2 days ago
ራፊንሃ እስከ ሰኔ 2030 የሚያቆየውን አዲስ ውል ከባርሴሎና ጋር ተፈራርሟል!
ሁሉም ነገሮች ከወኪሎቹና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ተስማምተው ተጠናቀዋል እናም አዲሱ ስምምነት ተጠናቆ ተዘጋጅቷል።
ሁሉም ነገር በሰነዶቹ መሠረት ከሄደ ይፋ ማድረጉ እና የስምምነት ሥነ ሥርዓቱ በዚህ ሳምንት ዐርብ ሊካሄድ ይችላል።
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

🚨 ሉካ ሞድሪች ስለ ሪያል ማድሪድ ወቅታዊ ሁኔታ፦
“ገና የውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ነው።
በሞውሪንሆ ስር ያለውን ማድሪድ ስመለከት፣ እንደተለመደው ለሁሉም ዋንጫዎች ለመፎካከር ዝግጁ የሆነ ድንቅ ቡድን አያለሁ።
ባርሴሎና በ6 ነጥብ እየመራ ነው ብሎ መጨነቅ ወይም ሁሉም ነገር አብቅቷል ብሎ ማሰብ አያስፈልግም።
ቡድኑ ያንን የነጥብ ልዩነት ሙሉ በሙሉ የማጥበብ እና ዋንጫውን የማሸነፍ አቅም አለው።”
@Bisrat_Sport_433et

5 days ago
“ በባርሴሎና ጫማ መስቀል እፈልጋለሁ ” ጋቪ
የባርሴሎናው የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቪ የእግርኳስ ህይወቱን በአንድ ክለብ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ ገልጿል።
“ በባርሴሎና ጫማዬን መስቀል እፈልጋለሁ በአንድ ክለብ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ ” ሲል ጋቪ ተናግሯል።
አክሎም “ ለእኔ ስኬት ማለት በባርሴሎና ለረጅም አመት መጫወት ያለኝን ሁሉ መስጠት መቻል ነው "ብሏል።
ጋቪ አያይዞም የገጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት የማሰቢያ ጊዜ እንደሰጠው እና አሁን ትንሽ የተረጋጋ እንዲሆን እንደረዳው ተናግሯል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

6 days ago
ራፊና የወሩ ምርጥ ሽልማት አሸንፏል !
የባርሴሎና የፊት መስመር ተሰላፊ ራፊና የመስከረም ወር የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።
ራፊና በተከታታይ ወር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት አሸንፏል።
ጥሩ የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው ራፊና በመስከረም ወር ባደረጋቸው የሊግ ጨዋታዎች :-
⏩ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ
⏩ ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
የባርሴሎና የፊት መስመር ተሰላፊ ራፊና የመስከረም ወር የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።
ራፊና በተከታታይ ወር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት አሸንፏል።
ጥሩ የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው ራፊና በመስከረም ወር ባደረጋቸው የሊግ ጨዋታዎች :-
⏩ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ
⏩ ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
7 days ago
“ የተከፈተ አዲስ ምርመራ የለም ” ባርሴሎና
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የተለየ ምርመራ አለመጀመሩን ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ባርሴሎና በመግለጫው ምርመራው በ 2023 መከፈቱን አስታውሶ እስካሁን አልተዘጋም እየተካሄደ ነው ብሏል።
ክለቡ ከነበረው ውጪ “ አዲስ ምርመራ ተጀመረ " መባሉን ሀሰተኛ ነው ሲል አስተባብሏል።
ዩኤፋ ከሪያል ማድሪድ አዲስ ፋይል መቀበሉን እና የቀድሞው ምርመራ አካል አድርጎ እየገመገመ መሆኑን ገልጿል።
ባርሴሎና በበኩሉ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የደረሰው አዲስ ጥያቄ አለመኖሩን አስታውቋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe “ የባርሴሎና ምርመራ ይፋጠን ” ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎና ላይ እየተካሄደ ለሚገኘው ምርመራ ፋይሎች እንደሰጠው ገልጿል። ሪያል ማድሪድ ከ ኔግሬራ ጉዳይ ጋር የተያያዘ 50ሺህ ገፆች ያሉት ፋይል ለዩኤፋ ሰጥቷል። ባርሴሎና ባለፉት አመታት ለቀድሞ የዳኞች ምክትል ሀላፊ ተቋም ገንዘብ ከፍሏል በሚል ምርመራ ላይ መሆኑ ይታወቃል። አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ…

Sponsored by
Surafel
7 days ago
“ የባርሴሎና ምርመራ ይፋጠን ” ሪያል ማድሪድ
የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎና ላይ እየተካሄደ ለሚገኘው ምርመራ ፋይሎች እንደሰጠው ገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ከ ኔግሬራ ጉዳይ ጋር የተያያዘ 50ሺህ ገፆች ያሉት ፋይል ለዩኤፋ ሰጥቷል።
ባርሴሎና ባለፉት አመታት ለቀድሞ የዳኞች ምክትል ሀላፊ ተቋም ገንዘብ ከፍሏል በሚል ምርመራ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የተሰጠውን ፋይል ተቀብሎ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ቅሬታውን መቀበሉን ገልጿል።
ክለቡ አክሎም ምርመራውን በፍጥነት እንዲካሄድ እና የመጨረሻ ውሳኔ ላይ እንዲደረሰ ጠይቋል።
ሪያል ማድሪድ ባርሴሎና በቀረበበት ቅሬታ ወቅት ያሸነፋቸውን 3️⃣3️⃣ ዋንጫዎች እንዲመልስ ይፈልጋል።

🚨 ይፋዊ የዩኤፋ መግለጫ፡
UEFA) ከኔግሬራ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያወጣው መግለጫ፤
“ዩኤፋ፣ ከሮያል ስፓኒሽ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ቴክኒክ ኮሚቴ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሆሴ ማሪያ ኤንሪኬዝ ኔግሬራ ጋር በተያያዘ በባርሴሎና ላይ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ዙሪያ፣ ከሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸውን ሰነዶች መቀበሉን ያረጋግጣል።”
“የዩኤፋ የስነ-ምግባር እና የዲሲፕሊን ጉዳዮች መርማሪዎችም እነዚህን አዳዲስ ሰነዶች የተረከቡ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ እያደረጉት ባለው ክትትል እና ግምገማ ሂደት ውስጥም ይመለከቷቸዋል።”

8 days ago
በአውሮፓ የቅርጫት ኳስ ሊግ ሊጀምር ነው !
የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የአውሮፓ ቅርጫት ኳስ ሊግ ለመጀመር በመስራት ላይ መሆናቸው ተነገረ።
ሊጉን ለማስጀመር ያቀዱት ሪያል ማድሪድ ፣ ፒኤስጂ ፣ ባርሴሎና ፣ ባየር ሙኒክ እና ኤሲ ሚላን መሆናቸው ተገልጿል።
ክለቦቹ የአውሮፓ ቅርጫት ኳስ ሊግ ለማስጀመር ከ " NBA " ጋር እየሰሩ መሆኑ ተዘግቧል።
የቅርጫት ኳስ ሊጉ " የአውሮፓ NBA " እንደሚባል ተገልጿል።

“ ለማንችስተር ሲቲ አክብሮት አለኝ ” ሁዋን ላፖርታ
የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ስለ ማንችስተር ሲቲ ክስ ተጠይቀው “ አያሳስበኝም ” ሲሉ መልሰዋል።
“ ይሄ የእነሱ ጉዳይ ነው ነገርግን ለማንችስተር ሲቲ አክብሮት አለኝ ” ሲሉ ሁዋን ላፖርታ ተናግረዋል።
አክለውም “ ማንችስተር ሲቲ ክሱን ይግባኝ እንደሚል አምናለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe “ ሲቲ ላይ ትልቁ ቅጣት መጣል አለበት ” ዣቪየር ቴባስ የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ማንችስተር ሲቲ ላይ ትልቅ ቅጣት እንዲጣል ጠየቁ። ዣቪየር ቴባስ ሲናገሩም “ በፕሪሚየር ሊጉ ያለው ትልቅ የቅጣት ህግ መተግበር አለበት ” ሲሉ ገልፀዋል። “ የማንችስተር ሲቲ ቅጣት ለወደፊት መማሪያነት ማገልገል አለበት ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ ከአስር አመት በላይ ህግ መጣስ ከባድ ነገር ነው “ ብለዋል።…

9 days ago
🚨 | የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆአን ላፖርታ በማንቸስተር ሲቲ ላይ ስለቀረቡት ክሶች፡-
"ይህ የእኔ ጉዳይ አይደለም። የማንቸስተር ሲቲ ጉዳይ ነው። እኔ ለእነሱ ትልቅ ክብር አለኝ። እናም ክሱ ላይ ይግባኝ ጠይቀው እንደሚያስተካክሉ እገምታለሁ።"
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
"ይህ የእኔ ጉዳይ አይደለም። የማንቸስተር ሲቲ ጉዳይ ነው። እኔ ለእነሱ ትልቅ ክብር አለኝ። እናም ክሱ ላይ ይግባኝ ጠይቀው እንደሚያስተካክሉ እገምታለሁ።"
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
13 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድ የሜዳ ላይ ሳሩን ለሽያጭ ማቅረቡ ግርምትን ፈጠረ
ማንቸስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል ባርሴሎና ይጠቀምበት የነበረውን የገቢ ማግኛ መንገድ በመከተል የኦልድ ትራፎርድ ስታዲየሙን የሜዳ ሳር ለደጋፊዎች መሸጥ መጀመሩ ተዘግቧል።
ክለቡ 7 ሴንቲሜትር ስፋት ያለውን የኦልድ ትራፎርድ የሜዳ ሳር በብርጭቆ ዕቃ (Turf Cube) ውስጥ አሽጎ በ125 ፓውንድ ለገበያ አቅርቦታል ተብሏል።
በታዋቂው የስፖርት ዘጋቢ ፖል ሂርስት እና በታዋቂ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፣ ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናን የካምፕ ኑ አሰራር በመከተል የታዋቂውን ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የሜዳ ሳር ለአንደኛ ደረጃ የትኬት ባለቤቶች (Season-ticket holders) እና ለደጋፊዎች መቸርቸር ጀምሯል።
ክለቡ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦልድ ትራፎርድን ሙሉ የሜዳ ሳር በአዲስ መቀየሩን ተከትሎ፣ በቅርቡ የፋይናንስ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት እና የ47 ሚሊዮን ፓውንድ ዓመታዊ ከታክስ በፊት ኪሳራ ባጋጠመበት ወቅት ይህንን ማድረጉ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ክለቡ ጥቂት ግራም ሳር በ125 ፓውንድ ከፍተኛ ዋጋ መሸጡን ተከትሎ ጉዳዩ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ እና የቀልድ ርዕስ ሆኗል።
Seledadotio

14 days ago
ኔዘርላንድስ ከ ጀርመን የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ኔዘርላንድስ እና ጀርመን አዲስ በሾሟቸው አሰልጣኞች መሪነት ምሽት 3:45 ላይ ይገናኛሉ።
በኔዘርላንድስ በኩል ሮናልድ ኩማን መልቀቃቸውን ተከተሎ የቀድሞ የባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ይመራሉ።
የጁሊያን ናጌልስማንን ቦታ የተኩት አሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕ በጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ዶንየል ማለን እና ጁስቲን ክላይቨርት በጉዳት ምክንያት ከኔዘርላንድስ ስብስብ ውጪ ሲሆኑ ፍሬንኪ ደ ዮንግ እና ማቲጅስ ደ ሊት ቀደም ብለው በጉዳት አልተካተቱም።
ሜምፊስ ዲፓይም በዣቪ ስብስብ ውስጥ አልተካተተም ነበር ነገር ግን አምበሉ ቨርጅል ቫን ዳይክ ብሔራዊ ቡዱኑን በአምበልነት ይመራል።
በአሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ጀርመን በኩል ለሁለቱ ጨዋታዎች የያዙትን ስብስብ በሁለት የከፈሉ ሲሆን ፍሎሪያን ቪርትዝ እና ኒክ ቮልቴማዴ በዚህ ጨዋታ አይሰለፉም። በሌላ በኩል ፊሊፕ ትሬው የመጀመሪያ ጨዋታውን ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ሊያደርግ ይችላል።
በጋዲሳ መገርሳ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

አምስተኛው የአውሮፓ ሀገራት ሊግ (ኔሽንስ ሊግ) ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
*******
እ.አ.አ በ2018 ጅማሮውን ያደረገው የአውሮፓ ሀገራት ሊግ ዛሬ በተለያዩ ከተሞች በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያደርጋል።
በምድብ አራት ምሽት 3፡45 የሁለት ጊዜ ሻምፒዮኗ ፖርቹጋል ከዌልስ የሚያደርጉት ጨዋታ ከዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች አንዱ ነው። በእግር ኳስ ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 1ሺህ ለማድረስ እየተንደረደረ የሚገኘው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም የትኩረት ማዕከል እንደሆነ ቀጥሏል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ሆርጌ ጄሱስ የሚመራው የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን፣ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ የተቋረጠውን መንገዱን ለማቃናት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታውን ያደርጋል።
ለ23ኛው ዓለም ዋንጫ ያላለፈበትን ጨምሮ ከጋሬዝ ቤል ስንብት በኋላ የውጤት ማሽቆልቆል የተስተዋለበት የዌልስ ብሔራዊ ቡድን በቀድሞ የሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ኮከብ ክሬግ ቤላሚ አሰልጣኝነት እየተመራ ጨዋታውን ያደርጋል።
ሁለቱ ሀገራት በታሪካቸው የተገናኙት አራት ጊዜ ሲሆን ሦስቱ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ሲጠናቀቅ፣ አንዱ ደግሞ በአቻ ውጤት ነው ፍፃሜውን ያገኘው።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በዕረፍት አሳልፈው የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን የተረከቡት ውጤታማው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ አምስተርዳም አቅንተው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድንን በመግጠም ጉዟቸውን ይጀምራሉ።
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በፓራጓይ ተረቶ ከ32ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ የተሰናበተው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን፣ በቀደመው ውድድር 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት የኔሽንስ ሊግ ትልቁ ውጤቱ ነው።
በቀድሞ የባርሴሎና ኮከብ ዣቪ ኸርናንዴዝ የሚመራው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በአንፃሩ በ2018 ውድድር እስከ ፍፃሜ የመጓዝ ታሪክ አለው።
በዮሃን ክራይፍ ስታዲየም የሚደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 3፡45 ይጀምራል።
ሰርቢያ ከ ግሪክ፣ ኖርዌይ ከ ዴንማርክ፣ ኦስትሪያ ከ እስራኤል እንዲሁም ኮሶቮ ከ አየርላንድ ሌሎቹ የዛሬ የኔሽንስ ሊግ መርሐ ግብሮች ናቸው።( EBC Sport )
@Bisrat_sport_433et @Bisrat_sport_433et

15 days ago
“ በሀንሲ ፍሊክ ሥራ ተደስቻለሁ ” ዣቪ
ስፔናዊው የኔዘርላንድ አሰልጣኝ ዣቪ አሰልጣኝ ሀርናንዴዝ ሀንሲ ፍሊክ በባርሴሎና እየሰሩ የሚገኙትን ነገር አድንቋል።
“ ሀንሲ ፍሊክ በጣም ጥሩ ሥራ እየሰራ ነው ይሄን ማየቴ በጣም አስደስቶኛል “ ሲል ዣቪ ተናግሯል።
ባርሴሎናን ሁልጊዜ እንደሚከታተል የገለፀው ዣቪ የአሁኑ ትውልድ ትልቅ ነገር ሊያሳካ እንደሚችል ገልጿል።
ስለ ላሚን ያማል ያነሳው ዣቪ “ ላሚን ያማል የተለየ ተጨዋች ነው ገና 19ዓመቱ ነው "ብሏል።
“ ያለ ጥርጥር አንድ ቀን ባሎን ዶር ያሸንፋል ነገርግን አሁን ለማሸነፍ ለእሱ ጥሩ አመት ሊሆን ይችላል " ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

