6 days ago
የፒያሳ ትዝታዎችን በዲጂታል ጥበብ ያስመለሰው “Echoes of Piassa” ኤግዚቢሽን በፈንዲቃ ተከፈተ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ታሪካዊ የከተማ ማዕከል የሆነችውን ፒያሳን ትዝታ፣ ታሪክና የባህል ውበት በዘመናዊ የዲጂታል ጥበብ መልክ ያቀረበው “Echoes of Piassa” የተሰኘ የጥበብ ኤግዚቢሽን በሃያት ሬጀንሲ በሚገኘው ፈንዲቃ የሥነ-ጥበብ ጋለሪ በይፋ ተከፍቷል።
ኤግዚቢሽኑ በአርቲስት ዳዊት ክፍሌ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የቀድሞዋን ፒያሳ የንግድ፣ የማህበራዊ ኑሮ፣ የሕንፃ ቅርስና የሰዎች ትዝታ በዲጂታል ምስሎች እና በዘመናዊ የጥበብ ቋንቋ ለተመልካቾች አቅርቧል።
ፒያሳ፤ ከሕንፃዎች በላይ የሕዝብ ትውስታ
በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ የፈንዲቃ ጋለሪ መስራች መላኩ እንደገለጹት፣ የአንድ ከተማ ባህል በሕንፃዎች ብቻ የሚለካ አይደለም።
“የሕንፃዎች መፍረስ የባሕል ሞት አይደለም፤ ባሕል የሚኖረው በሕዝቡ ልብ ውስጥ ነው”
በማለት ጥበብ ታሪክን ለመጠበቅ ያለውን ሚና አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፒያሳ በኢትዮጵያ የከተማ ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላት ሲሆን፣ የንግድ፣ የሙዚቃ፣ የስነ-ጥበብና የማህበራዊ ትስስር ማዕከል በመሆን ለብዙ ትውልዶች የማይረሳ ትዝታ ጥላለች።
ዲጂታል ጥበብ የተረሱ ታሪኮችን እንደገና ማስታወሻ
“Echoes of Piassa” የተለመደ የሥዕል አቀራረብ ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክ ቅርሶችን ከቴክኖሎጂ ጋር ያጣመረ የጥበብ ሙከራ ነው።
የዲጂታል ጥበብ በመጠቀም ያለፉ የከተማ ገጽታዎችን፣ የሰዎችን የግል ትዝታዎችና የአካባቢውን ማንነት ለአዲሱ ትውልድ ማቅረብ የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ ነው።
የጥበብ ትብብር
ኤግዚቢሽኑ በኃይሉ ክፍሌ እና ዮሴፍ ሰቦቅሳ አሰናጅነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሃያት ሬጀንሲ እና የፈንዲቃ ቡድን አባላት ለዝግጅቱ ድጋፍ አድርገዋል።
የፈንዲቃ ጋለሪ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ሥራዎች ለማስተዋወቅ የሚሰራ ማዕከል ሲሆን፣ በቀንም ሆነ በሌሊት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ጥበብ፣ ትውስታና የከተማ ማንነት
“Echoes of Piassa” የሚያስተላልፈው መልዕክት አንድ ከተማ በመንገዶቿና በሕንፃዎቿ ብቻ እንዳልተገነባች፣ በሰዎቿ ትዝታ፣ በባህሏና በጥበቧ እንደምትኖር ነው።
ይህ ኤግዚቢሽን ያለፈውን የፒያሳ ዘመን ከዛሬው የዲጂታል ዓለም ጋር በማገናኘት ታሪክን ለነገው ትውልድ ለማስተላለፍ የተደረገ የጥበብ ምስክርነት ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

በየመንገዱ ቆመው ብዙዎቻችንን ያቀራረቡ፣ ወረፋ እስኪደርሰን ትዕግስትን ያለማመዱን፣ የሳንቲም ድምፅ እየሰማን የተነጋገርንባቸው #የሕዝብ_ስልኮች 🤩
🙋♂️🙋♀️ በእነዚህ የሕዝብ ስልኮች የተጠቀማችሁ
✍️ ከትዝታዎቻችሁ የማትረሱትን አጋሩን
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

16 days ago
ታሪካዊው ምሽት በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል !
🏆 23ኛው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን 🇪🇸 የዓለም ዋንጫን ስታነሳ፣ በስካይላይት ሆቴል የነበረው ደስታ ይለይ ነበረ!
የብዙ ሳምንታት ጉጉት ፍፃሜውን አግኝቶ ስፔን የዓለምን እግር ኳስ የበላይነት ስትቆጣጠር፣ ይህንን ታሪካዊ የድል ምሽት ኮካ ኮላ ከDStv ጋር በመተባበር በስካይላይት ሆቴል ያዘጋጀው ይህ ልዩ ምሽት በደማቅ ሁኔታ ተቆጭቶል!
ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት በተወዳጆቹ ድምፃውያን ፀደኒያ ገ/ማርቆስ፣ አዲስ ለገሰ እና ልዑል ሲሳይ የሙዚቃ ትዕይንቶች ምሽቱ ሙሉ በሙሉ ደምቆ አምሽቷል። ቀዝቃዛ ኮካ ኮላ እየጠጡ፣ ይህንን ተጠባቂ ታላቅ ፍልሚያ በጋራ ከመመልከት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ!
በዝግጅቱ ላይ ተገኝታችሁ ይህንን የማይረሳ የዓለም ዋንጫ ትውስታ አብራችሁን ለተመለከታችሁ የክብር እንግዶቻችን ሁሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
#fifaworldcup2026 #cocacola #feelitall #ccbaethiopia #worldcupfinal #spainvsargentina #cocacolaethiopia #dstvethiopia

20 days ago
በ1974 ዓ.ም ከተዘረጋው አውቶማቲክ ቴሌፎን ማዞሪያ በኋላ በምስሉ ላይ ወደሚታየው የዲጂታል ቴሌፎን ማዞሪያ ማስፋፊያ ሥራ...
1988 ዓ.ም
መቀሌ
ትናንት በታታሪነት የተጣለው መሠረት ለዛሬው ፈጣን ግንኙነታችን መንገድ ጠርጓል!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚኒሶታ ግዛት ሮዝማውንት ከተማ ሰኞ ዕለት በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ፣ ምዕመናን ወደ አዲሱ ህንጻቸው በገቡ በጥቂት ወራት ውስጥ ህንጻው ሙሉ በሙሉ መውደሙ ህዝበ ክርስቲያኑን ለከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ዳርጓል።
የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል በሴንት ፖል ከተማ የነበረው ቦታ ከቁጥራቸው መበራከት የተነሳ ባለመበቃቱ ህንጻውን ከስድስት ወራት በፊት ገዝተውት ነበር። ምዕመናኑ ህንጻውን በይፋ ሚያዝያ (ኤፕሪል) ወር ላይ ከመክፈታቸው በፊት ለወራት ያህል የእድሳት ስራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።
የደብሩ ዲያቆን ዳግም ትልሁን ለኬር 11 ቴሌቭዥን በሰጠው መግለጫ፣ "በእድሳት ስራው ላይ ከፍተኛ ልፋት አፍስሰናል፤ ሁሉም ሰው ሳይተኛ ሌሊትና ቀን 24/7 እዚህ ነበር" ብሏል። ነገር ግን ቤተክርስቲያኑ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኖ ምዕመናኑን ማገልገል ከጀመረ ከሦስት ወራት በኋላ ሰኞ ዕለት በደረሰው አደጋ ህንጻው ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የእሳቱ መንስኤ ምን እንደሆነ እና ህንጻውን መልሶ መገንባት የሚቻል መሆን አለመሆኑ እስካሁን አልታወቀም። ዲያቆኑ አክሎም "ክስተቱ እጅግ የሚያሳዝን እና ልብ የሚሰብር ነው። በርካታ ሰዎች እዚህ ሲያለቅሱ አይቻለሁ" ሲል ሀዘኑን ገልጿል።
ይህ የህንጻው መውደም ከበርካታ አስርት ዓመታት በፊት ጀምሮ ከቦታው ጋር የቆየ ትውስታ የነበራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችንም ጭምር አሳዝኗል። የሌክቪል ነዋሪ የሆነችው ላሪን ናርቫ በልጅነቷ በዚያ ህንጻ ውስጥ የሰንበት ትምህርት ቤት ትከታተል እንደነበር፣ እዚያው ጋብቻ መመስረቷንና ልጆቿም በቤተክርስቲያኑ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሲሳተፉ ማየቷን አስታውሳለች። "ጉዳዩ በጣም እንግዳ ነው፤ ምክንያቱም ባለፉት ዓመታት ውስጥ የነበሩትን ክስተቶች ሳስብ እንዲህ አይነት ነገር ይፈጠራል ብዬ አስቤ አላውቅም" ስትል ስሜቷን ገልጻለች።
ከደረሰው ከባድ ሀዘንና የንብረት ውድመት ጀርባ ግን የወቅቱ የደብሩ አባላት ተስፋቸውን አላጡም። ዲያቆን ዳግም ትልሁን "ይህንን ቤተክርስቲያን ከመሰረቱ ጀምረን የገነባነው እና ሁሉንም ነገር ያደስነው እኛ ነን፤ ሁላችንም በአንድ ላይ ከቆምን ልናደርገው የማንችለው ነገር የለም" ሲል የመልሶ ግንባታ ተስፋውን ገልጿል።
የአካባቢው ባለስልጣናት ማክሰኞ ዕለት ባወጡት ማረጋገጫ በአደጋው የትኛውም ሰው ላይ የአካልና የህይወት ጉዳት እንዳልደረሰ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ምዕመናኑ ቀጣይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እና ቤተክርስቲያኑን መልሰው እንዲገነቡ ለመርዳት የኦንላይን (የእርዳታ ማሰባሰቢያ) ገጽ ተከፍቶ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

25 days ago
ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ከሰኞ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል
#ethiopia | እጅግ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ከፊታችን ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ለጎብኚዎች እና ለተገልጋዮች ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።
ሪዞርቱ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን፣ በ“ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት ማዕቀፍ የተገነባ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ነው። በተፈጥሯዊ ውበቱና በመዝናኛ አገልግሎቶቹ በቅርብም በሩቅም የብዙዎችን ትኩረት ሲስብ ቆይቷል።
ከሰኞ ጀምሮ ሪዞርቱ በይፋ ስራ በመጀመሩ፣ የአገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች የተፈጥሮ ውበቱን በመጎብኘት የተለያዩ የመዝናኛና የመስተንግዶ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በሪዞርቱ ዙሪያ ያሉ አገልግሎቶችና መስህቦችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በቀጣይ እንደሚቀርቡም ተገልጿል።
የወሎ አዲሱ የቱሪዝም ፈርጥ - ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት!
በ13.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው እና የወሎን ተፈጥሮ ከዘመናዊ የቱሪዝም አገልግሎት ጋር ያሰናኘው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት፤ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም የሚያሳይ አዲስ መዳረሻ ሆኗል።
ሪዞርቱ ምን ይዟል?
✅ ዓለም አቀፍ ደረጃ:
ዘመናዊ ምግብ ቤቶች እና መኝታ ክፍሎች።
✅ መዝናኛ:
የመዋኛ ገንዳዎች እና ለዓይን የሚማርኩ አረንጓዴ ስፍራዎች።
✅ መሰረተ ልማት:
የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶች እና የሄሊኮፕተር ማረፊያ (Helipad)።
✅ ተፈጥሮ:
በተለያዩ የፍራፍሬ ዞኖች እና በደን የተከበበ መሆኑ ልዩ ትውስታን ይፈጥራል።
ይህ ፕሮጀክት የወሎን ህዝብ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
#logolakeresort #wollo #tourismethiopia #dineforgenerations #gebetaletewled #pmabiy #ethiopia #nature #resort #getutemesgen #ጌጡተመስገን #getutemesgen #ethiopia #logohaykresort #tourism #ገበታለሀገር

Sponsored by
Surafel
26 days ago
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ለቀድሞ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ግድያ በቀል እንደሚፈጸም ቃል ገባ
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ አዛዥ የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ግድያ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ገብተዋል፣ “ከታሪካዊው ትውስታ አይጠፋም” ሲሉ ግድያዉን አዉግዘዋል።ብርጋዴር ጄኔራል አህመድ ቫሂዲ “ፍትህ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ እና ለወንጀለኞቹ፣ በተለይም ለህፃናት ገዳይ የአሜሪካ ጦር፣ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ” ጥሪ አቅርበዋል።
“የአሜሪካ ወንጀለኛ መሪዎች እና የኢራን አብዮት ጠላቶች በሙሉ እና የተቃውሞ ግንባር በዚህ መለኮታዊ መሪ ላይ በፈሪነት በመገደል፣ የመቋቋም ኃይላችንን ወደ መሬት እንደማያወርዱትማወቅ አለባቸው” ሲሉ ቫሂዲ በሴፓህ የዜና ወኪል ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።“ሰማዕታትን መበቀል እና የጥፋተኞቹን ቅጣት፣ ህጋዊ እና የማይረሳ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።” ሲሉ አክለዋል፡፡
የቫሂዲ አስተያየት የተሰደማዉ ካሜኒ ሐሙስ ዕለት በትውልድ ከተማቸው ማሽሃድ ከተቀበሩ በኋላ ነው፣ የካሜኒ አራት የቤተሰብ አባላት በአሜሪካ እና በእስራኤል የአየር ጥቃት ከሞቱ ከአራት ወራት በኋላ የቀብር ስነስርዓታቸዉ ተፈጽሟል።የኢራን ሚዲያዎች 43 ሚሊዮን ሰዎች የመሪውን የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደተከታተሉ ዘግበዋል።
የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከ41 እስከ 43 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በስድስት ቀናት ውስጥ የቀድሞ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።የኢራን ፕሬስ ቲቪ የካሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓትን “በዓለም ላይ እስካሁን ካየናቸው ትላልቅ ሰልፎች” ሲል ጠርቶታል። ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በአምስት ከተሞች ማለትም ቴህራን፣ ኩም፣ ናጃፍ፣ ካርባላ እና ማሽሃድ ነው።
Dagu
Addis_News

27 days ago
ለራሱ ምርቃት የተገዛው በሬ ወግቶት ህይወቱ ያለፈው ተመራቂ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ።
የሰው ልጅ ህይወትና መጨረሻዋ ምንኛ የማይታወቅና ተለዋዋጭ ነው? ዛሬ በደስታና በፈገግታ የደመቀ ቤት፣ በአንድ ጀንበር የልቅሶና የዋይታ ድምፅ ሲሰማበት ማየት ልብን እጅግ ይሰብራል።
በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ (Electrical Engineering) ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ወንድማችን ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስንሰማ የተሰማን ሀዘን ወሰን የለውም።
የነገው የሀገር ተስፋ፣ ለቤተሰቦቹ መከታ እና የብዙዎች ኩራት የነበረው ፍሰሐ፣ የለፋበትን የድካሙን ፍሬ አይቶ ገና ሳይጠግብ እንዲህ በወጣትነቱ መቀጠፉ እጅግ ያማል።
ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው። ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር።
ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ለአምላክ ምስጋና ይሁን ተብሎ ለደስታ ማክበሪያ የተዘጋጀው በሬ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የቤተሰቡን ተስፋና ደስታ ይዞ ተጓዘ።
የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል።
ለወላጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለጓደኞቹ በሙሉ ፈጣሪ ፍጹም መፅናናትን ይስጥልን። ወንድማችን ፍሰሐ ሆይ፣ ደክመህ ያገኘኸውን ፍሬ ሳትቀምስ በአጭር ብትቀጠፍም ትውስታህ ሁሌም በልባችን ይኖራል።
Via MA

የመጀመሪያው የአማርኛ ቴሌ ፕሪንተር መሣሪያ ሥራ በጀመረበት ጊዜ ያስቀረነውን ታሪካዊ ቅጽበት ለትውስታ አጋራናችሁ!
1963 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1963 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1 month ago
የታዋቂው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ተወዳጅ የራዲዮ
ዝግጅት “መቆያ” በመጽሐፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ
#ethiopia | ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት እና እሁድ ምሽት በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ጣቢያ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተላልፍ የቆየውና በአድማጮች ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው “እነሆ መቆያ” ፕሮግራም በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ለገበያ መቅረቡ ተገለጠ።
በአንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ የሚዘጋጀውና የበርካታ ግለሰቦች፣ አገራት እንዲሁም የተለያዩ ክስተቶች እውነተኛ ታሪኮችን በልዩ የአቀራረብ ስልቱ ሲያስደምጥ የነበረው ይህ ዝግጅት፣ አሁን ላይ ከአድማጮች አልፎ ለአንባቢያን እንዲደርስ ተደርጓል።
ይህ ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችንና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችን አቅፎ የያዘው ልዩ የራዲዮ ትውስታ፣ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሑፍ ዓለም በመሸጋገር ለአንባቢያን የተለየ የስሜት ጉዞን እንደሚያበረክት ታውቋል።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረው የጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” መጽሐፍ በአሁኑ ወቅት በጃፋር መጻሕፍት መደብር ውስጥ ለሽያጭ መቅረቡ ተረጋግጧል።
#እነሆመቆያ #እሸቴአሰፋ #ሸገርኤፍኤም #አዲስመጽሐፍ #ጃፋርመጻሕፍት #ኢትዮጵያ

የርቀትን ፈተና አልፈው ሀገርን ለማገናኘት በቁርጠኝነት ይተጉ የነበሩትን የቀድሞ የቴሌግራፍ ባለሙያዎቻችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
Sponsored by
Surafel
1 month ago
የርቀትን ፈተና አልፈው ሀገርን ለማገናኘት በቁርጠኝነት ይተጉ የነበሩትን የቀድሞ የቴሌግራፍ ባለሙያዎቻችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1 month ago
ማይክል ካሪክ - የኦልድ ትራፎርድ የልብ ትርታ፣ በታላላቅ ኮከቦች ጥላ ስር ተደብቆ የኖረ ድንቅ ጥበበኛ
***********************
ስለ እርሱ ሲታሰብ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና የሻምፒዮንስ ሊጉ ድል ትዝ ሊሉን ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛው ማይክል ካሪክ የተገነባው በብዙዎች ዘንድ በማይታወቁ፣ ልብ በሚነኩና አስገራሚ በሆኑ ድብቅ ታሪኮች ውስጥ ነው።
ዛሬ የምናውቀው ካሪክ በኳስ ቁጥጥሩና አርቆ አሳቢነቱ የሚታወቅ የአማካይ ስፍራ ኮከብ ነው። ነገር ግን ወደ ዌስትሃም አካዳሚ በ15 ዓመቱ ሲቀላቀል ሕልሙ ሌላ ነበር፤ ያኔ የፊት መስመር አጥቂ ነበር።
ካሪክ ያደገው እንደ አላን ሺረር እና ፒተር ቤርድስሌይ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ባፈራው ታዋቂው የዎልሰንድ ቦይስ አካዳሚ ውስጥ ነው። የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም፣ በ15 ዓመቱ ኒውካስልን ትቶ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ አቀና።
በ15 ዓመቱ ወደ ዌስትሃም አካዳሚ ሲቀላቀል የመስመር አጥቂ ነበር። በአንድ ጨዋታ ላይ ግን የመሃል አማካይ በመጥፋቱ በአጋጣሚ ቦታው ተቀይሮ የክፍለ ዘመኑ ብልህ አማካይ ሊሆን አጋጣሚው ተፈጠረ።
ካሪክ በቦታው መጀመሪያ ባይደሰትም ያለ እንቢታ ተጫወተ። ይህ አጋጣሚ ግን የእግር ኳስን ታሪኩን ቀየረች፤ አጥቂው ካሪክ ቀርቶ፣ የአውሮፓን መድረክ የሚገዛው ብልሁ አማካይ ተወለደ።
የካሪክ የጉርምስና ዕድሜ ደግሞ ሌላ አስገራሚ ፈተናን ይዞ መጣ። 17 ዓመቱ ላይ በአንድ ጊዜ 8 ኢንች ያህል ቁመት ጨመረ። በወቅቱ የነበረው ቀጭን ሰውነቱ ከቁመቱ ጋር ባለመመጣጠኑ ሜዳ ላይ መሮጥ እስኪያቅተው ተቸግሮ እንደነበር የቀድሞ አሰልጣኙ ሃሪ ሬድናፕ ያስታውሳሉ።
ብዙዎች የወደፊት መንገዱን ተስፋ ሲያጡበት፣ እርሱ ግን በትጋትና በጽናት ሰውነቱን ገነባ፤ በመጨረሻም ከሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጋር የዌስትሃም ወርቃማ ትውልድ አካል ሆነ።
ካሪክ ገና በወጣትነቱ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ ድንቅ ነበር። ከዌስትሃም፣ ስዊንደን፣ በርሚንግሃም እና ቶተንሃም በኋላ በ2006 ታላቁን ማንችስተር ዩናይትድን ሲቀላቀል፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በሮይ ኪን መልቀቅ የዛለውን የመሃል ሜዳ የሚያክምላቸውን የፈጠራ ሰው አገኙ።
በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ በችሎታ እንደማይደረስባቸው የመሀል ሜዳ ጣኦታት ይታዩ ነበር። ነገር ግን ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ልብ ውስጥ የነበረው እውነተኛው ንጉሥ ካሪክ ብቻ ነበር።
ፈርጉሰን በግል ማስታወሻቸው ላይ “...ላምፓርድና ጄራርድ ታላላቅ ስብዕና የነበራቸው ተጫዋቾች ናቸው፤ እውነተኛ ምርጥ ተጫዋቾች ግን አልነበሩም ፤ ካሪክ ግን የእግር ኳስ አዕምሮ ነበረው። የእንግሊዝ ሚዲያዎች ስለ እነርሱ አብዝተው በማወደስ ሲጮሁ፣ ካሪክ ግን በትህትናውና በአይናፋርነቱ ምክንያት በነርሱ ጥላ ስር ተደብቆ ተበደለ።” ሲሉ ነበር እንጋፋው አሰልጣኝ በብዕራችው ከትበው ስለካሪክ የመሰከሩት።
ማይክል ካሪክ ዛሬም ቢሆን ያው ነው - ዝምተኛ፣ አስተዋይና ልባም። የዩናይትድን ታላቅ ስም ለመታደግ በዋና አሰልጣኝነት ተሰይሟል። ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ዛሬም በዚያው ጥንቁቅ አዕምሮው የታላቁን ክለብ ታሪክ ለመጻፍ እየተዘጋጀ ነው።
ካሪክ እ.አ.አ በ2006 ከቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በ12 ወርቃማ ዓመታት 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የሻምፒዮንስ ሊግን እና የኤፍኤ ካፕን ጨምሮ በርካታ የክብር አክሊሎችን ደፍቷል።
ሆኖም ግን እንደ ፖል ስኮልስ ፣ ጄራርድ እና ላምፓርድ ባሉ ደማቅ ስሞች ጥላ ስር ተደብቆ አሳልፏል። ነገር ግን ሳይታይ የሚደምቅ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።
በኦልድ ትራፎርድ የነበረው ስፍራ ከብዙ ተጫዋቾች የተለየ ነበር። ግቦችን ብዙ አያስቆጥርም፣ አስደናቂ ትርዒቶችንም አያሳይም፤ ነገር ግን ጨዋታው በእርሱ እግር ይጀምር፣ በእርሱም አዕምሮ ይመራ ነበር።
ከተጫዋችነት በኋላ በሞሪንሆ እና ሶልሻየር ስር በረዳትነት የሰራው ካሪክ በ2021 ለአጭር ጊዜ ዩናይትድን በጊዜያዊነት መርቶ ጥሩ ውጤት አሳይቷል።
በመቀጠል ሚድልስብሮን በዋና አሰልጣኝነት ይዞ አስደናቂ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ፣ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሩበን አሞሪም ስር የተንኮታኮተውን ማንችስተር ዩናይትድን ለመታደግ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ኦልትራፎርድ ሲደርስ ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም ነበር።
ነገር ግን ዝምተኛው ካሪክ ፤ ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ታላቁን ክለብ ከመውረድ ውርደት ታድጎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ አበቃው።
ማይክል ካሪክ በተጫዋችነት ዘመኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አጋሮቹ "ሃቮክ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሩት ነበር። ይህ ስም የመጣው በወቅቱ ተጫዋቾቹ በፒኤስፒ (PSP) ላይ "SOCOM US Navy SEALs: Fireteam Bravo" የተሰኘውን ታክቲካዊና ስውር የጦርነት ጨዋታ(ኮምፒዩተር ጌም) በጋራ ሲጫወቱ ከነበራቸው ትውስታ ነው።
ዌይን ሩኒ እንደተናገረው ይህ ጨዋታና የካሪክ መሪነት ቡድኑን አንድ ላይ ለማሰባሰብ ትልቅ ሚና ነበረው። ካሪክ በጨዋታው ላይ ብቻ ሳይሆን በሜዳው ላይም ያንን ስውር እና ጥንቁቅ ታክቲክ የሚተገብር መሪ ነበር።
ካሪክ ብዙ ጊዜ በሚያወሩ ኮከቦች መካከል በዝምታ የበራ ኮከብ ነበር። የጨዋታውን ስልተ-ምት በአንድ ንክኪ የሚቀይር፣ የቡድኑን ልብ በጸጥታ የሚያስመታ ረቂቅ የሙዚቃ መሪ።
እሱን የሚለየው ያሸነፋቸው ዋንጫዎች ብቻ አይደሉም፤ ያለ ጩኸት ታሪክ መፍጠር የቻለ ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ኮከቦች በብርሃን ይደምቃሉ፤ ካሪክ ግን በዝምታው ታላቅ ሆነ።
ለዚህም ነው ዛሬም በኦልድ ትራፎርድ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ስሞች አንዱ ሆኖ የሚጠራው፤ እየመጡ ያሉትን ብሩህ የአሰልጣኝነት ዘመናቱንም ያስናፈቀው።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #football

የሻርክ እና የወይዘሮ ሸዋዬ ታሪክ እና ከሞት በላይ የሆነ ታማኝነት
በአንድ አረንጓዴማ በሆነች የገጠር ከተማ በስሟ ኩየራ በምትባል መንደር ውስጥ ሻርክ የሚባል እና ወይዘሮ ሸዋዬ የሚባሉ እናት አብረው ይኖሩ ነበር። ሻርክ ተራ ውሻ አልነበረም፤ እርጋታው፣ አስተዋይነቱ እና ለአሳዳጊው የነበረው ፍቅር በመንደሩ ሰው ሁሉ ዘንድ የሚደነቅ እና የሚወደድ ነበር። የእሱ አለም... የእሱ መጠለያ እና መላ ህይወቱ ወይዘሮ ሸዋዬ ነበሩ።
ወይዘሮ ሸዋዬ ሻርክን ከትንሽነቱ ጀምረው ነበር ያሳደጉት። በርግጥ ትንሽ ከፍ ብሏል። ጎረቤታችው በፓስፖርት ከውጭ አምጥተውት በሳምንቱ ከዛ ጠፍቶ ሸዋዬ ጋር ገባ። ቢሞክሩት ወስደው ቢያስሩት እሱ ምግብ አልበላም እያለ ገመድ እየበጠሰ መኖርያውን ከሸዋዬ ጋር አደረገ። እሷ ልጆቿ በስራ ምክንያት ውጭ ስለሚውሉ ሻርክ ደግሞ ብቸኝነቷን የሻረላት የልብ ጓደኛዋ ሆነ።
.
ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ በሁለቱ መካከል ያለው ትስስር እየጠነከረ መጣ። ወይዘሮ ሸዋዬ ማለዳ ተነስተው ወደ ማሳቸው ሲሄዱ ሻርክ ከፊት ቀደም እያለ መንገዱን ይመራ ነበር። እርሻ ውስጥ ስራቸውን ሲሰሩ እሱ ከዛፍ ጥላ ስር ሆኖ አካባቢውን በትኩረት ይጠብቃል። ማታ ወደ ቤት ሲመለሱም የእርሷን ድካም የሚያውቅ ይመስል እግሯ ስር ተኝቶ እጆቿን በምላሱ ይልስ ነበር። ውጣ ሲባል እንኳ ከሳሎን አይወጣም እያያቸው ነበር የሚውለው።
መንደርተኞቹ ሁልጊዜ፣ "የሸዋዬ ውሻ እኮ ከሰው በላይ ያስባል" ይሉ ነበር። ሻርክ ወይዘሮ ሸዋዬ ደስ ሲላቸው አብሮ ይቦርቃል፣ ሲከፋቸው ወይም ሲደክማቸው ደግሞ ዝም ብሎ አጠገባቸው በመቀመጥ አጋርነቱን ያሳይ ነበር።
ወይዘሮ ሸዋዬ ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ባሉት የመጨረሻ ወራት በጠና ታመው አልጋ ላይ ውለው ነበር።
በእነዚያ አስቸጋሪ ቀናት ሻርክ ከቤት አልወጣም። ለህክምና ሆስፒታል ሲሄዱም ተከትሎ ይሄዳል። የምግብ ፍላጎቱ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶም ነበር። ስትመለስም ከአልጋዋ ስር አይነሳም ነበር ፣ እሷ በምትሰቃይበት ጊዜ ሁሉ እሱም በሀዘን ያለቅስ ነበር። ወይዘሮ ሸዋዬ የመጨረሻዋን ትንፋሽ ከመውሰዷ በፊት፣ እየተንቀጠቀጠች ያለችውን እጇን ዘርግታ የሻርክን ጭንቅላት ዳሰሰችው። አይኖቿ የእንባ ጠብታ አውርደው ለዘላለም ሲከደኑ፣ ሻርክ ረዥም እና የሚያሳዝን የጩኸት ድምፅ አሰማ ወዳጁ መሄዷን ነፍሱ አውቃው ነበር።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ተፈጽሞ መንደርተኛው ሁሉ ወደየቤቱ ሲበተን ሻርክ ግን አብሮ አልተመለሰም። ሻርክ የመቃብር ስፍራ ላይ ልክ በህይወት እያለች እግሯ ስር እንደሚቀመጠው ሁሉ ዛሬም አንገቱን ደፍቶ ተቀምጧል። የመንደሩ ሰዎች ሊወስዱት፣ ምግብ ሊሰጡትና ሊያጽናኑት ሞክረውም ነበር። እሱ ግን ትንሽ ይበላና ትንሽ ቆይቶ ወደ መቃብሩ ይመለሳል ከዛም ቆይቶ ወደቤት።
ዝናብ ሲዘንብ፣ ፀሐይ ሲያቃጥል ሻርክ ከቦታው አይንቀሳቀስም። እሱ አሁንም እየጠበቃት ነው።
ሻርክ በዚህ ድርጊቱ ለሰው ልጆች ትልቅ ትምህርት አስተላልፏል... ፍቅር፣ ታማኝነት እና ትስስር በሞት እንኳ የማይበጠሱ መሆናቸውን። እሱ የአሳዳጊውን አካል አጥቶ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በእሱ ልብ ውስጥ የእሷ ትውስታ እና ፍቅር እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ህያው ሆኖ ይኖራል።
በኤፍሬም ታምሩ

ብራዚል ያነባች ዕለት - የጀርመኑ ዓለም ዋንጫ ትዝታዎች
****************
ያኔ ብራዚል እንዲህ ትሆናለች፣ በመሰል ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለው ብዙዎች አልጠበቁም። ሁለት አስርት ዓመታት አልፈው ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያስታውሱት የሆነው ግን እንደዚያ ነው። የ2006 ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የቀደመውን አሸናፊ ፈረንሳይ እና የወቅቱን ሻምፒዮን ብራዚልን አገናኝቷል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን የብራዚል ወርቃማ ትውልድ፣ ኳስ የጥበብ አውድማ መሆኑን ዳግም ያስመሰከሩት ጥበበኞች ስብስብ ጀርመን ምድር ለዓለም ዋንጫው ሲዘልቁ ለ6ኛ የመድረኩ አሸናፊነት፣ ለተከታታይ ሻፒዮንነት ነው የታጩት።
ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ፣ ሮናልዲንሆ ጎቾ፣ ካካ፣ ካፉ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ አድሪያኖ እና ዚ ሮቤርቶን የመሰሉ ክዋክብት እንደ ምን ይዘነጋሉ? የሰው አዕምሮ ሊዘነጋቸው ቢፈቅድ እንኳ የእግር ኳስ ታሪክ ሊረሳቸው አይቻለውም። ትዝታቸው ርቆ ያልራቀ፣ ደብዝዞ ያልጠፋ፣ ቀጥኖ ያልተበጠሰ ህልው ነው። ከመዘንጋት የራቀ ታሪክ!
የዚያች ዕለት ግን ቀን ከነርሱ በተቃራኒ የቆመች መሰለች። የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በተለይም ዚነዲን ዚዳን በዚያች ቀን ስል፣ አስፈሪ እና ባለ ግርማ ሞገስ ሆነው ነው የቀረቡት።
ዚዳን ፀጉሩ እንደከዳው፣ የጎልማሳነት ደጃፉ ላይ እንደቆመ፣ ከእግር ኳስ የመሰናበቻ ቀናቱ እንደደረሰ ሳይሆን የ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ ወጣት ነበር ይቦርቅ የነበረው።
በዚያ ጨዋታ ዚዳን የነበረው እንቅስቃሴ በዓለም ዋንጫ ታሪክ በግለሰብ ደረጃ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ምርጡ እንደሆነ የብዙዎች እምነት ነው። የዘመን ተጋሪው ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማም ያን ጨዋታ አስመልክቶ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ “በዚያ ጨዋታ ዚዳን ያደረገው እንቅስቃሴ ያለማወላዳት በዓለም ዋንጫው ታሪክ ከታዩ ምርጥ ብቃቶች እንደ አንዱ ሊመደብ የተገባ ነው” ነበር ያለው።
ፈረንሳይ በቴሪ ሄንሪ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፋ የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከውድድሩ አሰናበተቻት። ያኔ ብዙ አለማመኖች ነበሩ፣ የሆነው ከብዙዎቹ ጥበቃ በተቃራኒ ነው።
የ1998 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ፣ የነ ዚነዲን ዚዳን ሀገር የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከዓለም ዋንጫ አስወጣቻት የሚለው በመጨረሻ የዳኛውን ፊሽካ ተከትሎ የተሰማው ዜና ነበር።
ያ ታሪክ በፍራንክፈርቱ ባልድ ስታዲየም የመጫወቻ ሜዳ ብቻ ተፈፅሞ ያበቃ አልሆነም። ወደ ካናሪንሀ መልበሻ ክፍልም ተከትሎ አምርቷል። በዕለቱ ልዩ የነበረው፣ ለቴሪ ሄንሪም ለግብ የምትሆነውን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ዚነዲን ዚዳን ወደዚያች መልበሻ ክፍል አመራ።
አንድም ሊያፅናና አንድም በትልልቅ የእግር ኳስ መድረኮች እንደተለመደው መለያ ሊቀያየር።
‛ኤል ፌኖሜኖ’ ይህን የዚዳን ተግባር በበጎ አልተመከተውም። ሮናልዶ ከ20 ዓመታት በኋላ ሁነቱን አስመልክቶ ሲናገር “ሁላችንም ዛሬ ድረስ አብረን የቀጠልን ጓደኛሞች ነን፣ እርሱ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ግን የነበረው ድባብ አስፈሪ ነበር።
ብዙ ተጫዋቾች እያነቡ ነበር፤ እናም መለያ ለመቀያየር ወደ መልበሻ ክፍሉ የመጣበት ሰዓት ትክክለኛ እንዳልሆነና እንዲመለስ አስረግጬ ነገርኩት” ይላል።
እንደ ሮናልዶ እምነት ያች ዕለት የዓለም ዋንጫን ታሪክ ራሱን ቀይራለች። በእርግጥም በብራዚል በኩል ሆኖ ለተመለከተው ብዙ እውነት የሚመስሉ ነገሮችን የያዘ ሃሳብ ነው።
ለዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ናሙና የሆኑ ክዋክብትን ያበረከተችው ብራዚል ከትልቁ መድረክ አሸናፊነት እንደተናጠበች ሩብ ምዕተ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። እነዛን ኮከቦች ግን እግር ኳስ ሊዘነጋቸው አይቻለውም።
በእርግጥ ፈረንሳይ አስከ ፍፃሜ ብትጓዝም፣ በዚነዲን ዚዳን እና ማርኮ ማታራዚ ድራማ በታጀበው ጨዋታ፣ በነ ማርሴሎ ሊፒ እና አንድሪያ ፒርሎ ጣሊያን ተረታ ለሌላ ዓለም ዋንጫ አሸናፊነት 12 ዓመታት ለመጠበቅ ተገዳለች።
ዚዳንን የ2006ቱ ዓለም ዋንጫ ‛አንተ በእግር ኳስ ስንብትህ ደጃፍ ላይ ቆመህ በእኔ ያበራህ ኮከብ ነህ’ ብሎታል።
ዓለም ዋንጫ ትዝታ ነው። ድልና ሽንፈት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ ሳቅ እና ለቅሶ የሚመላለስበት የስፖርት አውድማ፤ የትውስታ መቼት ነው። መንገዱ ይቀጥላል!
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #brazil #sports #japan #ebc Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

የሞባይል አገልግሎት ምዝገባ መጀመሩን ያበሰረበትን ይህንን ምስል ለትውስታ አጋራናችሁ!
እስቲ ይሄ ስልክ የነበረው 🙋♂️🙋♀️
✍️ ማን እጅ ላይ አይታችሁታል?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
እስቲ ይሄ ስልክ የነበረው 🙋♂️🙋♀️
✍️ ማን እጅ ላይ አይታችሁታል?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1 month ago
የልጅነት እንባ እና የድል መንገድ - ሮናልዶ ከትላንት እስከ ዛሬ
**********************
የ2004 አውሮፓ ዋንጫ ብዙ ትዝታዎች አሉት። የኦቶ ሪሃግሎቹ ግሪኮች ፖርቹጋሎችን በጥብቅ መከላከል በገዛ ሜዳቸው የአውሮፓ ዋንጫውን መንጠቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሊመጣ ብቅ እያለ ያለው አዲስ ኮከብ ትኩስ እንባ በሊዝበኑ ስታዲዮ ዳሉዝ ሲፈስ ትዝታው ዛሬም ርቆ ያልራቀ ቅርብ ነው።
ያን የዘመናዊ እግር ኳስ ህልው ትዝታ አስታከን ወደ ዛሬ እንዘልቃለን። ብዙ ውብ ትላንቶችን፣ ደማቅ ቀኖችን እና ውብ ምሽቶችን አልፎ እውን ወደሆነው ዛሬ እንመጣለን። ትዝታ ቢርቅም አያረጀምና፣ በዘመን መፈራረቅም አይደበዝዝምና ብትውስታ ጎዳና እንመላለሳለን።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዶስ ሳንቶስ አቪየሮ የሚባል ስም፣ በአባቱ መሻት የሮናልድ ሬገንን መጠሪያ እንዲጋራ የሆነ፣ በልጅነቱ አይጋፈጡትን ፈተና የተጋፈጠ፣ የሊዝበን ሰዎች በአፍላነቱ ሳይጠግቡ የተለዩት፣ የላንክ ሻየር ሰዎች ደግሞ ውብ ማለዳውን የተጋሩት፣ ውለታን የማይረሳው ዛሬም በስኬት ደጃፎች እየተመላለሰ ያለ ህያው ኮከብ ነው።
በሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና በማንቸስተር ዩናይትድ መልማዮች ዓይን ውስጥ ከገባባት ከዚያች የወዳጅነት ጨዋታ ዕለት አንስቶ ዘመናዊ እግር ኳስ ሌላ መልክ ነው የያዘው። ማንቸስተር ዩናይትድ ከዚህ ኮከብ ጋር በበርካታ ዋንጫዎች የተገመደ ብዙ የድል ቀናትን አልፏል።
ወደ ሎስ ብላንኮዎቹ ቅፅር ዘልቆም በነጩ መለያ ለሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥም በአውሮፓ መድረክም የሚደረገውን ሁሉ አድርጓል። ቱሪንም እጇን ዘርግታ ነው የተቀበለችው። እዚያም ስኬት ከእርሱ ጋር ነበረች።
በድኅረ ኮቪድ 19 የመጀመሪያ ወቅቶች ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመለስ የቀዮቹ ደጋፊዎች ትዝታቸውን እንደሸከፉ ነበርና “እንኳን መጣህልን” ነበር ያሉት።
ሆኖም የማቸስተር ዩናይትድ ዳግም ምልሰቱ እንደ ትላንት ስል፣ እንደ ዕድሜውም በውጤት ብስል አልሆነም። ከኤሪክ ቴንሀግ ጋር የጋባበት መቃቃር ደግሞ ወደ መውጫው በር እንዲያማትር ዋነኛ ምክኒያት ሆነ።
ወደ መካከለኛው ምስራቅ ዘለቀ፤ በእግር ኳስ ብዙ መዋዕለ ንዋይ አፍስሳ ግዙፍ ለውጥ ወደ ሻተችው ሳዑዲ አረቢያ አቀና። ከሳምንታት በፊትም ለሦስት ዓመታት የተጠበቀውን የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮንነት ከክለቡ ዐል-ናስር ጋር አነሳ።
ሆኖም ጥያቄ ነበር። እነዚህን ሁሉ ቁጥራቸው የበረከቱ ስኬቶች ወደ ብሔራዊ ቡድን የሚተረጉማቸውስ መቼ ነው? የሚል።
በእርግጥ የ2016ቱን አውሮፓ ዋንጫ ሲያነሳ ይህ ጥያቄ በከፊል የተመለሰ መስሎ ነበር። የአውሮፓ ሀገራት ዋንጫ/ ኔሽንስ ሊግንም አንስቷል።
ግን ግዙፉ የዓለም ዋንጫስ? እግር ኳስ በታሪኩ ካስመለከታቸው ኮከቦች ለምሉዕነት አንድ መስፈርቱ ይኸው መድረክ ነውና፤ የእርሱስ ቀን አይመጣም ወይ? ተብሎ ተጠብቋል። እስካሁን ያ ቀን አልመጣም።
በእርግጥ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በተቆጠሩ ግቦች ከሊዮኔል ሜሲ እና ከኢራናዊው ዓሊ ዳይ በእጅጉ ርቋል። በዚህ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ደግሞ በመድረኩ ከተሳተፉ አንጋፋ ተጫዋቾች አንዱ ሆኖ ወደ አሜሪካ ምድር ሲዘልቅ ብዙ ጥበቃዎች ነበሩ። እነዛ ጥበቃዎች ግን በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያለግብ ሲለያዩ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገ ሆነ። በርከት ያሉ ትችቶች እርሱም ሆነ የቡድን አጋሮቹ ላይ መሰንዘራቸው አልቀረም።
ቀን ጠብቆ በአሉታ ለተቹትም፣ በበጎ ለጠበቁትም ምላሽ ሰጥቷል። ኡዝቤኪስታንን 5 ለ 0 በረቱበት ጨዋታ ከመረብ ያሳረፋቸው እነዚያ ሁለት ግቦች ትችቶቹን አቅጣጫ ማስቀየሪያ ብቻ አልሆኑም። አዳዲስ ክብረ ወሰኖችንም አስከትለዋል።
ሮናልዶ ከካሜሩናዊው ሮጀር ሚላ በመቀጠል በመድረኩ ግብ ያስቆጠረ አንጋፋ ተጫዋች ተሰኝቷል፤ ከ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ እስከ 23ኛው የአሜሪካ ምድር ዓለም ዋንጫ በተሳተፈባቸው 6 ውድድሮች በሁሉም ግብ በማስቆጠር ደግሞ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
በጨዋታ ዘመኑ ያስቆጠራቸው ግቦችም 975 ደርሰዋል። በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ 145ኛ ግቡን በማስቆጠር ከተከታዩ ሊዮኔል ሜሲ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ 23 አስፍቷል።
በጨለማ ከመሰለው አስቸጋሪ ሳምንት በኋላ፣ ትችት ከበረከተባቸው ሰሞናት በኋላ “ተመልሰናል” ብሏል ሮናልዶ። በግል የሚመዘገቡ ክብረ ወሰኖች መልካም ቢሆኑም፤ ቀዳሚ ግቡ ግን ቡድኑን መርዳትና ለአሸናፊነት ማብቃት መሆኑን ነው የገለፀው።
ያ መንገድ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬም ቀጥሏል። እንደ ትላንቱ ባይሰላም ለተባለው ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ አለ። የትችት ወጀብ ሳይገታው፣ የዕድሜ መግፋትም ሳይረታው እንደ ጥንቱ ስል ባይሆንም አለሁ እያለ ነው።
ዋይኒ ሩኒ የተናገው ይህን በሚገባ ይገልፃል።ሮናልዶ ትችትን ማስተናገድ፣ ለትችቱም አስፈላጊውን ተግባራዊ ምለሽ መስጠት በእግር ኳስ ዘመኑ ሁሉ የተጓዘበት እውነት ነው።
“ትዝታ አያረጅም” ሲባል በጎም ይሁን መጥፎ በአዕምሮ ጓዳ ደጋግሞ ስለሚመላለስ ነው። ሮናልዶ ግን ያለፈ ትዝታ፤ ያላለፈ ዛሬ ነው።
እነዚያ በፅናት የተጓዘባቸው ውጤታማ ዓመታት፣ ያንን የሊዝበን ሰታዲየም እንባ ይገልፃሉ። ያ የእልህ እና የቁጭት እንባ፤ ከዓመታት በኋላ ዛሬም ትኩስ ነው፣ አልቀዘቀዘም!
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #sports #ronaldo #football

2 months ago
የማኑዋል ቴሌፎን ማዞሪያ ኦፐሬተር በሥራ ላይ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
Sponsored by
Surafel
2 months ago
የማኑዋል ቴሌፎን ማዞሪያ ኦፐሬተር በሥራ ላይ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
2 months ago
የዓለም ዋንጫ ትዝታዎች...
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከጅማሮው ከኳስ ውበቱ ይልቅ ከጀርባው ያለው ፖለቲካ አይሎ ከመታየቱ ባለፈ በርካታ ውዝግቦችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ውስጥ ስማቸው ጎልቶ ከሚነሳና የብዙሃንን ቀልብ መሳብ ከቻሉ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ነው ጋዜጠኛ ማርቆስ ኤልያስ።
በተለያዩ ታዋቂ ጋዜጦች የስፖርት ዓምድ ላይ ለበርካታ ዓመታት በመጻፍ የዳበረ ልምድ አካብቷል፡፡ ጋዜጠኛ ማርቆስ በሬዲዮ ሞገድም በሚያቀርባቸው ተወዳጅ ስፖርታዊ ዝግጅቶቹ የብዙዎችን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
ማርቆስ በተለያዩ መድረኮች ላይ በሚያቀርባቸው ጥልቅ የስፖርት ትንታኔዎች በአድማጭና ተመልካች ዘንድ እጅግ የተወደደ ነው፡፡ በተለይም ያለፉ ክስተቶችን፣ ስታቲስቲክሶችን እና ታሪኮችን በቅጽበት አስታውሶ የመተንተን ልዩ ብቃቱ መለያው ነው።
መተሃራ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ማርቆስ፤ የእግር ኳስ ፍቅር ልቡን የገዛው ገና በልጅነቱ ነበር። በወቅቱ ትልቅ ሕልሙ ጎበዝ የእግር ኳስ ተጫዋች መሆን የነበረ ቢሆንም፣ለትምህርት ቅድሚያ በመስጠቱ የእግር ኳስ ህልሙን ሳያሳካ እንደቀረ ያስታውሳል፡፡
ሆኖም ግን የስፖርት ጋዜጠኛው ማርቆስ መጫወት ባይችልም ኳስን በጥልቅ ከመውደዱ የተነሳ ዛሬም የስፖርቱ ዓለም የዕለት ተዕለት ሕይወቱና የሙያ እንጀራው ሆኖ ቀጥሏል።
ሁልጊዜም ቢሆን "የሀገር ውስጥ ስፖርትን ማሳደግ" የዘወትር ትልቅ ምኞቱና የሥራው ዋና ግብ መሆኑን በኩራት ይናገራል።
ዛሬ በጉጉት የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ ውድድር በይፋ የሚጀመርበት ዕለት በመሆኑም ጋዜጠኛው ስለ ውድድሩ ያለፉ ታሪኮች እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማስመልከት ሰፊ ትንታኔ ሰጥቷል።
ያለፉትን የዓለም ዋንጫ ታሪኮች ሳያሰለች እና ትውስታዎችን እያጣቀሰ የሚተነትነው ማርቆስ፤ ዛሬ ስለሚጀመረው ታላቅ መድረክ አንኳር ሃሳቦችን አንስቷል፡
የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከጅማሮው ከኳስ ውበቱ ይልቅ፣ ከጀርባው ያለው ፖለቲካ አይሎ የታየበትና በርካታ ውዝግቦችን እያስተናገደ ነው ይላል፡፡
ጋዜጠኛው ማርቆስ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት የነበሩትን የሀገራት ፍጥጫዎች፣ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዎችና ከሜዳ ውጭ ያሉትን ትኩሳት በዝርዝር በመዳሰስ በርካታ አዳዲስ ሃሳቦችንና እይታዎችን አጋርቶናል።
በቅድስት ዘውዱ
ጋዜጠኛ ማርቆስ ኤልያስ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረገውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦ https://youtu.be/BA7Rsnkzj...

