Logo
FastMereja
ጎንደር ለሀገር ያላት አበርክቶ የሚያሳይ ኤግዚብሽን ተከፈተ
#fastmereja I የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት "የከተማችን ቀን" ፕሮግራም የከሰዓት መርሃ ግብር ኤግዚብሽን የተከፈተ ሲሆን በኤግዚብሽኑም በኪነ ጥበብ፣ በባህል፣ በኃይማኖት፣ በትምህርት፣ በመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎች ላይ ጎንደር ለሀገር ያላትን አበርክቶ የሚታይበት ነው።

የጎንደር ባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወልደአረጋይ ደለ መርሃ ግብሩን አስመልክተው ለፋስት መረጃ እንደገለጹት የጎንደር ባህል ማዕከል የጎንደር እና አካባቢውን የአማራን ክልል የሚያስተዋወቅ የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ መጠጠች፣ የፀጉር ስሪት፣ የገጠር እና የከተማ የሙሽራ ስርአት ያሳየንበት መድረክ ነው ብለዋል።

በፎቶግራይ ፋሲልደስ ኪነት ቡድን፣ የሰባተኛ ክፍለ ጦር የኪነት ቡድን፣ 603ኛው ኮር ኪነት ቡድን፣ የከተማው ፖሊስ ኪነት፣ ሰባተኛ ክፍለ ጦር ኪነት፣ የአዝማሪዎች መፍለቂያ ስለሆነችው ጎንደር ከኪነ ጥበብ አንፃር ጎንደር ትላንት እና እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ነገር የማስተዋወቅ መዛግብቶች ህዝብ እንዲጎበኝ እያደረጉ መሆኑን አቶ ወልደአረጋይ አክለው ገልጸውልናል።

ኤግዚብሽኑ ለሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው ነገ ለህዝብ ክፍት ሆኖ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.