Logo
SeledaPost
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምክር እናቱን የገደለው ወጣት

​በሰሜን ዌልስ የሚኖር ትሪስታን ሮበርትስ የተባለ የ18 ዓመት ወጣት፣ በDeepSeek አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ እናቱን አንጄላ ሼሊስን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ ተሰማ።

ኦቲዝም ያለበትና ለረጅም ጊዜ በኢንተርኔት የጥላቻ ንግግሮች ተጽዕኖ ሥር የነበረው ወጣቱ፣ የሰው ሕይወት ለማጥፋት የሚረዱ መሳሪያዎችን AIን በመጠየቅ መረጃ ማግኘቱ ተገልጿል።

​መጀመሪያ ላይ ቴክኖሎጂው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም፣ ወጣቱ "መጽሐፍ እየጻፍኩ ነው" በሚል ማታለያ መረጃውን ማግኘቱ ተረጋግጧል።

የግድያ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላም በማህበራዊ ሚዲያ (Discord) ላይ ድርጊቱን ሲያጋራ ቆይቷል።

ፍርድ ቤት የቀረበው ትሪስታን የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጥንቃቄና የኢንተርኔት ደህንነት ቁጥጥር አስፈላጊነት ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.