"ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ያገባናል!"
- የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በኢትዮጵያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የኤፕሪል የኦቲዝም መቀበልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።
ሶሳይቲው በመጋቢት 28 ቀን 2026 ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዘንድሮው ወር "ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ስለኦቲዝም ያገባናል" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተዛባ አመለካከትን መቀየር፦
ኦቲዝም እርግማንም ሆነ የኃጢአት ውጤት አለመሆኑን ማህበረሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባና ሚዲያዎችም ትክክለኛውን መረጃ ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል።
የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጫና፦
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ወላጆች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫና ለማቃለል የማህበረሰቡ ድጋፍና መቀበል ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
የአገልግሎቶች እጥረት፦
እንደ ስፒች ቴራፒ፣ ኦኩፔሽናል ቴራፒ እና የባህሪ ማስተካከያ ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች ለልጆቹ ዕድገት ወሳኝ ቢሆኑም፣ በሀገሪቱ ያለው የማዕከላት እጥረት ትልቅ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
የሚዲያ ሚና፦
መገናኛ ብዙሃን ስለኦቲዝም ልዩ ልዩ ዘገባዎችን በመስራት፣ አዎንታዊ ምስል በመፍጠርና የመብት ጥሰቶችን በማንሳት ግንዛቤ የማስጨበጫ ወሩን እንዲያከብሩ ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲና የተለያዩ የኦቲዝም ማዕከላት (ጆይ ኦቲዝም፣ ነህምያ ኦቲዝም፣ የኛ ልጆች ኦቲዝም ማህበር እና ብሩህ ፋውንዴሽን) ወሩን ሙሉ ግንዛቤ በመፍጠርና ድጋፍ በመሰብሰብ ተግባራት ላይ እንደሚሰማሩ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣
እባክዎን በዚህ ስልክ ያነጋግሩ፡
መላኩ ብርሃኑ
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሲሳይቲ ቦርድ አባል
የኮሚዩኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ተጠሪ
ስልክ +251-911-403884
#getu #autismawareness #autismacceptancemonth #ethiopia #autismsocietyethiopia #inclusion #supportautism #addisababa #joyautismcenter #neahmiahautismcenter #ኦቲዝም #ግንዛቤ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago