆሯቸውን ሲይዙ ስታዩ በነሱ ቦታ ራሳችሁን ተመልከቱ።
ድምጽ ብቻ አይደለም፣ ብርሃን አይንን አጥበርብረው ህዋሳትን ሲረብሹ አስቡት። እኛ የለመድነው የፀሀይ ብርሃን ወይም የክፍላችን አምፑል አይንን እንደሚያቃጥል ፍም ሲሆንባቸው አስቧቸው። ልክ በጨለማ ቤት ውስጥ ድንገት ሃይለኛ ፓውዛ መብራት ሲለቀቅባችሁ እንደሚሰማችሁ ከባድ ህመም ። 💔
ሀሳቦች ከቃላት በላይ ዐዕምሮ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት ሲጋልቡ... ጭንቅላት ውስጥ ሺ ሀሳቦች በአንድ ጊዜ ሲጋጩ፥ ነገር ግን አንዱንም አውጥቶ ለመናገር አንደበት ሲታሰር አስቡት።
እናንተ በሰማችሁት መጥፎ ዜና ሳቢያ በከፍተኛ ጭንቀትና ግራ መጋባት ውስጥ ሆናችሁ ሁሉም ነገር ሲዞርባችሁ፣ ማሰብ ሲሳናችሁእንደምትሆኑት ለነርሱ ሁሉም ነገር የሚያልፈው በዚያ ሁኔታ ነው። ያኔ ማምለጥ ይፈልጋሉ፣ እረፍት አልባ ሩጫ፣ ያልተለመደ የሰውነት እንቅስቃሴ፣ ትርጉም አልባ ድምፆች ያወጣሉ። በዚህ የውስጥ ትርምሳቸውን ያረግባሉ።
የሚነኩት ነገር ልስላሴ ወይም ሻካራነት በቆዳቸው በኩል አልፎ ዐምሯቸው ውስጥ ህመም እንደሚፈጥርስ አስባችሁ ታውቃላችሁ? አይጥ የምትፈሩ ሰዎች አይጥ በእጃችሁ ብትነኩ የሚሰማችሁን ስሜት ትገምታላችሁ አይደል? ለነዚህ ልጆች አንዳንድ ነገሮች እንዲዚያ ናቸው፣ ይረብሻሉ።
ዓለም አንድም እንኳን ረጋ የማትል ስትሆን፣ እንደአውሎ ነፋስ ፍጥነት ሁሉም ነገር ውልብልብ ብሎ መያዝ ሲያስቸግር ፣ .. ሁሉም ነገር ወደዐዕምሮ በአንድ ጊዜ ሲመጣ፥ ዐዕምሮ መረጃዎችን አጣርቶ ቦታ ቦታ ለማስያዝ እጅግ ሲጨነቅ አስቡት። 💔
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ይሄ ሁሉ የውስጥ ጦርነትና የህዋሳት ጫና (Sensory Overload) በውስጣቸው እየተካሄደ ከዚያ ለማምለጥ ሲታገሉ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ፣ የሚሆኑትን ሁኔታ እንደረብሻ እንቆጥረዋለን። ... ምንም እንዳልተፈጠረ "ረጋ በል ! " "ዝም በል !" "ስርዓት ያዝ !" "አታስቸግር !" “አትቁነጥነጥ” ብለን አጭር ትዕዛዝ እንሰጣቸዋለን።
እስኪ ለአንድ ሰከንድ አስቡት... አንድ ኦቲዝም ያለበት ልጅ ይህንን ሁሉ እረፍት የሚያሳጣ ስሜት በውስጥ ተሸክሞ፥ ማዕበሉን ብቻውን እየታገለ፥ ግን ደግሞ ያንን ስሜት የሚገልፅበት ቃል ሲያጣ! … "እባካችሁ ተቸግሬያለሁ፣ ይህ ነገር አልተመቸኝም፣ ተዉኝ! " ማለት ሳይችል ሲቀር!
እንደዚህ ያሉ ልጆችን አብዝቶ መታገስ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው! ለእንዲህ አይነት ልጆች ደግነት በጣም ብዙ ትርጉም ያለው ለዚህ ነው! ❤️
ጭንቀታቸውን፣ ያንን ጭንቀት ለማምለጥ የሚያደርጉትን መቅበጥበጥ፣ መሯሯጥ፣ መግቢያ ሲያጡ የሚሆኑትን ነገር መረዳት ብዙ ነገራቸውን ይቀይርላቸዋል !
እኛ የምንሰጣቸው ትንሿ መረዳት፥ ለእነሱ ከሚያስጨንቃቸው ዓለም ለማምለጥ ትልቅ ማረፊያ ትሆናቸዋለች:: ❤️
ምክንያቱም ኦቲዝም እንደ ደም መፍሰስ ወይም እንደ ስብራት ጉዳቱ በአይን በማየት ሊገለጽ አይችልም ። በእነሱ ዘንድ እኛ ከምንገምተው በላይ እጅግ በጣም ጠልቆ የሚሰማ የዕለት ተዕለት የውስጥ ረብሻ አለ ❤️
ኦቲዝም በሽታ አይደለም!
ኦቲዝም ያለባቸው ሰዎች ዓለምን የሚረዱት፣ መረጃን የሚያስተናግዱት እና የሚማሩት ከተለመደው በተለየ (Neurodivergent) መንገድ ነው ።
ሲበሉ፣ ሲጫወቱ፣ ሲፈልጉ በአጠቃላይ አለምን የሚረዱበትም፣ ሚተረጉሙበትም፣ የሚኖሩበትም መንገድ እኛ ከለመድነው የተለየ ነው።
ለመረዳት መሞከርና እነሱን ማገዝ እንጂ ያለልምምድ እና ስልጠና በራሳቸው ተነስተው ወደኛ አለም እንዲመጡ መቆጣት፣ ማመናጨቅ፣ ባስ ሲልም መምታት ተገቢ አይደለም።
የእነሱ የተለየ መሆን የኛን ዓለም ይበልጥ ውብ ያደርጋታል!!
እባካችሁ ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች ከመፍረድ ይልቅ ይበልጥ ጠጋ ብለን ልንረዳቸው እንሞክር ።
ዛሬ ይህንን መልዕክት ማየት፥ መስማት እና መረዳት ያለበት አንድ ሰው ይኖራልና፣ ጽሁፉ ስለ ኦቲዝም ትንሹም ቢሆን ግንዛቤ ከሰጣችሁ Share በማድረግ ለሌሎችም አጋሩ።
(ማስታወሻ! ይህ ጽሁፍ እስካሁን ኦቲዝምን በተመለከተ ከተጻፉት ሁሉ የላቀ ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ጸሃፊውን ባላውቀውም ኢንተርኔት ላይ አግኝቼው አብራርቼና አሻሽዬ ጽፌዋለሁ። ወደናንተ ደርሶ የኔ ስሜት ተጋብቶባችሁ ከሆነ ተሳክቶልኛል)

Sponsored by
Surafel
3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚኒሶታ ትዊን ሲቲ እና አካባቢው በሚኖረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማህበረሰብ ውስጥ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የአእምሮ ጤና ችግር ለመቅረፍ ያለመ አዲስ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ ይፋ ተደረገ። የግንዛቤ እጥረትንና አጉል ባህላዊ ተፅዕኖዎችን ለመስበር ያለመው ይህ ንቅናቄ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የማህበረሰብ ተወካዮች በሚተባበሩበት ታስክ ፎርስ (ግብረ-ኃይል) የሚመራ ይሆናል።
የኢስት አፍሪካ ዌልነስ ኤንድ ሪሶርስ ሴንተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበባየሁ አበበ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ወጣቶች እና ቤተሰቦች በአእምሮ ጤና እክል ክፉኛ እየተጎዱ ይገኛሉ። "ባለፉት አንድና ሁለት ወራት ብቻ ራሳቸውን ያጠፉ ወደ አራት የሚጠጉ ወጣቶችን አጥተናል፤ ይህ ለማህበረሰባችን ትልቅ የልብ ስብራት ነው" ያሉት ዶ/ር አበባየሁ፣ ሌሎች በርካታ ወጣቶች ወደ አልኮልና አደንዛዥ እፅ እየገቡ መሆናቸውንና ብዙ ቤተሰቦችም የችግሩ ሰለባ ሆነው ዲስፋንክሽናል እየሆኑ መምጣታቸውን አስረድተዋል።
በሚኒሶታ የብራይት ኒኖ ኦቲዝም ሴንተር ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰብለ ለማ በበኩላቸው፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ስለ አእምሮ ጤና በቂ ግንዛቤ አለመኖሩ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሯ አክለውም፣ "ህብረተሰቡ ስለ ልብ በሽታ በግልጽ እንደሚያወራው ሁሉ ስለ አእምሮ ጤናም ያለ አንዳች ፍርሃት እንዲያወራ ማበረታታት እና ተጎጂዎችን ከማግለል ይልቅ ድጋፍ ሆነን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ዋነኛ አላማችን ነው" ብለዋል።
በአሜሪካ የግንቦት (May) ወር "የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር" መሆኑን ተከትሎ የተጀመረው ይህ ንቅናቄ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን መገለል (Stigma) እና እርዳታ ከመጠየቅ ወደ ኋላ የማለት ባህላዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት ይሰራል።
ይህ ማህበረሰቡን መሰረት ያደረገ ንቅናቄ፣ ፖለቲካን ያላካተተና ሁሉንም ማህበረሰብ በእኩልነት የሚያሳትፍ ነው። የፊታችን ሜይ 9 የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት እና የእስልምና የሃይማኖት ተቋማትን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያና የኤርትራ ማህበረሰቦችን በአንድነት በማሰባሰብ ሰፊ ውይይት እንደሚያካሂድ እና አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት አዘጋጆቹ ገልጸዋል። እስካሁንም ከማህበረሰቡ እጅግ አዎንታዊ የሆነ ምላሽ ማግኘታቸው ተጠቁሟል።
ዶ/ር አበባየሁ አበበ የንቅናቄውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ ቀጣይ እቅዶችን አብራርተዋል/ልል የአጭር ጊዜ እቅዶች... ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ግብረ-ኃይል በማቋቋም፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ወይም በሀምሌ መጀመሪያ ትልቅ 'የአእምሮ ጤና የእግር ጉዞ' (Mental Health Walk) ማካሄድ። በተጨማሪም ባለሙያዎች እና ተሞክሮ ያላቸው ሰዎች ምስክርነታቸውን የሚሰጡበት ሰፊ የፓናል ውይይት እና ወርክሾፕ ማዘጋጀት ሲሆን የረጅም ጊዜ እቅዶች ደግሞ ስለ አእምሮ ጤና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ አጫጭር መረጃዎችን በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች አዘጋጅቶ በየማህበረሰቡ መገልገያ ቦታዎች ማሰራጨት። እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች በአእምሮ ጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ልዩ ስልጠና መስጠት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ይህ እንቅስቃሴ፣ በስደት በሚኖረው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ነውር የሚቆጠረውን የአእምሮ ጤና ጉዳይ ወደ አደባባይ በማውጣት ትውልድን ለመታደግ የተወሰደ ትልቅ እና ወቅታዊ እርምጃ መሆኑ ታምኖበታል።

