11 days ago
ከችርቻሮ የሱቅ ስራ የተነሳው ጊፍት ትሬዲንግ 35ኛ አመቱን አከበረ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በገቢና ወጪ ንግድ ዘርፍ አንጋፋ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ጊፍት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩ በዓል በዛሬዉ እለት አክብሯል።
በንግድ ማህበረሰቡ፣ በመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና በድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ኩባንያው ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከግማሽ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ያቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይም ወደ አግሮ-ኢንዱስትሪ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ይፋ ባደረገው እቅድ መሠረት በአዳማ እና ሞጆ ከተሞች መካከል በሚገኘው የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ፍሪ ዞን ውስጥ 7,527.54 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡን ገልፀዉ ቦታው ከጅቡቲ ኮሪደር እና ከሞጆ ደረቅ ወደብ አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ፣ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳልጠው የተገለጸ ሲሆን፤ የአካባቢው የዲዛይን ስራ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ምዕራፍ መሸጋገሩ ተመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው እሴት በተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች ዘርፍ መሰማራት የጀመረ ሲሆን፣ በተለይም በድፍድፍ የአቮካዶ ዘይት ማምረት እና በከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አስመጪነት ዘርፍ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን ለማሳደግ እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የጥቁር አዝሙድ እርሻ መጀመሩን የጠቆመው ጊፍት ትሬዲንግ፤ በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ 300 ሄክታርየቡና እርሻ መሬት ተረክቦ ወደ ምርት እንደሚገባ አስታውቋል።
ከ50 ዓመታት በፊት በመርካቶ በታዋቂው የቢዝነስ ሰው በአቶ ገብረኢየሱስ ኢጋታ ሲማ በትንሽ የችርቻሮ ሱቅ የተጀመረው ይህ የንግድ እንቅስቃሴ፣ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ወደ ገቢና ወጪ ንግድ በማደግ ለዛሬው ግዙፉ ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ (ጊፍት ሪል እስቴት፣ ጊፍት ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ብረታ ብረት፣ ጊፍት ፕሮፐርቲ እና ጊፍት ቱር ኤንድ ትራቭል) መፈጠር መሰረት መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም B-29 የልብስ ሳሙና፣ የሮድ ስቶን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የጂንዳል ቆርቆሮዎች፣ የብረትና የኬሚካል ምርቶችን ጨምሮ በርካታ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ በማስተዋወቅ ረገድ ኩባንያው የነበረው ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተገልጿል።
ኩባንያው እ.ኤ.አ በ2030 በኢትዮጵያ በቡና፣ ቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ እና ቅመማ ቅመም ላኪነት ከግንባርቀደም 5 ኩባንያዎች አንዱ የመሆን ራዕይ ሰንቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #gifttradingrealstate #construction #technology

ጊፍት ትሬዲንግ 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩውን አከበረ!
#fastmereja :- በኢትዮጵያ በገቢና ወጪ ንግድ ዘርፍ አንጋፋ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ጊፍት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩ በዓል በዛሬዉ እለት አክብሯል።

13 days ago
የ4 ዓመት ህጻን ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ባልና ሚስት በጽኑ እስራት ተቀጡ
ወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ከጠዋቱ 3 ሰአት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቀጠና አራት እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪ መታደል ታደሰ በ4ሺ ብር የወር ደመወዝ በቤት ሰራተኝነት በአቶ መልካሙ ረዳቴ እና በወ/ሮ ጥጋብ ጌታሁን መኖሪያ ቤት ትቀጠራለች።
ግለሰቧ በተቀጠረች በ10ኛ ቀን የቀጣሪዎቿን ወደ ስራ መሄድን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የ4 አመት እድሜ ያለውን ህፃን ዮሴፍ መልካሙን ችብስ ልግዛልህ በማለት ይዛው ትሰወራለች።የህፃኑ ወላጆች ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ልጃቸውን እና የቀጠሯትን የቤት ሰራተኛ ከቤት ያጧቸዋል።
የቤት ሰራተኛቸው የትዳር አጋር የሆነው ግለሰብ ወደህጻኑ ወላጅ አባት ስልክ በመደወል ልጅህን አግተንዋል 5 ሚሊየን ብር አምጣ ብሎ ስልኩን ይዘጋል ። የልጃቸውን መታገት ተደውሎ የተነገራቸው ወላጅ አባት እና እናትም ለአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያመለክታሉ።
ፖሊስ የቤት ሠራተኛዋ መታደል ታደሰ ከትዳር አጋሯ መሠረት አየለ ጋር በመሆን ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ ጫጫ ክፍለ ከተማ ህፃኑን እንደወሰዱት ይደርስበታል።
ኋላም ተጠርጣሪዎች ቤት ተከራይተው ልጁን ካስቀመጡበት በቁጥጥር ስር በማዋል ታግቶ የነበረው ህፃን ዮሴፍ መልካሙን ከነሙሉ ጤንነቱ ለወላጆቹ አስረክቧል። የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ እንዲመሰረት አድርጓል።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው በማግኘቱ 1ኛ:- ተከሳሽ መታደል ታደሰ በ8አመት ከ4ወር 2ኛ :-ተከሳሽ መሰረት አየለ ደግሞ በ7አመት ከ9ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል ።
Seledadotio

