3 months ago
ኢትዮጵያ በ2045 የዓለማችን ግዙፍ 10 ኢኮኖሚዎች ተርታ ትሰለፋለች ፤ አለምን ያስደመመው ስር ነቀል ለውጥ
#ethiopia #ethiocoders #madeinethiopia #ethiopianeconomy2045 #artificialintelligence #ethiopiandevelopment #addisababa #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያታምርት #ኢትዮኮደርስ #አርቴፊሻልኢንተለጀንስ
3 months ago
ኢትዮጵያ ታመርታለች፤ ምሉዕ ሉዓላዊነቷን የማረጋገጥ ጉዞዋን በሁሉም መስክ አጠናክራ ትቀጥላለች። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ደግሞ የዚህ መርኃችን ዋነኛ ዓምድ ነው።
#ኢትዮጵያታምርት #madeinethiopia #ethiopiatamrit #economicsovereignty #ethiopiandevelopment #manufacturing #industrialrevolution #homegrowneconomy
3 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈረሙት ለምንድን ነው?
*“ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፋሽን ተምሳሌት እናደርጋታለን” — አቶ ዘላለም መራዊ
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት
#ethiopia | በ“ኢትዮጵያ ታምርት” የንግድ ትርኢት ላይ የተሳተፉት የኬሬዠ ኢትዮጵያ መስራች አቶ ዘላለም መራዊ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድርጅታቸውን የፈጠራ ስራዎች መጎብኘታቸውንና ከፍተኛ አድናቆት መቸራቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየዓመቱ በሚያደርጉት ጉብኝት በምርቶቹ ላይ የሚታየው መሻሻልና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዳስደመሟቸው በድርጅቱ የክብር መዝገብ ላይ በፊርማቸው ጭምር አረጋግጠዋል።
በዓለም ላይ ያለው የፋሽን ኢንዱስትሪ እስከ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ እንደሚያንቀሳቅስ የገለጹት አቶ ዘላለም፣ ኢትዮጵያ እንደ ጣልያንና ፈረንሳይ የራሷን የፋሽን “ብራንድ” በመገንባት ከዚህ ገበያ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል።
ኬሬዠ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከውጭ ይገቡ የነበሩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች በሀገር ውስጥ በማምረት ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች የሚሰጡ የክብር ስጦታዎችን እያቀረበ ይገኛል።
በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን በፋሽንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ ላይ የማድረስ ጉጉት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አቶ ዘላለም የኬሬዠ ኢትዮጵያ መስራች ከመሆናቸው ባለፈ፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን መላው ዘርፍ በቴክኖሎጂ፣ በስልጠናና በጥሬ እቃ አቅርቦት እንዲሻሻል በንቃት እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት (ቆዳ) እና የሰው ኃይል በመጠቀም ኢትዮጵያን በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በመላው አፍሪካ ገበያዎች ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ ታላቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን የስራ መሪው በኩራት ተናግረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #amn
#የኢትዮጵያታምርት #ቆዳናየቆዳውጤቶች #ዘላለምመራዊ #ኢትዮጵያ #ፋሽን #የሀገርውስጥምርት #ethiopiatamrit #ethiopianfashion #leatherindustry

"ኢትዮጵያ ታምርት" የጎዳና ላይ ሩጫ
ነገ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል
#ethiopia | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር "ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 4ኛው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ነገ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።
ዓላማው
የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅና በራስ አቅም የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለገበያ ማሳየት ነው።
ተሳታፊዎ
ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና በግል የሚወዳደሩ ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ።
የገንዘብ ሽልማት
በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፦
1ኛ፦ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር
2ኛ፦ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር
3ኛ፦ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር
ይሄ ሩጫ ተራ ስፖርታዊ ውድድር አይደለም፤ የኢኮኖሚ ነጻነታችንን የምናውጅበት መድረክ ነው። 'ኢትዮጵያ ታምርት' በሚል መሪ ቃል የምናደርገው ይሄ ንቅናቄ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህላችንን ያሳድጋል። ነገ መስቀል አደባባይ የሚገኙ 15 ሺህ ሯጮች የሀገራቸውን ምርት እየለበሱ ለሀገራዊ ብልጽግና እንደሚሮጡ ጥርጥር የለኝም።
ነገ መስቀል አደባባይ ለሀገር ምርትና ለጤና እንሮጣለን
#getu #ethiopiatamirt #industryethiopia #10krun #addisababaevents #localproduction #economicgrowth #ethiopianathletics #ኢትዮጵያታምርት #የጎዳናላይሩጫ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
6 months ago
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የ"ኢትዮጵያ ታምርት" 2018 ንቅናቄን በይፋ አስጀምሩ
📌"ኢትዮጵያ ታምርት" ከግንዛቤ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋገረ፤የሀገሪቱ የማምረት አቅም ወደ 66 በመቶ አድጓል
#ethiopia | የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማነቃቃት የተጀመረው ሀገር አቀፍ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የመጀመራውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ምዕራፍ አጠናቆ ወደ "ድርጊት ምዕራፍ" መሸጋገሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት የ2018 በጀት ዓመት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ሲሆን፣ ንቅናቄው በሶስት ዋና ዋና የትግበራ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ከከፍተኛ አመራር እስከ ሰፊው ህዝብ ድረስ የነበረውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ሲሰራ መቆየቱን እና ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የተመዘገቡ ውጤቶች
መንግስት የወሰዳቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የግል ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ ማምጣታቸውን አቶ መላኩ አብራርተዋል።
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እና በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ለአምራች ኢንዱስትሪው የተሰጠው ትኩረት ዘርፉን ከነበረበት ዝቅተኛ አፈጻጸም እያወጣው ይገኛል ተብሏል።
በተለይም ከፖሊሲ፣ ከህግ ማዕቀፍ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የነበሩ ስር የሰደዱ ማነቆዎችን ለመፍታት በተወሰደው እርምጃ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል።
በዚህም መሰረት፡-
* በ2014 ዓ.ም፡ ከ50 በመቶ በታች (46%) ወርዶ የነበረው የማምረት አቅም፤
* በ2018 ዓ.ም (የመጀመሪያ 6 ወራት)፡ ወደ 66.3 በመቶ ማደግ ችሏል።
የመገናኛ ብዙሃን ሚና
የንቅናቄውን ዓላማና የተገኙ ለውጦችን ለህዝብ በማድረስ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በተለይም "ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖን ጨምሮ ሌሎች ኹነቶችን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ስኬታማ ስራ በመሰራቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ቀጣዩ የ"ድርጊት ምዕራፍ" የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በተግባር በመፍታትና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ በማሳደግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopiatamirt #industryminister #melakualebel #manufacturing #ethiopianeconomy #actionphase #ኢትዮጵያታምርት #ኢንዱስትሪ #ኢትዮጵያ

Comments