ልባም የኦቲዝም ማዕከል በወላይታ ሶዶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
#ethiopia | ማዕከሉ ከከተማ አስተዳደሩ ባገኘው ቦታ ላይ የቴራፒና የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት የህዝብና የባለሀብቶችን እገዛ ጠይቋል።
ወላይታ ሶዶ — በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ብቸኛ የሆነው "ልባም የኦቲዝም ማዕከል"፣ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች ካሏቸው ወላጆች ጋር በኦቲዝም ግንዛቤ ዙሪያ ያተኮረ ሰፊ የምክክርና የትምህርት መድረክ አካሄደ።
ማዕከሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኤፕሪል (ሚያዝያ) የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው በዚህ መድረክ፤ ስለ ኦቲዝም ምንነት፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ስላሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች እንዲሁም ልጆች ሊደረግላቸው ስለሚገባ የቴራፒና የእንክብካቤ አይነቶች ለወላጆች ዝርዝር ገለጻ ተደርጓል።
ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው ይህ ማዕከል፣ በወላይታ ሶዶና አካባቢው ለሚገኙ ኦቲዝም ያለባቸው ህጻናት ተስፋ ለመሆን አልሞ የተነሳ ተቋም ነው።
የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ለምለም ንጋቱ እንደገለጹት፤ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደርና ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ሀይለማሪያም ለማዕከሉ አገልግሎት መስጫ የሚሆን ቦታ በመፍቀድ ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።
ይሁን እንጂ የተፈቀደውን ስፍራ ለተሟላ አገልግሎት ምቹ አድርጎ ለመገንባትና ለማዘጋጀት የማዕከሉ አቅም ውሱን በመሆኑ ድጋፍ ፈልገው ወደማዕከሉ ለሚመጡ ወላጆችና ልጆቻቸው የሚፈለገውን አገልግሎት ለመስጠት እንቅፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡
ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት በከተማው መሀል ጊዜያዊ ቢሮ በመክፈት ስራ የጀመረ ሲሆን፣ አስፈላጊው ድጋፍ ተገኝቶ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆች እንደ የባህሪ ሕክምና (Behavioral Therapy)፣ የንግግር ሕክምና (Speech Therapy)፣የአካላዊ ቅንጅት ሕክምና (Occupational Therapy) ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ተዘጋጅቷል ብለዋል፦
ሲስተር ለምለም አክለውም፤ ብዙ እናቶች በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ሆነው ልጆቻቸውን ለማሳደግ እንደሚታገሉ በመጥቀስ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች፣ ባለሀብቶችና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በሰው ኃይል ማዕከሉን በመገንባትና ስራ በማስጀመር ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች በጋራ ከደገፍናቸው ከጥገኝነት የተላቀቀ ትርጉም ያለው ህይወት መምራት ይችላሉ” ብለዋል፡፡
ማዕከሉን ለመደገፍና ለበጎ አድራጎትና ተግባራት የሚከተሉትን የማዕከሉን የሂሳብ ቁጥሮች መጠቀም የሚቻል መሆኑንም በመግለጫቸው አካትተዋል፡፡
ልባም ኦቲዝም ማዕከል
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000727042222
• ብርሃን ባንክ፦ 2503240166663
• አድራሻ፦ ወላይታ ሶዶ፣ ሊጋባ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት (ሊጋባ ፔንሲዮን 1ኛ ፎቅ)
• ስልክ፦ 0912149990

"ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች የሀገር የፀረ-ሙስና ተስፋዎች ናቸው" ተባለ
#fastmereja I ሻምፒየንስ አካዳሚ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን "ኦቲዝም እና ሰብአዊነት እያንዳንዱ ሕይወት ዋጋ አለው!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ። አካዳሚው በአንድ ወቅት አካታች ትምህርትን (Inclusive Education) ለመተግበር በወሰደው ውሳኔ ምክንያት ወላጆች ልጆቻቸውን እስከ ማስወጣት የደረሰ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ያስታወሰ ሲሆን፣ ዛሬ ግን ለተማሪዎቹ ስኬትና ለአካታች ትምህርት ተምሳሌት መሆኑን አብስሯል።
በመድረኩ እንደተገለፀው አካዳሚው ከዓመታት በፊት "አካታች ትምህርት" እንግዳ በነበረበት ወቅት የጀመረው ጉዞ ፈታኝ ነበር ተብሏል። በተለይም ኦቲዝም ካለባቸው ልጆች ጋር ልጆቻችንን አብረን አናስተምርም በሚሉ ወላጆች ትምህርት ቤቱን ጥለው የመሄድ አስቸጋሪ ወቅት ቢኖርም፣ ተቋሙ በራዕዩ በመጽናቱ ዛሬ ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያሳየ ይገኛል ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተናን በብቃት አልፈው ወደ ቀጣይ ክፍል እንዲሸጋገሩ ተደርጓል። ተማሪዎቹ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ከፍተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቁ ሆነው ተገኝተዋል። መደበኛ ተማሪዎች ከልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ጋር አብረው በመኖራቸው ሌሎችን የመቀበልና የመደገፍ የህይወት ዘመን እሴት መቅሰማቸው ተጠቅሷል።
አካዳሚው አሁን ካለው ውጤት በመነሳት ወደፊት አካታች የሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ኮሌጅ የመመስረት ራዕይ እንዳለው ይፋ አድርጓል።
በመጨረሻም፣ ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በተፈጥሯቸው ታማኝ፣ ስርዓትን የሚከተሉና ለማጭበርበር የማይመቹ በመሆናቸው፣ ለሀገሪቱ የፀረ-ሙስና ትግል ትልቅ ተስፋዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ የተገለጸው ሃሳብ በዕለቱ ልዩ ትኩረት ስቧል። ማህበረሰቡም ከርህራሄ ባለፈ ወደ ተግባርና ወደ መከባበር እንዲሸጋገር ጥሪ ቀርቧል።

