አርሰናልን ወደ ቀደመው ከፍታ የመለሰው ሚኬል አርቴታ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ክቧ ኳስ በክቡ ምድር ከግለሰብ እስከ ታላላቅ ሀገራት መሪዎች ድረስ ጮቤ እያስረገጠች ነው።
በአርሰናል ጥላ ስር የነበሩ ደጋፊዎች ሁሉ ፈንጠዝያቸው እያደር አዲስ ያደረገው ደግሞ ''ትዕግስት መራራ ናት፤ ፍሬዋ ጣፋጭ'' የሚለውን አባባል ለ22 ዓመታት ስለተጋፈጡት መሆኑ ልብ ይለዋል።
የዚህ ሁሉ ዳንኪራና ድግስ፣ የጽናት እና የታማኝነት ገጾች ፀሐፊ ስፔናዊው ታክቲሽያን ሚካኤል አርቴታ ነው።
የ22 ዓመታት ውርስ ትርክት፣ የ6 ዓመታት እንደ እሳት የሚፋጀውን የአሰልጣኝነት መንበር ሽበት ጣል ጣል ሳይልበት፣ ፀጉሩም በብስጭት ሳይሸሸው፣ የተወረወሩበትን ጠጠሮች ላለፉት ቀናት ያየነውን የሀሴት ምትሃት ቀርጾበታል።
የአርሰናል እግር ኳስ ክለብን ወደ ቀደመ ክብሩ የመለሰ እና በስትራቴጂ የበሰለ ስብስብ መሃንዲስ በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ በግንባር ቀደምትነት እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል።
ሚካኤል አርቴታ የተወለደው በስፔን ባስክ ግዛት ሳን ሰባስቲያን ውስጥ ሲሆን÷ ይህ አካባቢ ጠንካራ ስራን፣ ትህትናን እና ጥልቅ ታማኝነትን በሚያስተምረው ባህሉ ይታወቃል። ይህ አስተዳደግ በአርቴታ ስብዕና ላይ ትልቅ አሻራ ጥሏል።
የእግር ኳስ ተንታኞች አርቴታን ዝርዝር ጉዳዮችን አጥባቂ በማለት ይገልጹታል። በስልጠና ሜዳ ላይ የተጫዋቾቹ የሰውነት አቀማመጥ፣ ኳስ ከመቀበላቸው በፊት ያላቸው እይታ እና የሚሮጡበት ሰኮንድ ሳይቀር በጥንቃቄ እንዲሰላ ይፈልጋል። ይህ ባህሪው በሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በግል ህይወቱም የሚንጸባረቅ ሲሆን÷ ንጽህናን፣ ሥነ ሥርዓትን እና የጊዜ አጠቃቀምን እጅግ አጥብቆ ይወዳል።
የማይታጠፍ ዲሲፕሊን እና የማይደፈሩ ህጎች አርቴታ አርሰናልን በተረከበ ማግስት ያስቀመጠው ትልቁ መርህ የባህል ለውጥ አምጥቶለታል። እሱ ዘንድ ለማንኛውም ተጫዋች ልዩ መብት አይሰጥም። ክለቡን፣ ደጋፊውን እና ባልደረባን ማክበር ቀዳሚው ግዴታ ነው። ይህንን ህግ የጣሱ እንደ ፒየር-ኤምሪክ ኦባምያንግ ያሉ ታላላቅ ኮከቦችን ከክለቡ እስከማሰናበት የደረሰበት ቆራጥ ርምጃ እሱ ለስኬት ያለው ታማኝነት ከግለሰቦች ከዋክብትነት በላይ መሆኑን አሳይቷል።
የአርቴታ የእግር ኳስ ቀለም ከታላላቅ መምህራን የተቀሰመ ለመሆኑ የኋላ ታሪኩ ነጋሪ ናቸው። እድገቱ ባርሴሎና ላ ማሲያ አካዳሚ፣ በሬንጀርስ፣ በፒኤስጂ እና በእንግሊዝ ኤቨርተን እና አርሰናል መጫወቱ ከጽንሰ ሐሳብ እስከ ተግባር እውቀቱን አሳድጎለታል።
