ዮም
ንሴብሖ ፍቅሬ
አሰናኝ፡፦ ጥላሁን ክፍሌ እርገጤ
#ethiopia | በተለያዩ ጊዜያት፣ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት፣ ከተለያዩ ቤተሰቦች የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ይወለዳሉ፡፡ በስልጣኔና በአመለካከት የበለጸጉት ሀገራትም ኦቲዝምን እንደአንድ የተፈጥሮ ጸጋ በመቀበል በኦቲዝም ጥላ ሥር ለመኖር ዓለማችንን የተቀላቀሉትን ህጻናት እንደየፍላጎታቸው ተንከባክበው በማሳደግ፣ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ለሚኖሩባት ዓለም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ይሠራሉ፡፡
በእርግጥ ከዓለማችን ሀገሮች ብዛት አንጻር በዚህ መልኩ የሚተጉት ጥቂት ናቸው፡፡ ቀላል ቁጥር የማይዘው የዓለማችን በተለይም የሀገራችን ማህበረሰብ ኦቲዝምን ድጋፍና እንክብካቤ የሚሻ እክል አድርጎ ከመቁጠር ይልቅ፣ “ርግማን” እንደሆነ አምኖ ይህንኑ የሚያስተጋባ ነው፡፡
የበኩር ልጃችን ዮም ንሴብሖ፣ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ እያደረግናቸው ያሉትን ወሰን አልባ ጥረቶች በመጽሐፍ ሰንዶ ለአንባቢያን ለማድረስ መነሳቱን ከተፈጠሩት ምክንያቶች አንዱም ኦቲዝምን በሚመለከት ያለን መረዳት ለማረቅ መሻት ነው፡፡
በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን የተዛባ አረዳድ በማስተካከል ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖር የሚረዳ ተጠቃሽ መጽሐፍ' ካበረከተው ከዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ጋር በዮም ምክንያት በተደጋጋሚ የመገናኘት አጋጣሚ ነበረኝ።
ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ዶክተር ዮናስ፣ “የሕይወት ተሞክሮህ በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለአንባቢ ቢቀርብ ብዙ ነገር ሊያስተምርይችላል" በሚል የሰነዘረው አስተያየት ልቤን ሰቅዞ ይዞት፣ ለረጅም ጊዜ ሳስብበት ቆየሁ:: የዶክተር ዮናስ ሃሳብ በልቤ ውስጥ ብቻ አልቀረም:: ከወዳጄ እና አብሮ አድጌ ጥላሁን ክፍሌ ጋር በመሆን ይህንን በእጃችሁ ላይ የሚገኘው መጽሐፍ እንዲወለድ ሆነ፡፡ በእርግጥም ምጡ ቀላል አልነበረም!
ከጥላሁን ጋር መጽሐፉን ለማዘጋጀት በምንተጋበት ጊዜ፣ እጅግ የሚወዳቸውና የሚሳሳላቸው እናቱ ወ/ሮ ጥሩወርቅ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ፡፡ በዚህ ሁኔታ የመጽሐፉን ዝግጅት ማስቀጠል፣ ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ እናቱን ለሚያስታምመው ጥላሁን ከባድ ነበርና፣ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቋረጥ ሆነ:: ሆኖም የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና፣ ለአምስት ወራት ያህል በሕክምና ሲረዱ የቆዩት እናቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ፡፡ ጥላሁን ክፍሌን የሚያውቅ ማንም ሰው እናቱን ያውቃል፧ ሁለቱን የሚያውቅ ደግሞ በመካከላቸው ያለውን የተለየ ፍቅር ያውቃል:: ያን ጊዜ፣ ጥላሁን የቀድሞው ጥንካሬ እና ሞራል ኖሮት ይህን ሥራ እንጨርሰዋለን