የዓለም ዋንጫ እና አርሲ ሱዴ
ሰዓቱ ምሽት ነው። አየሩ በአርሲ ሱዴ ቀዝቃዛ ንፋስ ታጅቦ በናፍቆት ይሞቃል። ዛሬ ዓለም በሜክሲኮ፣ አሜሪካ እና ካናዳ አስተናጋጅነት ለሚጀመረው የዓለም ዋንጫ በዝግጅት ላይ ሳለች፣ የእኔ ትውስታ ግን ከሃያ ዓመታት በፊት ወደ ነበረችው ኩላ ከተማ ያንገላታኛል።
ያ ዘመን... ቴሌቪዥን በየቤቱ አልነበረም። የኢቲቪ እሁድ መዝናኛን ለመመልከት 50 ሳንቲም በእጅ ይዞ፣ በአንድ ትልቅ ስክሪን ፊት ለፊት ተሰባስቦ የመታየት ጣፋጭ ድካም የነበረበት ዘመን ነበር።
ኩላ፣ ያቺ ትንሽዬ የወረዳ ከተማ፤ ከመኪና ወርደህ "የእከሌ ቤት የት ነው?" ብለህ ብትጠይቅ፣ ከመንገድ ዳር የሚጫወቱት ህፃናት "እኔ ላሳይህ!" ብለው የሚሻሙልህ፣ እያንዳንዱ ነዋሪ የአንዳችንን ማንነት የሚያውቅባት የሞቀች ከተማ። በዚያን ዘመን መብራት የሚባል ነገር አልነበረም። ጨለማውን የሚገፈው የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች ጄኔሬተር ድምፅ ብቻ ነበር። ማታ ማታ የውጪ ፊልሞችን፣ በዓል ሲመጣም የኢቲቪን ፕሮግራሞች በነጻም እያስከፈሉ ያሳዩን ነበር። በተለይ የስቅለት ለሊት ቪዲዮ... ያ ድባብ ዛሬም ድረስ በአይኔ ይደቀናል።
የሩጫ ውድድር፣ ዓለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ሲመጣ ደግሞ ከተማዋ ትናወጣለች! የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች በሰው ተጨናንቀው የትንፋሽ እስራት ይፈጠራል። በስሜት መጮህ፣ በጎል መዝለል፣ በሽንፈት ማዘን... ያ ሁሉ ስሜት የጋራ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የተመልካቹ ብዛት ሲበዛ፣ የወረዳው መስተዳደር ጽ/ቤት ጄኔሬተር በማንሳት የራሱን በር ለህዝቡ ይከፍት ነበር። ያኔ፣ በአንድ ስክሪን ፊት የተሰባሰበው የኩላ ወጣት እና ታዳጊ፣ እንደ አንድ ቤተሰብ ነበር የሚሰማው።
ዛሬ ግን ዘመኑ ተቀይሯል። ዓለም ዋንጫው በቴክኖሎጂው ዓለም ተውቦ፣ በእጅ ስልክ ስክሪን እየተመለከትን ነው። ርቀቶች ተሰርዘዋል።
የዛሬይቱ ኩላ ምን ትመስል ይሆን? በየቪዲዮ ቤቱ ትከሻ ለትከሻ ተያይዘን የዓለም ዋንጫን ስንመለከት የነበርን ታዳጊዎች ዛሬ የት ደረስን? ምናልባት አንዳንዶቻችን በአሰላ፣ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ አንዳችን በውጪ አገር፣ አንዳችንም በኩላ የልጅነት ትዝታችንን እየናፈቅን በየስልካችን ስንመለከት ይሆን?
ወይ ጊዜ! ያ የጋራ ትዝታ፣ ያ የተሰባሰበ ደስታ ዛሬም በልቤ ውስጥ የከበረ ቦታ አለው። ዛሬ ዓለም ዋንጫ ሲጀመር፣ ከሁሉም በላይ የናፈቀኝ ያ በኩላ ከተማ የነበረው የቡድን መንፈስ እና ያ የዋህ የልጅነት ደስታ ነው።
የት ናችሁ የልጅነት ጓደኞቼ? ያ የኩላ ምሽት፣ ያ የዓለም ዋንጫ ወኔ ዛሬም ትዝ ይላችሁ ይሆን?

የመቀሌ ከተማ አውቶማቲክ የቴሌፎን አገልግሎት!
ቴክኖሎጂው ሲቀየር ለሠራተኞቹ ምቹ የሥራ ሁኔታን መፍጠሩን የወቅቱ ቴሌ ነጋሪት "የመቀሌ ከተማ አውቶማቲክ የቴሌፎን አገልግሎት ካገኘች በኋላ ለኦፕሬተሮቻችን አመቺ የሥራ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል" በማለት ዘግቦ ነበር።
ከትላንትናው የዲጂታል ጉዟችን ማኅደር ለትውስታ አጋራናችሁ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
ቴክኖሎጂው ሲቀየር ለሠራተኞቹ ምቹ የሥራ ሁኔታን መፍጠሩን የወቅቱ ቴሌ ነጋሪት "የመቀሌ ከተማ አውቶማቲክ የቴሌፎን አገልግሎት ካገኘች በኋላ ለኦፕሬተሮቻችን አመቺ የሥራ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል" በማለት ዘግቦ ነበር።
ከትላንትናው የዲጂታል ጉዟችን ማኅደር ለትውስታ አጋራናችሁ!
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
Sponsored by
Surafel
2 months ago
የመቀሌ ከተማ አውቶማቲክ የቴሌፎን አገልግሎት!
ቴክኖሎጂው ሲቀየር ለሠራተኞቹ ምቹ የሥራ ሁኔታን መፍጠሩን የወቅቱ ቴሌ ነጋሪት "የመቀሌ ከተማ አውቶማቲክ የቴሌፎን አገልግሎት ካገኘች በኋላ ለኦፕሬተሮቻችን አመቺ የሥራ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል" በማለት ዘግቦ ነበር።
የትላንትና ጉዟችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!

ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
Federal Democratic Republic of Ethiopia
OFFICE OF THE PRIME MINISTER
ጋዜጣዊ መግለጫ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
#ethiopia | ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል።
በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፤ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆናቸውን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይህንን ምርጫ “የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ” ሲል ሰይሞታል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ከተሰጧቸው 55 ድርጅቶች 65,299 ታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፤ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።
አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይህንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከአውነታው የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሠረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣ 65,299 የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎችን ወይም 1,100 ዕውቅና የተሰጣቸውን የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችን መጋበዝ ባላስፈለገ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ ዜጎች፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ላሠማራቸው ከ350,000 በላይ ኃላፊዎች፤ ሂደቱን ለመጠበቅ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ግንባታ መጎልበት እና ለሂደቱ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት ላረጋገጡት የአፍሪካ እና ቀጠናዊ የታዛቢ ቡድኖች ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
ስለ ኢትዮጵያ ልማት
ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ውሳኔያቸውን ሲያስቀምጡ፤ ሀገራቸውን በፍጹም የዲሞክራሲ ባህል ውስጥ ለማንበር ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባላት ጸጋ ልክ የሚያስፈልጋትን ሁለንተናዊ ልማት በፍጥነት እውን የማድረግ ባህል እንዲቀጥል ሕዝባችን ተናግሯል።
ባለፉት ዓመታት የታየው እውነት እንደሚያሳየን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት የተስፋ ቃል መንግሥት አልነበረም፤ ይልቁንም በተጨባጭ የሚታዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ውጤት ተኮር መንግሥት ሲሆን፤ እነዚህም ውጤቶች በግልጽ የሚታዩ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን፤ ይህም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ዕድገቱ መነቃቃትን መሠረት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዕድገቱ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ዘርፎችን በከፍተኛ ደረጃ ያካተተ ሰፊ መሠረት ያለው ቢሆንም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ኢንዱስትሪው ለዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየመጣ ይገኛል። ይህም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭማሪና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት ያሳያል።
እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ናቸው። አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ይህም ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ አሳይቷል።
የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይህም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው። ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ጨምሮ፤ ውጫዊ ጫናዎች በነበሩበት ወቅት ነው።
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፤ ይህም የሀገሪቱን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል። ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንግድ ተቋማትና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል። ይህ ግድብ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተደገፈ፣ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች የተገነባ እና ቀጣይነት የነበረውን ውጫዊ
ጫናዎችን ተቋቁሞ የተጠናቀቀ ነው። ከሃይድሮ ፓወር ጎን ለጎን፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኘውን የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና በአርሲ ዞን የሚገኘውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ በመሳሰሉ ሥራዎች ታዳሽ ኃይል አቅርቦቷን እያሰፋች ሲሆን፤ ይህም የቀጣናዊ ኢነርጂ ትብብርን እያሳደገ የብሔራዊ ኃይል አቅርቦት መረቡን የመቋቋም ዐቅም ያጠናክራል። በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት አንዱ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው ተጀምሯል። እነዚህ ምኞቶች አይደሉም፤ ተጨባጭ ሐቆች ናቸው።
ግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ
በግብርናው ዘርፍ፤ የመንግሥት የምግብ ሉዓላዊነት አጀንዳ ወቅታዊ ለውጦችን ሳይሆን መዋቅራዊ ውጤቶችን እያስገኘ ቀጥሏል። በሶማሌ ክልል የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከአሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተፈረመው አጋርነት የዘመኑ ጉልህ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ማረጋገጫ ነው። ፋብሪካው በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ ማዳበሪያ አምራች ሀገራት ተርታ ያሰልፋታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤ “ይህ ፕሮጀክት በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢንዱስትሪ ዕድገትና በኢኮኖሚ ራስን መቻል ላይ የተደረገ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል። አስተማማኝ ባልሆነና ውድ በሆነ የማዳበሪያ አቅርቦት ለረጅም ጊዜ ለተገደቡት ኢትዮጵያውያን አምራቾች የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ ፈጣንና ተጨባጭ ነው።
ከዚህ ምርጫ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ ሲገኑ የታየው ተምሳሌትነት ለቦረና ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ይህ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅበት ስም የሀገርን አንገት ያስደፋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፤ እርሱም ድርቅ ነው።
ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዝናብ መጥፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን የገደለ፣ ቤተሰቦች ለውኃ ፍለጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን እንዲጓዙ ያስገደደ፣ እንዲሁም በእነዚህ የግጦሽ መሬቶች ላይ ለዘመናት ራሳቸውን ችለው የኖሩ ማኅበረሰቦችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እጅ እንዲዘረጉ አድርጎ ነበር። ዓለም የሚያውቃት ቦረና እርሷ ነበረች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንቦት ወር ጉብኝት ግን የተለየ ታሪክ አሳይቷል።
አሁን ላይ ለአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችና ለከብቶቻቸው ንጹሕ ውኃ እያቀረቡ ያሉትን የውኃና የመስኖ መሠረተ ልማቶችን የገመገሙ ሲሆን፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት አቧራ ብቻ በነበረው መሬት ላይ የክላስተር እርሻዎችን ጎብኝተዋል፤ በያቤሎ የባህል ማዕከል መርቀዋል፤ እንዲሁም በአየር ንብረት ሁኔታዎች ምክንያት ቀድሞ ተገልሎ ለነበረው ቀጣና ዓመቱን ሙሉ ትስስር የሚፈጥር አውሮፕላን ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።
የአምራች ዘርፉም ተመሳሳይ የለውጥ ታሪክ አለው። በግንቦት 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ፤ መንግሥት ለአራት ዓመታት የተመዘገበውን ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ውጤቶች አቅርቧል። የአምራች ዘርፉ የግብአት አቅርቦት በዓመት 9 ሚሊዮን ቶን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል። የምርት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ማደጉን፣ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው ፋይናንስ ከ8.1 ቢሊዮን ብር ወደ 50 ቢሊዮን ብር ማደጉን ያሳያል።
እነዚህ ስኬቶች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ኤክስፖው በተጠናቀቀ በሃያ ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃውን ከሀገር ውስጥ የሚያገኘውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት «ግራንዲዩር የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ» ፋብሪካን በሞጆ ከተማ መርቀዋል። ቀደም ሲል በገቢ የሴራሚክ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሴራሚክ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ለማቆምና ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ትገኛለች።
በቴክኖሎጂው ዘርፍም፤ ዘመናዊ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዳታ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥርዓቶች የሚወሰን መሆኑን በመገንዘብ፤ መንግሥት ኢትዮጵያን ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ 5.0 ማሕቀፎችን ቀድመው ከተገበሩ ሀገራት ተርታ እያሰለፋት ይገኛል።
የጽንፈኝነትን ፖለቲካ ውድቅ ማድረግ
በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከተሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና የቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ።
እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትንና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረ የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው።
መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረትና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር 'ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል። በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብትና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።
እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥሎ ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችንና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፣ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ ያካሄደው የሽብር እንቅስቃሴና ዝግጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጃቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም ይሄን የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል ፍላጎት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም። ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን አይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም ሁኔታውን በመቆጣጠር ፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል። በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል። ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል። መሰል ተግባሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃዎችን ይቀጥላል።
በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጸሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው። የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው።
ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም::
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ያኔ በ90ዎቹ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ሲጀመር እንዲህ አስተዋውቀን ነበር😊
የቅርብ ጊዜ ትዝታችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
❓✍️ ለመሆኑ የመጀመሪያው የሞባይል ስልካችሁ ምን ነበር?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
የቅርብ ጊዜ ትዝታችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
❓✍️ ለመሆኑ የመጀመሪያው የሞባይል ስልካችሁ ምን ነበር?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
2 months ago
ያኔ በ90ዎቹ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ሲጀመር እንዲህ አስተዋውቀን ነበር😊
የቅርብ ጊዜ ትዝታችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
❓✍️ ለመሆኑ የመጀመሪያው የሞባይል ስልካችሁ ምን ነበር?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
የቅርብ ጊዜ ትዝታችንን ለትውስታ አጋራናችሁ!
❓✍️ ለመሆኑ የመጀመሪያው የሞባይል ስልካችሁ ምን ነበር?
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
3 months ago
“ተጥለህ ነው ያገኘንህ"
በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት)
#ethiopia | በአብዛኞች የልጅነት ጊዜ የማይጠፋ ጨዋታ መሳይ ቀልድ አለ። "ተጥለህ እኮ ነው ያገኘንህ፤ ከጓሮ አግኝተንህ ነው እንጂ አንተ የኛ ልጅ አይደለህም።"
ሰሞኑን አንዲት ታካሚዬ የልጅነት ትውስታዋን ስታጋራኝ ይህ ንግግር ለዓመታት በውስጧ የፈጠረውን ባዶነትና የባዕድነት ስሜት ገልፃልኛለች።
ምንም እንኳን በጨወታ መሀል ወላጆች ይህን ቀልድ ቢያነሱም ለልጆች ግን የማንነት ጥያቄ የሚያስነሳ የጭንቀት ምንጭ ሊሆን ይችላል።
ህጻናት ዓለምን የሚያዩት በወላጆቻቸው አይን ነው። ወላጅ "የኛ አይደለህም" ሲል ልጁ የሚሰማው የመተው ፍርሃት እንዲሁም "እነዚህ ሰዎች ካልወለዱኝ ነገ ሌላ ሰው መጥቶ ቢወስደኝስ? ወይም እነሱ መልሰው ቢጥሉኝስ? የሚል ጭንቀት በውስጡ ሊፈጠር ይችላል።
ልጅነት "እኔ ማን ነኝ?" የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ወሳኝ ወቅት እንደመሆኑ ከጓሮ ተገኘህ የሚለው ቃል ልጁን ከማንነቱ በመነጠል ራሱን ሲያይ በቤተሰቡ መሃል እንደ እንግዳ እንዲሰማው ያደርገዋል።
በእያንዳንዱ ግጭት ወይም ቅጣት ወቅት ልጁ ያንን የጓሮ ታሪክ ያስታውሳል። "የእነርሱ ስላልሆንኩኝ ነው የሚቆጡኝ" ብሎ እንዲያስብና የራሱን ማንነት እንዳይቀበል እንዲሁም ሁልጊዜ ተቀባይነት ፍለጋ እና "እኔ እዚህ ቦታ አይገባኝም" የሚል የበታችነት ስሜት ሊያሳድርበት ይችላል።
"ተጥዬ የተገኘሁ ስለሆንኩ ዋጋ እንዲኖረኝና እንዳይጥሉኝ ሁልጊዜ ሰዎችን ማስደሰት አለብኝ" የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። ይህም የራሱን ፍላጎትና ስሜት ደብቆ ለሌሎች ይሁንታ ብቻ የሚኖር ስብዕና እንዲላበስ ሊያደርገዉ ይችላል።
ወደፊትም የፍቅር ሆነ የጓደኝነት ግንኙነት ሲመሰርት ሰዎችን ለማመን ይቸገራል። ሰዎች አንድ ቀን ጥለውኝ ይሄዳሉ የሚል ስጋት ስላለዉ ወይ ራሱን ቀድሞ ያገላል ካልሆነ ከመጠን በላይ ሰዎች ላይ ሊጣበቅ ይችላል። ታካሚዬ ላይ ያየሁትም ይሄንኑ ነበር።
ይህ ቀልድ መሳይ ጨዋታ በልጆች እያደገ ባለ ስነልቦና ላይ ከባድ አሻራ ይጥላልና መቅረት ያለበት ልማድ ነዉ።
#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር #mentalhealthawarenessmonth

ራስ መኮንን ግቢ ላይ ከቆሙት ሬዲዮ ጣቢያ አንቴናዎች የአንዱ ተከላ በተፈጸመበት ጊዜ ካስቀረነው ምስል ለትውስታ አጋራናችሁ!
1927 ዓ.ም
ሐረር

Comments