12 days ago
"በርበሬ" እና "አዝማሪ"ን ያካተተው አዲሱ ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ኢትዮጵያን በረሀብ ምሳሌነት የሚያነሳውን ክፍል ሰረዘ
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሚያታትመው የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት የ2026 እትም «በርበሬ» እና «አዝማሪ» የሚሉ የአማርኛ ቃላትን ያካተተ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን በረኃብ ምሳሌነት ያነሳ የነበረውን ክፍል ማስወገዱ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ምስክትል ኮሚሽነር ቢኒያም ታዬ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፣ «በርበሬ» እና «አዝማሪ» የሚሉት ቃላት መካተታቸው ከቃላቱ ጋር ተያይዘው ያሉ ትርጉሞችና ባህሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲዳሰሱ በር ይከፍታል።
ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም፤ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን በረኃብ የሚያነሱ ምሳሌዎች በአዲሶቹ መዝገበ ቃላት ላይ እንደሌሉ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ፤ ቀደም ሲል በነበረው የረኃብ ሁኔታ ላይ ተመስርተው የተሠሩ የመገናኛ ብዙኃን ሥራዎች አሁንም በሀገሪቱ ገጽታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አሁንም የቀድሞውን ገጽታ ለማሳየት መፈለጋቸው በቱሪዝም ኮሚሽኑ ሥራ ላይ ፈተና መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህንንም ሁኔታ በተቀናጀ ዘመቻ በመቀየር የመልካም ነገሮችን ማስተዋወቅ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
በመሰረት ሙሉ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 months ago
🎭 "እንዛታ" — ትውፊታዊ ቲያትር በአዲስ አበባ ይታያል !
በዉቢቱ ባህርዳርና በነገሥታት መዲና ጎንደር ከተማ የተመልካቾችን ልብ በመግዛት ከፍተኛ አድናቆትና ውዳሴ ያተረፈው "እንዛታ" ትውፊታዊ ቲያትር ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል ።
ይህ የመድረክ ድንቅ ሥራ በአዝማሪዎች ሕይወት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ዜማን ከፍልስፍና፣ ቃልን ከታሪክ፣ ባህልን ከዘመናዊ የመድረክ ጥበብ ጋር በልዩ ክህሎት ያጣመረ ትዉፊታዊ ቲያትር ነው።
📍 የእይታ መርሃ ግብር
🎭 ዛሬ እሁድ ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — ከቀኑ 8፡00
🎭 ማክሰኞ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — 11፡00
🎭 ሀሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም.
ሀገር ፍቅር ቲያትር — ከቀኑ 10፡30 ይታያል ።
ከቤተሰብዎ፣ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር በመታደም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክእና የመድረክ ጥበብ በአንድ የሚያገናኘውን ይህን ድንቅ ሥራ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል ።

3 months ago
አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሄል ዮሐንስ
ከግራውንድ ሆስተስ እስከ ታዋቂ ድምፃዊነት ከመቀጠር ወደ መቅጠር ፣ ከሰራተኝነት ወደ ጀኔራል ማናጀርነት ተሸጋግራም አገልግላለች፡፡ ራስ ሆቴል ፣ ጊዮን ሆቴል ፣ አርጀንቲና ፣ ታንዛኒያ እና ፊሊፕስ ኢምባሲ ፣ ሸበሌ ሆቴል ፣ ሂልተን ሆቴል ፎርሺፕ ትራቭል ፣ አነስ ያለች ሆቴል (በግሏ ከፍታ) ሰርታለች፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ድምፃዊነቱ አምርት በርካታ ስራዎቿን ለአድናቂዎቿ ያደረሰችው። የወይን ስፔሳሊስቷ አርቲስት ራሄል ዮሀንስ።
መዲናችን አዲስ አበባ ካዛንቺስ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ሚያዚያ 27 ቀን 1939 ዓ.ም ነው የተወለደችው፡፡ ለቤተሰቦቿ የበኩር ልጅ የሆነችው ራሄል ዮሀንስ ከታናሽ ወንድሟ ድምፃዊ ሰይፉ ዮሀንስ ጋር የቄስ ትምህርትን እስከ ዳዊት ቆጥራለች፡፡ አንጋፋው ድምፃዊ ሰይፉ ዮሀንስን “ሀና ሀና” በተሰኘ ስራው ታስታውሱታላችሁ፡፡
ራሄል የ 1ኛ ደረጃ ትምህርቷን በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት ተከታትላለች፡፡ ወደ ሆቴል ሙያ ያዘነበለችው ራሄል ዮሀንስ በራስ ሆቴል ለ 3ወር አጠቃላይ የመስተንግዶ ስነ ስርዓት ተምራለች፡፡ በመቀጠልም በምርጫዋ በጊዮን ሆቴል የወይን መስተንግዶ ትምህርትን ለሁለት አመታት ተከታትላ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡
ድምፃዊት ራሔል በሆቴል ቆይታዋም ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ባለስልጣናትን እና የአፍሪካ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት መሪዎችን አስተናግዳለች፡፡ እነ ጋማል አብዱል ናስር ፣ ሴኩ ቱሬ ፣ ክዋሚ ንኩርማ እና ሌሎችንም፡፡ ገና በልጅነቷ ሆስተስ (የበረራ አስተናጋጅ) የመሆን ህልም የነበራት በኋላ ግን ግራውንድ ሆስተስ (የሆቴል አስተናጋጅ) የሆነች ራሄል ዮሀንስ በሆቴሎቹ ባገለገለችባቸው ጊዜያት ውስጥ ከ 80 እስከ 200 ብር ይከፈላት ነበር፡፡ ቲፕ ተሰብበስቦ ለሁላችንም እንደ የደረጃችን በፐርሰንት ይከፈለን ነበርና ከደሞዛችን ይልቅ ይኸ ሻል ያለ ነበር ትላለች ራሔል ያንን ጊዜ ስታስታውሰው፡፡
አንድ ቀን ድምፃዊ ከተማ መኮንን እና ሌሎች አንጋፋ ሰዎች በቤቷ ተገኝተው ምግብ ከተመገቡ በኋላ በጋሽ ከተማ አጋፋሪነት ጨዋታው ደራ፡፡ እሱ ማሲንቆ ሲጫወት እሷም ማንጎራጎሯን ቀጠለች በድምጧ የተደነቁት ሰዎች ምግብ ቤቱን ትታ ዘፋኝ አንድትሆን ይገፋፏታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወደ ድምፃዊነት ሙያ ገባች፡፡
ከዚያም ከጥቂት አመታት በኋላ በ 70ዎቹ (1973/74ዓ.ም) የመጀመሪያ ስራዋን “አንቺ ባለድሪ” የተሰኘ አለበም ከሻምበል በላይነህ ጋር አወጣች፡፡ በወቅቱም ለዚህ ስራ አምባሳል ሙዚቃ ቤት 10,000 ብር ከፍሏታል፡፡ በዚህ ካሴት ውስጥ በግጥም – ይልማ ገብረአብ እና በዜማ – አበበ መለሰ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በ 1983 ዓ.ም ከታዋቂዎቹ የሀገር ባህል ተጨዋቾች ከባህሩ ቀኜ እና ከይርጋ ዱባለ ጋር የሰራቻቸው ዘፈኖችም በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡
አራዳ ፣ ትዝታ ፣ ምኒልክ እና ሀገሬ ኢትዮጵያ ያሉት ደግሞ በግሏ ከሰራቻቸው ተወዳጅ ዜማዎቿ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ አርቲስት ራሄል ዮሀንስ ሙዚቃ እስካቆመችበት ጊዜ ድረስ ወደ 13 የሚጠጉ አልበሞችን ሰርታለች፡፡ በነገራችን ላይ ድምፃዊት ራሄል ዮሀንስ ከዘፋኝነቷ ባሻገር የዜማ ደራሲም ጭምር ናት፡፡
ለአብነትም ምኒልክ ፣ ጀግናው ሰራዊት ፣ እንደ እየሩሳሌም (የአስናቀች ወርቁን በድጋሚ በራሷ ዜማ የሰራችው) እና ሌሎችንም ዜማ ደርሳለች፡፡ የመጨረሻ ስራዋ “ዘናበል” የሚል አልበሟ ሲሆን በያሬድ ተፈራ የተቀናበረ አልበም ነበር፡፡
በአንድ ወቅት እንዲህ ተብሎም ተገጥሞላት ነበር፡-
“አዝማሪ ይሏታል ራሄል ሆዴን
አዝማሪ ይሏታል ጭንቄ ራሄልን
ልጆች ለማሳደግ ያደረገችውን፡፡” በማለት ……..