ሞዴል ናርዶስ አበበ የ2026 ተፅዕኖ ፈጣሪ በመባል በሁለት ዘርፎች አሸነፈች
ሞዴል ናርዶስ አበበ በጋና የሚገኘው "ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን" (The Street of Gold Foundation) ከ"ማይስ ጋና" (MICE Ghana) እና ከ"ስቱዋርት ኤም.ሲ.ኢ ሊሚትድ ኢንተርናሽናል" (Stuart MCE Limited International) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መርሃግብር የ 2026 ተፅዕኖ ፈጣሪ በመባል በሁለት ዘርፎች አሸንፋለች፡፡
ሞዴሊስቷ በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን ወክላ በአለም አቀፍ ደረጃ በሞዴሊንግ እና በተለያዩ ልዩ ስጦታዋች በምታገኛቸው ድጋፎች ዘር ፣ቀለም እና ሃይማኖት ሳትለይ ድጋፍ የሚሹ ኢትጵያዊያንን እየደገፈች ትገኛለች።
"በዚህም የተነሳ ላበረከተቻቸው መልካም ነገሮች በዝግጅቱ ላይ አሸናፊ ሆናለች፡፡ እንደዚህ አይነት ሽልማቶች የሚያስገኙት ደግሞ በሞዴሊንግ፣በጋዜጠኝነት፣በአርት እንዲሁ በሌሎች ዘርፎች ልዩ ስጦታ ያላቸው ከሆነ ነው።
በዚህም የተነሳ በእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ በመካተት የሽልማቱ እድለኛ ሆናለች። ልዩ ስጦታ ላላቸው ሴቶች የሽልማት መረሃ ግብሩን ያዘጋቸው ዘ ስትሪት ኦፍ ፋውንዴሽን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም 11ኛ አውደ ርዕይ አካሂዷል ።
ሞዴል ናርዶስ ምንም እንኳን የሁለት የጎልድ ዋንጫ ተሸላሚ ብትሆንም፣እሷን ጨምሮ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ተሸላሚ ሆነዋል። ሞዴል ናርዶስ ባለትዳር እና የአራት ልጆችና እናት ስትሆን በቲክታክ ገጿም ከ700 ሺህ በላይ ተከታዮችን ያፈራች ናት ።
ይህንን ፔጅ በመጠቀም የተለያዩ ድጋፎችን ከተከታዮቿ በመሰብሰብ አጋዥ ለሌላቸው ህፃናት፣ሴቶች፣አቅመ ደካሞች የበኩሏን አስተዊፅኦ እያደረገች ትገኛለች።
በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በመልካም ስራ ኢትዮጵያን ወክሎ የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኜት ከራስ ደስታ በላይ ለሃገር ያለው ኩራት ከፍተኛ መሆኑን ሞዴል ናርዶስ ተናግራለች።
በቅርቡም ኢትዮዮጵያዊያና ጀርመናዊ በጋራ ሆነው ሆፕ ፎር ኦል (Hop For All) የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት በእናቶችና በህፃናት ዘርፍ ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ተደርጎ በተዋቀረ ድርጅት አጋር ሆና እንደምትመጣም እና አጋዥ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊን ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቁማለች።
ሞዴል ናርዶስ ከ16 ዓመቷ ጀምራ ኢትዬጵያን በመወከል በሞዴሊስት ዘርፍ በመወዳደር ጥረት ስታዳረግ መቆየቷንም እንዲሁም እንደ ሚስ -አፍሪካ ባሉ ውድድሮች በአምስተኛ ደረጃነትን በመያዝ (Top Five ) በመውጣት አጠናቃለች።
በተጨማሪ በተለያዩ ድርጅቶች ላይ በፍቃደኝነት በመሳተፍ በካንሰር፣ በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎች እንደምታግዝ ተናግራለች።
በሌላ በኩል ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዲሽን ዋና መስራች ማጀስትይ ሮያል ፓንፎርድ እንደገፁት ከሆነ፣ ይህን አውደ ርዕይ ለማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያትም በተለዬ መልኩ ሴቶች በግብርናው፣ በበጎ ስነምግባር፣ በሞደሌንግ፣ በኢንዱስተሪያ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ያላቸው ተነሳሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ድግፉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም የተነሳ የዘንድሮው አውደ ርዕይ ላይ 6 ኢትዮጵያዊን ሴቶች ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ በድምሩ ለ20 ሴቶች የተለያዩ ሽልማቶችን ድርጅቱ ለማበረታት በማለም ድጋፍ ማድረጉን ግልጸዋል፡፡
በዚህ አውደ ረዕይ ላይ ከ120 በላይ የሚሆኑ በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅት ሃላፊዎችና ተስጦ ያላቸው አፍሪካዊን ተሳትፈዋል።

በኦቲዝም ላይ የምትሰሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ወይም ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች ያላችሁ ወላጆች በሙሉ !!
አንድ ጊዜ ስሙኝ
አውቃለሁ ፣ እዚህ ሃገር ብዙ የሚያማርሩ የትኩረት ማጣት ፈተናዎች አሉ። በተለይ ስለኦቲዝም መንግሥትን ጨምሮ የግል ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ፣ እንዲሁም ሚዲያዎች ብዙም ግድ አይሰጣቸውም ። የችግሩን ሥፋት እና የስርጭቱን መጠን ገና በውል አልተረዱትም። ህመሙ በራቸውን ካላንኳኳ የማይነቁ ብዙ ናቸዉ። ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉ እሙን ነው።
ነገር ግን በማስ ሚዲያ፣ በማሕበራዊ ሚዲያም ይሁን በምታገኙት መድረክ ሁሉ ስለ አቲዝም ለማውራት ዕድል ስታገኙ "ኦቲዝም እርግማን አይደለም " የሚል አንድ ቃል ብቻ በመደጋገም የኦቲዝምን ምንነት ለህብረተሰቡ ማስገንዘብ እንደማይቻል ተረዱ ።
ኮሚዩኒኬሽን የራሱ ሣይንስ አለዉ። ህዝቡን ላስተምር፣ ላስገንዝብ እያሉ መክሰስና መውቀስ በሰሚው ዘንድ መሰልቸትን ያመጣል :: ገና በአግባቡ ኮሚዩኒኬት ያልተደረገውን ኦቲዝምን የሚያክል ትልቅ ማህበራዊ ችግር ገና በጠዋቱ የተሰለቸ ርዕስ አታድርጉት።
አንድ ቃል ሲደጋገም ይቸካል ፣ ይሰለቻል።" አቲዝም እርግማን አይደለም " ማለት ብቻ ስለ አቲዝምን ማስረዳት አይደለም ። "እሺ ምንድነው ? "ለሚል ጥያቄ የተዘጋጀ መልስ ያስፈልጋል።
ኦቲዝም ላይ እየሠራችሁ ያላችሁም ሁኑ ወይም ወላጆች ስለ ኦቲዝም ለማውራት ከመነሣታችሁ በፊት ስለኦቲዝም በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል። ግልፅ ያለና ሣይንሳዊ መልስ መስጠት አለባችሁ ። ይህን ለማድረግም ኦቲዝምን በቅጡ ማጥናትና ዓለም የተሰማማበትን ትርጉሙን ማወቅ አለባችሁ።
ዛሬ እናንተ ዘወትር እንደመፈክር የምትደጋግሙት " ኦቲዝም እርግማን አይደለም" የሚል ቃል በሆነ ጊዜ እጅግ በጣም አስፈላጊ የማንቂያ ደወል ነበር። ገና ስለ ኦቲዝም ምንም ግንዛቤ ባልነበረበት ከዛሬ 10 ዓመታት በፊት ማንኛውም የዐዕምሮ ዕድገት ሁኔታ (neurodevelopmental condition ) ከመናፍስት እና ከእርግማን ጋር ይያያዝ ነበር። አሁንም ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ማለት አይቻልም።
ነገር ግን አሁን አሁን በአብዛኛው ይህ አመለካከት እየተቀየረ ነው። በተለይ "ኦቲዝም እርግማን ነዉ" የሚል ዕምነት ያለዉ ሰው ቍጥር አሁን አሁን ያን ያህል የገነነ አይደለም።
በኔ ዕምነት አሁን ህዝቡ ጋር ያለዉ ክፍተት እዚህ ሃሣብ ተሻግሮ ኦቲዝም ምን ማለት እንደሆነ አለመገንዘብና ኦቲዝም ራሱ ምን እንደሆነ አለማወቅ ነዉ። ስለዚህ የማያውቀውን ኦቲዝምን "እርግማን አይደለም" እያሉ ልክ ህዝቡ ሁሉ እርግማን አድርጐ እንደሚቆጥረዉ ማወጅ ትልቅ ፍረጃና ስህተት ነው።
ይህ "ኦቲዝም እርግማን አይደለም" የሚል ወቅቱን ያላገናዘበና ከድጋፍ ይልቅ ወዳልተፈለገ ሽሽትና ሥልቹነት የሚመራ ቃል "ስለኦቲዝም እንወቅ" በሚል መሪ ቃል መተካት አለበት።
ኦቲዝም የዕምሮ ዕድገት ሥርዓት መዛባት ( Neuro developmental disorder ) መሆኑ፣ ህመምም በሽታም አለመሆኑ፣ ከኛ በተለየ መንገድ ዓለምን በልዩነት መረዳት መሆኑ ፣ በራስ ዓለም ውስጥ መኖርና ነገሮችን ሁሉ በራስ መንገድ መረዳት መሆኑ ወዘተ ከነመገለጫውና ይህንን ለማሻሻል ከሚሠጠው ህክምና (ቴራፒ) ጋር አዛምዶ መግለፅ በቂ ነው።
ህዝብ እንዲያውቅ በር መክፈት እንጂ በተሰለቸ ቃል "ኤጭ!" ብሎ በር እንዲዘጋ ከማድረግ እንቆጠብ ። ይህ ሴንሴቲቭ የሆነ መረጃ ወደህዝብ የሚደርስበት መንገድ አሠልቺ እንዳይሆንና የምንፈልገው የአመለካከትም ይሁን የዕውቀት ክፍተት ሳይደፈን እንዳይቀር መጠንቀቅ አለብን።
ስታወሩ በዕውቀት ይሁን!
በርቱ!!

