Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ስለመመለሱ የተናገረው ልብ የሚነካ ንግግር "ለማንቸስተር ዩናይትድ የመጨረሻ ጨዋታዬን ተጫውቼ አብቅቼ ይሆን? እያልኩ ራሴን ስጠይቅ ወራትን አሳልፌያለሁ። ይህንን ማሰብ ብቻ... በህይወቴ ከገጠሙኝ ትችቶች ሁሉ በላይ ልቤን ክፉኛ ያደማው ነበር።

"የሌሎች ክለቦችን ማልያ ለብሼ ሜዳ ላይ ወጥቻለሁ፤ ሆኖም አንዳቸውም እንደገዛ ቤቴ ሞቅታ አልሰጡኝም። ወደ ሌላ ክለብ መልበሻ ክፍል እርምጃዬን ባቀናሁ ቁጥር፣ የውስጤ አንዱ አካል አሁንም ድረስ በግድግዳው ላይ የዩናይትድን አርማ ለማየት ይመኝ ነበር።

"ለዚህም ነው የባርሴሎናው ምዕራፍ እንደተጠናቀቀ ለወኪሌ እንዲህ ያልኩት 'ወደ ዩናይትድ መመለስ የማይቻል ከሆነ፣ እዚሁ ውጪ ሀገር እንድቆይ አድርገኝ። ከዩናይትድ ውጪ ሌላ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ስም እንዳታነሳልኝ!'

"ካሪክ መቼም ቢሆን ከህሊናዬ የማይጠፋ አንድ ቃል ነገረኝ። 'ማርከስ... የምትመለሰው ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አመለካከት ስህተት መሆኑን ለማረጋገጥ አይሁን፤ ይልቁንም የምትመለሰው ትክክለኛ ማንነትህ ማን እንደሆነ ለራስህ ለማስታወስ ይሁን' አለኝ።

"ይህ ንግግሩ የልቤን በር ነው ያንኳኳው። በዙሪያዬ ያሉትን ጩኸቶች እና ትችቶች ዝም ለማሰኘት ስታገል፣ በነጻነት ኳስ መጫወት ምን አይነት ስሜት እንዳለው ጭራሹኑ ረስቼው ነበር። ያ ቃል ለእኔ ከበቂ በላይ ነበር። ደግሞም፣ አንዳንድ ታሪኮች ከጀመሩበት ውጪ ሌላ ስፍራ ላይ ሊያልቁ አልተጻፈላቸውም።"

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.