21 days ago
ወልቂጤ : የመሐመድ ናስር ታሎር (MNT) የታዳጊዎች እግር ኳስ አካዳሚ
#ethiopia | ወልቂጤ — በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የ"መሐመድ ናስር ታሎር" (MNT) የታዳጊዎች እግር ኳስ አካዳሚ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ረገድ ተስፋ ሰጪና ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን አርአያነት ያለው ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰይፈ ዓለሙን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ የሚገኙ የስፖርት ሥልጠና ፕሮጀክቶችን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።
የክረምት ወቅት ስፖርታዊ ንቅናቄና የተተኪዎች ሥልጠና*
የቢሮ ምክትል ኃላፊው አቶ ሰይፈ ዓለሙ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በክረምት ወቅት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም የቴክኒክ ቡድን ተቋቁሞ በሁሉም ዞኖች በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የታጀቡ ሥራዎችን የማስጀመር ተግባር እየተከናወነ ይገኛል።
በክረምት ወቅት ታዳጊዎች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በማድረግ በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያሳልፉ ማድረግ እንደሚገባ ያሳሰቡት ኃላፊው፤ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመፍጠር በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ሰፊ የንቅናቄ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የሰርከስ ሰልጣኞችን እየመለመለ እንደሚገኝና በ2019 በጀት ዓመት የክልሉን የሰርከስ ቡድን በአንድ የስልጠና ማዕከል ሰብስቦ ሥራ ለማስጀመር ማቀዱን አስታውቀዋል።
በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ምልከታ ቡድኑ እጅግ መደሰቱን የገለጹት አቶ ሰይፈ፤ በተለይም በእግር ኳስ በየዕድሜ ክልሉ የሚሰጠው ሥልጠና ጠንካራና የአሰልጣኞችን ቁርጠኝነት በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማው የሚገኘው የMNT እግር ኳስ አካዳሚ በተተኪ ታዳጊዎች ላይ እየሠራ ያለው ሥራ ለሀገርና ለክልሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቁመው፣ በዞኑ የሚገኙ ባለሀብቶች ይህንን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የማኅበረሰብ ድጋፍ**
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር በበኩላቸው፤ በዘንድሮው ክረምት ወጣቶችን በማስተባበር ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣቶችና ታዳጊዎች በአካባቢ ጽዳት፣ በችግኝ ተከላ፣ በኪነ-ጥበብ እና በስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሳተፉ እየተደረገ ከመሆኑም በላይ፤ አቅመ-ደካሞችን የመደገፍና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ደብተር የማሰባሰብ ሥራዎች በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ስለ መሐመድ ናስር ታሎር (MNT) አካዳሚ
የአካዳሚው አሰልጣኝና ሥራ አስኪያጅ አብድልህኒ ተሰማ እንደገለጹት፤ አካዳሚው በአሜሪካ ሀገር በሚኖረውና የከተማው ተወላጅ በሆነው በአቶ መሐመድ ናስር የተመሠረተ ነው።
ከተመሠረተ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ አካዳሚ፦
* ከ6 እስከ 18 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎችን ያቅፋል።
* በአሁኑ ወቅት ከ400 በላይ ታዳጊ ስፖርተኞችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የጉራጌ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

1 month ago
እንኳን ደስ አላችሁ - ከለቡ ገብርኤል የምሥራች ተሠማ
ከ100,000,000.00 - ከአንድ መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ በድል ተጠናቀቀ
የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ለማጠናቀቅ ሰኔ 27 እና 28 በተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በቃል ኪዳን ሰነድ ተሰብስቧል ።
ከ13 ዓመታት በፊት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ወደ ግንባታ የገባው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና መርጡለ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም በውስጡ የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እና ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን የያዘ ነው።
በደብሩ የሚገኘው የቅድስት አርሴማ ሕንጻ ቤተመቅደስ በአቶ ሰማቸው ከበደን እና ቤተሰቦቻቸው ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ቤተክርስቲያኑ ለአገልግሎት መብቃቱን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ አስጠፋኖስ ይርጋ አስተታውሰዋል።
አስተዳዳሪው እዚያው ግቢ ውስጥ ከቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ቀድሞ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ከቅድስት አርሴማ በኋላም እንኳ ማለቅ ያልቻለው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተክርስቲያንን ለማጠናቀቅ ሰኔ 27 እና 28 በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ሕንጻውን ለማጠናቀቅ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በቃል ኪዳን ሰነድ ተሰብስቦ በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ቸሩ በግላቸው 9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው ፣ በደብሩ አስተዳዳሪ አስተባባሪነት ወልደጊዮርጊስ ተብሎ በጥምቀት ስሙ የተገለጸ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ 10 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለመርጡለ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የክርስትና ቤት ለመሥራት ቃል መግባቱን ገልጸዋል።
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ አስጢፋኖስ በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ አቶ ሰማቸው ከበደን እና ባለቤታቸውን ወ/ሮ ሀናን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትና በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናን ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በተለይም አቶ ስማቸው ከበደ በሆቴላቸው መርሐ ግብሩ በነጻ እንዲከናወን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነጻ አገልግሎት መስጠታቸው እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው ለሌሎች ባለሀብቶችም አርአያነታቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ደብሩ ገቢ የተደረገውን እና በቃል ኪዳን ሰነድ ቃል የተገባውን ገንዘብ በመሰብሰብ በአጭር ጊዜ ቀሪውን የማጠናቀቂያ ሥራ ፈጽሞ ሕንጻ ቤተመቅደሱን ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው በሥራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል ።
የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና መርጡለ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም በ1986 ዓ.ም የተመሠረተ ደብር ነው።
ኹነቱን በበጎ አድራጎት ያስተባበረው ሎዛ ኹነቶች አዘጋጅ መኾኑን የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ተናግረው ለሚዲያዎች፣ ለአገልጋዮች እና ለምእመናን ምስጋናቸውን አቅርበዋል

Sponsored by
Surafel
1 month ago
እንኳን ደስ አላችሁ - ከለቡ ገብርኤል የምሥራችጨተሠማ
ከ100,000,000.00 - ከአንድ መቶ ሚሊያን ብር በላይ በመሰብሰብ በድል ተጠናቀቀ

ከ13 ዓመታት በፊት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ወደ ግንባታ የገባው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና መርጡለ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም
በውስጡ የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እና ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን የያዘ ነው።

#ethiopia | የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ለማጠናቀቅ ሰኔ 27 እና 28 በተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በቃል ኪዳን ሰነድ ተሰብስቧል ።

ኹነቱን በበጎ አድራጎት በብቃት ያስተባበረው ሎዛ ኹነቶች አዘጋጅ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ችሎት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ህብረት ባንክ እና አቢሲንያ ባንክ በኮዝሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በአቶ ኃይለኢየሱስ መንግስቱ ስም ያሉትን የባንክ ሂሳቦች እንዲያግዱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም እስከ 400 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ዝውውር ታግዷል ሲል በአዲስ አባባ ታትሞ የሚወጣው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገበ:
ጋዜጣው እንደዘገበው ይህ ትዕዛዝ የተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በውርስ እና አከራካሪ በሆኑ የንግድ ንብረቶች ላይ የተነሳውን የህገ-መንግስት ትርጉም ክርክር መርምሮ እስኪያጠናቅቅ ድረስ፣ ቀደም ሲል የተሰጡ የንግድ ውሳኔዎች አፈፃፀም እንዲታገዱ ኤፕሪል 27, 2026 (ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም) ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።
የክርክሩ ዋና ማጠንጠኛ በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ላይ የሚገኝ እና ግምቱ ወደ 800 ሚሊዮን ብር አካባቢ የሚያወጣ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሆቴል ነው። አቶ ኃይለኢየሱስ መንግስቱ እና ልጆቻቸው አቤል እና ኖኤል፣ ይህ ንብረት እና የኩባንያው አክሲዮኖች ለ18 ዓመታት የውርስ ጉዳያቸው እልባት ሳያገኝ የቆየው የሟች ወ/ሮ ርብቃ ኃይሉ የጋራ ንብረት እንደነበሩ ይከራከራሉ።
በመሆኑም የእርሷ ድርሻ ነው ያሉትን 400 ሚሊዮን ብር የሚጠይቁ ሲሆን፣ በ2017 (እ.ኤ.አ) የተካሄደው የ20 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ያለ ፈቃድ የተፈጸመ ህገ-ወጥ ሽያጭ ነው በማለት ይሞግታሉ። ጉዳዩን የያዙት ዳኛ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ከባንክ ሂሳቦቹ በተጨማሪ አምስት ተሽከርካሪዎች እና ቀደም ሲል የተፈጸመ የ2.3 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንዲታገድ ተጨማሪ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