4 months ago
ምሉዕ ፋውንዴሽን 'እራት በምክንያት' በሚል ሀሣብ ፕሮግራም ሊያደርግ ነው
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ የሚሠራው ምሉዕ ፋውንዴሽን ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ሜ በሸራተን አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫና 'ራት በምክንያት' በሚል ስያሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ- ግብር ሊያደርግ ነው።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ትዕግሥት ኃይሉ የአለም የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በሚደረገው ልዩ ዝግጅት ትላልቅ ተቋማት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይታደማሉ ስትል በላከችው መግለጫ አስታውቃለች።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የምናከብራት ድምፃዊት ቤቲ ጂ ከስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች ታጅባ ሥራዋን ታቀርባለች።
አብረዋት የሚያጅቡትም የፒያሳ ትሪዬ ባንድ አባላት አንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ዳዊት አደራ ናቸው።
በወግ መፅሐፎቿ የምትታወቀው የሥነ- ፅሑፍ ባለሙያ ህይወት እምሻው ሥራዎቿን የምታቀርብ ሲሆን የመድረኩ አጋፋሪም መቲሸዋዬ ይልማ እንደሆነችም ታውቋል።
ምሉዕ ፋውንዴሽን፣ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ባላቸው ወላጆች በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና በአቶ ክንፈ ፅጌ ተመስርቶ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ነው።
ምሉዕ ፣ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የተቀናጀ ቴራፒ አገልግሎት፣ ተግባር ተኮር ስልጠና፣ የወላጆች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም ሁሉን አካታች ትምህርት ላይ በትኩረት የሚሠራ ፋውንዴሽን ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም በምሉዕ የተቀናጀ የቴራፒ ማዕከል 50 ልጆች የመሠረታዊ ቴራፒ አገልግሎት እንዲሁም እድሜያቸው ከ13-19 ላሉ ታዳጊዎች ደግሞ የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸውን በሥነልቦና እና በተግባር ተኮር ዕውቀት የማብቃት ሥራ እየሰራ ይገኛል፣ ከ300 በላይ የሚሆኑ ልጆች ደግሞ በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሰል ተግባርም ምሉዕ ፋውንዴሽን በስልጠና መርሃግብሩ ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም በትምህረት ቤቶች፣ በሕፃናት ማሳደጊያዎች፣ በሆስፒታሎች እና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ በዕውቀት የተደገፈ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በምሉዕ ቤተ-መጻሕፍት በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገለገሉበት ከ3ሺ 6መቶ በላይ ዘርፈብዙ መጻሕፍት ያሉ ሲሆን ከዚህም ጋር በማያያዝ የቤተ-መጻሕፍት አባልነትን ከአረንጓዴ ልማትና አካባቢን ከማስዋብ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ይህን በጎ አላማ ለማስቀጠል አብራችሁን እንድትቆሙ ሲል ፋውንዴሽኑ በገቢ ማሰባሰብ ሥራው ላይ እንዲሳተፉ፣ ለድርጅቶችም ሆነ በግል ቲኬቶችን ለሚገዙ ጥሪ አቅርቧል።
የዚህ መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባዎች አስተባባሪ ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

የጆይ ኦቲዝም የልህቀት ማዕከል የግንባታ ማጠናቀቂያ ገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቀረበ!
#fastmereja : ኒያ ፋውንዴሽን (ጆይ ኦቲዝም ማዕከል) ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የልህቀት ማዕከል የፊኒሺንግ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል መጠነ-ሰፊ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ገልጿል።
ፋውንዴሽኑ “ሚያዝያ ለኒያ ለእናት ጉያ'' በሚል መሪ ቃል ንቅናቄውን ይፋ ያደረገው፣ ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ፈጠራ ወርን በማስመልከት ነዉ የተዘጋጀዉ።
የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ እሌኒ ዳምጠው እንደገለጹት፤ በ4,824 ካሬ ሜትር ላይ እያረፈ ያለው የህንፃ ግንባታ የስኬሌተን ሥራ ተጠናቆ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ መሸጋገሩነሰ ገልፀዉ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት መቶ በመቶ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።
ይህ ለአንድ ወር የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከሚያዚያ 6 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከሉ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን፣ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ተገልጿል።
ማዕከሉ ህንፃውን 50 በመቶ ለማጠናቀቅ “100 ሺህ ልቦች" እንደሚያስፈልጉት የጠቀሰ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ደጋፊ 300 ብርቢለግስ የሚፈለገውን 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ግንባታውን ማጠናቀቅ እንደሚቻል ተመልክቷል፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅ በኦቲዝም እና በሌሎች የአእምሮ እድገት ውስንነቶች ላይ ለሚገኙ ዜጎች ዘመናዊ የሕክምና፣ የትምህርትና የማገገሚያ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
ለመርዳት የሚፈልጉ ወገኖች በቴሌብር 9616 ላይ "OK" ብለው በመላክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጭር የሒሳብ ቁጥር 2135 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ የሚሠራው ምሉዕ ፋውንዴሽን ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ሜ በሸራተን አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫና 'ራት በምክንያት' በሚል ስያሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ- ግብር ሊያደርግ ነው።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ትዕግሥት ኃይሉ የአለም የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በሚደረገው ልዩ ዝግጅት ትላልቅ ተቋማት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይታደማሉ ስትል በላከችው መግለጫ አስታውቃለች።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የምናከብራት ድምፃዊት ቤቲ ጂ ከስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች ታጅባ ሥራዋን ታቀርባለች።አብረዋት የሚያጅቡትም የፒያሳ ትሪዬ ባንድ አባላት አንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ዳዊት አደራ ናቸው ።በወግ መፅሐፎቿ የምትታወቀው የሥነ- ፅሑፍ ባለሙያ ህይወት እምሻው ሥራዎቿን የምታቀርብ ሲሆን የመድረኩ አጋፋሪም መቲሸዋዬ ይልማ እንደሆነችም ታውቋል።
ምሉዕ ፋውንዴሽን፣ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ባላቸው ወላጆች በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና በአቶ ክንፈ ፅጌ ተመስርቶ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ነው።
ምሉዕ ፣ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የተቀናጀ ቴራፒ አገልግሎት፣ ተግባር ተኮር ስልጠና፣ የወላጆች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም ሁሉን አካታች ትምህርት ላይ በትኩረት የሚሠራ ፋውንዴሽን ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም በምሉዕ የተቀናጀ የቴራፒ ማዕከል 50 ልጆች የመሠረታዊ ቴራፒ አገልግሎት እንዲሁም እድሜያቸው ከ13-19 ላሉ ታዳጊዎች ደግሞ የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸውን በሥነልቦና እና በተግባር ተኮር ዕውቀት የማብቃት ሥራ እየሰራ ይገኛል፣ ከ300 በላይ የሚሆኑ ልጆች ደግሞ በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሰል ተግባርም ምሉዕ ፋውንዴሽን በስልጠና መርሃግብሩ ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም በትምህረት ቤቶች፣ በሕፃናት ማሳደጊያዎች፣ በሆስፒታሎች እና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ በዕውቀት የተደገፈ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በምሉዕ ቤተ-መጻሕፍት በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገለገሉበት ከ3ሺ 6መቶ በላይ ዘርፈብዙ መጻሕፍት ያሉ ሲሆን ከዚህም ጋር በማያያዝ የቤተ-መጻሕፍት አባልነትን ከአረንጓዴ ልማትና አካባቢን ከማስዋብ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ይህን በጎ አላማ ለማስቀጠል አብራችሁን እንድትቆሙ ሲል ፋውንዴሽኑ በገቢ ማሰባሰብ ሥራው ላይ እንዲሳተፉ፣ ለድርጅቶችም ሆነ በግል ቲኬቶችን ለሚገዙ ጥሪ አቅርቧል።
የዚህ መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባዎች አስተባባሪ ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
4 months ago
"ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ያገባናል!"
- የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በኢትዮጵያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የኤፕሪል የኦቲዝም መቀበልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።
ሶሳይቲው በመጋቢት 28 ቀን 2026 ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዘንድሮው ወር "ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ስለኦቲዝም ያገባናል" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተዛባ አመለካከትን መቀየር፦
ኦቲዝም እርግማንም ሆነ የኃጢአት ውጤት አለመሆኑን ማህበረሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባና ሚዲያዎችም ትክክለኛውን መረጃ ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል።
የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጫና፦
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ወላጆች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫና ለማቃለል የማህበረሰቡ ድጋፍና መቀበል ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
የአገልግሎቶች እጥረት፦
እንደ ስፒች ቴራፒ፣ ኦኩፔሽናል ቴራፒ እና የባህሪ ማስተካከያ ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች ለልጆቹ ዕድገት ወሳኝ ቢሆኑም፣ በሀገሪቱ ያለው የማዕከላት እጥረት ትልቅ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
የሚዲያ ሚና፦
መገናኛ ብዙሃን ስለኦቲዝም ልዩ ልዩ ዘገባዎችን በመስራት፣ አዎንታዊ ምስል በመፍጠርና የመብት ጥሰቶችን በማንሳት ግንዛቤ የማስጨበጫ ወሩን እንዲያከብሩ ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲና የተለያዩ የኦቲዝም ማዕከላት (ጆይ ኦቲዝም፣ ነህምያ ኦቲዝም፣ የኛ ልጆች ኦቲዝም ማህበር እና ብሩህ ፋውንዴሽን) ወሩን ሙሉ ግንዛቤ በመፍጠርና ድጋፍ በመሰብሰብ ተግባራት ላይ እንደሚሰማሩ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣
እባክዎን በዚህ ስልክ ያነጋግሩ፡
መላኩ ብርሃኑ
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሲሳይቲ ቦርድ አባል
የኮሚዩኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ተጠሪ
ስልክ +251-911-403884
#getu #autismawareness #autismacceptancemonth #ethiopia #autismsocietyethiopia #inclusion #supportautism #addisababa #joyautismcenter #neahmiahautismcenter #ኦቲዝም #ግንዛቤ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምክር እናቱን የገደለው ወጣት
በሰሜን ዌልስ የሚኖር ትሪስታን ሮበርትስ የተባለ የ18 ዓመት ወጣት፣ በDeepSeek አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ እናቱን አንጄላ ሼሊስን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ ተሰማ።
ኦቲዝም ያለበትና ለረጅም ጊዜ በኢንተርኔት የጥላቻ ንግግሮች ተጽዕኖ ሥር የነበረው ወጣቱ፣ የሰው ሕይወት ለማጥፋት የሚረዱ መሳሪያዎችን AIን በመጠየቅ መረጃ ማግኘቱ ተገልጿል።
መጀመሪያ ላይ ቴክኖሎጂው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም፣ ወጣቱ "መጽሐፍ እየጻፍኩ ነው" በሚል ማታለያ መረጃውን ማግኘቱ ተረጋግጧል።
የግድያ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላም በማህበራዊ ሚዲያ (Discord) ላይ ድርጊቱን ሲያጋራ ቆይቷል።
ፍርድ ቤት የቀረበው ትሪስታን የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጥንቃቄና የኢንተርኔት ደህንነት ቁጥጥር አስፈላጊነት ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።