የሁለት ወንድ እና አራት ሴት ልጆችን ያፈራቸው ድምፃዊ ራሔል አሁን ላይ አያት የሆነችው ራሄል በርከት ያሉ የልጅ ልጆችንም አይታለች፡፡
Ⓒ EthiopiaAnything

5 months ago
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደርና የ"እስክስታው ንጉሥ" መላኩ በላይ 50ኛ ዓመት ልደት ተከበረ
#fastmereja I የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜና ሙዚቃ በዓለም መድረክ ያስተዋወቀው የጥበብ ሰው ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያበረከተውን የዘለቀ አሻራ የሚዘክር የክብር መርሃ-ግብር 50ኛ ዓመት የልደቱ በዓል በማስመልከት ተካሄደ። "የእስክስታው ንጉሥ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው መላኩ፣ የሀገርን ባህል ከዘመናዊነት ጋር በማቀናጀትና ለወጣቱ ትውልድ የጥበብ ዕድል በመፍጠር ረገድ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታላቅ ምስጋና ቀርቦለታል።
ይህ የ50ኛ ዓመት ልደት የምስጋና ስነ-ሥርዓት እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሀያት ሬጄንሲ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን
ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ በኢትዮጵያ የጥበብ ታሪክ ውስጥ በተለይም "ኢትዮ-ከለር" የተሰኘውን የባህል ሙዚቃ ቡድን በማቋቋም፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት ረገድ የሚጠቀስ ስም አለው።
ከግል ስኬቱ ባለፈ፣ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘውን የ"ፈንድቃ" የባህል ማእከልን ከትንሽ አዝማሪ ቤትነት ወደ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መገኛነት በመለወጥ፣ የኢትዮጵያን ባህልና ማንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ (እንደ TED እና Lincoln Center ባሉ መድረኮች) እንዲታወቅ አድርጓል።
ከዚህም በተጨማሪ ከታዋቂው የማካሌስተር ኮሌጅ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውዝዋዜ ጥበብ በምርምርና በትምህርት እንዲደገፍ የላቀ ሚና ተጫውቷል።
እ.አ.አ በ2020 በCommunity Cultural Development ዘርፍ የክብር "Prince Claus Award" ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የባህል ዘርፍ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
ይህ በክብር እንግዶችና በጥበብ ወዳጆች ታጅቦ የተከናወነው የምስጋና ምሽት፣ ለሀገር ባለውለታው መላኩ በላይ የሚገባውን ክብር ለመስጠትና የጀመረውን የጥበብ ጉዞ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

Sponsored by
Surafel
7 months ago
“እንዛንታ” ትውፊታዊ ቲያትር ተመረቀ
#ethiopia | በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል፣ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ትውፊትና የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎችን ጥበባዊ ታሪክ የሚዘክረው “እንዛንታ” የተሰኘው ትውፊታዊ ቲያትር በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
በምረቃው መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የጥበብ ባለሙያዎችና የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተው የጥበብ ስራውን ተከታትለዋል።
በምረቃው ወቅት ንግግር ያደረጉት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ካሳ፣ እንዲህ ያሉ ትውፊታዊ ስራዎች የህዝብን ታሪክና ማንነት ጠብቆ ለማቆየት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ወይዘሮ የሺ አክለውም፣ “እንዛንታ” ቲያትር የክልሉን አልፎም የሀገሪቱን የቆዩ ባህላዊ እሴቶችና የአዝማሪዎችን የጥበብ ጉዞ ለዘመኑ ትውልድ በሚመጥን መልኩ ማቅረቡ ለዘርፉ ትልቅ እመርታ መሆኑን ጠቁመዋል። መንግስት እንዲህ ያሉ ማንነትን የሚገልጹ የጥበብ ስራዎች እንዲስፋፉና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል የሙሉዓለም የባህል ማዕከል ምክትል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረማርያም ይርጋ በበኩላቸው፣ ማዕከሉ የጥበብ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። “እንዛንታ” ቲያትር በውስጡ የያዘው የታሪክ ጥልቀትና የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ጥበባዊ አበርክቶ፣ ማዕከሉ ለሚያከናውናቸው የባህልና የኪነ-ጥበብ ስራዎች እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግል መሆኑን አብራርተዋል።
አቶ ገብረማርያም አክለውም፣ ቲያትሩ መመረቁ ብቻ ሳይሆን በቀጣይም ለተመልካች ቀርቦ የባህል ግንባታ ስራውን እንዲያግዝ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ይህ “እንዛንታ” የተሰኘው ትውፊታዊ ቲያትር በታሪክ አወቃቀሩና በአቀራረቡ የባህላዊ ኪነ-ጥበብን እሴት የጠበቀ ሲሆን፣ በተለይም ለጥበብ ስራው እንደ መነሻነት ያገለገሉት የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ታሪክ በጥልቀት የተዳሰሰበት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#enzanta #barbakanazmaris #bahirdar #ethiopianculture #artdiscussion #mulualemhall #culturalheritage #ethiopiantheatre #traditionalart

የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎችን ህይወት መነሻ ያደረገ ጥበባዊ አበርክቶና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የጥናት ውይይት ተካሄደ
#ethiopia | በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ለ“እንዛንታ” ተውኔት እንደ ግብዓት በሆኑት የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ዙሪያ የሚያተኩር የጥናት ውይይት ተካሂዷል ።
በመርሐግብሩ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ገብረማርያም ይርጋ አዝማሪ በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ የተለየ ቦታ ያለው የጥበብ ተሸካሚ መሆኑን ገልጸዋል ። አዝማሪው በመሰንቆ ዜማ ሲዘምር፣ በቃል ቅኔ ሲያወጣ፣ የህዝብን ሐሳብ፣ ደስታና ሐዘን ወደ ጥበብ ይቀይራል ሲሉ ተደምጠዋል ።
እነዚህ አዝማሪዎች በእንዛታ የቃል ብልሃት፣ ቀልድ፣ ምሳሌና አስተዋፅኦ የተሞላ ጥበብ ይታወቃሉ። ይገልጣሉ ። ያስተምራሉ ። ያሰርጻሉ።
“እንዛታ የአዝማሪነት ” ጥበብ መዝናኛ ብቻ አይደለም፤ የህዝብ አስተሳሰብን የሚገልጥ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን በቀልድና በቅኔ የሚያቀርብ፣ ታሪክን የሚያስታውስ እና ትውልድን የሚያስተምር ትልቅ የባህል ትምህርት ነው።
በእነዚህ አዝማሪዎች ዘፈንና ቅኔ ውስጥ ጥበብ፣ ሳቅ፣ ጥበቃ እና ማስተማር በአንድ ይገናኛሉ።
ዛሬ እኛ ለትዉፊታዊ ቲያትር የተጠና የአዝማሪነት ጥበብን መድረክ እና የታሪክን ድምፅ ለማስቀጠል፣ የአዝማሪዎችን ጥበብ ለማክበር እና ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ በመነሳሳት የተገለጥንበት ነዉ ብለዋል።
አቶ ገብረማርያም ይርጋ አክለዉ ባህል በመዘመር እንጂ በመዝጋት አይኖርም፤ በመካፈል እንጂ በመርሳት አይቆይም።
ስለዚህ የቀድሞውን ጥበብ እንድንያዝ፣ የዛሬን እንድንከብር እና የነገን እንድንገነባ የሚያግዝ ይሁን በማለት የእንዛታ አዝማሪዎች ድምፅ በህዝብ ልብ ውስጥ ዘላቂ እንዲሆን ለመደገፍና ለማክበር የተሰናዳ መሆኑን አብራርተዋል ።
መርሃ ግብሩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውይይቱም ላይ የዘርፉ ባለሙያዎችና የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል።

የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ጥበባዊ አበርክቶና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የጥናት ውይይት ተካሄደ
#ethiopia | በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ለ“እንዛንታ” ተውኔት እንደ ግብዓት በሆኑት የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ዙሪያ የሚያተኩር የጥናት ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረክ ላይ በዋናነት የአዝማሪነትን ሙያዊ እሴት፣ የታሪክ አወቃቀርና በዘርፉ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በጥልቀት ለመመርመር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የጥናት መድረክ በተለይ ለ“እንዛንታ” ተውኔት ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ታሪክና ጥበባዊ ጉዞ ለመዘከር እንደ መነሻ ተወስዷል።
በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት የባህላዊ ኪነ-ጥበብን እሴት ሳይበረዝ ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። ይህም ጥበባዊ ቅርሳችንን ከዘመኑ ጋር አዋህዶ ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
መርሃ ግብሩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውይይቱም ላይ የዘርፉ ባለሙያዎችና የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#enzanta #barbakanazmaris #bahirdar #ethiopianculture #artdiscussion #mulualemhall #culturalheritage #ethiopiantheatre #traditionalart
#ethiopia | በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ለ“እንዛንታ” ተውኔት እንደ ግብዓት በሆኑት የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ዙሪያ የሚያተኩር የጥናት ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረክ ላይ በዋናነት የአዝማሪነትን ሙያዊ እሴት፣ የታሪክ አወቃቀርና በዘርፉ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በጥልቀት ለመመርመር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የጥናት መድረክ በተለይ ለ“እንዛንታ” ተውኔት ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ታሪክና ጥበባዊ ጉዞ ለመዘከር እንደ መነሻ ተወስዷል።
በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት የባህላዊ ኪነ-ጥበብን እሴት ሳይበረዝ ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። ይህም ጥበባዊ ቅርሳችንን ከዘመኑ ጋር አዋህዶ ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
መርሃ ግብሩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውይይቱም ላይ የዘርፉ ባለሙያዎችና የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#enzanta #barbakanazmaris #bahirdar #ethiopianculture #artdiscussion #mulualemhall #culturalheritage #ethiopiantheatre #traditionalart
7 months ago
"እንዛታ"
— አዲስ ትውፊታዊ ቴአትር ነገ በባህር ዳር በድምቀት ይመረቃል!
