የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎችን ህይወት መነሻ ያደረገ ጥበባዊ አበርክቶና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የጥናት ውይይት ተካሄደ
#ethiopia | በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ለ“እንዛንታ” ተውኔት እንደ ግብዓት በሆኑት የ“ብርቧክስ” አዝማሪዎች ዙሪያ የሚያተኩር የጥናት ውይይት ተካሂዷል ።
በመርሐግብሩ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ገብረማርያም ይርጋ አዝማሪ በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ የተለየ ቦታ ያለው የጥበብ ተሸካሚ መሆኑን ገልጸዋል ። አዝማሪው በመሰንቆ ዜማ ሲዘምር፣ በቃል ቅኔ ሲያወጣ፣ የህዝብን ሐሳብ፣ ደስታና ሐዘን ወደ ጥበብ ይቀይራል ሲሉ ተደምጠዋል ።
እነዚህ አዝማሪዎች በእንዛታ የቃል ብልሃት፣ ቀልድ፣ ምሳሌና አስተዋፅኦ የተሞላ ጥበብ ይታወቃሉ። ይገልጣሉ ። ያስተምራሉ ። ያሰርጻሉ።
“እንዛታ የአዝማሪነት ” ጥበብ መዝናኛ ብቻ አይደለም፤ የህዝብ አስተሳሰብን የሚገልጥ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን በቀልድና በቅኔ የሚያቀርብ፣ ታሪክን የሚያስታውስ እና ትውልድን የሚያስተምር ትልቅ የባህል ትምህርት ነው።
በእነዚህ አዝማሪዎች ዘፈንና ቅኔ ውስጥ ጥበብ፣ ሳቅ፣ ጥበቃ እና ማስተማር በአንድ ይገናኛሉ።
ዛሬ እኛ ለትዉፊታዊ ቲያትር የተጠና የአዝማሪነት ጥበብን መድረክ እና የታሪክን ድምፅ ለማስቀጠል፣ የአዝማሪዎችን ጥበብ ለማክበር እና ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ በመነሳሳት የተገለጥንበት ነዉ ብለዋል።
አቶ ገብረማርያም ይርጋ አክለዉ ባህል በመዘመር እንጂ በመዝጋት አይኖርም፤ በመካፈል እንጂ በመርሳት አይቆይም።
ስለዚህ የቀድሞውን ጥበብ እንድንያዝ፣ የዛሬን እንድንከብር እና የነገን እንድንገነባ የሚያግዝ ይሁን በማለት የእንዛታ አዝማሪዎች ድምፅ በህዝብ ልብ ውስጥ ዘላቂ እንዲሆን ለመደገፍና ለማክበር የተሰናዳ መሆኑን አብራርተዋል ።
መርሃ ግብሩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውይይቱም ላይ የዘርፉ ባለሙያዎችና የጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል።

7 months ago