♦️ኢትዮጵያዊነት በኩራት የተንፀባረቀበት፣ባህልና አንድነት የደመቁበት ታሪካዊ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት
ድፍን 43 ዓመታትን ኢትዮጵያዊያንን በአንድ ጥላ ስር አሰባስቦ ናፍቆታቸውን የሚወጡበት፣ ባህላቸውን፣ታሪካቸውን፣ቋንቋቸውን፣አልባሳታቸውን ለአዲሱ ትውልድ የሚያስተላልፉበትና ለሌላው ዓለም የሚያስተዋውቁበት ከስፖርትም በላይ ትልቅ ትርጉም ያለው የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በሠሜን አሜሪካ (ESFNA) በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ዓመታዊ ክብረ በዓል በልዩ ድምቀት ተከፈተ።
በመክፈቻው ስነ-ስርዓት በሚኒሶታ ግዛት የሚገኘው የTCO Vicking ስታዲየም ከወትሮው በተለየ በኢትዮጵያውያን ባህል፣ ባንዲራና አንድነት ልዩ ውበት ፈሶበት ውሏል።
የኢትዮጵያ ቀለማት በስታዲየሙ ላይ ሲያበሩ፣ ባህላዊ አልባሳት፣ ዜማዎች እና የደስታ ድምፆች ለተሰበሰበው ሕዝብ ከስፖርትም ባለፈ የታላቅ ክብረ በዓል ድባብን አላብሠውታል።
በሚኒሶታ ግዛት"ኢትዮጵያ"የምትባለው ሀገርን በመፍጠር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባህላቸውን፣ አንድነታቸውን እና ኩራታቸውን በአስደናቂ ሁኔታ ያሳዩበት ዕለትም ሆኖ ተመዝግቦ አልፏል።
በአጭር ቃል የTCO ስታዲየም በዕለቱ የትርዒትና የባህል ድምቀት ማዕከል ሆኖ ነበር ያለፈው፤የኢትዮጵያ ባንዲራ በክብር ሲውለበለብ ማየት ባህላዊ አልባሳት በውበታቸው የብዙዎችን ቀልብ ይስቡ፣ዐይንንም ይማርኩ ነበር።
በተለይ በዕለቱ የቀረቡትና ኢትዮጵያ የብዙ ባህልና ታሪኮች ባለቤት መሆኗን የሚያሳዩት የአፋርና የጋምቤላ ብሄረሠብ የባህል ሙዚቃዎችና ውዝዋዜዎች፣በአረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ባንዲራችን ያሸበረቁት ታዳጊዎች ያሳዩት የተለያዩ የኪነጥበብ ትርዒቶች መድረኩን ሕይወት ሞልተውበት ለተመልካች ትልቅ ደስታን ለግሠውትም ታይቷል።
በዕለቱ ፕሮግራሙን በታደሙት ላይ የሚታየው የፈገግታ ፊት፣ የአንድነት ስሜት እና የኢትዮጵያዊነት ኩራት ተሳታፊዎቹን በልዩ የደስታ ስሜት አስተሳስሮ ነበር፤
በድምፀ ነጎድጓዱ ታዋቂው የመድረክ መሪ ጋዜጠኛ ወንድወሠን ከበደ መድረኩን በማራኪ ድምፁ ተቆጣጥሮት ተጨማሪ ውበት ፈጥሮለት፣ግርማ ሞገስም አላብሶት ታይቷል፤
በሠልፍ የሚጓዙትን 32 ቡድኖች ሲያሳዩት የነበረው ባህላዊ ጭፈራና የተለያዩ ዳንሶችና ትርዒቶች ለሜዳው ተጨማሪ ውበቶችም ነበሩ።
የዕለቱ የመክፈቻ ፕሮግራም ከመዝናኛነቱ ባሻገር ባህልን የሚያከብር፣ትውልድን ከትውልድ የሚያገናኝ እና የኢትዮጵያውያንን አንድነት በግልጽ የሚያንጸባርቅ የማይረሳ በዓል ሆኖ ማለፉ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የሌሎች ሀገር ዜጎችን ጭምር በግርምት እጃቸውን አፋቸው ላይ እንዲጭኑ አስገድዷል።
በዕለቱ ሌላኛው የመክፈቻው ፕሮግራሙ አካል ሆኖ ያለፈው በውድድሩ ከመሸናነፍ ባለፈ ለወገኖቹ ተቆርቋሪና አጋር መሆኑን ያሳየበት መድረክ መሆኑ ነው፤
የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሆነው በአቶ ያሬድ ነጋሽ ሃሳቡ የተመዘዘው በአርሲ ዞን በንፁሀን ዜጎች ላይ የደረሠውን ጉዳትና ሞት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የታሠበ ሲሆን የድጋፍ ማሠበሰቢያ መዘርጋቱንም ይፋ በማድረግ ፌዴሬሽኑ ድርጊቱን ከማውገዝ ባለፊ በዜጎቹ ችግርም ሆነ በደስታ ወቅት ከጎናቸው መሆኑን በተግባር በማሳየቱ ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ አመራር ከየአቅጣጫው የምስጋና ዝናብ እንዲዘንብለት አድርጓል።
በልዩ ልዩ የእግር ኳስ ውድድሮች የተጀመረውና በደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በይፋ የተከፈተው 43ኛው ዓመታዊ ክብረ በዓል እስከ ጁላይ 4 እንደደመቀ የሚቀጥል ሲሆን በተለይ በሚኒሶታ ግዛት ገዥ ጭምር ጁላይ 3 የኢትዮጵያዊያን ቀን በሚል የታወጀለት የ "Ethiopian Day" ከወዲሁ ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት ቀንም ሆኗል።መልካም ክብረ በዓል!!
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ኤገን ሚኒሶታ

የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ ተካሄደ
የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣በአርቲስት ወይንሸት አበጀና በአርቲስት አሸናፊ ማህሌት አዘጋጅነት በብሉ ናይል ሪዞርት (አቫቫንቲ) ትናንት ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በተካሄደው የጥበብ ዝግጅት የተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በዚህ መርሐ-ግብር አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች እና የዘንድሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴአትርና ሲኒማ ጥበባት ዲፓርትመንት ተመራቂዎች በጋራ ተስናስለው ጥበባዊ ስራዎችን አቅርበዋል ።
በመርሐ-ግብሩ ላይ አየለ አናውጤ (ዶክተር) የአ.ብ.ክ.መ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣ አቶ ግ/ማርያም ይርጋ ባህል፣ ኪነጥበብና ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የስራ ሀላፊዎቹ አያይዘውም የባህርዳር ከተማን የጥበብ እና የጥበበኞች ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል። ከተማዋ ለምታስበው የጥበብ ከተማነት እቅድም የአንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ለዚህም ስኬት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።
አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎችም በተለየ ሁኔታ የዘንድሮ ተመራቂዎች ወደ እውነተኛው የጥበብ አለም ሲመጡ ማስተዋል ስላለባቸው ጉዳዮች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል። የከተማዋ ወጣት ከያኒያንም የጥበብ ስራዎችን ለታዳሚው አቅርበዋል።
ሌሎች ስለባህርዳር ከተማ እና የጥበብ ቁርኝት እንዲሁም መሰል መርሐ-ግብሮች በተጠናከረ መንገድ ስለማከናወን መልእክቶች በተላለፉበት ዝግጅት ለዚህ ዝግጅት መቃናት ታላቁን ሚና ለተወጣችው አርቲስት ወይንሸት አበጀ ከከተማው ወጣቶች የክብር ስጦታ እና ሜዳሊያ ተበርክቶላታል። አርቲስት አሸናፊ ማህሌት እና አንጋፋው አርቲስት ተስፉ ብርሐኔም የሜዳልያ ሽልማት ተቀብለዋል።
ደማቅና በርካታ ታድሚያንን ያሳተፈው የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ በአቶ ግርማው አሸብር የባህርዳር ዩንቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልእክት ተቋጭቷል።
የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ የተቃና እንዲሆን የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣ አባይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ዘመን ኮንስትራክሽን፣ ልህቀት ዲዛይን እና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን፣ ብሉ ናይል ሪዞርት እና ቶሎ ትራንስፖርት ድጋፍ አድርገዋል።

ያልተዘመረለት ጀግና!
* በኢትዮጵያ 30 ትምህርት ቤት አስገንብቷል
***
የአቶ አዲስ ገሠሠ አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | አቶ አዲስ ገሰሰ ከአባታቸው ከግራዝማች ገሰሰ መንገሻ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስናቀች መልሴ ጥር 8 ቀን 1945 ዓ.ም. በቀድሞው ኢሊባቦር ጠቅላይ ግዛት ጎሬ ከተማ ተወለዱ፡፡
እስከ 9ነኛ ክፍል በጎሬ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ት/ቤት ከተማሩ በኋላ፤ የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው፤ ወደ ጅማ በመሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚያዝያ 27 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በህይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡትና “ ስብዕናዬን በዲሲፕሊን ገንብቶታል” የሚሉትን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በ1961 ዓ.ም. በመቀላቀል ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በበረራ ቴክኒሻንነት ተመርቀዋል፡፡
በሙያቸው አንድ ዓመት ካገለገሉ በኋላ፤ በ1964 ዓ.ም. ነፃ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሀገር ሺካጎ ከተማ በማቅናት በራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ፤ እና በቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በወጣትነት ዘመናቸው ያን ጊዜ ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በመቀጠልም በኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ወንድሞቻቸውን ሙሉጌታ ገሰሰን፤ ዘለቀ ገሰሰንና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታን ወደ ሺካጎ ካመጡ በኋላ ዳሎል ባንድን መስርተዋል፡፡ አቶ አዲስ ገሰሰ በሚማሩበት ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ በሚል መጠሪያ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር በሚከበር በዓል ላይ፤ ዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርብ በማስቻል የሙዚቃ ማኔጅመንት የህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በመቀጠልም ዳሎል ባንድን ይዘው በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ እና በመላው አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን-በኢትዮጵያ ባንድ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ሙዚቃን ማኔጅ በማድረግ ጉዟቸው የእውቁን የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ የቦብ ማርሌን ቤተሰብ ሃብትና ንብረቱን በማስተዳደር ብቻ ሳይሆን፤ የቦብን ልጆች በስነ ምግባር ኮትኮቶ ለማሳደግ ከአሜሪካ ኒውዮርክ -ጃማይካ ኪንግስተን እየተመላለሱ በትጋትና በታማኝነት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በዚያን ጊዜም ዘመን አይሽሬውን የቦብ ማርሌይ “ሌጀንድ አልበም" እንዲሰራ ባቀረቡት ንድፈ-ሃሳብ መሰረት ከአይላንድ ሪከርዲንግ ጋር በመፈራረም ውጤማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በቦብ ማርሌይ ቤተሰቦች የተዘጋጁትንና ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ የተደረጉትን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ኮንሰርቶች ሃሳብ ከመጠንሰስ ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት ያክል ስራውን በሃላፊነት መርተዋል፡፡ አስተዳድረዋል፡፡
በዚሁ የአስተዳደር ዘመናቸው በዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል በማይናወጥ መሰረት ላይ አፅንተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ዚጊ ማርሌይን ከጃማይካ… የነዘለቀን ገሰሰን ዳሎል ባንድ ደግሞ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ፤ ከሲግማ ስቱዲዮ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በመፈራረም በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ ተደማጭ የነበረውን ኮንሺየስ ፓርቲ አልበም እንዲለቀቅ አድርገዋል፡፡
በአልበሙ ከተካተቱት ስራዎች መካከል ቱሞሮ ፒውፕል የተሰኘው ሙዚቃ በዓለም ላይ እጅግ ከመወደዱ የተነሳ ብዙዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ያዜሙት ነበር፡፡
በአቶ አዲስ ገሰሰ ማናጀርነት በተመራው በዚሁ የሙዚቃ አልበም ዚጊ ማርሌይ የአሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያው ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማት እንዲወስድ በማስቻል ታሪክ የማይረሳውን ስራ ሰርተዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲስ ገሰሰ ከወንድማቸው ከአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ለመዘከር የሚዘጋጀውን “አፍሪካ ዩናይት” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግና አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት ፤ በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን አስችለዋል፡፡ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሪታ ማርሌይና አምስቱ የቦብ ልጆች ተገኝተዋል፡፡
ይኸው ፌስቲቫል በፈጠረው መልካም አጋጣሚም ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጋብዘው የራሳቸውን የዜግነት ድርሻ ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ ለዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮን/ከመጀመሪያው አልበሙ ጀምሮ ማኔጅመንቱን በመያዝ ፤ እንዲሁም እጅጋየው ሽባባው /ጂጂን/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት ለልጆቹ ውጤታማነት አቶ አዲስ ገሰሰ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ አቶ አዲስ “ጃናናይት” የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘ ባንድ መስርተው ስኬታማ ለማድረግ ያደረጉት ጥረትም የሚወሳ ነው፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው- እጅግ ገዝፈው፤ በተለያየ የአድናቆት ቃል የሚጠሩት አቶ አዲስ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎረን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ ኧርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ስራን መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲስ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍም ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም ለሀገራቸው እድገት ቀን ከሌት ያለእረፍት ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንትና በኢንቨስትመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ አድራጎታቸውም አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮች ቀድመው በመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
በዋናነትም ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን አሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ስለእነኚሁ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ስላሰሯቸው 30 ትምህርት ቤቶች ሲናገሩ “ተስፋ ሳልቆርጥ በፅናት የታገልኩበት በጎ ተግባር በመሆኑ ያስደስተኛል” ይሉ ነበር፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በጠራቻቸው ጊዜ ሁሉ እየተገኙም በመላው ኢትዮጵያ አዳዲስ ቤተክርስቲያኖችን በማሰራት ፤ የተጎዱ ገዳማትንና ቤተክርስቲያኖችን በማደስ ፤ የተዘጉ ቤተክርስቲያኖችን በማስከፈት፤ የቤተክርስቲያኖችን ንዋየ ቅዱሳን በማሟላትና የካህናት ደሞዝን በመክፈል እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ ድምፃቸውን አጥፍተው አገልግለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ-ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበራቸው የፀና ትዳር አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ አፍርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ፤ በአሜሪካ ሀገር ኒውጄርሲ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ፣ ሰኔ 20 ቀን 2018ዓ.ም በ6:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
አቶ አዲስ ገሰሰን ከአጠገቡ ሳትለዩ ላስታመማችሁትና ለጠየቃችሁት ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር ብድራችሁን ይከፈላችሁ፡፡
የአቶ አዲስ ገሰሰን ነፍስ ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ አብርሃም ይስሐቅ እና ያቆብ ጎን ያሳርፍልን፡፡
ለቤተሰቡ፤ ለወዳጆቹ፤ ለዘመዶቹ፤ ለሙያ አጋሮቹ፤ ለአድናቂዎቹ ሁሉ መፅናናቱን ይስጣቸው፡፡