#ethiopia | በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውና የአዝማሪዎችን እውነተኛ ሕይወት የሚዳስሰው "እንዛታ" የተሰኘ ድንቅ ትውፊታዊ ቴአትር ነገ ይመረቃል።
ቴአትሩ በጎንደር የሚገኙ አዝማሪዎች መንደር "ቡርቧክስ" ድረስ በመሄድ፣ የአዝማሪዎችን አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ በጥናት ላይ ተመስርቶ የቀረበ ነው።
የአዝማሪዎችን እውነተኛ የኑሮ ገጽታ፣ ሳቅ፣ ደስታና ሐዘን በመሰንቆ ክርና በአውታር መካከል የተደበቁ የሕይወት መንገዶችን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
# እንዛታ !!
ገብረማርያም ይርጋ #gebremaryam Yirga
የአብክመ ባህል ኪነጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት
#እንዛታ #ባህርዳር #ትውፊታዊቴአትር #አዝማሪ #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የእግዚአብሔር መላእክት ስለእኔ ደስ ሲላቸው አያለሁ🙏
ቅዱስ ፊልሞን አናጉንስጢስ በጭካኔውና በከሃዲነቱ ወደር የማይገኝለት የመኮንኑ አርያኖስ አዝማሪና አጫወች የነበረ ሰው ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ አናጉንስጢስ ማለት በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻህፍትን አሰምቶ የሚያነብ ማለት ነው፡፡
በአንድ አጋጣሚ መኮንኑ አናጉንስጢስ አስቃሎንን ጠርቶ ለአጵሎን ሠዋ አለው፡፡ አስቃሎንም ወደ ፊልሞን በመሄድ በእኔ ፈንታ ብትሠዋ አራት የወርቅ ዲናር እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ፊልሞንም በአስቃሎን ሀሳብ ተስማምቶ ልብስህን ስጠኝና ተሸፋፍኜ በአንተ ፈንታ እሠዋለሁ አለው፡፡ ፊልሞንም ሲገባም ዐውቀውት ምን ሆንክ አሉት፡፡ እርሱም በክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ አላቸው፡፡ አርያኖስም በሕይወት እንድትኖር ለአማልክት ሠዋ አለው፡፡ ፊልሞንም ክርስቶስ በስተቀር ሕይወት የለም አለው፡፡ መኮንኑ አርያኖስም ጥምቀትን ሳታገኝ ፈጥኜ እገድልሃለሁ፣ ተስፋህን ታጣለህ አለው፡፡
ፊልሞንም ይህን ሲሰማ የክርስትና ጥምቀትን ያድለው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ከሰማይ ብሩህ ደመና መጥቶ አጠመቀው፡፡ መኮንኑ በዚህ አፍሮ ምናልባት ፊልሞን ቢመለስ ብሎ ሦስት ወታደሮቹን እንዲደበድቡት አዘዘ፡፡ ቅዱስ ፊልሞንም የእግዚአብሔር መላእክት ስለእኔ ደስ ሲላቸው አያለሁና ከዚህ የከፋ ቢጸፉኝም እኔ አልፈራም አለ፡፡ ባላ ባለው ግንድ ላይ ሰቅለው በፍላጻዎች ቀጠቀጡት ነገር ግን ቅዱስ ፊልሞንን ጸጋ እግዚአብሔር ጠብቆት ምንም እንዳልነካው ሆነ፡፡ መኮንኑም እኔ እያየሁ በፍላጻዎቹ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ከፍላጻዎቹ አንዲቱ ተመልሳ የአርያኖስን ዐይን ነድፋ አሳወረችው፡፡
አርያኖስም በዚህ እጅግ ተናዶ ቅዱስ ፊልሞንን ከተሰቀለበት አውርደው ከአናጉንስጢስ አስቃሎን ጋር ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም አደረጉ፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን ገድላቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ የቅዱስ ፊልሞንና የአናጉንስጢስ አስቃሎን የሰማዕታቱም ሁሉ የከበረች በረከታቸው በሁላችን ላይ ትደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ገዳማውያን የቅዱሳንን ፈለግ ተከትለው ዓለም ከምትሰጣቸው ክብር ይልቅ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን ታግሰው መጋደልን መረጡ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውም እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

9 months ago
ያልተፈታ ቅኔ
……………
(ጋሻው ደበበ )
…………….
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
ደንቢያ -ተላከኝ
ፊት በር -ታዘዘኝ
አርማጭሆ -ግድም
ቋራም -‹እሺ› በለኝ
ለልሂቃን-ንገር ከሀሳብ አድነኝ፡፡
‹‹በዚህች ብላቴና -ቅኔ የታሰረ
ብዕሩን እንደ እንዝርት -ጧት ማታ እያሾረ
ይሄ ጉብል ወጣት -ከመንገድሽ ቢቀር
ደርሶ ላያስችልሽ -ላትጨክኝ ነገር
…ቅጣቱ ምንድነው? ››
ብሎ ለመጠየቅ -ጎርጎራስ አንሶ ነው?
አረ በአባ ታጠቅ -በቋራው አንበሳ!
የቡርቧክስ አዝማሪ-መሰንቆህን አንሳ!
ጎረቤት ጨከነ -ዝ…ም አለኝ በለሳ
ልክ እንደአያቶችሽ -እንደነገስታቱ፤
አገርሽን ፍለጋ
በ ‹ጎ› የሚጀምር - ቦታ ያገኙ ዘንድ
በራዕይ ተመርተው- አሀዱ እንዳሉቱ፤
የቅኔሽን መፍቻ-አንድ ቃል ንገሪኝ-እስኪ ባርባራቱ፡፡
‹‹ቃል ማለት- ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ገና ከከተራው -ከጥምቀቱ ቀድሞ
ሺ ጥቁር- እንግዳሽ -ውበትሽን ታድሞ
በምጥን ፈገግታ -በአርምሞ ታዝበሽ
በኩራት እርምጃ-የሄድሽው አቋርጠሸ
ዱካሽ ባረፈበት -ቅኔም ታስቀምጫለሽ ?
