የጆይ ኦቲዝም የልህቀት ማዕከል የግንባታ ማጠናቀቂያ ገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቀረበ!
#fastmereja : ኒያ ፋውንዴሽን (ጆይ ኦቲዝም ማዕከል) ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የልህቀት ማዕከል የፊኒሺንግ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል መጠነ-ሰፊ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ገልጿል።
ፋውንዴሽኑ “ሚያዝያ ለኒያ ለእናት ጉያ'' በሚል መሪ ቃል ንቅናቄውን ይፋ ያደረገው፣ ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ፈጠራ ወርን በማስመልከት ነዉ የተዘጋጀዉ።
የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ እሌኒ ዳምጠው እንደገለጹት፤ በ4,824 ካሬ ሜትር ላይ እያረፈ ያለው የህንፃ ግንባታ የስኬሌተን ሥራ ተጠናቆ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ መሸጋገሩነሰ ገልፀዉ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት መቶ በመቶ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።
ይህ ለአንድ ወር የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከሚያዚያ 6 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከሉ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን፣ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ተገልጿል።
ማዕከሉ ህንፃውን 50 በመቶ ለማጠናቀቅ “100 ሺህ ልቦች" እንደሚያስፈልጉት የጠቀሰ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ደጋፊ 300 ብርቢለግስ የሚፈለገውን 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ግንባታውን ማጠናቀቅ እንደሚቻል ተመልክቷል፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅ በኦቲዝም እና በሌሎች የአእምሮ እድገት ውስንነቶች ላይ ለሚገኙ ዜጎች ዘመናዊ የሕክምና፣ የትምህርትና የማገገሚያ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
ለመርዳት የሚፈልጉ ወገኖች በቴሌብር 9616 ላይ "OK" ብለው በመላክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጭር የሒሳብ ቁጥር 2135 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

4 months ago