Logo
Getu Temesgen
🎭 "እንዛታ" — ትውፊታዊ ቲያትር በአዲስ አበባ ይታያል !

በዉቢቱ ባህርዳርና በነገሥታት መዲና ጎንደር ከተማ የተመልካቾችን ልብ በመግዛት ከፍተኛ አድናቆትና ውዳሴ ያተረፈው "እንዛታ" ትውፊታዊ ቲያትር ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል ።

ይህ የመድረክ ድንቅ ሥራ በአዝማሪዎች ሕይወት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ዜማን ከፍልስፍና፣ ቃልን ከታሪክ፣ ባህልን ከዘመናዊ የመድረክ ጥበብ ጋር በልዩ ክህሎት ያጣመረ ትዉፊታዊ ቲያትር ነው።

📍 የእይታ መርሃ ግብር

🎭 ዛሬ እሁድ ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — ከቀኑ 8፡00

🎭 ማክሰኞ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
ብሔራዊ ቲያትር — 11፡00

🎭 ሀሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም.
ሀገር ፍቅር ቲያትር — ከቀኑ 10፡30 ይታያል ።

ከቤተሰብዎ፣ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር በመታደም፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክእና የመድረክ ጥበብ በአንድ የሚያገናኘውን ይህን ድንቅ ሥራ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል ።

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.