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ ሶስት፣ ኤርፖርት ሞቴል ጊቢ ውስጥ የሚገኘው እና በምግብ ቤትነት ፈቃድ አውጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ስካይ ላይን ክለብ ህገወጥ የሺሻ ማስጨስ ተግባር ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ በመያዙ በፖሊስ ታሽጓል።
በአቶ ማለደ ጉዴ ስም ህጋዊ የምግብ ቤት ንግድ ፈቃድ የተመዘገበው ይህ ተቋም፣ ከተሰጠው የስራ ዘርፍ ውጪ ከህግ እውቅና ውጪ በሆነ መንገድ ሺሻ ሲያስጨስ ነው የተገኘው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ የቁጥጥር ዘመቻ (ኦፕሬሽን) በርካታ የሺሻ እቃዎች እና ተያያዥ ማጨሻ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ድርጅቱም በፖሊስ በታሸገበት ሁኔታ ላይ ይገኛል።
ይህ ክስተት በከተማዋ ውስጥ ስር ሰዶ እየተስፋፋ ለመጣው ህገወጥ አሰራር እና ሙስና ትልቅ ማሳያ ሆኗል። በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በርካታ ምግብ ቤቶች እና መዝናኛ ስፍራዎች ህገወጥ የሺሻ ማስጨስ ተግባርን በድፍረት የሚያካሂዱ ሲሆን፣ ይህንንም ከለላ ለማግኘት ሲሉ ለየክፍለ ከተማው አመራሮች እና የቁጥጥር ስራ ለሚሰሩ አካላት በየቀኑ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉቦ (ሙስና) እንደሚከፍሉ በስፋት ይነገራል።
በተለይም የክፍለ ከተማ አመራሮች ህግን ማስከበር ሲገባቸው፣ በየቀኑ በሚሰበስቡት የጉቦ ገንዘብ ተደልለው ለህገወጥ አሰራሩ ዋና ተባባሪ መሆናቸው የነዋሪዎችን ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል። የስካይ ላይን ክለብ እርምጃ እንደ አንድ ጅማሮ የሚታይ ቢሆንም፣ የከተማዋ አስተዳደር እና የፀረ ሙስና ተቋማት ከድርጅቶቹ ባሻገር ጉቦ እየተቀበሉ ህገወጥ ድርጊቱን የሚያበረታቱትን አመራሮች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ተብሎ በጥብቅ እየተጠየቀ ይገኛል።