ምንጭ፦ Daily Mail

5 months ago
ዳውን ሲንድረም እና ኦቲዝም ይለያያሉ?
#ethiopia | ምንም እንኳን ዳውን ሲንድረም እና ኦቲዝም ሁለቱም የዕድገት ውስንነቶች ቢሆኑም፣ በመንስዔያቸውም ሆነ በባሕሪ መገለጫዎቻቸው እጅግ የተራራቁ መሆናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች አስታወቁ። እነዚህን ልዩነቶች ጠንቅቆ ማወቅ ለልጆቹ የሚደረገውን ድጋፍ ውጤታማ ለማድረግ ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ተመላክቷል።
አካላዊ መገለጫ እና መንስዔ
ዳውን ሲንድረም በቀጥታ ከዘረ-መል (ክሮሞዞም) መብዛት ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በተለይም በ21ኛው ክሮሞዞም ላይ በሚፈጠር ተጨማሪ ቅጂ ምክንያት ይከሰታል። ይህም እንደ፦
* ጠፍጣፋ የፊት ገጽታ፣
* የአንገት ማጠርና የጡንቻ መላላት፣
* እንዲሁም ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመርን የመሰሉ ግልጽ አካላዊ ምልክቶችን ያስከትላል።
በአንጻሩ የኦቲዝም መንስዔ በውል ባይታወቅም፣ ከአንጎል አወቃቀር እና ከነርቭ ሥርዓት ዕድገት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታመናል። ኦቲዝም እንደ ዳውን ሲንድረም ግልጽ የሆነ አካላዊ መልክ የሌለው በመሆኑ፣ ልጆቹ ከሌሎች እኩዮቻቸው ጋር ተመሳሳይ የሰውነት ገጽታ አላቸው።
ማኅበራዊ መስተጋብርና ተግባቦት
ሁለቱ ሁኔታዎች በማኅበራዊ ግንኙነት ረገድ ተቃራኒ ባሕሪን ያንጸባርቃሉ። ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች በአብዛኛው፦
* ተግባቢና ከሰዎች ጋር መገናኘት የሚወዱ፣
* የሌሎችን ስሜት የመረዳት ፍላጎት ያላቸውና ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ በቀላሉ የሚቀላቀሉ ናቸው።
በተቃራኒው ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ከፍተኛ ፈተና ይገጥማቸዋል። ዓይን ለአይን መገጣጠም የሚከብዳቸው ሲሆን፣ ስሜታቸውን የመግለጽ ውስንነት ስላለባቸው ብዙ ጊዜ ብቸኝነትን ይመርጣሉ። በመግባቢያ ክህሎትም ረገድ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ንግግር ቢዘገይባቸውም ለመግባባት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ፤ ኦቲዝም ያለባቸው ግን የቋንቋ ዕውቀት ቢኖራቸውም እንኳ ያንን ለግንኙነት የመጠቀም ችግር ሊታይባቸው ይችላል።
የትምህርት አቀባበልና ተሰጥዖ
በትምህርት ረገድ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች በዕይታ የታገዙ ትምህርቶችን የመረዳት የተሻለ ብቃት አላቸው። በሌላ በኩል ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በሒሳብ፣ በሥዕል ወይም በሙዚቃ ዘርፍ ልዩ ተሰጥዖ ሊኖራቸው ስለሚችል፣ የሚሰጣቸው ድጋፍ በባህሪ ለውጥ ሥልጠና ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።
አልፎ አልፎ ሁለቱም ሁኔታዎች በአንድ ልጅ ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ፣ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በትኩረት በመከታተል የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #downsyndrome #autismawareness #specialneeds #ethiopia #healtheducation #inclusiveeducation

"ዮም" የተሰኘ በኦቲዝም ዙሪያ የሚያጠነጥነው የእውነተኛ ታሪክ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በኦቲዝም ጥላ ስር ያለ ልጅ ያለው አባት ልጁን ለማሳደግ የሚያልፈበትን እውነተኛ የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርከውና "ዮም" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
በደራሲ ንሴብሖ ፍቅሬ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆች የሚገጥሟቸውን ማኅበራዊ ጫናዎችና ቤተሰቦቻቸው የሚጋፈጡትን መሪር የሕይወት ፈተና ከራሳቸው ገጠመኝ በመነሳት በዝርዝር ዳስሰዋል።
መጽሃፉ በዚህ የህይወት ሰልፍ ውስጥ ያሉ ልጆችን ህይወት በማሳየት ለበርካት ቤተሰቦች መንገድ መሪ መሆን የሚችል መሆኑ በምርቃት መድረኩ ተገልጿል፡፡
ደራሲው የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው "ዮም" የተባለ በኦቲዝም ጥላ ስር ያለ ልጅ አባት ሲሆኑ፣ ልጃቸው የሕይወት ዘመን ክትትልና ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ ሁኔታው በቤተሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ማለቂያ የሌለው መሆኑን በመጽሐፋቸው ገልጸዋል።
በመሆኑም ይህ ችግር በአንድ ቤተሰብ ጥረት ብቻ የሚፈታ ሳይሆን ማኅበረሰቡ፣ የግል ድርጅቶችና መንግሥት በጋራ ሊረባረቡበት እንደሚገባ ደራሲው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ትምህርት ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ተቀብለው ለማስተማርና ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ ደራሲ ንሴብሖ ከራሳቸው የሕይወት ተሞክሮ በመነሳት ጥሪ አቅርበዋል።
በ254 ገጾች ተቀንብቦ ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በዘርፉ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላትና ለሌሎች ወላጆችም የሞራል ጥንካሬ ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

