ምሉዕ ፋውንዴሽን 'እራት በምክንያት' በሚል ሀሣብ ፕሮግራም ሊያደርግ ነው
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ የሚሠራው ምሉዕ ፋውንዴሽን ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ሜ በሸራተን አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫና 'ራት በምክንያት' በሚል ስያሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ- ግብር ሊያደርግ ነው።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ትዕግሥት ኃይሉ የአለም የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በሚደረገው ልዩ ዝግጅት ትላልቅ ተቋማት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይታደማሉ ስትል በላከችው መግለጫ አስታውቃለች።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የምናከብራት ድምፃዊት ቤቲ ጂ ከስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች ታጅባ ሥራዋን ታቀርባለች።
አብረዋት የሚያጅቡትም የፒያሳ ትሪዬ ባንድ አባላት አንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ዳዊት አደራ ናቸው።
በወግ መፅሐፎቿ የምትታወቀው የሥነ- ፅሑፍ ባለሙያ ህይወት እምሻው ሥራዎቿን የምታቀርብ ሲሆን የመድረኩ አጋፋሪም መቲሸዋዬ ይልማ እንደሆነችም ታውቋል።
ምሉዕ ፋውንዴሽን፣ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ባላቸው ወላጆች በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና በአቶ ክንፈ ፅጌ ተመስርቶ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ነው።
ምሉዕ ፣ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የተቀናጀ ቴራፒ አገልግሎት፣ ተግባር ተኮር ስልጠና፣ የወላጆች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም ሁሉን አካታች ትምህርት ላይ በትኩረት የሚሠራ ፋውንዴሽን ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም በምሉዕ የተቀናጀ የቴራፒ ማዕከል 50 ልጆች የመሠረታዊ ቴራፒ አገልግሎት እንዲሁም እድሜያቸው ከ13-19 ላሉ ታዳጊዎች ደግሞ የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸውን በሥነልቦና እና በተግባር ተኮር ዕውቀት የማብቃት ሥራ እየሰራ ይገኛል፣ ከ300 በላይ የሚሆኑ ልጆች ደግሞ በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሰል ተግባርም ምሉዕ ፋውንዴሽን በስልጠና መርሃግብሩ ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም በትምህረት ቤቶች፣ በሕፃናት ማሳደጊያዎች፣ በሆስፒታሎች እና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ በዕውቀት የተደገፈ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በምሉዕ ቤተ-መጻሕፍት በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገለገሉበት ከ3ሺ 6መቶ በላይ ዘርፈብዙ መጻሕፍት ያሉ ሲሆን ከዚህም ጋር በማያያዝ የቤተ-መጻሕፍት አባልነትን ከአረንጓዴ ልማትና አካባቢን ከማስዋብ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ይህን በጎ አላማ ለማስቀጠል አብራችሁን እንድትቆሙ ሲል ፋውንዴሽኑ በገቢ ማሰባሰብ ሥራው ላይ እንዲሳተፉ፣ ለድርጅቶችም ሆነ በግል ቲኬቶችን ለሚገዙ ጥሪ አቅርቧል።
የዚህ መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባዎች አስተባባሪ ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

2 months ago