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የጃኖ ባንድ መስራች፣ የዳሎል ባንድ አባል የነበሩት ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሰሰ ወንድም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸው የገነነ ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ፣ በኒው ጀርሲ፣ አሜሪካ ባደሩበት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የቅርብ ወዳጆቻቸው አሳዝነው አስታውቀዋል። የሞታቸው ምክንያት ገና በውል ያልታወቀ ሲሆን፣ አስከሬናቸው ወደ ውዲቷ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚሸኝም መረጃዎች ያመለክታሉ።
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀየሩ እና የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያቆሙ ታላቅ ሰው ነበሩ። እኚህ የሙዚቃ ማኔጅመንት ባለሙያ፣ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉትን የሬጌው ንጉስ የቦብ ማርሊ ቤተሰቦችን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሙዚቀኞች የጀርባ አጥንት በመሆን አገልግለዋል። የእሳቸው የህይወት ጉዞ ከኢትዮጵያ ጀምሮ፣ በቺካጎ፣ ጃማይካ፣ ኒው ዮርክ እና በመጨረሻም ኒው ጀርሲን ያዳረሰ ረዥም እና አስደናቂ መንገድ ነበር።
አቶ አዲስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ፣ ከ30 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው ማኔጅመንት አጠኑ። ከዚያም ወንድሞቻቸው ሲከተሏቸው፣ ህይወታቸውን ሙሉ ለሙሉ ለወንድሞቻቸው የሙዚቃ ስኬት አዋሉ። ወንድሞቻቸውና ጓደኞቻቸው የመሰረቱት "ዳሎል" የተሰኘው ባንድ፣ ከኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ወደ ሬጌ በማዘንበል፣ በአቶ አዲስ አመራር ስር በቺካጎ ስሙን ማግነን ጀመረ።
በ1982 የቦብ ማርሊ ባለቤት ሪታ ማርሊ ባቀረበችላቸው ጥሪ መሰረት፣ ዳሎል ባንድ በጃማይካ ኪንግስተን በተካሄደው የመጀመሪያው የቦብ ማርሊ መታሰቢያ ላይ ለመጫወት በቅቷል። አቶ አዲስ ሪታ ማርሊ በባለቤቷ ሞት እያዘነች በነበረችበት ወቅት የሰጧት ድጋፍ፣ ጠንካራ ወዳጅነትን ፈጠረ። ይህ ግንኙነት ዳሎል ባንድ ከ1988 እስከ 1991 ድረስ የዚጊ ማርሊ ይፋዊ ባንድ እንዲሆን አስችሎታል። ዳሎል ባንድ በ "Conscious Party" አልበም ፕላቲነም፣ እና በ "One Bright Day" አልበም ጎልድ ደረጃ በመድረስ፣ ይህን ታሪካዊ ስኬት ያገኘ የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያን ባንድ ለመሆን በቅቷል።
አቶ አዲስ ከሪታ ማርሊ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊን 'Legend' አልበም ዓለም አቀፍ ጉብኝት አደራጅተዋል። ከሁሉም በላይ ግን፣ አቶ አዲስ በ2005 በአዲስ አበባ የተካሄደውንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የታደመበትን ታሪካዊውን "Africa Unite" ኮንሰርት በዋናነት የጠነሰሱት እሳቸው ነበሩ። ይህ ኮንሰርት የቦብ ማርሊን 60ኛ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የቦብ ማርሊ ቤተሰብ፣ አንጀሊክ ኪጆን ጨምሮ በርካታ ከዋክብትን በአዲስ አበባ ያሰባሰበና ስለ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ገጽታ ለዓለም ያሳየ ታላቅ ኩነት ነበር።
አቶ አዲስ የዓለም አቀፍ ከዋክብትን ከማስተዳደር ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ለማሸጋገር ትልቅ ህልም ነበራቸው። ለዚህም ነው "አዲስ ማኔጅመንት" የተሰኘውን ድርጅታቸውን መስርተው በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን የደገፉት።
ታዋቂውን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በማግኘትና ለረጅም ጊዜ ማኔጀሩ በመሆን አገልግለዋል። እንዲሁም፣ ታዋቂዋን ድምጻዊት ጂጂን በአጋጣሚ ቤታቸው ውስጥ ካገኟት በኋላ፣ ችሎታዋን አይተው፣ ኒው ዮርክ እንድትመጣ በመምከር፣ ከታዋቂው የአይላንድ ሪከርድስ መስራች ክሪስ ብላክዌል ጋር አስተዋውቀዋት፣ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውል እንድትፈራረም አድርገዋል።
አቶ አዲስ ዓለም አቀፍ ኔትዎርክ ያላቸውና ስኬታማ ቢሆኑም፣ እንደቅርብ ወዳጆቻቸው ምስክርነት እጅግ ትሁት ነበሩ። ኒው ጀርሲ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ሹራብና አጭር ሱሪ ለብሰው ከሶስት ዓመት ልጃቸው ሀና ጋር ጊዜ ማሳለፍን የሚወዱ አባት ነበሩ። ከሙዚቃ ስራቸው በተጨማሪ በቺካጎ የሬጌ ክለብ፣ በኢትዮጵያ የእርሻ ስራ እና በ "One Love Africa Foundation" አማካኝነት በኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ሰፊ ራዕይ ነበራቸው።
አቶ አዲስ ገሰሰ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ በክብር ያስጠሩ፣ የሙዚቃውን ኢንደስትሪ ያሳደጉ እና ለብዙዎች መነሻ የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸው። በድንገተኛ ህልፈታቸው የሙዚቃው ዓለም፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም አድናቂዎቻቸው ጥልቅ ሀዘን ላይ ይገኛሉ።
ነፍስ ይማር! አቶ አዲስ ገሰሰ፣ ስራዎ እና አሻራዎ ለዘለዓለም ሲታወስ ይኖራል።