በውበትሽ ከንፎ-በፍቅርሽ እፍፍፍ ብሎ-
በአንቺ ያበደን ሰው፤
በቅኔ ሰንሰለት -ጠፍንጎ መፈተን
ምንኛ ቅጣት ነው?
አረ በአባ ታጠቅ ! ጃን ተከል ተላከኝ
ደንቢያ ወገራ
ቅዳሜ ገበያ
ማራኪ ‹እሺ› በለኝ
ቅኔዋን ትፍታና -ከልቧ-ታኑረኝ፡፡
‹‹ያቺ-ነገር እርሙ
ያች -ፀበል ሀኪሙ
ያች - አርብ ሮብ -ብርቁ
ያቺ -የሰንበት ፈርጥ
የአባይ ዳር ቄጤማ
የአዲስ አለም- ቀንበጥ››
ተብሎ -የተዘመረው
የቅኔሽ መግቢያ ነው?
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ -ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ -ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ከጥምቀተ ባህሩ-ማልጄ እሄዳለሁ
በቅዱሱ መሬት- ታቦት እሸኛለሁ
የጥንካሬና የክብርሽን ምስጢር -ተገንዝቤዋለሁ!
ፀበሉን አስረጭኝ-እጠመቀዋለሁ፡፡
የልብሽ መገኛ-ፍቅር መዳረሻው
የሽር ጉድ ወጉ-የአብሮነት ምምሻው
አንቺነትሽን ማወቅ -ከሆነ ነገሩ
እምቢ! ጎንደር ልቅር-አልወጣም ካገሩ!
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ያልተፈታ ቅኔ እያብሰለሰልኩኝ -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ፍቻ…!!
……………
(ጋሻው ደበበ )
…………….
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
ደንቢያ -ተላከኝ
ፊት በር -ታዘዘኝ
አርማጭሆ -ግድም
ቋራም -‹እሺ› በለኝ
ለልሂቃን-ንገር ከሀሳብ አድነኝ፡፡
‹‹በዚህች ብላቴና -ቅኔ የታሰረ
ብዕሩን እንደ እንዝርት -ጧት ማታ እያሾረ
ይሄ ጉብል ወጣት -ከመንገድሽ ቢቀር
ደርሶ ላያስችልሽ -ላትጨክኝ ነገር
…ቅጣቱ ምንድነው? ››
ብሎ ለመጠየቅ -ጎርጎራስ አንሶ ነው?
አረ በአባ ታጠቅ -በቋራው አንበሳ!
የቡርቧክስ አዝማሪ-መሰንቆህን አንሳ!
ጎረቤት ጨከነ -ዝ…ም አለኝ በለሳ
ልክ እንደአያቶችሽ -እንደነገስታቱ፤
አገርሽን ፍለጋ
በ ‹ጎ› የሚጀምር - ቦታ ያገኙ ዘንድ
በራዕይ ተመርተው- አሀዱ እንዳሉቱ፤
የቅኔሽን መፍቻ-አንድ ቃል ንገሪኝ-እስኪ ባርባራቱ፡፡
‹‹ቃል ማለት- ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ገና ከከተራው -ከጥምቀቱ ቀድሞ
ሺ ጥቁር- እንግዳሽ -ውበትሽን ታድሞ
በምጥን ፈገግታ -በአርምሞ ታዝበሽ
በኩራት እርምጃ-የሄድሽው አቋርጠሸ
ዱካሽ ባረፈበት -ቅኔም ታስቀምጫለሽ ?
በውበትሽ ከንፎ-በፍቅርሽ እፍፍፍ ብሎ-
በአንቺ ያበደን ሰው፤
በቅኔ ሰንሰለት -ጠፍንጎ መፈተን
ምንኛ ቅጣት ነው?
አረ በአባ ታጠቅ ! ጃን ተከል ተላከኝ
ደንቢያ ወገራ
ቅዳሜ ገበያ
ማራኪ ‹እሺ› በለኝ
ቅኔዋን ትፍታና -ከልቧ-ታኑረኝ፡፡
‹‹ያቺ-ነገር እርሙ
ያች -ፀበል ሀኪሙ
ያች - አርብ ሮብ -ብርቁ
ያቺ -የሰንበት ፈርጥ
የአባይ ዳር ቄጤማ
የአዲስ አለም- ቀንበጥ››
ተብሎ -የተዘመረው
የቅኔሽ መግቢያ ነው?
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ -ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ -ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ከጥምቀተ ባህሩ-ማልጄ እሄዳለሁ
በቅዱሱ መሬት- ታቦት እሸኛለሁ
የጥንካሬና የክብርሽን ምስጢር -ተገንዝቤዋለሁ!
ፀበሉን አስረጭኝ-እጠመቀዋለሁ፡፡
የልብሽ መገኛ-ፍቅር መዳረሻው
የሽር ጉድ ወጉ-የአብሮነት ምምሻው
አንቺነትሽን ማወቅ -ከሆነ ነገሩ
እምቢ! ጎንደር ልቅር-አልወጣም ካገሩ!
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ያልተፈታ ቅኔ እያብሰለሰልኩኝ -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ፍቻ…!!
9 months ago
የአርቲስት ያየህይራድ አላምረው (1957-2017)÷ መዘክር እና የስብስቦቹ ቤተመጻሕፍት፤
(ሠርጸ ፍሬስብሐት)
አጭር ማስታወሻ
#ethiopia | ኹላችን በምናውቀው ታሪኩ፤ ያየህይራድ አላምረው፤ የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፕሮዲውሰር እንዲያም ሲል የታላላቅ ሙዚቃዊ ፕሮጀክቶች ነዳፊ ኢንተርፕረነር ነበር፡፡ ለብዙዎቻችን በሚያስገርም እና በሚያስደንቅ፣ ብዙም ባልተነገረለት፣ ጥቂት የቅርቦቹ በኾኑ ወዳጆቹ እና በቤተሰቦቹ ዘንድ ብቻ በሚታወቅ ልምዱ ደግሞ፤ የንባብ ፍቅሩን ብዙ እጥፍ የሚያስከነዳ መጽሐፍ ሰብሳቢነቱ አስደናቂ ነበር፡፡
ከኅልፈቱ በኋላ የተገለጸው ምሥጢሩ ይህ መጻሕፍትን እጅግ አድርጎ የመውደዱ ነገር ነው ቢባል ማጋነን አይኾንም፡፡ “ምን ሲያደርግ ሰበሰባቸው?” የሚያስብሉ መጻሕፍትን እና ያልታተሙ መዛግብትን ሰብስቧል፡፡ የኅልፈቱ ዜና ከተሰማበት ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀደም ባሉ ቀናት የወጡ ዐዳዲስ መጻሕፍትን ሳይቀር ገዝቶ እያነበበ ነበር፡፡ እነዚህን መጻሕፍት በወጉ አደራጅቶ የሚያስቀምጥበት ቤት እንደሚያስፈልገው ለቤቶች ኮርፖሬሽን ማመልከቻ እስከመጻፍ ባደረሰ ፍቅር፣ መጻሕፍቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ቢጠበውም እንኳ፣ መጻሕፍትን ከመሰብሰብ ግን አልቦዘነም፡፡
ምናልባት የግጥም ድርሰቶቹ ጠለቅ ማለት፣ የሀገር ፍቅርን፣ ታሪክን፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን፣ ለየት ያሉ የሕይወት ፍልስፍናዎችን እንዲያነሳ ሰበቡ ከንባብ ልምዱ የተነሳ ነበርን? ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ፣ በሕይወት ዘመኑ ሙሉ የሰበሰባቸውን መጻሕፍት አግኝተን ተደንቀናል፡፡