16 days ago
ደራርቱ እና ልቅና‼️
ከአራት አመት በፊት በዚሁ በመስከረም ወር፦
ለደራርቱ መልዕክት አስቀመጥኩላት፤ ፈጣን ምላሽ ላከችልኝ
#ethiopia | ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አትሌት ልቅና አምባው በጤና እክል ምክንያት ስፔን ውስጥ ችግር ላይ ነበረች፤ የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ደግሞ በባርሴሎና ኦሊምፒክ 30ኛ አመት የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት ተጋብዛ እሷም ስፔን ተገኝታ ነበር፤ አጋጣሚውን ተጠቅሜ የአትሌቷን ጉዳይ አነሳሁላት፤ ለመፍትሄ ጊዜ አልወሰደችም
በቅድሚያ ልቅና አምባው ያጋጠሟትን ችግሮች የተመለከቱ መረጃዎችን ሰበሰበች፤ የኢትዮ ራነር ዘጋቢው ወንዴ ተጨማሪ ግብአት ሰጣት
ቀጥላ በስፔን ለኢትዮጵያ አምባሳደር ጉዳዩን አሳወቀችና አትሌቷን ለማግኘት ጥረት ጀመረች፤ ተሳካላት፦
"ወርቅነህ የተባለ ልጅ በስልክ አገናኝቶኝ ልቅናን አውርቻታለሁ፤ ማድሪድ ከተማ ነው ያለችው፤ ከሆስፒታል ወጥታ ቤቷ መግባቷን ነግራኛለች፤ ወደ ሀገር ቤት መመለስ ትፈልጊያለሽ ወይ ስላት 'ቢያንስ ለአራት ወራት እዚሁ ሆነሽ ህክምናሽን ተከታተይ ስላሉኝና የምወስደው መድሀኒት ስለሚኖር ስፔን ብቆይ ይሻላል' ብላኛለች፤ ጉዳዩን በዝርዝር ለኤምባሲያችን አሳውቄያለሁ፤ በቅርበት ያግዟታል፤ ከማናጀሯ አልቤርቶ ጋርሺያ ጋርም አውርተናል፤ ከእኛ ፌዴሬሽን ጋር አብሮ የሚሰራ ሰው ነው፤ እሱም ሀላፊነቱን እንደሚወጣ አረጋግጦልኛል። ሀገር ቤት ያለ የቤተሰብ አካል ከጎኗ እንዲሆን ከፈለገችም ከኤምባሲያችን ጋር ተነጋግረን ሁኔታዎችን እናመቻቻለን ብያታለሁ፤ ከእኛ ሀኪሞች ጋር እንድትገናኝም እናደርጋለን፤ ቶሎ ተሽሎሽ ወደ ልምምድ ተመልሰሽ ለፓሪሱ ኦሊምፒክ እንድትደርሺልን እፈልጋለሁ ብያት ተለያይተናል" ብላኝ ነበር ደራርቱ
ከአራት አመት በኋላ በዚሁ ወር መስከረም፦
ያጋጠማትን ፈተናዎች በፅናት ተግላ ያሸነፈችው ልቅና አምባው ሰሞኑን ደግሞ በመምና በጎዳና ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክላ ስሟን በአኩሪ ድል በደማቁ ፅፋ አሸንፋለች፤ በዳይመንድ ሊግ ደምቃ፥ በአልትሜት ሻምፒዮንሺፕ ሀንጋሪ ቡዳፔስት ላይ በ5000 ሜትር ኢትዮጵያን ወክላ አሸንፋ፥ በስድስት ቀን ልዩነት ደግሞ ዴንማርክ ኮፐንሀገን በ5ኪ.ሜ ቀዳሚ ሆና ገብታ ሀገሯን አኩርታለች
ይህንን ተከትሎ ከአራት አመት በፊት ትልቅ ትብብር ያደረገችላት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ምን እንደተሰማት ጠይቄያት ነበር፤ አጭር ምላሽ ሰጥታኛለች፦
"ልቅና ከዛ ሁሉ ችግር ወጥታ ዛሬ እዚህ በመድረሷ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከምንም በላይ ደግሞ የምንወዳት ኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ እንድታደርግ እግዚአብሔር እንኳን ረዳት፤ ለወደፊቱም መልካሙን ሁሉ እመኝላታለሁ" ብላለች፤ ደራርቱ በአትሌቷ የችግር ወቅት ፈጥነው ከደረሱና ለመፍትሄ ከተባበሩት አንዷ በመሆኗ ምስጋና ይገባታል፤ ሌሎች ድጋፍ ያደረጉላትም ምስጋና ይድረሳቸው
ከዚህ ጋር ተያይዞ ልቅና ሀገሯን ለመወከል ያላትን ፅኑ ፍላጎት በመረዳት ኢትዮጵያን እንድትወክል እድል የሰጧትና በሙሉ ድምፅ የተቀበሏት በኮማንደር ስለሺ ስህን የሚመሩት የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚዎች በተመሳሳይ ምስጋና ይገባቸዋል፤ አሁን ልቅና አምባው በቀጣዩ የቤጂንግ የአለም ሻምፒዮናና በሎስአንጀለሱ ኦሊምፒክ ለአሸናፊነት የምትጠበቅ ኢትዮጵያዊት ተስፈኛ አትሌት ሆናለች፥ እንደጨለመ አይቀርም፥ ይነጋል !
(ታምሩ ዓለሙ)

17 days ago
እግር ኳስን ለማቆም ጫፍ ደርሶ የነበረው ኮከብ - ራፊንሃ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢቢሲ ስፖርት አምደኛው ጊሌም ባላጌ፥ ብራዚላዊው ኮከብ "የእግር ኳስ ህልሜ አክትሞለታል" የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን አጋጣሚ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይተርካል።
በብራዚሏ ፖርቶ አሌግሪ ከተማ የተወለደው ራፋኤል ዲያዝ ቤሎሊ (ራፊንሃ) እግር ኳስን የጀመረው እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳስ ባለው ፍቅር ብቻ አልነበረም።
ስኬታማ እግር ኳስ ተጫዋች መሆን፥ በከፋ ድህነት፣ በወንጀልና በአደንዛዥ ዕጽ ከሚታወቀው የትውልድ መንደሩ ማምለጫው ብቸኛ መንገድ መሆኑን ስለተረዳም ጭምር ነው።
የህልሙን መንገድ ተከትሎ ገና በልጅነቱ እግር ኳስን ቢጀምርም፤ የ18 ዓመት ወጣት እያለ ያጋጠመው የህይወት አጣብቂኝ ለዛሬ ስኬቱ መስፈንጠሪያ ሆኖታል።
የስፖርት አምደኛው እንደሚለው፥ በዚያ ወቅት ራፊንሃ ከሚጫወትበት የአቫይ ወጣት ቡድን ውጪ ሆኗል፤ ጉዳት አስተናግዷል፤ ፈላጊ ክለብ አጥቶ የእድል በሮች ሁሉ ተከርችመውበት ነበር።
እነዚህ ሁኔታዎች እግር ኳስ የማቆም አፋፍ ላይ አድርሰውት በነበረበት ወቅት፥ እናቱ የሰጡት ምክር ያበቃለት ለመሰለው ህልሙ ነፍስ ዘርቶለታል።
"የእግር ኳስ ጉዞህን ለማቆም ከወሰንክ፤ ቀሪውን እድሜህን አሁን ባለህበት ሁኔታ ለመኖር እንደወሰንክ እወቀው" ነበር ያሉት።
ጊሌም ባላግ በዚህ አምዱ፥ ከዚያች ቅጽበት በኋላ ራፊንሃ እስከ ባርሴሎና መልበሻ ቤት ያደረገው ጉዞ የጽናት፣ የዲሲፕሊን እና ራስን የማብቃት ታሪክ ነው ሲል ይገልጻል።
በእግር ኳስ ሕይወቱ ያሳየው ከፍታ የተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን፤ የዓላማ ጽናት፣ የመስዋዕትነትና ለህልም የመኖር መሻት ውጤት መሆኑን ያነሳል።
ራፊንሃ እንደ አብዛኞቹ ብራዚላውያን ከዋክብት ብቃቱን በሀገሩ ብራዚል ሊጎች ለማሳየት አልታደለም፤ በዚህም ምክንያት ከአውሮፓ ዝቅተኛ ሊጎች መጀመር ግድ ብሎታል።
በፈረንጆቹ 2016 የፖርቹጋሉን ክለብ ቪቶሪያ ጊማሬሽ የወጣት ቡድን ከተቀላቀለ በኋላ ወደ ዋናው ቡድን ያደገ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ ሌላኛው የፖርቹጋል ክለብ ስፖርቲንግ አመራ።
በቀጣዩ ዓመት ወደ ፈረንሳዩ ሬን በማምራት ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማቅናት ሊድስ ዩናይትድን መቀላቀል ችሏል።
የሊድስ ቆይታው በማርሴሎ ቤልሳ ስር ከኳስ ክህሎቱ ባሻገር ተክለሰውነቱን ያጠነከረበትና ቴክኒካዊ ብቃቱን ያጎለበተበት ነበር።
በሁለት ዓመት የኢላንድ ሮድ ቆይታው በፕሪሚየር ሊጉ በ29 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ባሳየው አስደናቂ ብቃት በ50 ሚሊየን ፓውንድ መነሻ የዝውውር ሂሳብ ባርሴሎናን መቀላቀሉ አይዘነጋም።
በብሉ ግራናዎቹ ቤት በወቅቱ የክለቡ አሰልጣኝ በነበረው ዣቪ ስር፥ ራፊንሃ እንደ ስብስቡ አማራጭ የሚቆጠር እንጂ በቋሚነት የሚሰለፍ ተጫዋች አልነበረም።
በቋሚነት በሚጀምርባቸው ጨዋታዎችም በጊዜ ተቀይሮ የሚወጣ የነበረው ተጫዋቹ፤ በባርሴሎና ቤት በፍጥነት ለመድመቅ ተቸግሮ ነበር።
በፈረንጆቹ 2024 የካታላኑ ክለብ ከቀድሞ ተጫዋቹ ጋር ተለያይቶ ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ሲሾም ለራፊንሃ ሁኔታዎች ተቀየሩ።
በሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎና ተከላካዮችን ለማለፍ የማይቸገር፣ በግብ ፊት ምህረት የለሽ ቁልፍ ተጫዋች መሆን ችሏል፤ በአሰልጣኙ የተሰጠው ሚና በራስ መተማመኑን ከፍ እንዳደረገለት ይነገራል።
በዚህ የውድድር ዓመት ብቻ በላሊጋው ለተከታታይ ሁለት ጊዜ ሀትሪክ መስራት የቻለው ብራዚላዊ የመስመር አጥቂ፥ በ12 ግቦች የላ ሊጋውን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ይገኛል።
በሀንሲ ፍሊክ ስር ለክለቡ ባደረጋቸው 98 ጨዋታዎች 69 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል፤ 32 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ከባርሴሎና ጋር ሦስት ጊዜ የላ ሊጋ ሻምፒዮን ሆኗል፤በ2024/25 የውድድር ዓመት የውድድሩ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ገና በ18 ዓመቱ እግር ኳስን ለማቆም ተቃርቦ የነበረው የባርሴሎና አምበል፤ በ2025ቱ የባሎንዶር ሽልማት ምርጥ 5 ውስጥ መካተት ችሎም ነበር።
በኃይለማሪያም ተገኝ

