4 months ago
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የ"ኢትዮጵያ ታምርት" 2018 ንቅናቄን በይፋ አስጀምሩ
📌"ኢትዮጵያ ታምርት" ከግንዛቤ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋገረ፤የሀገሪቱ የማምረት አቅም ወደ 66 በመቶ አድጓል
#ethiopia | የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማነቃቃት የተጀመረው ሀገር አቀፍ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የመጀመራውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ምዕራፍ አጠናቆ ወደ "ድርጊት ምዕራፍ" መሸጋገሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት የ2018 በጀት ዓመት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ሲሆን፣ ንቅናቄው በሶስት ዋና ዋና የትግበራ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ከከፍተኛ አመራር እስከ ሰፊው ህዝብ ድረስ የነበረውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ሲሰራ መቆየቱን እና ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የተመዘገቡ ውጤቶች
መንግስት የወሰዳቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የግል ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ ማምጣታቸውን አቶ መላኩ አብራርተዋል።
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እና በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ለአምራች ኢንዱስትሪው የተሰጠው ትኩረት ዘርፉን ከነበረበት ዝቅተኛ አፈጻጸም እያወጣው ይገኛል ተብሏል።
በተለይም ከፖሊሲ፣ ከህግ ማዕቀፍ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የነበሩ ስር የሰደዱ ማነቆዎችን ለመፍታት በተወሰደው እርምጃ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል።
በዚህም መሰረት፡-
* በ2014 ዓ.ም፡ ከ50 በመቶ በታች (46%) ወርዶ የነበረው የማምረት አቅም፤
* በ2018 ዓ.ም (የመጀመሪያ 6 ወራት)፡ ወደ 66.3 በመቶ ማደግ ችሏል።
የመገናኛ ብዙሃን ሚና
የንቅናቄውን ዓላማና የተገኙ ለውጦችን ለህዝብ በማድረስ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በተለይም "ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖን ጨምሮ ሌሎች ኹነቶችን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ስኬታማ ስራ በመሰራቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ቀጣዩ የ"ድርጊት ምዕራፍ" የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በተግባር በመፍታትና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ በማሳደግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopiatamirt #industryminister #melakualebel #manufacturing #ethiopianeconomy #actionphase #ኢትዮጵያታምርት #ኢንዱስትሪ #ኢትዮጵያ