በአንድ መልኩ በክዋኔ ጥበባት ባለሙያዎች (በከያንያን) ልማድ ውስጥ “እምብዛም አይስተዋልም” የሚባለውን የንባብን ጉዳይ፣ “ለካ እንዲህ በጥልቀት የሚያነበም አለ፤” እንድንል የ“ቆምታ” ዕድል ፈጥሮልናል፡፡
እንዲህ ለመኾን መቼም መሠረት ያስፈልጋል፡፡ መሠረቱ ከወላጆቹ፣ በተለይም ከወታደር አባቱ ከሻለቃ አላምረው መንገሻ የተነሳ ይመስላል፡፡ የእናቱ የወ/ሮ አዳም ከበደ አስተዋጽዖም ለያየህይራድ አላምረው በሀገር ፍቅር የነደደ ማንነት የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡
የወታደሮች ካምፕ (ሚሊተሪ ካምፕ) የነበረው፣ የጦር ሠራዊት የሙዚቃ ክፍልን ዕያየ ለማደግ ዕድል የሠጠው የልደታ አቅራቢያው የቶሎሣ ሠፈር ልጅ መኾን በራሱ፣ የሙዚቃንም የሀገር ፍቅርንም አዛንቆ ለማደጉ ሰበብ ሳይኾን ይቀራል? የተማረባቸው ተማሪ ቤቶች÷ ተስፋ ኮከብ እና ልዑል መኮንን ከስማቸው በሚነሣ ማንነት፣ ያየህይራድን በሀገር እና በጥበብ ፍቅር አንጾ፣ በንባብ ልምድ ቀርጾ ለማሳደግ የሚበቃ የተማሪ ቤት ባህል የዘረጉ ነበሩ፡፡
እንዲያውም፤ ያየህይራድ ራሱ እንደገለጸው፤ ከዘፈን ግጥም የመጻፍ ዝንባሌው አስቀድሞ የጻፋት አንዲት የሬዲዮ ድራማ፣ በእሑድ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ የመተላለፍ ዕድል ማግኘቷ፣ በተማሪ ቤቱ መምህራን እና በተማሪ ጓደኞቹ ዘንድ ዝነኛ እና የወደፊት በጥበብ ሕይወት የመዝለቅ ተስፋውን በሩቅ እንዲያይ ዕድል የሠጠ የልጅነት አጋጣሚም ነበር ማለት ይቻላል፡፡
የጥበብ ሥራ ከክዋኔው በላይ፣ ከማጊያጊያጥ ከማሠማመሩ በላይ ፈጠራው እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ መንገድ እና ሥልቱ የማይታወቅ፣ በቀመር የማይሠላ፣ ዛሬ የሔዱበት መንገድ ለነገው የማይሠራ፣ በየቀኑ ተአምር የመጠበቅ ያህል ከባድ ጉዳይ ነው፡፡
በተለይ እንደ ሥነ ግጥም ያለው፣ ከግጥምም፤ ለዜማ ወይም ለሙዚቃ የሚኾን ግጥምን መጻፍ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ለዜማ የሚኾን ግጥምን የመድረስን ሥራ ከባድ የሚያደርገው፣ ግጥም ራሱ ዜማዊ መኾኑ ሲኾን፣ ይሄው ራሱ ሙዚቃዊ የኾነው ግጥም፣ ዜማዊ ሥልጣኑ ከፍ ባለው ሙዚቃ ውስጥ “ና ግባ” ሲባል፣ የራሱ መግደርደር እና እምቢ ባይነት ስላለው ነው፡፡ ግጥሙ ለዜማ ሥልጣን ለመሸነፍ ግዴታ አለበት፡፡
ዜማ ባወጣለት ሐዲድ ለመጓዝ ይገደዳል፡፡ ለዜማው ምጣኔ ሲባል ቃል ይቆረጣል፡፡ ቅርፁ እንዲያጥር ወይም እንዲረዝም ይደረጋል፡፡ የራሱን ምት ትቶ፣ የሙዚቃውን ሥልተ ምት፣ ባር እና ሪዝም እንዲከተል ይገደዳል፡፡
በብዙ የሚያከራክር ቢኾንም፤(ከዜማ ወደ ግጥም ድርሰት መምጣት ይሻላል? ወይስ ግጥሙን ወደ ዜማ መተርጎም ይሻላል? የሚለውን የማይቋጭ ክርክር ለጊዜው እናቆየውና፤) የዜማ ግጥም ጸሐፊ የኾነ ሰው፣ የዜማን ልሣን ወደ ቃል የመተርጎም ችሎታ የታደለ ቢኾን ይበልጥ ይሳካለታል፡፡
እንዲህ ያለው ተሠጥዖ ለገጣሚዎች ኹሉ የተሠጠ አይመስልም፡፡ የራሳቸውን የቃል እና የቤት ነጻነት ለሚፈልጉ ባለቅኔዎች፣ ይህ ዓይነቱ የሙዚቃዊ ዜማ ሥልጣን አይዋጥላቸውም፡፡ በቅኔያዊ መራቀቃቸው እጅግ የሚያስደንቁን ጠቢባን፣ ወደ ሙዚቃዊው የዜማ ግጥም ሲመጡ ግር የሚላቸው ለዚህ ነው፡፡
ያየህ ይራድ አላመረው፤ የዚህ ምሥጢር የተገለጠለት ድንቅ የዘፈን ግጥም ደራሲ ነው፡፡ በጻፋቸው የዘፈን ዜማ ግጥሞች ላይ ኹሉ የምናየው ጸጋው፣ የዜማን ልሳን በቃል የመተርጎም ችሎታውን ነው፡፡ ይህንንም በሕይወት ታሪኩ ላይ ለተጠቀሱት ድምጻውያን በሠጣቸው ሥራዎች ላይ ኹሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃዊ ባህል ውስጥ ኾኖ የዘፈን ግጥም ጸሐፊ መኾን ሌላም ከባድ ነገር አለው፡፡ የጥንታዊ ሕዝብ ጠንካራ የገጣሚነት ጣጣ፡፡ በተለምዶ “ጥንታዊ ሕዝቦች ቀልድ እና ግጥም ዐዋቂዎች ናቸው፤” ይባላል፡፡
ለዚህም የመካከለኛው ምሥራቅ ጥንታውያን ሀገራትን፣ እና ኢትዮጵያንን ምሣሌ የሚያደርጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የኹሉንም እንተወውና የሀገራችን የገጣሚነት ባህል ጠንካራነቱ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ጋሽ ጸጋዬ ገብረ መድኅን እንዳሉት “ኢትዮጵያዊ፤ ከአንቀልባው እስከ መቃብሩ በግጥም የተከበበ ነው፤” ጭራሽ፣ አዝማሪው የሚያዜመው ግጥም አልበቃ ብሎት፣ “ተቀበል” ብሎ ግጥም የሚሠጥ ሕዝብ ነው፡፡ እዚህ ገጣሚ ሕዝብ መሐል፣ አንጀት አርስ የዘፈን ግጥም ጸሐፊ ኾኖ መገኘት እጅግ ከባዱ ፈተና ነው፡፡
የያየህይራድ አላምረውን የጥበብ ሕይወት እጅግ እንድናደንቅ የሚያደርጉን ጉዳዮች ይሄንን መሠረትም ሊሰቱት አይገባም፡፡ ኹሉም የፈጠራ ጉዞዎች የየራሳቸው ፈተና ያለባቸው ቢኾንም፣ የዘፈን ግጥም ደራሲነት የሚጨምራቸው፣ ከሌላኛው የሙዚቃ ጥበብ ጓዝ እና ቅንጣቶች የሚነሱ ፈተናዎች አሉበት፡፡
እንደ ያየህ ይራድ አላመረው ያሉትን የዘፈን ግጥም ደራሲዎች እጅግ እንድናደንቃቸው የምንገደደው በዚህ እና ከራሱ ከገጣሚነት ችሎታቸው በሚመነጭ ጠቢብነታቸው ምክንያት ነው፡፡ የሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ፣ የተዘራ ኃይለ ሚካኤል፣ የተስፋዬ አበበ፣ የሸዋ ሉል መንግሥቱ፣ የዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ የይልማ ገብረ አብ፣ የሙሉጌታ ተስፋዬ፣ የተመስገን ተካ እና የሌሎችም ታላላቅ የዘፈን ግጥም ደራስያን፤ የዜማ ግጥም ደራሲነት ጉዞ መንግድ፣ ሥልቱ እና ዐቅዱ ይሄንኑ ይመስላል፡፡