19 days ago
ባርሴሎና የድል ጉዞውን ቀጥሏል
#ethiopia | ባርሴሎና በላሊጋ 7ኛ ሳምንት ሴቪያን 3–1 በማሸነፍ ፍጹም የድል ጉዞውን አስቀጥሏል።
በተለይ ራፊንሃ ሃትሪክ በመስራት የባርሴሎናን የጥቃት ኃይል እንደገና አሳይቷል።
ከስድስት የላሊጋ ጨዋታዎች በፊት 28 ጎሎችን ያስቆጠረው ባርሴሎና፣ ከሴቪያ ጨዋታ በኋላ የጎል ያስቆጠረውን 31 አድርሷል።
ባርሳ አሁን በእሳት ላይ ነው

20 days ago
20 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማክሰኞ ዕለት ማንቸስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ በይፋ ደብዳቤ ያስገባው የጄጄ ገብርኤል ውሳኔ፣ በእግር ኳሱ ዓለም ያልታሰበ ማዕበል ፈጥሯል። ገና በ15 ዓመቱ በአውሮፓ ከሚገኙ እጅግ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች አንዱ ተብሎ የሚታሰበው ይህ ድንቅ አጥቂ፣ ከዘጠኝ ዓመቱ ጀምሮ ያሳለፈበትን ክለብ ለመሰናበት ቋምጧል፤ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችም እሱን ለመጥለፍ አሰፍስፈዋል።
ሪያል ማድሪድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ በጥሩ ቁመና ላይ ሲገኝ፣ ባርሴሎና፣ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን እና ባየር ሙኒክም ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። ዩናይትዶች ልጁን ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ነገሮች ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ይመስላሉ። ገብርኤል ባለፈው ሀሙስ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ከ19 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር በዩኤፋ የወጣቶች ሊግ ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ወደ ስፍራው ድርሽ አላለም፤ አሁን ባለው ሁኔታም ይመለሳል ተብሎ አይጠበቅም። በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ዩናይትድ ወደፊት 100 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያወጣ የሚችልን አልማዝ በገዛ እጁ እያጣ መሆኑን ይገምታሉ።
ይህ ውሳኔ ድንገት የመጣ አይደለም። የችግሩ ጭላንጭል የታየው ባለፈው ሀሙስ ነበር። ገብርኤል በኦልድ ትራፎርድ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሚጫወተው ዋናው ቡድን ጋር ከመሰለፍ ይልቅ፣ ከአዘርባጃኑ ሳባህ ጋር ለሚጫወተው የ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲሰለፍ ተደረገ። በጨዋታው ሶስት ግቦችን ቢያስቆጥርም፣ እሱና ቤተሰቡ ግን የሻምፒዮንስ ሊግ ድባብን በዋናው ቡድን ውስጥ ሆኖ እንዲቀምስ ፈልገው ነበር። ይህ ክስተት ትልቅ ስብራት ፈጠረ፤ ውሳኔውም ወዲያውኑ ለክለቡ ተነገረ። ቅዳሜ ዕለት ከዋናው ቡድን አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ጋር ልምምድ ማድረግ ሲገባው፣ ከካሪንግተን በመቅረት ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል አቃጨለ። ወዲያውም ከኢንስታግራም ገጹ ላይ ስለ ዩናይትድ የሚገልጹ መረጃዎችን በሙሉ አጠፋ። ሰኞ ዕለት ደግሞ ምዝገባው እንዲሰረዝለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለክለቡ አስገባ። የማንቸስተር ዩናይትድ ኃላፊዎች፣ በተለይም ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ እና አብሮ ባለቤቱ ሰር ጂም ራትክሊፍ በጉዳዩ ክፉኛ ተደናግጠዋል።
ሪያል ማድሪድ ይህንን ታዳጊ ለማስፈረም በስውር ሲሰራ ወራት አልፈውታል። ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ፣ የፊፋን ጥብቅ ህጎች ላለመጣስ ሲባል ክለቡ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። የማድሪድ እቅድ ልጁን መጀመሪያ ለካስቲላ (የማድሪድ ሁለተኛ ቡድን) እና ከ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲጫወት አድርጎ፣ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ነው። ይህ ከዚህ ቀደም በአያክሱ የ17 ዓመት ታዳጊ አብደላ ኦዋዛኔ ላይ ሊሞክሩት ያሰቡት ዓይነት ስልት ነው። የማድሪድ ሰዎች የገብርኤልን የሀሙስ ዕለት ሀትሪክ በቅርበት ሲከታተሉና ሲያከብሩ ነበር።
በህግ አግባብ ዩናይትድ የልጁን ውል የመቀደድ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ገብርኤል የአውሮፓ ህብረት ፓስፖርት ካገኘ፣ ልክ ጥቅምት 6 ቀን 16 ዓመት ሲሞላው ወደ ሌላ የአውሮፓ ክለብ መዘዋወር ይችላል። አባቱ ጆ ኦኬሩይል የተወለደው ለንደን ቢሆንም ለአየርላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል፤ እናቱም የሳይፕረስ ትውልድ አላት። ይህ ደግሞ ፓስፖርቱን በቀላሉ እንዲያገኝ በር ይከፍትለታል። ከዚህም ባሻገር፣ ገብርኤል መደበኛ የትምህርት ቤት ትምህርቱን በቤት ውስጥ የሚከታተል በመሆኑ፣ በዩናይትድ ሙሉ ጊዜ አካዳሚ ስር አይወድቅም፤ ይህም ክለቡ በልጁ ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያላላዋል። ገብርኤል ዩናይትድን የሚለቅ ከሆነ፣ ፊፋ ባስቀመጠው የካሳ ስሌት መሰረት ዩናይትድ ከ100,000 ፓውንድ በላይ የማሳደጊያ ካሳ ሊያገኝ ይችላል።
ገብርኤል ገና በዘጠኝ ዓመቱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ ሲወጣ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ይነጻጸር ነበር። ነገር ግን የእሱ ተወዳጅ ተጫዋች ኔይማር ሲሆን፣ ኳስን አጣብቆ የመያዝ፣ ፈጣን እንቅስቃሴ የማድረግ እና በሁለቱም እግሮቹ ግሩም አጨራረስ ያለው በመሆኑ የጨዋታ ስታይሉ ከብራዚላዊው ኮከብ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። በዩናይትድ የዋናው ቡድን ልምምዶች ላይ በተደጋጋሚ በመሳተፍ፣ አንጋፋ ተጫዋቾችን ሳይቀር በቴክኒክ ብቃቱ አስገርሟል። በአካላዊ ጥንካሬ ከእሱ በሚበልጡ ተጫዋቾች ቢገፋም፣ በተፈጥሮ ያገኘው ክህሎት ወደፊት ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታ እንደሚያሰልፈው ብዙዎች ይስማሙበታል። ባለፈው ታህሳስ በኤፍኤ የወጣቶች ዋንጫ ለዩናይትድ በመሰለፍ እና ግብ በማስቆጠር ታሪካዊ ሪከርድ ሰብሯል፤ በወጣቶች ሊግ ባደረጋቸው 34 ጨዋታዎችም 31 ግቦችን እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዩናይትድ ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ታላቅ ታሪክ አለው። "በቂ ብቃት ካለህ፣ በቂ ዕድሜ አለህ" የሚለው የሰር ማት ባስቢ ብሂል ክለቡን ለዘመናት መርቶታል። ገብርኤልም የዚህ ታሪክ ቀጣይ አካል ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን በቅርብ ጊዜ የተፈጠሩ ክስተቶች ጥርጣሬን አጭረዋል። በክረምቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ በቂ የመጫወት ዕድል አላገኘም፤ በአትሌቲኮ ማድሪዱ ጨዋታ ከተፈጥሮ ቦታው ውጪ እንዲጫወት ሲደረግ፣ አዲሱ ፈራሚ የ18 ዓመቱ ታይናን ቶምሰን ግን በገብርኤል ተወዳጅ ቦታ በግራ ክንፍ ላይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቷል። በሻምፒዮንስ ሊግ የ'ኤ' ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም ሌላው ቅር ያሰኘው ጉዳይ ነው። አርሰናል የ15 ዓመቱን ማክስ ዶውማንን በዝርዝሩ ውስጥ አካቶ ክብረ ወሰን ሲሰብር፣ የገብርኤል ስም ግን አልነበረም። አላማው በቋሚነት መሰለፍ ሳይሆን፣ ክለቡ በእሱ ላይ ያለውን እምነት በተጨባጭ ማየት ነበር።
ባለፈው ክረምት ማንቸስተር ሲቲ ገብርኤልን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ የዩናይትድ የስፖርት ዳይሬክተር ጄሰን ዊልኮክስ እና የድርድር ዳይሬክተሩ ማት ሀርግሪቭስ ጣልቃ ገብተው አክሽፈውት ነበር። ወደ ሌላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ማምራቱ በህግ አግባብ እጅግ ፈታኝ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዩናይትድ ልጁን ለማሳመን ከቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና ከታላቁ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ጭምር አገናኝቶታል። ማይክል ካሪክ በቅርበት ያሰለጠነው ሲሆን፣ የዋናው ቡድን ማሊያ ቁጥር 77ም ተሰጥቶታል።
አሁን ላይ ዩናይትዶች በቀጣዩ ወር 16ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲያከብር የማበረታቻ የትምህርት ኮንትራት እና በ17 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ውል ለማቅረብ እየተዘጋጁ ነበር። በፋይናንስ አቅርቦት ማንም ክለብ እንደማይበልጣቸው ያምናሉ። ነገር ግን የገብርኤል ውሳኔ የተቆረጠ ይመስላል፤ ስለዚህ ዩናይትድ ውጤቱን በትዕግስት ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። አርብ ዕለትም ክለቡ ለቀረበው የምዝገባ ስረዛ ደብዳቤ ይፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

