"ዮም" የተሰኘ በኦቲዝም ዙሪያ የሚያጠነጥነው የእውነተኛ ታሪክ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በኦቲዝም ጥላ ስር ያለ ልጅ ያለው አባት ልጁን ለማሳደግ የሚያልፈበትን እውነተኛ የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርከውና "ዮም" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
በደራሲ ንሴብሖ ፍቅሬ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆች የሚገጥሟቸውን ማኅበራዊ ጫናዎችና ቤተሰቦቻቸው የሚጋፈጡትን መሪር የሕይወት ፈተና ከራሳቸው ገጠመኝ በመነሳት በዝርዝር ዳስሰዋል።
መጽሃፉ በዚህ የህይወት ሰልፍ ውስጥ ያሉ ልጆችን ህይወት በማሳየት ለበርካት ቤተሰቦች መንገድ መሪ መሆን የሚችል መሆኑ በምርቃት መድረኩ ተገልጿል፡፡
ደራሲው የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው "ዮም" የተባለ በኦቲዝም ጥላ ስር ያለ ልጅ አባት ሲሆኑ፣ ልጃቸው የሕይወት ዘመን ክትትልና ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ ሁኔታው በቤተሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ማለቂያ የሌለው መሆኑን በመጽሐፋቸው ገልጸዋል።
በመሆኑም ይህ ችግር በአንድ ቤተሰብ ጥረት ብቻ የሚፈታ ሳይሆን ማኅበረሰቡ፣ የግል ድርጅቶችና መንግሥት በጋራ ሊረባረቡበት እንደሚገባ ደራሲው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ትምህርት ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ተቀብለው ለማስተማርና ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ ደራሲ ንሴብሖ ከራሳቸው የሕይወት ተሞክሮ በመነሳት ጥሪ አቅርበዋል።
በ254 ገጾች ተቀንብቦ ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በዘርፉ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላትና ለሌሎች ወላጆችም የሞራል ጥንካሬ ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

5 months ago