ምክንያት አለው ብዬ ራሴን አሳመንኩ። እንዴት ይበረታ ይሆን? እያልኩ ብጨነቅም ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና አጽናኝ መላእኩን ልኮ እኒያን ጥቋቁር የሐዘን ቀናት በጸጋው አሳለፋቸው:: ብርቱው ባለተሰጥኦ ጥላሁንም በሚያስደንቅ ትጋትና ብርታት መጽሐፉን አጠናቆ እነሆኝ አለኝ፡
ባሳለፍኩት የሕይወት መንገድ ያጋጠሙኝን የደስታም ሆነ የሐዘን፣ የከፍታም ሆነ የዝቅታ፣ የስኬትም ሆነ የመፈተን ውጣ ውረዶችን በዚህ መጽሐፍ ለማጋራት ሞክሬአለሁ፡፡ በተለይም ልጃችን ዮም ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ መፍትሔና ፈውስ ፍለጋ፣ የወጣን የወረድንባቸው ጎዳናዎች፣ ያንኳኳናቸው ደጆች፣ የገፋናቸው የመከፋትና የመፈተን ወራት እና ለዐይን ጥቅሻ ዕድሜ እንኳን ከጎናችን ባልተለየንና ይልቁንም ከፊታችን ይቀድም በነበረው እግዚአብሔር የቻልናቸውን ስኬቶች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታነባላችሁ፡፡
ከሕይወት ልምዴ ከተወሰደ ቀጥተኛ ተሞክሮ በተጨማሪ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከንባብ እና በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ካላቸው ወላጆችም ጋርበነበረኝ ማኅበራዊ ግንኙነቶች የተረዳኋቸውን ግንዛቤዎች በመጽሐፉ ለማካተት ሞክሪያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኦቲዝምን በተመለከተ ህብረተሰባችን ያለው ግንዛቤ በአብዛኛው የተዛባ ነው፡፡ ይህም ወላጆች/አሳዳጊዎች ሊሻሻል በሚችለው በዚህ የአእምሮ ዕድገት እክል የተጠቁ ልጆቻቸውን ለማገዝ የሚችሉትን እንዳያደርጉ፣ በዚህም የእነሱና የልጆቻቸው ስቃይ ቀጣይና ማብቂያ የሌለው እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይህ መጽሐፍ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ላላቸው ወላጆች እና በኦቲዝም ሳቢያ የሚፈጠሩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም ለመላው ማኅበረሰባችን የተሻለ ግንዛቤን በማስጨበጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡
መጽሀፉ በአራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ ዮም ከመወለዱ በፊት የነበረኝን ህይወት በመጠኑም ቢሆን የሚያስቃኝ ነው:: ሁለተኛው ምዕራፍ የመጽሃፉ ዋና አስኳል ሲሆን ይህም ዮም ከተወለደ ጀምሮ ይህ መጽሀፍ እስኪዘጋጅ ድረስ የተኖረውን ዋና ዋና የህይወት ክፍል ይዳስሳል:: ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ልጆቻቸው በኦቲዝም የተጠቁ እና በእኔ ማህበራዊ ህይወት ዙሪያ የነበሩ ወላጆች ቅንጫቢ ታሪኮች ስብስብ ነው:: በመጨረሻው ምዕራፍ ከእኔ የህይወት ልምድ እና ትዝብት በተጨማሪ በኦቲዝም ዙሪያ ከተለያዩ ምንጮች የቃረምኳቸው ጠቃሚ እውነታዎች ተገልፀዋል:: በእኔ እና በልጄ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ለበጎ አላማና ተግባር የተዘጋጀውን ይህን መፅሃፍ በአክብሮት ታነቡልኝ ዘንድ የምጋብዛችሁ በፍፁም ትህትና ዝቅ ብዬ ነው፡፡
መልካም ንባብ!
ንሴብሖ ፍቅሬ ወንድማገኝ
***
አቶ ንሴብሖ ፍቅሪ ከባለቤቱ ጋር በመሆን የኦቲዝም ተግዳሮት ያለበትን ልጃቸውን በመንከባከብ ያለፉበትንና እያደረጉ ያለውን ልምድ ለህብረተሰቡ ለማካፈል ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀቱ እጅግ እመሰግነዋለሁ።
ጥንዶቹ ባጋጠማቸው ተግዳሮት ተስፋ ላይቆርጡ ስለሁኔታውና መወለድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች በራሳቸው ጥረት ተረድተው አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ በፍጹም ፍቅር እያደረጉ መገኘታቸው የሚደነቅ ነው።
ይህ ልምዳቸውም በመጽሐፍ መታተሙ፣ ተመሳሳይ ተግዳሮት በቤተሰባቸው ውስጥ ኖሮ ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ለተጋቡና፣ ምናልባትም የማይገቡ እርምጃዎችን ለሚተገብሩ ቤተሰቦች ተገቢውን መንገድ በማመላከት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።
በህብረተሰቡ ውስጥ ከሚወለዱ እንድ መቶ ህፃናት አንዱ ወይም ሁለቱ የኦቲዝም ተግዳሮት የሆነ የነርቭ እና የእድገት ልዩነት ሊያጋጥማቸው ይችላል ፤ ነገሩ እጣ ነው። እጣው በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛችንም ቤት ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ሁላችንም በተጨባጭ ልምድ ከካበተው ንሴብሖና ቤተሰቡ በመማር ስለጉዳዩ እውቀት እንዲኖረን እመክራለሁ። ለዚህም የዚህ መጽሐፍ አስተዋጽኦ የጎላ ነው።
ዶ/ር ምኒልክ ደስታ
የአዋቂዎችና ህፃናት አእምሮ ሐኪም
***
ልጆቻቸው የኦቲዝም ችግር ያለባቸው በርካታ ወላጆች ፣ የሰዎችን አላዋቂ አንደበትና መገለል በመፍራት የልጆቻቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ችግርና ስቃይ በሚደብቁበት ወቅት፣ ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ የሆነውን ልጁን ችግርና የቤተሰቡን ውጣ ውረድ በመጽሐፍ መተረኩ የሚያስመሰግነው ነው።
እርግጥ ነው ንሴብሖ በልጁ ዮም ምክንያት በብዙ መረበሸ፤ እንቅልፍ ማጣት፤ ማህበራዊ መገለል ተከብቦ ያሳለፈውን ህይወት እና የከፈለው ዋጋ ቀላል አልነበረም፤ ይህም ሆኖ "የዮም መፃኢ እድል ፈንታ ምን ይሆን?'' የሚለው ከባድ የሃሳብ ሸክም አሁንም ከትከሻው አልወረደም።
ይህ ግለ ታሪክ በዚህ ችግር ውሰጥ የምናልፍ ቤተሰቦችን ችግሮች ገልጦና አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ፣ መጽሐፉን ልዩ የሚያደረገው ዋናው ነገር እንደተለመደው ስለ ችግሩ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎች ሳይሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ በሆነ አባት መቅረቡ ነው።
መልዕክቱ የኦቲዝምን ችግር እየተጋፈጡ ላሉ ቤተሰቦች አስተማሪና ጉልበትን የሚሰጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ተጋብተው መውለድ ለሚያቅዱ ጥንዶች፣ ለእምነትና ለትምህርት ተቋማት፣ በኦቲዝም ላይ ለሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ ጥልቅ ግንዛቤን በማስጨበጥ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው።
ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ፣ በፈተና ውስጥም ሆነን በጎ ማሰብና ፣ ከችግራችን በላይ በሆነ ጠንካራ ማንነት መታነጽ እንደሚቻል አይቻለሁና ሁሉም እንዲያነበው እመኛለሁ።
ዶ/ር ፍርድአወቀ ማሞ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
***
ለብዙዎቻችን ፈተና (መከራ) ሁልጊዜ የኃጢአት ውጤት ይመስለናል። አንድ ሰው ጤናን፣ ሀብትን፣ ልጅንና የመሳሰሉትን ሲያጣ እግዚአብሔር በኃጢአቱ እየቀጣው ነው ብለን እንደመድማለን፡፡
አቶ ንሴብሖ ፍቅሬና ባለቤቱ ወይዘሮ ሳምራዊት ድንቁ ፈተናን በመጋፈጥ የጽናት ተምሳሌት ሆነውናል… አቶ ንሴብሖ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆችን ለሚያሳድጉ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ጉልበትን የሚሰጥ፣ ጥበብን የሚያመላክት ሥራን መሥራቱ ደስ ያሰኛል።
ይኸውም ያላዋቂዎችን ትችት በመፍራት በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ያሉ ወገኖችን ከማግለል ይልቅ ማቀፍና መንከባከብ፣ ሰብአዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን በመጽሐፍ ሰንዶ በማቅረቡ ሊመሰገን ይገባል።
በብዙ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ንሴብሖ አሁንም አምላኩን አመስጋኝ መሆኑ ሌላው በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ይህንን መጽሐፍም ማንበብ ለሁሉም፣ በሁሉ መንገድ አቅም ይሰጣል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
***
ንሴብሖ ፍቅሬ
ስልክ
+251911212012
ኢ-ሜይል
yomnesebehogmail.com

11 months ago