"ዮም"፦
በኦቲዝም ጥላ ሥር ያለ የሕይወት ተጋድሎና የተስፋ ስንቅ! ✨
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ሥር የሚኖርን ልጅ የማሳደግ ፈተና፣ የወላጆች የሥነ-ልቦና ጫና እና ማህበራዊ መገለልን የሚዳስሰው "ዮም" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአባትነት ፍቅር፦
ደራሲው የ11 ዓመት የኦቲዝም ተማሪ የሆነው የዮም አባት ሲሆኑ፣ ልጃቸውን ለማሳደግ የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያጋጠማቸውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጫና በ254 ገጾች ተርከዋል።
የግንዛቤ ጥሪ፦
መጽሐፉ ማህበረሰቡ ለኦቲዝም ያለውን የተሳሳተ አመለካከት እንዲቀይርና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች በዕኩልነት እንዲቀበል ያሳስባል።
የመንግሥት ድርሻ፦
ለኦቲዝም ልዩ ትኩረት የሚሰጡ የትምህርትና የሕክምና ተቋማት እንዲስፋፉ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ መጽሐፍ ለወላጆች መመሪያ፣ ለባለሙያዎች ግብዓት፣ ለተስፋ ለቆረጡ ደግሞ የሞራል ስንቅ ነው!
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ካልታወቀላቸውና ድጋፍ ካላገኙ በቤታቸው ተዘግተው እንዲቀሩ ይገደዳሉ። "ዮም" ይህንን ግድግዳ ሰብሮ በመውጣት ለውጥ ለማምጣት የመጣ የብርሃን መጽሐፍ ነው።
#ኦቲዝም #ዮም #አዲስመጽሐፍ #ግንዛቤ #ኢትዮጵያ #autismawareness #yombook #ethiopia #inclusion #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📚 "ዮም"፦
በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆችና የወላጆቻቸው የጽናት መስታወት! ✨
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ሥር የሚኖሩ ልጆችን የማሳደግ ውጣ ውረድ፣ የወላጆች እሮሮ እና የጽናት ጉዞ እንደ መስታወት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል!
📖 ስለ መጽሐፉ፦
"ዮም" የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በአቶ ንሴብሆ ፍቅሬ እና በወ/ሮ ሳምራዊት ድንቁ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የራሳቸውን ልጅ በማሳደግ ሂደት ውስጥ ያለፉበትን ፈታኝ መንገድና መሰል ኢትዮጵያውያን ወላጆች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት ይዳስሳል።
🗓 የምረቃ ሥነ-ሥርዓት መርሃ-ግብር፦
ቀን፦ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ
ቦታ፦ ሀይሌ ግራንድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Haile Grand International Hotel)
🌟 የጥሪ መልዕክት፦
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ እርስዎም በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ በመገኘት በኦቲዝም ጥላ ሥር ላሉ ልጆችና ለሚደክሙ ወላጆቻቸው ድምፅ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
💰 ማሳሰቢያ፦
መጽሐፉ በዕለቱ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
"የኦቲዝም ልጆችን እና የወላጆቻቸውን የጽናት ጉዞ አብረን እንደግፍ!"
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ።
#ዮም #ኦቲዝም #autismawareness #ethiopia #booklaunch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
ዮም
ንሴብሖ ፍቅሬ
አሰናኝ፡፦ ጥላሁን ክፍሌ እርገጤ
#ethiopia | በተለያዩ ጊዜያት፣ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት፣ ከተለያዩ ቤተሰቦች የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ይወለዳሉ፡፡ በስልጣኔና በአመለካከት የበለጸጉት ሀገራትም ኦቲዝምን እንደአንድ የተፈጥሮ ጸጋ በመቀበል በኦቲዝም ጥላ ሥር ለመኖር ዓለማችንን የተቀላቀሉትን ህጻናት እንደየፍላጎታቸው ተንከባክበው በማሳደግ፣ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ለሚኖሩባት ዓለም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ይሠራሉ፡፡
በእርግጥ ከዓለማችን ሀገሮች ብዛት አንጻር በዚህ መልኩ የሚተጉት ጥቂት ናቸው፡፡ ቀላል ቁጥር የማይዘው የዓለማችን በተለይም የሀገራችን ማህበረሰብ ኦቲዝምን ድጋፍና እንክብካቤ የሚሻ እክል አድርጎ ከመቁጠር ይልቅ፣ “ርግማን” እንደሆነ አምኖ ይህንኑ የሚያስተጋባ ነው፡፡
የበኩር ልጃችን ዮም ንሴብሖ፣ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ እያደረግናቸው ያሉትን ወሰን አልባ ጥረቶች በመጽሐፍ ሰንዶ ለአንባቢያን ለማድረስ መነሳቱን ከተፈጠሩት ምክንያቶች አንዱም ኦቲዝምን በሚመለከት ያለን መረዳት ለማረቅ መሻት ነው፡፡
በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን የተዛባ አረዳድ በማስተካከል ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖር የሚረዳ ተጠቃሽ መጽሐፍ' ካበረከተው ከዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ጋር በዮም ምክንያት በተደጋጋሚ የመገናኘት አጋጣሚ ነበረኝ።
ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ዶክተር ዮናስ፣ “የሕይወት ተሞክሮህ በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለአንባቢ ቢቀርብ ብዙ ነገር ሊያስተምርይችላል" በሚል የሰነዘረው አስተያየት ልቤን ሰቅዞ ይዞት፣ ለረጅም ጊዜ ሳስብበት ቆየሁ:: የዶክተር ዮናስ ሃሳብ በልቤ ውስጥ ብቻ አልቀረም:: ከወዳጄ እና አብሮ አድጌ ጥላሁን ክፍሌ ጋር በመሆን ይህንን በእጃችሁ ላይ የሚገኘው መጽሐፍ እንዲወለድ ሆነ፡፡ በእርግጥም ምጡ ቀላል አልነበረም!
ከጥላሁን ጋር መጽሐፉን ለማዘጋጀት በምንተጋበት ጊዜ፣ እጅግ የሚወዳቸውና የሚሳሳላቸው እናቱ ወ/ሮ ጥሩወርቅ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ፡፡ በዚህ ሁኔታ የመጽሐፉን ዝግጅት ማስቀጠል፣ ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ እናቱን ለሚያስታምመው ጥላሁን ከባድ ነበርና፣ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቋረጥ ሆነ:: ሆኖም የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና፣ ለአምስት ወራት ያህል በሕክምና ሲረዱ የቆዩት እናቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ፡፡ ጥላሁን ክፍሌን የሚያውቅ ማንም ሰው እናቱን ያውቃል፧ ሁለቱን የሚያውቅ ደግሞ በመካከላቸው ያለውን የተለየ ፍቅር ያውቃል:: ያን ጊዜ፣ ጥላሁን የቀድሞው ጥንካሬ እና ሞራል ኖሮት ይህን ሥራ እንጨርሰዋለን
ምክንያት አለው ብዬ ራሴን አሳመንኩ። እንዴት ይበረታ ይሆን? እያልኩ ብጨነቅም ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና አጽናኝ መላእኩን ልኮ እኒያን ጥቋቁር የሐዘን ቀናት በጸጋው አሳለፋቸው:: ብርቱው ባለተሰጥኦ ጥላሁንም በሚያስደንቅ ትጋትና ብርታት መጽሐፉን አጠናቆ እነሆኝ አለኝ፡
ባሳለፍኩት የሕይወት መንገድ ያጋጠሙኝን የደስታም ሆነ የሐዘን፣ የከፍታም ሆነ የዝቅታ፣ የስኬትም ሆነ የመፈተን ውጣ ውረዶችን በዚህ መጽሐፍ ለማጋራት ሞክሬአለሁ፡፡ በተለይም ልጃችን ዮም ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ መፍትሔና ፈውስ ፍለጋ፣ የወጣን የወረድንባቸው ጎዳናዎች፣ ያንኳኳናቸው ደጆች፣ የገፋናቸው የመከፋትና የመፈተን ወራት እና ለዐይን ጥቅሻ ዕድሜ እንኳን ከጎናችን ባልተለየንና ይልቁንም ከፊታችን ይቀድም በነበረው እግዚአብሔር የቻልናቸውን ስኬቶች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታነባላችሁ፡፡
ከሕይወት ልምዴ ከተወሰደ ቀጥተኛ ተሞክሮ በተጨማሪ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከንባብ እና በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ካላቸው ወላጆችም ጋርበነበረኝ ማኅበራዊ ግንኙነቶች የተረዳኋቸውን ግንዛቤዎች በመጽሐፉ ለማካተት ሞክሪያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኦቲዝምን በተመለከተ ህብረተሰባችን ያለው ግንዛቤ በአብዛኛው የተዛባ ነው፡፡ ይህም ወላጆች/አሳዳጊዎች ሊሻሻል በሚችለው በዚህ የአእምሮ ዕድገት እክል የተጠቁ ልጆቻቸውን ለማገዝ የሚችሉትን እንዳያደርጉ፣ በዚህም የእነሱና የልጆቻቸው ስቃይ ቀጣይና ማብቂያ የሌለው እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይህ መጽሐፍ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ላላቸው ወላጆች እና በኦቲዝም ሳቢያ የሚፈጠሩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም ለመላው ማኅበረሰባችን የተሻለ ግንዛቤን በማስጨበጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡
መጽሀፉ በአራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ ዮም ከመወለዱ በፊት የነበረኝን ህይወት በመጠኑም ቢሆን የሚያስቃኝ ነው:: ሁለተኛው ምዕራፍ የመጽሃፉ ዋና አስኳል ሲሆን ይህም ዮም ከተወለደ ጀምሮ ይህ መጽሀፍ እስኪዘጋጅ ድረስ የተኖረውን ዋና ዋና የህይወት ክፍል ይዳስሳል:: ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ልጆቻቸው በኦቲዝም የተጠቁ እና በእኔ ማህበራዊ ህይወት ዙሪያ የነበሩ ወላጆች ቅንጫቢ ታሪኮች ስብስብ ነው:: በመጨረሻው ምዕራፍ ከእኔ የህይወት ልምድ እና ትዝብት በተጨማሪ በኦቲዝም ዙሪያ ከተለያዩ ምንጮች የቃረምኳቸው ጠቃሚ እውነታዎች ተገልፀዋል:: በእኔ እና በልጄ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ለበጎ አላማና ተግባር የተዘጋጀውን ይህን መፅሃፍ በአክብሮት ታነቡልኝ ዘንድ የምጋብዛችሁ በፍፁም ትህትና ዝቅ ብዬ ነው፡፡
መልካም ንባብ!
ንሴብሖ ፍቅሬ ወንድማገኝ
***
አቶ ንሴብሖ ፍቅሪ ከባለቤቱ ጋር በመሆን የኦቲዝም ተግዳሮት ያለበትን ልጃቸውን በመንከባከብ ያለፉበትንና እያደረጉ ያለውን ልምድ ለህብረተሰቡ ለማካፈል ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀቱ እጅግ እመሰግነዋለሁ።
ጥንዶቹ ባጋጠማቸው ተግዳሮት ተስፋ ላይቆርጡ ስለሁኔታውና መወለድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች በራሳቸው ጥረት ተረድተው አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ በፍጹም ፍቅር እያደረጉ መገኘታቸው የሚደነቅ ነው።
ይህ ልምዳቸውም በመጽሐፍ መታተሙ፣ ተመሳሳይ ተግዳሮት በቤተሰባቸው ውስጥ ኖሮ ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ለተጋቡና፣ ምናልባትም የማይገቡ እርምጃዎችን ለሚተገብሩ ቤተሰቦች ተገቢውን መንገድ በማመላከት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።
በህብረተሰቡ ውስጥ ከሚወለዱ እንድ መቶ ህፃናት አንዱ ወይም ሁለቱ የኦቲዝም ተግዳሮት የሆነ የነርቭ እና የእድገት ልዩነት ሊያጋጥማቸው ይችላል ፤ ነገሩ እጣ ነው። እጣው በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛችንም ቤት ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ሁላችንም በተጨባጭ ልምድ ከካበተው ንሴብሖና ቤተሰቡ በመማር ስለጉዳዩ እውቀት እንዲኖረን እመክራለሁ። ለዚህም የዚህ መጽሐፍ አስተዋጽኦ የጎላ ነው።
ዶ/ር ምኒልክ ደስታ
የአዋቂዎችና ህፃናት አእምሮ ሐኪም
***
ልጆቻቸው የኦቲዝም ችግር ያለባቸው በርካታ ወላጆች ፣ የሰዎችን አላዋቂ አንደበትና መገለል በመፍራት የልጆቻቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ችግርና ስቃይ በሚደብቁበት ወቅት፣ ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ የሆነውን ልጁን ችግርና የቤተሰቡን ውጣ ውረድ በመጽሐፍ መተረኩ የሚያስመሰግነው ነው።
እርግጥ ነው ንሴብሖ በልጁ ዮም ምክንያት በብዙ መረበሸ፤ እንቅልፍ ማጣት፤ ማህበራዊ መገለል ተከብቦ ያሳለፈውን ህይወት እና የከፈለው ዋጋ ቀላል አልነበረም፤ ይህም ሆኖ "የዮም መፃኢ እድል ፈንታ ምን ይሆን?'' የሚለው ከባድ የሃሳብ ሸክም አሁንም ከትከሻው አልወረደም።
ይህ ግለ ታሪክ በዚህ ችግር ውሰጥ የምናልፍ ቤተሰቦችን ችግሮች ገልጦና አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ፣ መጽሐፉን ልዩ የሚያደረገው ዋናው ነገር እንደተለመደው ስለ ችግሩ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎች ሳይሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ በሆነ አባት መቅረቡ ነው።
መልዕክቱ የኦቲዝምን ችግር እየተጋፈጡ ላሉ ቤተሰቦች አስተማሪና ጉልበትን የሚሰጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ተጋብተው መውለድ ለሚያቅዱ ጥንዶች፣ ለእምነትና ለትምህርት ተቋማት፣ በኦቲዝም ላይ ለሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ ጥልቅ ግንዛቤን በማስጨበጥ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው።
ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ፣ በፈተና ውስጥም ሆነን በጎ ማሰብና ፣ ከችግራችን በላይ በሆነ ጠንካራ ማንነት መታነጽ እንደሚቻል አይቻለሁና ሁሉም እንዲያነበው እመኛለሁ።
ዶ/ር ፍርድአወቀ ማሞ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
***
ለብዙዎቻችን ፈተና (መከራ) ሁልጊዜ የኃጢአት ውጤት ይመስለናል። አንድ ሰው ጤናን፣ ሀብትን፣ ልጅንና የመሳሰሉትን ሲያጣ እግዚአብሔር በኃጢአቱ እየቀጣው ነው ብለን እንደመድማለን፡፡
አቶ ንሴብሖ ፍቅሬና ባለቤቱ ወይዘሮ ሳምራዊት ድንቁ ፈተናን በመጋፈጥ የጽናት ተምሳሌት ሆነውናል… አቶ ንሴብሖ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆችን ለሚያሳድጉ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ጉልበትን የሚሰጥ፣ ጥበብን የሚያመላክት ሥራን መሥራቱ ደስ ያሰኛል።
ይኸውም ያላዋቂዎችን ትችት በመፍራት በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ያሉ ወገኖችን ከማግለል ይልቅ ማቀፍና መንከባከብ፣ ሰብአዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን በመጽሐፍ ሰንዶ በማቅረቡ ሊመሰገን ይገባል።
በብዙ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ንሴብሖ አሁንም አምላኩን አመስጋኝ መሆኑ ሌላው በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ይህንን መጽሐፍም ማንበብ ለሁሉም፣ በሁሉ መንገድ አቅም ይሰጣል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
***
ንሴብሖ ፍቅሬ
ስልክ
+251911212012
ኢ-ሜይል
yomnesebehogmail.com