ያየህ ይራድ፤ ዜማን ወደ ግጥም የመተርጎም ሥራን ብቻ ሳይኾን፤ ዜማን እና ግጥምን በአንድ ላይ የመፍጠር ሥራ የሠራባቸው የሙዚቃ ሥራዎችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ዜማ እና ግጥም መንታ ኾነው ከአንድ የፈጠራ ሰው ሲወለዱ የሚታይ ሌላ ውበትም አለ፡፡
ታላቁ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ ፕሮዲውሰር እና የትላልቅ ሙዚቃዊ ፕሮጀክቶች አዘጋጅ የነበረው፤ ያያየህ ይራድ አላምረው፤ ከበርካታ የድርሰት ሥራዎቹ መካከል፤
ለኩኩ ስብስቤ (“ይቺ ነች ሀገሬ” ያለበትን አልበም፤ በርካታ ሥራዎች ግጥም፤ በኋላ ደግሞ “የአፍሪካ ገናና” አልበም ውስጥ ያሉ ድርሰቶችን)፣
ለአስቴር ዐወቀ(የ“ሰበቡ” አልበም ሙሉ ድርሰት)፣
ለዳምጠው አየለ፣
ለኤልያስ ተባባል (“ቅሪብኝ”)፣
ለፀሐይ ዮሐንስ፣
ለቴዎድሮስ ታደሰ፣
ለተሾመ አሰግድ፣
ለተሾመ ወልዴ፣
ለኃይልዬ ታደሰ (ይሞታል ወይ አልበም ፕሮዲውሰሩ ራሱ ያየህ ይራድ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ አምላክ እና ይሞታል ወይ የራሱ የያየህ ይራድ ድርሰቶች ናቸው፡፡
ለጽጌሮማን አስናቀ (ባቲ)፣
ለጸጋቸው ኃይለ ኢየሱስ (ለመለም)፣
ለታደለ ሮባ እና ለብርሃኑ ተዘራ፣
ለደረጀ ደገፋው፣
ለጌራወርቅ ነቅዓ ጥበብ፣ እና
በመጨረሻ ደግሞ፤ “ቆሜ ልመርቅሽ” የጥላሁን ገሠሠ አልበም ላይ ራሱን “ቆሜ ልመርቅሽ”ን ጨምሮ የአልበሙን ድርሰት የሠራው ያየህ ይራድ አላምረው ነበር፡፡
ያየህይራድ፤ በተምሣሌት እና በፈሊጥ የበለጸጉ ግጥማዊ ይዘቶችን እጅግ ይወዳል፡፡ በተለይም የአዝማሪዎችን የግጥም ሥልት አጅግ አድናቂ ሙዚቀኛ ነው፡፡ በአገጣጠም ሥልቶቹ ውስጥ የአዝማሪዎችን የግጥም መንገድ የተከተለባቸው ሥራዎች በርካታ ናቸው፡፡
ለማርታ አሻጋሪ፣ ለተሾመ አሰግድ፣ ለበዛወርቅ አስፋው እና ለኤልያስ ተባባል የሠጣቸው ድርሰቶች፤ ይህንን ፍላጎቱን በይበልጥ ጎልተው እንዲወጡ ያደረገባቸው ሥራዎቹ ናቸው፡፡ በአስቴር ዐወቀ ሰበቡ አልበም ውስጥ የፎክ ግጥሞችን መቀላቀሉ የዚህ አዝማሚያው ማሣያ ነው፡፡ ምናልባት፤ ታላቁን የባህል ጥበበኛ እና አዝማሪ ባሕሩ ቀኜን የማድነቁ እና ሥራዎቻችው ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ እና እንዲሸለሙ የማድረጉ ፍላጎትም ከዚህ የረዥም ጊዜ ጥረቱ የመነጨ ሊኾን ይችላል፡፡
በማኅበራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ በርካታ ሥራዎችንም ሠርቷል፡፡ በተለይ “እንኖራለን ገና” አልበም፤ ፕሮጀክቱን ከመምራት እስከ ድርሰት ትልቅ ሥራ የሠራበት አልበም ነው፡፡ ይህ አልበም፤ አንድን ማኅበረሰባዊ መልእክት በጥበብ ለማቅረብ ዘወትር የምንጠቀማቸውን የተሰለቹ መንገዶች እንደገና እንድንመረምር፣ በፖፕ ሙዚቃ ቅርጽ እና ደረጃ መልእክቱ ቀጥተኛ ትምህርት ሳይኾን፣ በጥበብ የተዋዛ መኾን እንደሚችል ያሣየበት ሥራው ነው፡፡
ለዚህ አልበም ስኬት፣ የሙዚቃ ባለሙያዎቹ እና የድምጻውያኑ አስተዋጽዖ ምንም ምትክ የማይገኝለት ቢኾንም፤ የፕሮዳክሽን አቅጣጫውን እና ፍልስፍናውን የመወሰን ሥራው አልበሙን እጅግ የተዋጣለት ያደርገዋል፡፡ ዛሬ ፍቅረዐዲስ ነቅዓ ጥበብ የተጫወተቺውን በዚያ አልበም ውስጥ የተካተተውን የዶ/ር ተሸገር ሺፈራው ድርሰት የኾነውን ሙዚቃ፣ ለኤች.አይ.ቪ. የተሠራ ሥራ ነው ብለን ብንናገር ብዙ ሰው እውነት አይመስለውም፡፡
ለአብነት ያህል እሱን አነሳን እንጂ፣ በዚህ አልበም ላይ የተካተቱት፤ የንዋይ ደበበ፣ የአስቴር ዐወቀ፣ የበዛወርቅ እና የኤልያስ፣ የቴዎድሮስ ታደሰ፣ የኄኖክ መሐሪ፣ የጼዴንያ ገብረ ማርቆስ፣ የዳዊት መለሰ… ሥራዎች ይሄንኑ እውነት የሚያረጋግጡልን ሥራዎች ናቸው፡፡
የዚሁ አልበም ማስተዋወቂያ ሌላ ሥራ ኾኖ የወጣው፤ ዘሪቱ ከበደ፣ አብነት አጎናፍር፣ ጆኒ ራጋ የተጫወቱት “መኖርህን ሌሎች ይሻሉ ይፈልጋሉ” የሚለው መዝሙር የግጥም ድርሰት ያየህ ይራድ አላምረው ከኤልያስ መልካ ጋር የጻፈው ነው፡፡ የመልእክት ጥልቀቱ ከኤልያስ ኅልፈት ጋር ተያይዞ በሰፊው የተተርኳል፡፡ ነገር ግን፤ የኤልያስ መልካ እና የያየህ ይራድ አላምረው ስሜት እና ሐሳብ ምን ያህል ውሕደት እንደነበረው ለማየት በአብነት የሚጠቀስ ድንቅ ሥራ ነው፡፤ የዚህ ሙዚቃ በእነዚህ ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቹ ውስጥ የሚታየው የጥበብ ልቀት፤ ማኅበራዊ ጉዳይን ርእሳቸው አድረገው የሚነሱ ሥራዎች፣ መዝሙር መሳይ ብቻ ሳይኾን፣ የዘመኑን የፖፕ ሙዚቃ ቅርጽ ተሸክመው፣ በጥበብ ልቀው መሠራት እንደሚችሉ መረጋገጫ እና ማስተማሪያ ጭምር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በያየህ ይራድ ድርሰት ውስጥ የትልቅ ብዕሩ መገለጫ ነች፡፡ ከሀገር ውጪ በነበረው ሕይወት ናፍቆት ብቻ የተፈጠረች ጉዳይ አይደለቺም “ኢትዮጵያ” ለያየህ ይራድ አላምረው፡፡ እንዲያውም፤ በወታደር ልጅነቱ፣ በወታደር ሠፈር በማደጉ የተፈጠረች “ከ-ይቺ ነች ሀገሬ” እስከ “ቆሜ ልመርቅሽ የዘለቀች፣ የዕድሜ ልክ ጉዳዩ ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ ትንቢትም ተናግሮላል፡፡
“የሺ ዓመታት የአፍሪቃ ገናና፣
ተከብራ የኖረች በዓለም ዙሪያ ገና፤
ኢትዮጵያ ዳግም እንደገና፣
ይታየኛል ያገር አውራ ኾና፤” (ኩኩ ሰብስቤ)
“የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር፣
ይጥልላታል ጠላቷን እባንዲራው ሥር፤
አይቀር አንድ ቀን መድረሱ ወቅቱን ጠብቆ፣
ማሪኝ ይላታል ጠላቷ እግሯ ላይ ወድቆ፤” (ኃይልዬ ታደሠ)
“አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
