ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አንድም የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ያልተካተተበት የስፔን ብሔራዊ ቡድን
#ethiopia | ስፔን ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ፣ 26 ተጫዋቾችን የያዘውን ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።
ባርሴሎና ፔድሪ፣ ጋቪ፣ ዳኒ ኦልሞ እና ፌራን ቶሬስን ጨምሮ ስምንት ተጫዋቾችን በማስመረጥ በስብስቡ ውስጥ ከፍተኛ የበላይነት ይዟል።
በተጨማሪም የባርሴሎናው የ18 ዓመቱ ተጫዋች ላሚን ያማል በስብስቡ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ወር በጭን ጡንቻ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ እርቆ መቆየቱ ይታወሳል።
ከአርሰናል ዴቪድ ራያ፣ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ሚኬል ሜሪኖ ስብስብ ውስጥ ተካተዋል።
ከሪያል ማድሪድ አንድም ተጫዋች ያልተካተተ ሲሆን እ.አ.አ ከ1950 በኋላ በስፔን የዓለም ዋንጫ ስብስብ አንድም የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ያልተካተተበት የስፔን ብሔራዊ ቡድን በመሆን አነጋጋሪ ሆኗል።
ዲን ሁይሰን እና ዳኒ ካርቫሃል ከስብስቡ በጉዳት ምክንያት ውጪ ሲሆኑ ፣ አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፎንቴ ምርጫው ሙሉ በሙሉ በወቅታዊ አቋም እና በጤንነት ላይ የተመሰረተ እንጂ ከክለብ ወገንተኝነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተናግረዋል።
በዓለም ዋንጫው በምድብ 8 የተደለደለችው የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ስፔን ውድድሩን ከኬፕ ቨርዴ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ትጀምራለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #sport #worldcup

2 months ago