ልጆቻችሁን እዩዋቸው! ችግራቸውን ተረዷቸው!!
ልጆቻችሁ መጻፍ አይሆንላቸውም? ...ማንበብስ? ...ሂሳብ ማስላት ላይስ እንዴት ናቸው? ....ትምህርትስ አይገባቸውም?
መቼም ብዙዎቻችሁ ስለኦቲዝም ስታስቡ የምታስቡት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ ልጅ ፊቱ ላይ ከሌሎች ልጆች የተለየ አይነት መልክ ሲኖረው፣ ከንፈሩን መግጠምና ምላሱን መሰብሰብ አዳግቶት የአፉን ፈሳሽ መቆጣጠር ሳይችል ሲቀር ፣ ወይም ራሱን የሚመታ ወይም ሰው የሚተናኮል ሲሆን ወዘተ ነው እናንተ ኦቲዝም ያለበት የሚመስላችሁ አይደል?
ትልቅ ስህተት ነው፡፡
እንዲህ ያሉ ምልክቶች ብዙ ጊዜ 'ዳውን ሲንድረም' የሚባለው አይነት የዐዕምሮ እድገት መዘግየት ችግር ባለባቸው ልጆች ላይ የሚከሰት ነው፡፡ እሱን ሌላ ጊዜ እናወራዋለን፡፡
ኦቲዝም ግን ምንም በአይን ታይቶ የሚታወቅ መልክ የለውም፡፡ አንድን ህጻን አይታችሁ ኦቲዝም እንዳለበት መበየን በፍጹም አትችሉም፡፡ ኦቲዝም ምንም አይነት የፊት ቅርጽ መለየት ወይም የአካል አፈጣጠር ልዩነት አይስተዋልበትም፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ ብዙዎችን በሚያስገርም ሁኔታ ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በጣም ቆንጆዎችና መልከቀናዎች ናቸው፡፡
ኦቲዝም ብዙ መገለጫዎች አሉት፡፡ አሁን ስለኦቲዝም ሳይሆን ከኦቲዝም ጋር ተመሳሳይ በሆነ የዐዕምሮ ዕድገት ስርዓት መዛባት ሳቢያ የሚፈጠሩ ችግሮችን ላወራችሁ ነው፡፡
የማንበብ ክህሎትን ማጣት፣ የመጻፍ ክህሎትን ማጣት እና ሂሳብ የማስላት ክህሎትን ማጣት የሚባሉ ችግሮች አሉ፡፡
"ሂሳብ የማስላት ክህሎትን ማጣት " ከዐዕምሮ ዕድገት ስርዓት መዛባት ኹኔታዎች (Neurodevelopmental disorder conditions) ውስጥ የሚካተተው የትምህርት ክህሎት ማጣት (Learning disability) ችግር አንዱ መገለጫ ነው፡፡
Learning disability ከምንላቸው የመማር ክህሎትን የማጣት ችግሮች ውስጥ የሚመደበው ሂሳብ የማስላት ችግር በሳይንሳዊ አጠራሩ Dyscalculia ተብሎ ይጠራል፡፡ አንድ ተማሪ ህጻን ቀላልና ማንም ሊሰራቸው የሚችል የሂሳብ ስሌቶችን ለመስራት ሲያዳግተውና በአጠቃላይ ስሌት አልገባ ሲለው Dyscalculia ሊኖርበት እንደሚችል መጠርጠርና ለባለሙያ ማሳየት አይከፋም፡፡
ማንበብ እየቻሉ እርሳስ ወይም ስክሪፕቶ ይዘው መጻፍ በፍጹም የማይሆንላቸው ልጆች ደግሞ አሉ፡፡ "መጻፍ አይወዱም፣ ይቸከችካሉ" እየተባሉ ለቅጣት ይዳረጋሉ፡፡ ስክሪፕቶና እርሳስ አጥብቀው መያዝም ሆነ በአግባቡ መስመር ተከትለው መጻፍ አይሆንላቸውም፡፡ ፈልገው አይደለም፡፡ ይህ ችግር Dysgraphia ይባላል፡፡ ብዙ ልጆች ጎበዝ ተማሪዎች ሆነው ሳለ መጻፍ ግን 'ሞታቸው' ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ ችግራቸውን የሚረዳላቸው ስለሚያጡ ለቅጣትና ለቁጣ ይዳረጋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ልጆች ካሏችሁም ለባለሙያ አሳዩዋቸው፡፡
የትምህርት ክህሎት ማጣት ችግር ሌላው መገለጫ ደግሞ "የማንበብ ክህሎትን ማጣት " ወይም በህክምና ቋንቋ Dyslexia የሚባለው ነው፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች መጻፍ ቢችሉም ማንበብ ግን አይችሉም፡፡ ፊደሎቹ አይናቸው ስር ስለሚንቀሳቀሱባቸው ተረጋግተው አይታዩዋቸውም፡፡ በዚህ ሳቢያ ዐዕምሯቸው ይረበሻል፡፡ እንዲህ አይነት ልጆችም በተመሳሳይ ትምህርት ቤት ገብተው ማንበብ ስለማይሆንላቸው ለቅጣት እና ለቁጣ ይዳረጋሉ፡፡ ችግራቸውን የሚረዳላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል፡፡
በአጠቃላይ "ልጄ ትምህርት አይገባውም፣ ትምህርት አይወድም፣ ሰነፍ ነው፣ ደደብ ነው" ወዘተ እያሉ ልጆችን መቅጣትና በልጆች ላይ መጮህ ትርጉም ያለው ውጤት አያመጣም፡፡ የገለጽኩላችሁ ነገር ሁሉ በቴራፒ መስተካከል የሚችል ነገር ስለሆነ ለባለሙያ ማሳየትና ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳይንሳዊ ቴራፒ ድጋፍ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
ኦቲዝም (ASD) ፣ የመረጋጋትና የትኩረት ማጣት (ADHD) ፣ ወይም የትምህርት ክህሎት ማጣት ( learning Disability) በተመሳሳይ የዐዕምሮ ዕድገት ስርዓት መዛባት (Neuro developmental disorder) ምክንያት የሚመጡ ችግሮች ናቸው፡፡ ሶስቱም የመሻሻል ተስፋ ያላቸው በመሆናቸው ባለሙያ ማማከር እንጂ "ልጄ ይህ ችግር የለበትም" ብሎ ለመቀበል አለመፈለግ ወይም መደበቅ ማንንም አይጠቅምም፡፡
የልጆቻችሁን ችግር ሳታውቁ ዳተኛ አድርጋችሁ አትፈርጇቸው፡፡ ተረዷቸውና አግዟቸው፡፡
መላኩ ብርሃኑ
የኦቲዝም መብቶች ተሟጋችና የበጎ ፍቃድ አምባሳደር

