26 days ago
በክሪስቲያኖ ሮናልዶ የስልክ ጥሪ በኦልድትራፎርድ የደመቁት መንትዮች - ራፋኤል እና ፋቢዮ ዳ ሲልቫ
********************************
ቁመናቸው፣ መልካቸው እና የአጨዋወት ዘይቤያቸው እጅግ በመመሳሰሉ ምክንያት፣ ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እንኳን ለመለየት እንደሚቸገሩ የሚነገርላቸው ራፋኤል እና ፋቢዮ ዳ ሲልቫ፤ በኦልድ ትራፎርድ በነበራቸው ቆይታ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎችን ልብ የገዙ ተጫዋቾች ናቸው።
ብራዚላውያኑ የሪዮ ዲ ጄኔሮ ተወላጅ መንትዮች ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ ቡድን፣ በአንድ ክፍልና በአንድ ህልም ያደጉት መንትዮቹ፤ በ15 ዓመታቸው እ.አ.አ በ2005 በሆንግ ኮንግ በተደረገ የወጣቶች ውድድር ላይ በዩናይትድ የስካውቲንግ ቡድን አይን ውስጥ ገቡ።
በወቅቱ አርሰናልን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ተጫዋቾቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ቢገቡም፣ የውሳኔያቸውን አቅጣጫ የቀየረው ያልተጠበቀ የስልክ ጥሪ ነበር።
በወቅቱ የዩናይትድ ኮከብ የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጥታ ደውሎ፣ "ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ኑ፤ በፍጹም አትቆጩም!" በማለት አበረታታቸው። ይህ ጥሪ የመንትዮቹን ውሳኔ አስቀይሮ፣ በጥር 2008 በይፋ የ"ቲያትር ኦፍ ድሪምስ" አባል እንዲሆኑ አደረጋቸው።
በወቅቱ የአውሮፓ እግር ኳስን በበላይነት ለሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ አዲስ ጉልበትና ተስፋ ይዘው የመጡት ታዳጊዎች፤ በአሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ዘንድ "የወደፊቶቹ ኮከቦች" የሚል ታላቅ ሙገሳን አገኙ።
ሆኖም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሁለቱን መለየት እጅግ አስቸጋሪ ነበር። ተጫዋቾች፣ የክለቡ ሰራተኞች እና ሰር አሌክስ ራሳቸው ጭምር ብዙ ጊዜ ያሳስቷቸው ነበር።
በአንድ ወቅት በዩናይትድ ፖድካስት ላይ እንደተናገሩት፤ በአንድ ጨዋታ ላይ ራፋኤል ስህተት ይሰራል። በእረፍት ሰዓት ፈርጉሰን በቁጣ ወደ መልበሻ ክፍል በመግባት ፋቢዮን ራፋኤል መስሏቸው አጥብቀው ገሰጹት። ሪዮ ፈርዲናንድ እና ማይክል ካሪክ ግን "ያ ራፋኤል አይደለም፣ ፋቢዮ ነው" ብለው ሲነግሯቸው፤ ፈርጉሰን "ሁለቱም አንድ ናቸው!" ብለው ቁጣቸውን መቀጠላቸው እስከዛሬ በዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ በፈገግታ ይታወሳል።
አንዳንድ ጊዜ ፋቢዮ ጥፋት አጥፍቶ ራፋኤል ካርድ የተቀበለበት አጋጣሚም ነበር። በልምምድ ሜዳም አሰልጣኞችን ለማደናገር ሆን ብለው ማሊያቸውንና ጫማቸውን እንደሚቀያይሩ ከዓመታት በኋላ በሳቅ ታጅበው የገለጡት የኦልድትራፎርድ ምስጢራቸው ነው።
መንትዮቹ በዩናይትድ ቆይታቸው በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበዋል። በተለይም ራፋኤል በቀኝ ተከላካይ መስመር የጋሪ ኔቪልን ቦታ በብቃት መተካት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነው። 170 ጨዋታዎችን አድርጎ 5 ግቦችን አስቆጥሯል፤ 3 የፕሪሚየር ሊግ፣ 1 የሊግ ካፕ እና 1 የክለቦች ዓለም ዋንጫ አንስቷል።
በሌላ በኩል ፋቢዮ በግራ ተከላካይ መስመር ላይ ከፓትሪስ ኤቭራ ጋር ከባድ ፉክክር ነበረበት። ለዩናይትድ 56 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 3 ግቦችን አስቆጥሯል፤ 1 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫንም አሽንፏል። 2011 ላይ ዩናይትድ በባርሴሎና በተሸነፈበት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ላይ በቋሚነት የመጀመር ዕድል አግኝቷል።
የሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከማንቸስተር መልቀቅና የሉዊስ ቫን ሀል ወደ አሰልጣኝነት መምጣት ለመንትዮቹ የኦልድትራፎርድ ቆይታ ማብቃት ምክንያት ሆነ።
ቫን ሀል ለብራዚላውያኑ መንትዮች ዕድል የመስጠት ፍላጎት እንዳልነበራቸው ራፋኤል ከዓመታት በኋላ ለሚዲያ በግልጽ ተናግሯል።
በዚህም ምክንያት ራፋኤል በ2015 ወደ ፈረንሳዩ ሊዮን አቀና። በዚያም ለ5 ዓመታት ስኬታማ ቆይታ ካደረገ በኋላ፣ ወደ ቱርኩ ባሻክሼሂር አምርቶ በሻምፒዮንስ ሊግ የቀድሞ ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድን በመግጠም ጭምር አሸንፏል።
ፋቢዮ ደግሞ ከዩናይትድ በኋላ በካርዲፍ ሲቲ፣ ሚድልስብሮ እና በፈረንሳዩ ናንትስ ክለቦች ተጫውቷል።
ትላንት 36ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት መንትዮቹ፤ በአሁኑ ሰዓት በትውልድ ሀገራቸው ብራዚል ይገኛሉ። ራፋኤል ለቦታፎጎ፣ ፋቢዮ ደግሞ በግሬሚዮ በመጫወት ላይ ናቸው።
ዛሬም ቢሆን ማንቸስተር ዩናይትድ ያላቸው ፍቅር አልቀነሰም። በቅርቡ በ"ኢንሳይድ ካሪንግተን" ፖድካስት ላይ ተገኝተው ስለ ዩናይትድ የቆይታ ዘመናቸው፣ ስለ ፈርጉሰን እና ስለ ማይክል ካሪክ በኩራት ተናግረዋል። አሁንም የዩናይትድን ውጤቶች በቅርበት እንደሚከታተሉና ልባቸው ኦልድትራፎርድ እንደሚገኝ ይገልጻሉ።
ራፋኤል እና ፋቢዮ ዳ ሲልቫ በዩናይትድ ታሪክ ውስጥ እንደ ሮናልዶ ወይም ሩኒ በግንባር ቀደምትነት ላይጠቀሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ባሳዩት የማይበገር የብራዚላውያን ስሜት፣ ለክለቡ በሰጡት ታማኝነትና ሜዳ ላይ በሚያሳዩት ውብ ፈገግታ በደጋፊዎች ልብ ውስጥ ምንጊዜም የማይረሳ አሻራ ጥለው ያለፉ ድንቅ መንትዮች ናቸው።
በአዲስ የሺዋስ
#manchesterunited #theatreofdreams #cr7cristianoronaldo #fabiodasilva #rafaeldasilva #twinbrothers #football #sports

Comments