ማግስቱን ይውሰደኝ ዐሥር ሞት ይምጣና፤”
(ቆሜ ልመርቅሽ-ጥላሁን ገሠሠ)
እነ “አንድ ብር ለአንድ” ወገን፣ “ሀገር ፍቅር ክብር፤ ኢትዮጵያ በፊትም ወደፊትም” የተሰኙ ትላልቅ ሀገራዊ መድረኮችን እና ፕሮጀክቶችን በመምራት፣ ከዩ.ኤስ.አይ.ዲ.፣ ከአሜሪካን ኤምባሲ፣ ከዚ.ዲ.ሲ.፣ ከወርልድ ባንክ፣ ከናይክ ፋውንዴሽን ጋር ሠርቷል፡፡
1957 ዓ.ም. ወደዚህች ዓለም መጥቶ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በድንገት ከዚህች ዓለም በሞት የተለየው ያየህይራድ አላምረው፣ በዚህች አጭር ማስታወሻ ተዘርዝረው የማያልቁ በጥበብ ሰውነቱ በግዝፈት ምንጊዜም የሚያስጠሩትን በርካታ ሥራዎች ሠርቶ አፏል፡፡
በሥራዎቹ ምንጊዜም የመታወሱ ነገር አንድና ኹሉት ባይኖረውም፣ በቤተሰቦቹ አማካኝነት፣ ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) የሚሠጡት(የሚበረከቱት) የዕድሜ ልክ ስብስብ መጻሕፍቱ እና እነዚህን መጻሕፍት ተረክቦ የሚያስነብብበት የማንበቢያ ክፍል ደግሞ፤ በልዩ ኹኔታ እንዲታወስ እንደሚያደርገው አይጠረጠርም፡፡
አንባብያን፤ በዚህ በያየህይራድ አላምረው ስም በተሰየመ የንባብ ክፍል ውስጥ የሚያሳልፉት ጊዜ ከንባብም በላይ ነው፡፡ የዚህን ታላቅ ደራሲ ቀልብ መግዛት የቻሉ፣ የእርሱ መዳፍ ይዟቸው፣ የዐይን ትኩረቱ ያረፈባቸውን መጻሕፍት ማንበብ ትርጉሙ “እንዲህ እና እንዲያ ነው” የሚባል አይደለም፡፡
ይህ ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. መርቀን የምንከፍተው “የአርቲስት ያየህይራድ አላምረው÷መዘክር እና የስብስቦቹ ቤተመጻሕፍት”፤ ሌሎች ጠቢባንም እንዲሁ ሥራዎቻቸውን እና የመጻሕፍት ስብስቦቻቸውን ለዚህ ታላቅ ተቋም እንዲሠጡም ያነሣሣል የሚል ተስፋ አለን፡፡ በመጨረሻም፤ ይህ እንዲኾን ትልቁን ድርሻ የተወጡትን፣ የያየህይራድ አላምረውን ቤተሰቦች፣ በተለይም እኅቱን ወ/ሮ ኂሩት አላምረውን፣ መጻሕፍቱ በዚህ ተቋም እንዲህ ያለ ሥፍራ አግኝተው ለትውልድ የሚተርፍ ቁም ነገር እንዲሠራባቸው ላደረጉት ጥረት እና ልግስና፤ ተቋማችን እጅግ አድርጎ ያመሰግናል፡፡

1 year ago
ፈንድቃ አዲስ የሚያስገነባውን ህንፃ ይፋ አደረገ
በካርሎ ራትቲ አሶሺያቲ የሚመራው በዓለም ታዋቂ የሆነ የኢጣሊያ የስነ ሕንፃ ተቋም ለአዲሱ የፈንድቃ ህንፃ ንድፍ ይፋ አድርጓል። ፈንድቃ የባህል ማዕከል በጥቅምት 2017 ከፈረሰ በኋላ በቦታው የራሱን ህንጻ እንዲሰራ ቦታው ለፈንድቃ መሰጠቱ ይታወሳል።
ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ፈንድቃ ከሀያት ሬጀንሲ ጋር በመተባበር ኮንሰርቶችንና እና አዝማሪ ፕሮግራሞችን እያቀረ ይገኛል።

የአዉሮጳ ዘማቹ ቃኘዉ ክፍለጦር ሲታወስ !
“አጨደው ከመረው ወቃው እንደ ገብስ፤
የኢትዮጵያ አርበኛ ኮሪያ ድረስ።”
ከዛሬ 75 ዓመታት በፊት ነበር ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያን በመውረር የጦርነት አዋጅ ያስነገረችው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያን የጠብ ጫሪነት ተግባሯን በአስቸኳይ እንድትታመኑ ወረራዋን እንድታቆም ወደ ሰላማዊ ህይወቷ እንድትመለስ አስጠነቀቀ ሰሜን ኮሪያ አሻፈረኝ አለች ።
የጸጥታው ምክር ቤትም ለዓለም ሰላም ሲባል ወረራው ለመቀልበስ ውሳኔውን የደገፉ አሥራ ስድስት የዓለም ሀገራት ወታደሮቻቸውን ወደ ስፍራው እንዲልኩ ጥሪ አቀረበ ።ከነዚህ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ ትገኝበታለች ።
ከአሥር መድፈኛ ሻለቆች ተውጣጥቶ 1122 መኮንኖችንና ወታደሮችን ያካተተ አዲስ “ቃኘው ሻለቃ” የተሰኘ ክፍለጦር ተቋቋመና ስምንት ወራት የፈጀ ስልጠና ሲወስድ ቆየ ።
በመጨረሻም ሚያዚያ 5 ቀን 1943 ዓ.ም ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ባሉበት የቃኘው ሻለቃ አባላት ችሎታቸውን ለማሳየት ወታደራዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡
ንጉሡም፡- “እነሆ በጋራ ደኅንነት መርሕ መሠረት፤ እጅግ ቅዱስ ለሆነው ለዓለም ሰላም ዘብ ልትቆሙ፣ የዓለምን ግማሽ የሚሆን ጉዞ ትጓዛላችሁ። ሂዱና ወራሪዎችን ድል ንሱዋቸው። በኮሪያ ልሳነ ምድርም ሕግና ሥርዓትን አስከብሩ፡፡ ይሄን ሰንደቅ ዓላማ መመሪያ አድርጋችሁ እንድትዘምቱ፣ በተሰማራችሁበት ቦታ ጀግንነት ሠርታችሁ በደረታችሁ ላይ ልዩ ምልክት አድርጋችሁ በኩራት ስትመለሱ በአደራ የሰጠናችሁን አርማ መልሳችሁ እንድታስረክቡን” በማለት ነበርሞራል ሰጥተው በክብር የሸኟቸው፡፡
ከጀግኖች ምድር የበቀሉት 1122 የመጀመሪያው ዙር የቃኘው ሻለቃ አባላት “እልም አለ ባቡሩ እልም አለ ባቡሩ፣ ወጣቱን ይዞ በሙሉ” በሚለዉ በድምፃዊ ካሳ ተሰማ ታጅቦ በባቡር ወደ ጅቡቲ ከኋላም በመርከብ ፑዛን ወደተሰኘችው የኮሪያ የወደብ ከተማ ደረሱና ፕሬዚዳንት ሲንግ ማን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው በሁለተኛው ዙርም ተጎዘ ሶስተኛዉም ሰለሰ በአጠቃላይ በአምስት ዙር 6037 ወታደሮች የቃኘው አባላት ኮሪያ ዘምተዋል ።
ታዲያ በወቅቱ አንድም ከአፍሪካ የዘመቱ ብቸኛ ወታደሮች በመሆናቸው ሁለትም ነጮች ለጥቁር በነበራቸው ንቀት ይህን ጦርነት ይቋቋማሉ ብሎ ያመነ አልነበረም አንዳንዶቹም እንዲያዉ ለአመል እንጂ የት የለመዱትን ዉጊያ ተጠቅመው ድል ሊያስመዘግቡ እያለ ተሳለቀ፡፡
የማይቀረው የሜዳ ላይ ዉጊያዉ ተጀመረ አለም የጠበቀዉ ቀርቶ ያላሰበዉ ሆነ የጦረኞቹ ደም በዉስጣቸዉ ያለዉ የቃኘዉ ክፍለጦር ወታደሮች ጠላትን ያርበደብዱት ገቡ ።