10 months ago
ዘመን ባንክ ለግብረሰናይ ድርጅቶች 29.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
#ethiopia | ዘመን ባንክ ማኅበራዊ ሐላፊነቱን በመወጣት በማኅበረሰብ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ 19 ግብረሰናይ ድርጅቶች 29.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢና አቶ ደረጀ ዘበነ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ድጋፉን ለግብረሰናይ ድርጅቶቹ አስረክበዋል፡፡ የተሰጠው ድጋፍ እንደ ድርጅቶቹ የሥራ ስፋትና የሚሰጡት አገልግሎት ከአንድ ሚሊየን ብር እስከ ሁለት ሚሊየን ብር የሚደርስ ነው፡፡
ከእነዚህ መካከል አስራ አምስቱ አዲስ አበባ ሆነው አገልግሎታቸውን የሚሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ አራቱ በባህርዳር፣ መቀሌ፣ ሀዋሳና አዳማ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር ባደረጉት ንግግር ዘመን ባንክ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎችን የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚረዱ ድጋፎችን በመስጠት ተቋማዊ ማኅበራዊ ሐላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ባንኩ ይህንን መልካም ምግባር አጠናክሮ በመቀጠል ለግብረሰናይ ድርጅቶቹ ይደግፈል ብለዋል፡፡
ከዘመን ባንክ ድጋፍ የተደረገላቸው ግብረሰናይ ድርጅቶች መቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ዲቦራ ፋውንዴሽን፣ የኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን፣ ችልድረን ኸርት ፈንድ፣ ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ፣ ትኩረት ለሴቶችና ለህጻናት ማኅበር፣ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል፣ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የኩላሊት ህመም ማኅበር፣ ፍሬምናጦስ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህሙማንና የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ ቤቴል ችልድረንስ ሆም አሶሴሽን፣ ቤዛ ለህይወት የልማት ድርጅት፣ ክብር ለአረጋውያን፣ ርኆቦት ፊዲንግ ኤንድ ስተዲ ሴንተር፣ ህይወት ኢትዮጵያ እና ብራይት ወርልድ ብላይንድ ውሜን አሶሴሽን ናቸው፡፡

11 months ago
ፓራስታሞል የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ነፍሰጡር ሴቶች እንዳይወስዱ አሳሰቡ‼
ትራምፕ ለህመም ማስታገሻ የሚሰጠው ታይሌኖል የተባለው መድኃኒት ኦቲዝምን ያስከትላል በማለት ነፍሰጡር ሴቶች እንዳይወስዱ አሳሰቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመድኃኒቱ እና በኦቲዝም መካከል ያለውን አወዛጋቢ ግንኙነት በመጥቀስ በአሜሪካ ያሉ ዶክተሮች የህመም ማስታገሻውን ታይሌኖልን ለነፍሰ ጡር ሴቶች በቅርቡ እንዳይያዙ ይመከራሉ ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሰኞ እለት ፓራሲታሞል በመባል የሚታወቀውን ታይሌኖልን መውሰድ ጥሩ አይደለም ፤ ነፍሰ ጡር እናቶች የከፋ ትኩሳት ሲያጋጥማቸው ብቻ እንዲወስዱት መክረዋል።
የሕክምና ባለሙያዎች ግን ማስጠንቀቂያውን ተችተዋል ፣ አንዳንዶች የፕሬዚዳንቱን አስተያየት አደገኛ ሲሉ ተናግረዋል ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የጤና ባለስልጣናት ፓራሲታሞል ለነፍሰ ጡር ሴቶች በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ የህመም ማስታገሻ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአሜሪካ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ስቲቨን ፍሌይሽማን በሰጡት አስተያየት የትራምፕ ማሳሰቢያ “በተሟላ ሳይንሳዊ ማስረጃ ያልተደገፈ ብለውታ፤ በህፃናት ላይ ያሉ በርካታ እና ውስብስብ የነርቭ ችግሮች መንስኤዎችን በአደገኛ ሁኔታ ያቃልላል” ሲሉ አክለዋል። የሕክምና ቡድኑ በመላ አገሪቱ ያሉ ዶክተሮች ታይሌኖልን ለነፍሰ ጡር ሴቶች አስተማማኝ የህመም ማስታገሻዎች መካከል አንዱ መሆኑን በተከታታይ ለይተው አውቀዋል።
መድሃኒቱ በሌሎች ዋና ዋና የሕክምና ቡድኖች እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ባሉ ሌሎች የጤና አመራሮች ይመከራል።

ትራምፕ ኦቲዝም ያስከትላል ያሉትን መድኃኒት ነብሰ-ጡር ሴቶች እንዳይወስዱ አሳሰቡ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ዶክተሮች ለነብሰ-ጡር ሴቶች ታይሌኖል የተባለውን ማስታገሻ መድኃኒት እንዳይሰጡ አሳስበዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት መድኃኒቱ ከኦቲዝም ጋር ግንኙነት አለው ብለው ቢሆንም ይህ በሳይንስ የተረጋገጠ አይደለም።
ፕሬዝደንቱ ከጤና ሚኒስትራቸው ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ጁኒየር ጋር በመሆን ከዋይት ሐውስ በሰጡት መግለጫ ነው ይህን ያሉት።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት የታይሌኖል ዋነኛ ግብዐት የሆነውን ፓራሴታሞል መውሰድ "ጥሩ አይደለም" ብለው ነብሰ-ጡሮች እጅግ የከፋ ትኩሳት ሲኖርባቸው ብቻ እንዲወስዱት መክረዋል።
አንዳንድ ጥናቶች ታይሌኖል በሚወስዱ ነብሰ-ጡር ሴቶች እና በኦቲዝም መካከል ግንኙነት እንዳለ ቢያሳዩም ጥናቶች ያልተጠናቀቁ እና ያልተሟሉ ናቸው።
ታይሌኖል የተባለው ክኒን አምራች የሆነው ኬንቩዌ ሴቶች መድኃኒቱን እንዳይወስዱት መባሉን አጣጥሏል።
ድርጅቱ ለቢቢሲ በላከው መግለጫ "ገለልተኛ እና ጠንካራ ሳይንስ ኤስታሚኖፊን በመውሰድ እና በኦቲዝም መካከል ግንኙነት እንደሌለ አሳይቷል ብለን እናምናለን። ከዚህ ውጭ የሚሰጥን አስተያየት አጥብቀን እንቃወማለን። ይህ ምክር ለነብሰ-ጡር ሴቶች የሚያስከተለው የጤና ቀውስም ያሳስበናል" ብሏል።
ትራምፕ ሰኞ በሰጡት መግለጫ በኦቲዝም የሚጠቁ ሕፃናት ቁጥር መጨመርን "ከፍተኛ ቀውስ" ሲሉ ገልፀውታል።
ነገር ግን ሙያተኞች ባለፉት አስርት ዓመታት ጥናት የተካሄደበትን ኦቲዝም መንስኤው ምንድነው የሚለውን በአጭር ጊዜ ማወቅ ቀላል አይደለም ይላሉ።
በጠቅላላው የኦቲዝም መንስኤ ተደርገው የሚወሰዱት ምክንያቶች በዘር የሚመጡ እና አካባቢያዊ አስተዋፅኦዎች ናቸው።
ETHIO FM

በእርግዝና ወቅት ፓራሲታሞል መውሰድ በህፃናት ላይ ኦቲዝም ሊያመጣ ይችላል፡ ጥናት
በእርግዝና ወቅት በስፋት የሚታወቀውን የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ፓራሲታሞል (አሲታሚኖፌን) መውሰድ በሚወለዱ በልጆች ላይ ኦቲዝም እና ትኩረት ማጣት ተጋላጭነትን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።
ጥናቱን ያካሄዱት በአሜሪካ ሃርቫርድ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት እና ማውንት ሲናይ ሆስፒታል የሚገኙ ተመራማሪዎች ናቸው።
ከ100,000 በላይ ሰዎችን መረጃ ያካተቱ 46 የቀድሞ ጥናቶችን መረጃ ተንትነዋል።
በተጨማሪም እናቶች ፓራሲታሞልን የወሰዱበትን የእርግዝና ደረጃ (የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ወር፣ ወይም ሙሉ እርግዝና) ላይ ያለ መረጃም ተመርምሯል።
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው በእርግዝና ወቅት ፓራሲታሞልን መጠቀም በልጆች ላይ ከነርቭ እድገት ጋር በተያያዙ ችግሮች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። በተለይም ለኦቲዝም እና ትኩረት ማጣት ተጋላጭነትን ይጨምራል።
ባለሙያዎች ነፍሰ ጡር እናቶች ድንገት መድሃኒቱን ማቆም እንደሌለባቸው ይመክራሉ። በማውንት ሲናይ ሆስፒታል የህዝብ ጤና ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ዲዲየር ፕራዳ፣ መድሃኒቱን ያለሀኪም ምክር መወሰድ ማቆም እንደሌለበት ተናግረዋል። ምክንያቱም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ህመም ወይም ትኩሳትም በጨቅላ ህፃኑ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ነው።
በተጨማሪም ከመድሀኒት ወጭ ሌሎች ዘዴዎችን ከሐኪም ጋር መነጋገር መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ አንዳንድ ቀደምት ጥናቶች የረዥም ጊዜ የፓራሲታሞል አጠቃቀም ለጨጓራና አንጀት ደም መፍሰስ፣ ለረዥም ጊዜ የኩላሊት ችግሮች፣ ለልብ ድካም እና ለደም ግፊት የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር አሳይተዋል።
Seledadotio

Comments