23 days ago
ባላንዶር ለእኔ ብቻ ይገባል! - ላሚን ያማል
የባርሴሎናው ወጣት አጥቂ ላሚን ያማል የ2026 የባሎንዶር ክብር ለእሱ እንደሚገባው በራስ መተማመን የተሞላበት አስተያየት የሰጠ ሲሆን፣ ራሱን እና ፈረንሳያዊውን አጥቂ ኪሊያን ምባፔን አሁን ላይ በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ያሉ ሁለት ምርጥ ተጫዋቾች እንደሆኑ ተናግሯል።
የ19 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች በውድድር ዘመኑ በባርሴሎና እና በስፔን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አስደናቂ የስኬት ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን፣ በተለይም ስፔን የዓለም ዋንጫን እንድታነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በክለብ ደረጃም ከባርሴሎና ጋር በርካታ ዋንጫዎችን በማሳካት እና ድንቅ የግል ብቃት በማሳየት፣ በሁሉም ውድድሮች በ45 ጨዋታዎች ተሰልፎ 24 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን 17 ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
በላሊጋው በ28 ጨዋታዎች ተሰልፎ 16 ግቦችን በማስቆጠር በከፍተኛ ግብ አግቢነት 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ 11 ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ደግሞ የሊጉ ከፍተኛ ኳስ አመቻች ሆኖ አጠናቋል።
በያዝነው የ2026/27 አዲስ ውድድር ዘመንም በ4 ጨዋታዎች 4 ግቦችን በማስቆጠር አስደናቂ ብቃቱን እንደቀጠለ ይገኛል።
ከባርሴሎና ጋር የላሊጋ ሻምፒዮንነትን የተቀናጀ ሲሆን፣ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ደግሞ የ2026 የዓለም ዋንጫን በማንሳት የታሪክ አካል ሆኗል።
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ያስመዘገባቸው እነዚህ አስደናቂ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የስታቲስቲክስ የበላይነቶች ለዓለማችን ከፍተኛ የግል ክብር (Ballon d'Or) ቀዳሚ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጉት የሚታመን ሲሆን፣ ተጫዋቹ ራሱም ይህ የግል ክብር እንደሚገባው ተናግሯል።
የዘንድሮው የባሎንዶር አሸናፊ ማን እንደሆነ በቀጣዩ ወር የሚታወቅ ይሆናል።

25 days ago
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች
🏴ኮትላንድ
8:00 ሬንጀርስ ከ ሴልቲክ
ኢትዮጵያ
10:00 ሲዳማ ቡና ከ ኤግሎን
እስፓንያ
11:15 ሌቫንቴ ከ ባርሴሎና
4:00 ሪያል ሶሴዳድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
🏴እንግሊዝ
12:30 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
ጀርመን
12:30 ኤልቨርስበርግ ከ ባየርን ሙኒክ
ጣሊያን
1:00 ናፖሊ ከ ቦሎኛ
3:45 ሳሱኦሎ ከ ጁቬንቱስ
ፈረንሳይ
3:45 ብሬስት ከ ፒኤስጂ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
🏴ኮትላንድ
8:00 ሬንጀርስ ከ ሴልቲክ
10:00 ሲዳማ ቡና ከ ኤግሎን
11:15 ሌቫንቴ ከ ባርሴሎና
4:00 ሪያል ሶሴዳድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
🏴እንግሊዝ
12:30 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
12:30 ኤልቨርስበርግ ከ ባየርን ሙኒክ
1:00 ናፖሊ ከ ቦሎኛ
3:45 ሳሱኦሎ ከ ጁቬንቱስ
3:45 ብሬስት ከ ፒኤስጂ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
28 days ago
ከተስፋ ወደ ክብር፤ አርቴታ ያልጨረሰው ጉዞ
✍️ በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | የሰሜን ለንደን ቀይ ለባሾቹ አርሰናል በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከታላላቅና ስኬታማ ክለቦች ተርታ ቢመደቡም፣ በአውሮፓ ትልቁ መድረክ ያላቸው ሕልም እስካሁን እውን አልሆነም።
“ባለትልቅ ጆሮው” በሚል ቅጽል የሚጠራውን የUEFA ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማንሳት ሕልማቸው በ2006 በፍራንክ ራይካርድ ባርሴሎና ፊት ተገትቶ ቀርቷል። በቅርቡም በፓሪስ ሴን-ዠርመን ፊት የደረሰባቸው ሽንፈት ያንን የቆየ ቁጭት ዳግም ቀስቅሶታል።
ከክለቡ ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ስንብት በኋላ የውጤት መንገዱን ያጣውን አርሰናል የተረከበው የፔፕ ጋርዲዮላ ደቀ መዝሙር ሚኬል አርቴታ፣ መድፈኞቹን በትዕግሥት እና በተከታታይ ሥራ ወደ ከፍታቸው መልሷል።
አርቴታ የረጅም ዓመታትን የዋንጫ ጥማት በማስታገስ ክለቡን እንደገና ከእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች ጋር በአንድ ደረጃ አስቀምጧል። አሁን ግን የቀረው አንድ ትልቅ ፈተና ብቻ ነው—የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ኢሚሬትስ ማምጣት።
በአለት የጠነከረ የተከላካይ ክፍል፣ በአውሮፓ ምርጥ ከሚባሉ የአማካይ ስብስቦች አንዱ እና በዝውውር መስኮቱ የተጨመሩ አዳዲስ ኃይሎችን ይዘው፣ መድፈኞቹ ለታላቅ የአውሮፓ ዘመቻ ዝግጁ ናቸው።
ያለፈው የቁጭት ስሜት ገና አልበረደም፤ የዘንድሮው ጉዞ ግን የታሪክ ጉዞ ሊሆን ይችላል?
ከቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊነት እጩዎች ቀዳሚዎቹ መካከል የሚጠቀሱት መድፈኞቹ፣ የአውሮፓ ዘመቻቸውን ከኔፕልስ ይጀምራሉ።
ጥያቄው አንድ ነው...
በመጨረሻ ባለትልቅ ጆሮውን ዋንጫ ወደ ኢሚሬትስ ያመጣሉ?