በኮሪያው ዘመቻ ወቅት ዋና ዋና ውጊያዎች የሻለቃ ጦር ጀብደኝነት መታየት ጀመረ ። በሽምቅና በደፈጣ ውጊያ የሚደርስበት ታጣ የከባድ መሳሪያ ተኳሽና የሞርታር ዓላሚነትም እየመረጡ ይቀነድቡት ተያያዙ ።
በግግር በረዶ ሥር ተቀብረው የቆዩ ፈንጂዎች የሚመክኑት በቃኘው ሻለቃ አባላት ነበር ።
ከአፍሪካ የሄዱ ብቸኛ ወታደሮችም ቃኘዉ ክፍለጦር
በቁጥር 238 ግዳጅ ተሰጥቷቸው ሁሉንም በድል የቆጨ ብቸኛው ጦር ሆነ ።
ከዘመቱት ከስድስት ሽህ በላይ ዘማቾች መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል። 536 ወታደሮች ቆስለዋል። የተማረከ ግን አልነበረም፡፡
በጦርነቱ ማብቂያ ከአሜሪካ ወገን ሆነው ከተዋጉት ሃያ አንድ ሀገራት መካከል ሁሉም በኮሙኒስቶች እጅ የወደቁ ምርኮኛ እስረኞች ሲኖሯቸው ኢትዮጵያ አንድም ምርኮኛ እስረኛ ያልነበራት ብቸኛ ሃገር ናት፡፡ ጦርነቱ አብቅቶ የምርኮ ልውውጥ ሲደረግ ደቡብ ኮሪያ 8343፣ አሜሪካ 4714፣ እንግሊዝ 977፣ ቱርክ 244፣ አውስትራሊያ 26፣ ካናዳ 33፣ ፈረንሳይ 12፣ ግሪክ 3፣ ኮሎምቢያ 28፣ ታይላንድ 5፣ ኔዘርላንድ 3፣ ቤልጅየም 1፣ ፊሊፒንስ 97፣ ፣ ኒውዚላንድ 1 ፣ ኖርዌይ 3 ምርኮኛ ሲመለስላቸው ኢትዮጵያ ግን አንድም ሰው ያልተማረከባት ብቸኛ ሀገር ነበረች።
የኢትዮጵያ ጀግንነት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ይሰማ ጀመር የቃኘው ሻለቃ አባላት በጦርነት የተሰዉ አባሎቻቸውን አስከሬን ለጠላት ጥለው እንደማይሮጡ እሳት እየዘነበባቸው የጓዶቻቸውን ክቡር አስከሬን ተሸክመው ሲሮጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጨ።
የቃኘው ሻለቃ ጦር አባላት በኮሪያ ምድር በቆዩበት ጊዜ ሰሜን ኮሪያዎች እንደ ልዩ አይቀመሴ ፍጡር ያዪቸው ነበር። እንግሊዛዊው የጦርነት ታሪክ ጸሐፊ ጆን ኬጋን፤ “ኢትዮጵያውያን እልኸኞች ናቸው። መማረክን አይቀበሉም። ያለ ድል ለመመለስ ፈጽሞ ፍላጎት የላቸውም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከፍ ብሎ ማየት የዘወትር ሕልማቸው ነው፤ ቃኘው ማለት ይህ ነው በቃ” ሲል ለማወደስ ጽፎላቸዋል።
ኢትዮያ በኮሪያ ዘመቻ ወቅት ሰራዊቷን ወደ ጦርነቱ ከመላክ በተጨማሪ የ400 ሺ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች፡፡
በሐምሌ ወር 1945 ዓ.ም የኮሪያ ጦርነት ጦርነትን በማቆም ስምምነት ተጠናቀቀ።
ከጦርነቱ በኋላም የቃኘው ሻለቃ አባላት ለሶስት ዓመታት በኮሪያ ምድር በተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሥር የሰላም እያስከበሩ ቆይተዋል።
ለመጨረሻም በመጋቢት ወር 1948 ዓ.ም የጦሩ አባላት ሙሉ ለሙሉ የኮሪያን ምድር ለቀዉ ሀገራቸው ገቡ ።
አንደኛው ሻለቃ ለመጀመርያ ጊዜ ከጠላት ነፃ በወጣው ‹‹ቻንቹን›› ከተማ ውስጥ ለኢትዮጵያ የኮርያ ዘማቾች መታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል። ይህንን ሐውልት የመረቁት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ፡፡ በሐውልቱ አካባቢ ጣሪያቸው በሳር ክዳን የተሸፈኑና የኢትዮጵያን ባህላዊ ገጽታ የሚያንፀባርቁ ጎጆዎች ተገንብተዋል፡፡ በጦርነቱ ከፍተኛ ተጋድሎ የፈጸሙና ድል የተቀዳጁ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለአራት የተመድ አባል አገራት መከላከያ ኃይሎች መታሰቢያ የሚሆንና በየአገሮቻቸው ስም የሚጠሩ አዳራሾችም ታንፀዋል። ከሁሉም ትልቁ አዳራሽ የኢትዮጵያ አዳራሽ ነው፡፡
ዘማቾችን ወደር የለሽ ጀግንነት አዝማሪዎች በስንኝ አወድሰውታል፡፡
“አይዞሽ አሞራ አይዞሽ ጭልፊት
ቃኘው ሻለቃ አልፏል ከፊት”
እኛም ለዛሬው ይህንን ባለታሪክ ክፍለጦር በዚህ መልኩ ልናስታውሰው ወደድን ።
ታዴ የማመይ ልጅ

ጎንደር ለሀገር ያላት አበርክቶ የሚያሳይ ኤግዚብሽን ተከፈተ
#fastmereja I የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት "የከተማችን ቀን" ፕሮግራም የከሰዓት መርሃ ግብር ኤግዚብሽን የተከፈተ ሲሆን በኤግዚብሽኑም በኪነ ጥበብ፣ በባህል፣ በኃይማኖት፣ በትምህርት፣ በመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎች ላይ ጎንደር ለሀገር ያላትን አበርክቶ የሚታይበት ነው።
የጎንደር ባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወልደአረጋይ ደለ መርሃ ግብሩን አስመልክተው ለፋስት መረጃ እንደገለጹት የጎንደር ባህል ማዕከል የጎንደር እና አካባቢውን የአማራን ክልል የሚያስተዋወቅ የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ መጠጠች፣ የፀጉር ስሪት፣ የገጠር እና የከተማ የሙሽራ ስርአት ያሳየንበት መድረክ ነው ብለዋል።
በፎቶግራይ ፋሲልደስ ኪነት ቡድን፣ የሰባተኛ ክፍለ ጦር የኪነት ቡድን፣ 603ኛው ኮር ኪነት ቡድን፣ የከተማው ፖሊስ ኪነት፣ ሰባተኛ ክፍለ ጦር ኪነት፣ የአዝማሪዎች መፍለቂያ ስለሆነችው ጎንደር ከኪነ ጥበብ አንፃር ጎንደር ትላንት እና እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ነገር የማስተዋወቅ መዛግብቶች ህዝብ እንዲጎበኝ እያደረጉ መሆኑን አቶ ወልደአረጋይ አክለው ገልጸውልናል።
ኤግዚብሽኑ ለሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው ነገ ለህዝብ ክፍት ሆኖ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

Comments