በርካቶች እንደሚስማሙት ከእግር ኳስ ሊቁ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስር በማንቼስተር ሲቲ ረዳት ሆኖ ያሳለፋቸው ዓመታት የታክቲክ ብስለቱን ስል አድርጎታል።
አርቴታ ቡድኑ የጨዋታውን ፍሰት እንዲቆጣጠር ይፈልጋል። ተጫዋቾቹ ሜዳውን ሙሉ በሙሉ ተጠቅመው ተጋጣሚን እንዲያስጨንቁ፣ ኳስ ሲያጡ በሰኮንዶች ውስጥ መልሰው እንዲነጥቁ ያደርጋል። ይህ የጨዋታ ፍልስፍና አርሰናልን በአውሮፓ ውስጥ ለማጥቃት እጅግ አስቸጋሪ እና በሊጉ ጠንካራ የተከላካይ ግድግዳ ያለው ቡድን አድርጎታል።
በአውሮፓ አምስት ታላላቅ ሊጎች ውስጥ አርሰናል አነስተኛ ግብ ያስተናገደ እና ብዙ ጨዋታዎችን ያለ ግብ ያደረገው ግስጋሴ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ለሁለተኛ ጊዜ ለዋንጫ እስኪቀርብ መርቶታል።
እንግሊዛዊው የስካይ ስፖርት ተንታኝ ጋሪ ኔቪል "አርቴታ ወደ አርሰናል ሲመጣ ክለቡ ማንነቱን አጥቶ ነበር፤ እሱ ግን ታላቅ ስራ ሰርቷል፤ የተጫዋቾችን አስተሳሰብ ቀይሯል፤ አርቴታ ሜዳ ላይ የሚሰጣቸው መመሪያዎች እና ተጫዋቾችን የሚከላከልበት መንገድ እውነተኛ የአመራር ጥበብ ምን ማለት እንደሆነ ያሳያል" ብሏል።
የአርሰናል የምንጊዜውም ኮከብ ፈረንሳዊው ቲዬሪ ኦንሪ በበኩሉ÷ "ሚኬል አርቴታን ልዩ የሚያደርገው ለክለቡ ያለው ጥልቅ ፍቅር ነው፤ እሱ የተጫዋቾችን ስሜት መኮረጅ ይችላል፤ በክፍል ውስጥ ሲያወራ ተጫዋቾቹ ለእሱ ሊሞቱለት ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ የማሳመን ብቃት አለው፤ አርሰናልን መልሶ ትልቅ ቡድን አድርጎታል" ሲል ገልጿል።
የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እንደገለጹት÷ የአርቴታ ስኬት የመነጨው ከቤተሰባዊ መረጋጋቱ ነው። ከባለቤቱ ሎሬና በርናል (የቀድሞዋ ሚስ ስፔን) እና ከሦስት ልጆቹ ጋር ያለው ጠንካራ ትስስር፣ ከእግር ኳሱ ግፊት ውጭ ሰላማዊ ህይወት እንዲኖረው አድርጎታል። ይህ ሚዛናዊነት በሜዳ ላይ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን በረጋ መንፈስ እንዲያስተላልፍ ይረዳዋል።
ሚኬል አርቴታ ለስራው ያለው ፍቅር፣ የማይናወጠው ግለሰባዊ ማንነቱ እና ስልታዊ ብልሃቱ አርሰናልን ብቻ ሳይሆን ዘመናዊው እግር ኳስ በሚመራበት መንገድ ላይ ተጽእኖ እስከመፍጠር እየደረሰ ይገኛል። አርቴታ ገና ወጣት አሰልጣኝ ቢሆንም፣ ያሳየው ስኬት እና ያሳደረው ተፅዕኖ ግን በዋንጫ መታጀብ ዛሬ በለንደር ጀምሯል።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

3 months ago