30 days ago
የ2026 የባሎንዶር እጩዎች ይፋ ሆኑ
#ethiopia | የዓለማችን ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋቾች የሚሸለምበትና በጉጉት የሚጠበቀው የ2026 የባሎንዶር (Ballon d’Or) ሽልማት ፉክክር በይፋ መጀመሩን ተከተሎ ለዘንድሮው የክብር ሽልማት የታጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በታዋቂው የፈረንሳይ እግር ኳስ መጽሔት የሚዘጋጀውና የዓለማችንን ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች የሚለየው ይህ ታላቅ መድረክ፣ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በየክላቦቻቸው እና በብሔራዊ ቡድኖቻቸው ድንቅ ብቃት ያሳዩ ታዋቂ ኮከቦችንና ተስፋ ሰጪ ተጫዋቾችን በአንድ ላይ አሳታፊ አድርጎ አቅርቧል።
ለ2026 የወንዶች ባሎንዶር ክብር በይፋ የታጩት 30 ተጫዋቾች እነሆ ፦
ጁድ ቤሊንግሃም (ሪያል ማድሪድ)
ፓው ኩባርሲ (ባርሴሎና)
ማርክ ኩኩሬያ (ቼልሲ / ሪያል ማድሪድ)
ኡስማን ዴምቤሌ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሉዊስ ዲያዝ (ባየርን ሙኒክ)
ብሩኖ ፈርናንዴዝ (ማንቸስተር ዩናይትድ)
ገብርኤል (አርሰናል)
ኤርሊንግ ሀላንድ (ማንቸስተር ሲቲ)
አሽራፍ ሀኪሚ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሃሪ ኬን (ባየርን ሙኒክ)
ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ላሚን ያማል (ባርሴሎና)
ሳዲዮ ማኔ (አል ናስር)
ማርኪንዮስ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ላውታሮ ማርቲኔዝ (ኢንተር ሚላን)
ኪሊያን ምባፔ (ሪያል ማድሪድ)
ኑኖ ሜንዴዝ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ሊዮኔል ሜሲ (ኢንተር ማያሚ)
ዦአኦ ኔቨስ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ማይክል ኦሊሴ (ባየርን ሙኒክ)
ዊሊያም ፓቾ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ጁሊያን ኪኖኔዝ (አል ካድሲያ)
ዲክላን ራይስ (አርሰናል)
ሮድሪ (ማንቸስተር ሲቲ / ባርሴሎና)
ፋቢያን ሩይዝ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ዊሊያም ሳሊባ (አርሰናል)
ፌራን ቶረስ (ባርሴሎና / ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
ዳዮት ኡፓሜካኖ (ባየርን ሙኒክ)
ቪኒሲየስ ጁኒየር (ሪያል ማድሪድ)
ቪቲንሃ (ፓሪስ ሴንት ዠርሜን)
የትኛው ተጫዋች ሽልማቱ ይገባዋል ይላሉ?