በአቶ ግርማ ዋቄ የሚመራው የኡጋንዳ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የ982 ሚሊዮን ዶላር ግዙፍ ስምምነት አደረገ
#ethiopia | የኡጋንዳ ብሔራዊ አየር መንገድ 10 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውንና 982 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ታሪካዊ የጋራ ስምምነት ከታዋቂው የቦይንግ ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ታውቋል።
ይህ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት ግዢ አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2019 አገልግሎቱን በድጋሚ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የፈጸመው ትልቁ የአውሮፕላን ኢንቨስትመንት ተብሎ ተመዝግቧል።
የስምምነቱ ማጠናቀቂያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በኢንቴቤ ቤተ መንግሥት የተከናወነ ሲሆን፣ የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በክብር ታዛቢነት ተገኝተዋል።
ይህንን ታላቅ ውል በኡጋንዳ አየር መንገድ ስም የፈረሙት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ግርማ ዋቄ ሲሆኑ፣ በቦይንግ ኩባንያ በኩል ደግሞ የአፍሪካ የሽያጭ ኃላፊው አቶ አንበሴ ይትባረክ ውሉን አጽድቀዋል።
በገንዘብ ሲሰላ በግምት 3 ነጥብ 7 ትሪሊዮን የኡጋንዳ ሺሊንግ የሚያወጣው ይህ የ10 አውሮፕላኖች ግዢ ጥቅል አራት የቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር እና አራት የቦይንግ 737 ማክስ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ያካተተ ነው።
በተጨማሪም አንድ ወደ ጭነት አገልግሎት የተቀየረ ቦይንግ 767 እንዲሁም ሌላ አንድ ወደ ጭነት አጓጓዥነት የተቀየረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በስምምነቱ ውስጥ ተካተዋል።
ይህ የተወሰደው ስትራቴጂካዊ እርምጃ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች በረራውን በከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት ከመጣር ባለፈ፣ በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍም ጠንካራና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት ያለውን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው።
በያፌት ገብረሕይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ugandaairlines #boeing #aviationnews #girmawake #business #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ኦብነግ ከታጠቁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አለው መባሉን ውድቅ አደረገ
*************
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከታጠቁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አለው መባሉን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ፣ ከሀገር ውስጥ የሰላም ስምምነቶችና ከሕጋዊ የፖለቲካ ሥርዓቱ ጎን መቆሙን የሚያረጋግጥ ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፤ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ፈጽሞ እንደማይተባበር፣ ስለ ድርጅቱ ወቅታዊ የአመራር ለውጥ እና በትክክለኛ የአሠራር መስመሮች ላይ ብቻ መደገፍ ስለሚያስፈልግበት ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ኦብነግ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከታጠቁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አለው መባሉን በጽኑ የሚቃወም ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል፤ የስምምነቱን ድንጋጌዎች በሙሉ ለማክበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነትም ያረጋግጣል።
በተመሳሳይ ኦብነግ የኢትዮጵያ መንግሥት የገባውን ቃል እንዲያከብር እና የስምምነቱን ሙሉ አፈጻጸም በቅን ልቦና እንዲያረጋግጥ ይጠብቃል።
እ.አ.አ በጥቅምት 21 ቀን 2018 በአስመራ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ዛሬ በሶማሊ ክልል ለሚታየው ሰላምና መረጋጋት እንደ መሠረት ሆኖ አገልግሏል። ስምምነቱ ከተተገበረበት ጊዜ ጀምሮ ክልሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሰላማዊና የተረጋጉ ክልሎች አንዱ ለመሆን የበቃ ሲሆን፣ ይህም የስምምነቱን አስፈላጊነት እና ሁሉም ወገኖች ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ኦብነግ የአስመራው የሰላም ስምምነት ለሶማሊ ክልልና ለሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ጥቅም እንዳስገኘ ያምናል። ከዚህም በላይ ኦብነግ በታሪኩ ሲታገላቸው የነበሩ በርካታ ዓላማዎች እንዲሳኩ አወንታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በመሆኑም ኦብነግ በሶማሊ ክልል የተገኘውን ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት ሊያናጋ የሚችል ማንኛውንም ድርጊት ወይም ባህሪ በጥብቅ ይቃወማል። እንዲሁም በሰላም ስምምነቱ አማካኝነት የግል ፍላጎታቸውን ማሳካት ያቃታቸው ጥቂት ግለሰቦች አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር የድርጅቱን ስም ያለፈቃድ መጠቀማቸውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋል።
ኦብነግ መሰል ጥረቶች የድርጅቱን መርሆዎች እንደማያንጸባርቁ ወይም የሶማሊ ክልልን እና የሕዝቡን ጥቅም እንደማያገለግሉ ያምናል። ይልቁንም እነዚህ ጥረቶች በክልሉ የተገኘውንና በብዙ ልፋት የመጣውን ሰላምና መረጋጋት ጥርጥር የሌለው አደጋ ላይ የሚጥሉ ሲሆን፣ ከክልሉ ውጪ የሆኑና ከሶማሊ ክልል ሕዝብ ሕጋዊ ምኞት ጋር የሚጋጩ አጀንዳዎችን የሚያራምዱ ናቸው።
በተጨማሪም ኦብነግ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት ለመጣል ዓላማ ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ጥምረት እንዳልመሠረተ ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ግልጽ ማድረግ ይሻል።
በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በኃይል ለማስወገድ መታገል ወይም ብቸኛ ዓላማቸው የመንግሥትን ሥልጣን በትጥቅ መያዝ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር መሳተፍ የኦብነግ ዓላማ ሆኖ አያውቅም። የኦብነግ ተልዕኮ ሁልጊዜም የሶማሊ ክልል ሕዝቦችን መብት፣ ጥቅም እና ምኞት ማስከበር ላይ ያተኮረ ነው። እነዚህን ዓላማዎች በውይይት እና በጋራ ስምምነት መርሆዎች ላይ በመመሥረት፣ በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለማሳካት ቁርጠኛ ሆኖ ይቀጥላል።
ስለሆነም ኦብነግ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በግጭት ውስጥ ከሚሳተፉ የታጠቁ ቡድኖች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት፣ ትብብር ወይም ተሳትፎ እንደሌለው በድጋሚ ያረጋግጣል። ኦብነግ ለሰላማዊ ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን፣ የሶማሊ ክልልን ሰላም፣ መረጋጋት እና የሕዝብ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውንም ድርጊቶች ውድቅ ያደርጋል።
ኦብነግ አክሎም ከድርጅቱ ምንም ዓይነት ውክልና እና ፈቃድ ሳይኖራቸው በተናጠል በሚንቀሳቀሱት የቀድሞው የፓርቲው ሊቀመንበር በአቶ አብዲራህማን ማህዲ አማካኝነት የድርጅቱ ስም ያለአግባብ ጥቅም ላይ መዋሉን ያብራራል። አቶ አብዲራህማን ማህዲ በአሁኑ ወቅት በኦብነግ ፓርቲ ውስጥ ምንም ዓይነት የአመራር ቦታ የሌላቸው ሲሆን፣ ፓርቲውን፣ ፖሊሲዎቹን ወይም ዓላማዎቹን አይወክሉም።
እ.አ.አ በሰኔ 2025 በጅግጅጋ በተካሄደው የኦብነግ ጉባኤ ላይ አቶ አብዲራህማን ማህዲ ከሊቀመንበርነት ኃላፊነታቸው በይፋ የተነሱ ሲሆን፣ አቶ አብዲካሪም ሼክ ሙሴ የኦብነግ ፓርቲ አዲስ ሊቀመንበር ሆነው በሥርዓቱ ተመርጠዋል። በመሆኑም ከዚያ ቀን በኋላ በአቶ አብዲራህማን ማህዲ የተወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች፣ የተላለፉ ውሳኔዎች ወይም የተሰጡ መግለጫዎች የኦብነግ ፓርቲን ይፋዊ አቋም የማይወክሉ በመሆናቸው እንደ ግል አመለካከታቸውና ተግባራቸው ሊቆጠሩ ይገባል።
የኦብነግ ፓርቲ ONLFofficial በሚል የሚታወቀው የኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) አካውንት የፓርቲው ይፋዊ አካውንት እንዳልሆነ መግለጽ ይወዳል። ይህ አካውንት በአቶ አብዲራህማን ማህዲ የሚተዳደር የግል አካውንት ሲሆን፣ በዚህ አካውንት አማካኝነት የሚታተሙ ይዘቶች የኦብነግ ፓርቲን ይፋዊ ፖሊሲዎች፣ አቋሞች ወይም መግለጫዎች አይወክሉም።
ኦብነግ ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች፣ ደጋፊዎች፣ የሚዲያ ድርጅቶች እና የሕዝብ አባላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ስለ ፓርቲው አቋም እንዲሁም እንቅስቃሴዎች መረጃ ለማግኘት በይፋ በተፈቀዱ የአሠራር መስመሮች ላይ ብቻ እንዲደገፉ ያሳስባል።
አብዲካሪም ሼክ ሙሴ
የኦብነግ ሊቀመንበር