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ክሪስቲያኖ ሮናልዶና ኒዮኔል ሜሲ በአንድ ቡድን ተሰልፈው ሊጋጠሙ ነው፡፡ ይህ ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች ህልም ሊመስል ይችላል፡፡ ሮናልዶና ሜሲ በስፔን ላሊጋ በባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ተሰልፈው ችሎታቸውን አሳይተዋል፡፡ አንዳቸው ከአንዳቸው ለመብለጥ በሚያደርጉት ጥረትም በስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቁ የሚባለው ፉክክር ውስጥ አልፈዋል፡፡ ሜሲ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በ39 አመቱ ራሱን ከአለም አቀፍ ውድደር አግልሏል፡፡
ሮናልዶም በሚቀጥለው አመት 42 አመት ስለሚሞላው ጫማውን እንደሚሰቅል ይጠበቃል፡፡ እነዚህን ሁለት ኮከቦች በአንድ ቡድን ውስጥ ተሰልፈው ሲጫወቱ ማየት ጊዜው ያለፈበት ይመስላል፡፡ ነገር ግን የቀድሞ የቡድን አጋሮቻቸው ይህ እድል የሚፈጠርበትን አጋጣሚ ፈጥረውላቸዋል፡፡ የአርጀንቲናው ታይሲ ስፖርት እንደዘገበው በመጪው ታህሳስ ወር ካርሎስ ቴቬዝ በታዋቂው ቦካ ጁኒየርስ ስታዲየም የኳስ ጨዋታ ስንብቱን በተመለከተ የኳስ ግጥሚያ ማድረግ አቅዷል፡፡ ለዚህ ግጥሚያ የቦካ ጁኒየርስ ፕሬዝደንት ሁዋን ሮማን ሪኬልሚ ስታዲየሙን እንደፈቀዱለት ዘገባው አስታውቋል፡፡
ምንም እንኳ ጨዋታው የሚካሄድበት እለት እስካሁን ያልተወሰነ ቢሆንም ከዲሴምበር 12 እስከ 20 ባሉት ቀናት እንደሚሆን ግን ተገልጿል፡፡ የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድና የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን አጥቂው ካርሎስ ቴቬዥ ከቦካ ጁኒየር ሀላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ምክክር እንዳደረገ የጠቀሰው ዘገባው ለጨዋታው ወደ60 ለሚሆኑ ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በዚህ የስንብት ጨዋታ ላይ እንዲገኙ ከሚፈልጋቸውና ጥሪ ካቀረበላቸው መካከል ደግሞ ሮናልዶና ሜሲ በግንባር ቀደምነት ተጠቅሰዋል፡፡
ቴቬዥ ከእነዚህ ሁለት ኮከቦች ጋር የቡድን አጋር ሆኖ የተጫወተ ነው፡፡ ከሜሲ ጋር በአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ውስጥ አብሮ የተሰለፈ ሲሆን ከሮናልዶ ጋር ደግሞ በማንችስተር ዩናይትድ በርካታ የውድድር ወቅቶችን አሳልፏል፡፡ እንደዘገባው ለሁለቱ ተጨዋቾች ያቀረበላቸው ጥሪ በአንድ ቡድን ውስጥ ተሰልፈው የወዳጅነት ግጥሚያውን እንዲያደርጉ ነው፡፡ ተጨዋቾቹ ጥሪውን ከተቀበሉ በእግርኳስ አለም ህልም የሚመስለው ክስተት እውን ይሆናል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ሴፕቴምበር 1 የዝውውር መስኮቱ በተዘጋበት የመጨረሻ ሰዓት፣ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በአንድ ጥያቄ ላይ አተኩረው ነበር፦ "የግራ መስመር ተከላካይስ?" የ2025-26 የውድድር ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ በማይክል ካሪክ ስብስብ ውስጥ በጉልህ የሚታየውን ይህንን ክፍተት ክለቡ እንደሚደፍነው በስፋት ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን መስኮቱ ሲዘጋ ዩናይትዶች ይህን ቦታ በተጫዋች ሳይሸፍኑ በመቅረታቸው አጓጊ እና አደገኛ ቁማር ውስጥ ገብተዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሉክ ሾው ብቸኛው አንጋፋ የግራ መስመር ተከላካይ ነው። ምንም እንኳን ባለፈው የውድድር ዘመን ሁሉንም 38 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢጀምርም፣ የ31 ዓመቱ ተጫዋች ከ60 በላይ ጨዋታዎችን በሚያስተናግደው አዲሱ የውድድር ዘመን ሙሉ ጤንነቱን ጠብቆ ይዘልቃል ተብሎ አይታሰብም። ታይረል ማላሲያ ኮንትራቱ አልቆ ክለቡን መልቀቁ ደግሞ ክፍተቱን ይበልጥ አግዝፎታል።
ዩናይትድ የተለያዩ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ቢሞክርም ሳይሳካ ቀርቷል። ከእነዚህም መካከል ዩናይትዶች አጥብቀው የፈለጉት የ22 ዓመቱ የኒውካስሉ ሉዊስ ሆል ይገኝበታል፤ ነገር ግን ኒውካስል የጠየቀው የተጋነነ ዋጋ ዝውውሩን አጨናግፎታል። በሌላ በኩል ክለቡ ያለውን ውስን በጀት ለግራ ተከላካይ ከማውጣት ይልቅ፣ የ70 ሚሊዮን ፓውንድ ትኩረቱን የአማካይ ስፍራውን በማጠናከር ላይ በማድረግ የብራይተኑን ካርሎስ ባሌባን አስፈርሟል። የባርሴሎናውን አሌሃንድሮ ባልዴ በውሰት ፈልጎት የነበረ ቢሆንም ባርሳ በሽያጭ ብቻ በመስማማቱ እንቅፋት ሲሆንበት፣ በመጨረሻው ሰዓት ከተቀናቃኛቸው ማንቸስተር ሲቲ ሪያን አያት-ኑሪን በውሰት ለማምጣት የተደረገው ሙከራም በሲቲ ውድቅ ተደርጓል።
የማይክል ካሪክ 'ፕላን ቢ' - "ከዚህ ቀደም እንደ አሌክስ ቴሌስ ወይም ሰርጂዮ ሬጉይሎን ያሉ ስሜታዊ እና የድንጋጤ ዝውውሮችን ከማድረግ፣ ጥራታቸው ባልተረጋገጠ ተጫዋቾች ላይ ገንዘብ አለማባከን ብልህነት ነው።"
አሁን ዩናይትድ ባለው ስብስብ ላይ ብቻ ተንጠልጥሏል። ሉክ ሾው ቀዳሚ ምርጫ ሲሆን፣ ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዚሁ ቦታ የሚጫወተው ኑሳይር ማዝራዊ ተጠባባቂ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ቦታውን መሸፈን የሚችለው ዲዮጎ ዳሎት እና ገና ሚናው በግልጽ ያልታወቀው የ19 ዓመቱ አካዳሚ ምሩቅ ሃሪ አማስ አሉ።
በተለይም የተከላካይ ክፍሉን ለማመጣጠን የ20 ዓመቱን ፈጣን የመሀል ተከላካይ ሌኒ ዮሮ በቀኝ መስመር ላይ ማሰለፍ እንደ አማራጭ ተይዟል። ዮሮ ከኢፕስዊች ጋር በነበረው ጨዋታ በዚህ ቦታ ላይ ያሳየው ብቃት፣ ልክ ጆስኮ ግቫርዲዮል በማንቸስተር ሲቲ እንዳደረገው የተሳካ የቦታ ሽግግር ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ሰጥቷል።
ይህ ስሜታዊነትን ያስወገደ የካሪክ ስሌት በአብዛኛው ትክክለኛ ውሳኔ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን የውሳኔውን ትክክለኛነት ፈትኖ የሚወስነው የሜዳ ላይ ውጤት ብቻ ነው።
ይህ በማይክል ካሪክ የተወሰደው የዝውውር ስጋት በማንቸስተር ዩናይትድ የዋንጫ ጉዞ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ የሚያመጣ ይመስልዎታል?

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ረጅም ጊዜ የወሰደው የኤንዞ ፈርናንዴዝ የዝውውር ዶሴ በመጨረሻም እልባት አግኝቷል። ማንቸስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን አማካይ ከቼልሲ ለማስፈረም በ125 ሚሊዮን ፓውንድ (169 ሚሊዮን ዶላር) ከስምምነት ላይ ደርሷል። ይህ አስገራሚ የገንዘብ መጠን፣ ባለፈው ክረምት ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢሳክን ከኒውካስል ዩናይትድ ሲያስፈርም ያስመዘገበውን የብሪታንያ የዝውውር ሪከርድ የሚስተካከል ነው። ቼልሲም ተጫዋቹ የህክምና ምርመራውን እንዲያደርግ ይፋዊ ፈቃድ ሰጥቶታል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ፣ ሲቲ እስከ ነሐሴ 14 ድረስ 120 ሚሊዮን ፓውንድ ካላቀረበ ተጫዋቹ በክለቡ እንደሚቆይ ገልጾ ነበር። ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ ሲቲ ምንም ዓይነት የዝውውር ጥያቄ ባለማቅረቡ ኤንዞ በስታምፎርድ ብሪጅ እንደሚቀጥል ታምኖ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ ሌላ መልክ የያዘው፣ ማንቸስተር ሲቲ ኮዲ ጋክፖን ለማስፈረም ለሊቨርፑል ያቀረበው የ80 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ነው። በዚህ የተነሳ የሲቲ አመራሮች ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ኤንዞ በማዞር ይህንን ግዙፍ ስምምነት በፍጥነት አጠናቀዋል።
ኤንዞ በቼልሲ ቆይታው ማገባደጃ ላይ ከደጋፊዎች ጋር የነበረው ግንኙነት ክፉኛ ሻክሮ ነበር። ከሪያል ሶሴዳድ ጋር በተደረገው የአቋም መፈተሻ እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ከፉልሀም ጋር ሲጫወቱ በደጋፊዎች ፊሽካ ሲንጓጠጥ ታይቷል። ጨዋታው ሲጠናቀቅም ከቡድን አጋሮቹ ጋር ደጋፊውን ከማመስገን ይልቅ በቀጥታ ወደ መልበሻ ክፍል ማምራቱ ሁኔታውን አባብሶታል። ይህንን ተከትሎም በካራባዎ ካፕ ከሉተን ታውን፣ እንዲሁም በሊጉ ከብራይተን ጋር በተደረጉት የቅርብ ጊዜ ጨዋታዎች ላይ በስብስቡ ውስጥ አልተካተተም።
ይህ ዝውውር ለሁለቱም ክለቦች የራሱ የሆነ ትርጉም አለው። በቼልሲ በኩል አዲሱ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እየገነባው ላለው አዲስ ቡድን ኤንዞን መሸጡ ትልቅ እፎይታ ነው። አሎንሶ በሚተገብረው የ'ሁለት ተከላካይ አማካዮች' ጥምረት አጨዋወት ውስጥ፣ ኤንዞ ከሞይሰስ ካይሴዶ ጋር ሲጣመር ኳስ በማይኖርበት ጊዜ የሚታይበት የመከላከል ድክመት ለአሰልጣኙ ትልቅ ፈተና ነበር። በሌላ በኩል ቼልሲ በተጫዋቹ የሜዳ ላይ ቋንቋ እና ለቀድሞው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በነበረው ጥብቅ ታማኝነት ደስተኛ አልነበረም። ክለቡ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም ክፍተቱን ቀድሞ የደፈነ ሲሆን፣ የኤንዞ መሸጥ አሎንሶ በቡድኑ ውስጥ ለማምጣት ላሰበው የባህል ለውጥ በእጅጉ ይረዳዋል።
በማንቸስተር ሲቲ በኩል ደግሞ፣ ሮድሪ ወደ ባርሴሎና ማምራቱን እና ቲጃኒ ሬንደርስ ወደ ሳዑዲው አል ቃድሲያህ መጓዙን ተከትሎ የአማካይ ክፍሉን ማጠናከር ግድ ብሎታል። አዲሱ የሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በቼልሲ ቤት ለ18 ወራት አብሮት የሰራውን እና 15 ግቦችን ያስቆጠረለትን ኤንዞ ፈርናንዴዝን፣ አሁን በእንግሊዝ ሻምፒዮኖቹ ቤት ዳግም አግኝቶታል። ሲቲ ከዚህ ቀደም ኤሊዮት አንደርሰንን እና አዩብ ቡዋዲን በከፍተኛ ዋጋ በማስፈረም አዲሱን የአማካይ ክፍሉን በአስፈሪ ሁኔታ እያደራጀ ይገኛል። ማሬስካ ወደ ተጋጣሚ ሳጥን ሰብሮ በመግባት የሚታወቀውን የኤንዞን ብቃት በሲቲ ቤት ዳግም እንደሚያጎላው ይጠበቃል።

በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ማልያ የሚናፈቀው ኮከብ - ሜሲ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን የዓመታት የዓለም ዋንጫ ጥያቄ የመለሰ ኮከብ ነው ሊዮኔል ሜሲ።
አርጀንቲና በፈረንጆቹ 1986 የዓለም ዋንጫን ካሳካች በኋላ በድጋሚ ከዋንጫው ጋር ለመገናኘት የሜሲን ተዓምራዊ እግሮች መጠበቅ ግድ ብሏት ነበር።
አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ አስደናቂ ብቃት ታግዛ በ2022 በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከ36 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ከዋንጫው ጋር በድጋሚ መገናኘቷ ይታወሳል።
እስከ ኳታሩ የዓለም ዋንጫ ድረስ አርጀንቲናውያን ሜሲ የባርሴሎና እንጂ የእኛ አይደለም እስከማለት ደርሰውም ነበር።
የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ግን የመላው አርጀንቲናውያንን ልብ ወደ ሜሲ የመለሰ ነበር።
ምክንያቱም ምስጋና ለሜሲ ይግባውና የዓመታት የዓለም ዋንጫ ጥያቄያቸውን ከቡድን አጋሮቹ ጋር መመለስ ችሏል።
በወቅቱ አርጀንቲና ዋንጫውን ከዓመታት በኋላ እንድታሳካ ትልቁን ሚና የተወጣው ሜሲ ነበር።
ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ድል በኋላ ግን መላው አርጀንቲናውያን ሜሲ ውዱ ልጃችን ብለው ለመዘመር ተገድደዋል።
ሜሲ ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን አገልግሏል።
የስምንት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በ39 ዓመቱ ራሱን ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ማግለሉን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ሜሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ ውሳኔው ቢጎዳኝም ትክክለኛው ጊዜ ግን አሁን ነው ብሏል።
የስንብት መልዕክቱን ከ2026 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ሁለት ቀናት በኋላ መጻፉን የገለጸው ሜሲ፤ ከአባቱ ሕልፈት በኋላ በውሳኔው ይበልጥ እርግጠኛ መሆኑን አብራርቷል።
ወላጅ አባቱ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ባለፉት ዓመታት አብረውት ለነበሩት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ምስጋናውን ያቀረበው ኮከቡ በሜዳ ውስጥ ሆኜ ድምጻችሁን መስማት ይናፍቀኛል ሲልም ገልጿል።
ሁሉንም ነገር ባሸነፍንባቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ሳይሆን፤ ከዚያ በፊትም ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ሁሉንም ነገር ሰጥቻለሁ ነው ያለው።
በእግር ኳስ አርጀንቲናዊ በመሆናችሁ እንድትኮሩ ለማድረግ ብዙ ለፍቻለሁ ብሏል።
ሜሲ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የዓለም ዋንጫ፣ ሁለት የኮፓ አሜሪካ እና አንድ የፊናሊሲማ ዋንጫን አሳክቷል።
ሜሲ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን 207 ጨዋታዎችን አድርጎ 125 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ 68 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
በዚህም ለአርጀንቲና በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ፣ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረ እና በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለ ተጫዋች በመሆን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ተሰናብቷል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ

ባርሴሎና ጋብሬል ጄሱስን ለማስፈረም ተስማማ
የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ለማስፈረም ተስማምቷል።
ባርሴሎና ለተጨዋቹ ዝውውር 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ በአርሰናል በኩል ጥያቄው ተቀባይነት ማግኘቱን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
ብራዚላዊው ተጫዋች የሕክምና ምርመራውን ለማድረግ እና በይፋ ውሉን ለመፈረም በነገው ዕለት ወደ ስፔን የሚያመራ ይሆናል።

የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጨዋታ ድልድል ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የጨዋታ ድልድል በዛሬው ዕለት በሞናኮ ይፋ ሆኗል። እንደ መርሃ ግብሩ ገለጻ ውድድሩ በጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ የቀደመውን የምድብ ድልድል አሰራር በመቀየር 36 ክለቦች በ 4 ቋቶች ተከፋፍለው የሚወዳደሩበትን የሊግ ደረጃ አዲስ ፎርማት መተግበሩ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በዘመነኛው ውድድር የተካተቱት 36 ክለቦች በእያንዳንዱ ቋት 9 ቡድኖች እንዲይዙ ተደርገው ተከፋፍለዋል።
በቋት አንድ ውስጥ የወቅቱ ሻምፒዮን ፒኤስጂን ጨምሮ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተካተዋል።
በቋት ሁለት ደግሞ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ሮማ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አስቶንቪላ፣ ፖርቶ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ክለብ ብሩዥ፣ ሪያል ቤቲስ እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ይገኛሉ።
በቋት ሶስት ላይፕዚግ፣ ቪያሪያል፣ ናፖሊ፣ ሊል፣ ፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ቦዶ ግሊምት፣ ፊነርባቼ፣ ሻክታር ዶኔስክ እና ጋላታሳራይ ተደልድለዋል።
በቋት አራት ስቱትጋርት፣ ሌንስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ፣ ኤኢኬ አቴንስ፣ ላስክ፣ ኮሞ፣ ቫይኪንግ እና ሳባህ ተመድበዋል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት አንድ ክለብ ከራሱ ቋት ከተካተቱ ሁለት ቡድኖች እንዲሁም ከቀሪዎቹ ሶስት ቋቶች ከእያንዳንዳቸው ከሁለት ክለቦች ጋር የሚጫወት በመሆኑ በጠቅላላው 8 ጨዋታዎችን ያደርጋል።
በሊግ ደረጃ ከሚወዳደሩት 36 ክለቦች መካከል በ 8 ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ የሚያስመዘግቡ የመጀመሪያዎቹ 8 ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ያልፋሉ።
ከ 9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በሁለት ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ተወዳድረው ቀሪዎቹን 8 የጥሎ ማለፍ ቦታዎች ይይዛሉ። ከጥሎ ማለፉ ዙር ጀምሮ ያለው የጨዋታ ፎርማት ከዚህ ቀደም ይተገበር ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው።
በመጀመሪያው ሳምንት ከሚጠበቁ Select Item ጨዋታዎች መካከል ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከባርሴሎና፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና ከፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጓቸው ተጠቃሽ ናቸው።
የጣሊያኑ ኮሞ እና የአዘርባጃኑ ሳባህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሚሳተፉ ይሆናል።
#championsleague #ucl #uefa #football #sports #soccer #europe #realmadrid #barcelona #manchesterunited #arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አትሌቲኮ ማድሪድ የሁሊያን አልቫሬዝን ወደ ባርሴሎና መዛወር በይፋ ውድቅ አደረገ
አትሌቲኮ ማድሪድ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ሁሊያን አልቫሬዝን ለኤፍሲ ባርሴሎና የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለውና ከካታሎኑ ክለብ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር እንዳላደረገ በይፋዊ መግለጫው አስታወቀ።
የክለቡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባወጣው መግለጫ፣ ክለቡ አልቫሬዝን ወደ ባርሴሎና ላለመሸጥ የወሰነውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፈው ገልጿል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በተጫዋቾች ዝውውር ወቅት ለድርድር ክፍት ቢሆንም፣ ሂደቱ ሙያዊ ክብርን እና የስነ-ምግባር ደንቦችን የተከተለ መሆን እንዳለበት አፅንዖት ሰጥቷል።
ኤፍሲ ባርሴሎና ግን እነዚህን መስፈርቶች ያላሟላ በመሆኑ ከክለቡ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ያልተደረገ ሲሆን ወደፊትም ቢሆን የዝውውር ውይይት እንደማይኖር በግልጽ አስታውቋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ አክሎም ሁሊያን አልቫሬዝ የክለቡን ውሳኔ እንደሚረዳና ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ስኬት ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል።

Comments