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ቡድን በጅግጅጋ ከተማ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ቡድን በጅግጅጋ ከተማ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በአቶ አደም ፋራህ የተመራው ቡድን የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችን እና የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ነው።
ቡድኑ የሶማሌ ክልል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታልን፣ የሶማሌ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን፣ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ህንጻን እና በጅግጅጋ ከተማ የተሰራውን የኮሪደር ልማት ነው የጎበኘው።
የብልፅግና ፓርቲ የብሔራዊ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፓርቲው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም በጅግጅጋ ከተማ መገምገም መጀመሩ ይታወቃል።
በዘመን በየነ

በትግራይ የተከናወነው ፍፁም ህገወጥና እውቅና የሌለው ድርጊት ነው፦ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ
የቀድሞው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል፡፡
ጄኔራሉ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የትግርኛ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በክልሉ በህወሓትና “በአቶ መለስ ዜናዊ ስም ተገን” በማድረግ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ “የራስ አስተዳደር አዋቀርኩ” የሚለውን አካሄድ የተቃወሙት ጄኔራል ሳሞራ፣ ድርጊቱ ፍጹም ሕገ-ወጥና እውቅና የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህ ቡድን በአክሱም ከተማ ተሰብስቦ ያደረገውን ውሳኔ “ሕጋዊነት የጎደለው መንግሥት ምስረታ” ሲሉ የገለጹት ጄኔራሉ፣ መጀመሪያ በአቶ ጌታቸው ረዳ በመቀጠልም በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመሩትን ጊዜያዊ አስተዳደሮች ሥራቸውን እንዳይሠሩና ሕዝቡን ወደ ምርጫ እንዳይወስዱ እንቅፋት ሲፈጠርባቸው መቆየቱንና በመጨረሻም ማኅተምና የአሠራር መሣሪያዎችን በመቀማት የማባረር ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ፖለቲከኞች ዋና ዓላማ ሥልጣን ብቻ መሆኑንና ይህንን ሥልጣን የሚፈልጉት ከተጠያቂነት ለማምለጥ እንደሆነ የገለጹት ጄኔራሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በትዕግሥትና በሰላማዊ መንገድ እየያዘበት ያለውን አካሄድ አድንቀዋል፡፡
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተፈረመበት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ደስታውን የገለጸ ቢሆንም፣ በክልሉ ያሉት ፖለቲከኞች ግን ወደ ሥልጣን ሽሚያ ማምራታቸውን ጄኔራሉ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ስላለው “የወጣቶች አፈሳ” ሲያብራሩም፣ ድርጊቱ ከሻዕቢያን የድሮ የትግል ስትራቴጂ የተቀዳ መሆኑንና ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የማተራመስ ስትራቴጂውን እንዳልቀየረ ገልጸዋል፡፡
ከፌዴራል መንግሥት በጀት እየወሰዱ መንግሥትን “ጠላት” ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን የጠቀሱት ጄኔራል ሳሞራ፣ የክልሉ አመራሮች “ከምርጫ በኋላ መንግሥት ይወጋናል” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለወጣቶች አፈሳ እየተጠቀሙበት እንደሚገኝና በአንጻሩ መንግሥት ጉዳዩን በጦርነት ለመፍታት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
ጄኔራል ሳሞራ ለትግራይ ሕዝብና ለወላጆች ባቀረቡት ጥሪም የወላጆች ስጋት የሆነውን የወጣቶች አፈሳ ለመግታት ወላጆች ተደራጅተው ሊቃወሙትና “ልጆቻችንን አንሰጥም” ብለው ሊታገሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ምርጫ በተካሄደበት በዚህ ወቅት የትግራይ ሕዝብ እንዳይመርጥ መከልከል እንደሌለበትና በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ በመግለጽ የሕዝቡ ዋና ዋስትና እራሱ ሕዝቡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
EBC

የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ የሞት ቅጣት ወሰነ
#fastmereja | የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በሰው ሕይወት ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ሲጠየቁ የቆዩት አቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ የሞት ቅጣት ውሳኔ አሳለፈ።
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት፣ ለዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ የነበረውን የምርመራና የውሳኔ ሂደት በማጠናቀቅ ተከሳሹን በሞት እንዲቀጡ ወስኗል።
ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል ለግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የነበረውን የቅጣት ውሳኔ ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የቀረቡ የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ነጥቦችን ለመመርመር ለዛሬ ቀጠሮ አስተላልፎ ነበር።
በዛሬው የችሎት ውሎ፤ ተከሳሹ ካቀረቧቸው የቅጣት ማቅለያዎች መካከል ሁለቱን ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል።በተመሳሳይ፣ አቃቤ ህግ ካቀረባቸው ልዩ የቅጣት ማክበጃዎች መካከል ሁለቱን ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ የቀረቡትን የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ነጥቦች በአንክሮ በመገምገም፣ በሂደቱ የነበረውን የሞት ቅጣት መነሻ ውሳኔ በማጽናት የመጨረሻ ብይን ሰጥቷል።
የዲላ ማረሚያ ተቋም የተላለፈውን የሞት ቅጣት ውሳኔ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል።

3 months ago
የቻይና አቶሚክ ኃይል ባለስልጣን የኢትዮጵያን የኒውክሊየር ፕሮግራም ለማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
*************
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሳንዶካን ደበበ፣ በኒውክሊየር ዘርፍ ስትራቴጂካዊ ትብብር ዙሪያ ለመምከር የመጡትን በቻይና አቶሚክ ኢነርጂ ባለስልጣን (CAEA) ምክትል ሊቀመንበር ሊ ጂንግ የሚመራ ከፍተኛ የቻይና ልዑካን ቡድን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ይህ ወሳኝ የሁለትዮሽ ምክክር በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ የሰው ኃይል ልማት እና በተቋማዊ አቅም ግንባታ ላይ ሲሆን፤ በዘርፉ ቁልፍ የሆኑ የቴክኒክ ልምዶችን ለመለዋወጥ እንዲሁም የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ስትራቴጂዎችን ለመቅረጽ የሚያስችሉ ሰፊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን የኒውክሊየር ልማት ተነሳሽነት በላቀ እውቀት ወደፊት የሚያራምድ ብቁ የሀገር ውስጥ ባለሙያ ለማፍራት እንዲቻል፤ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እና ለኮሚሽኑ ሰራተኞች ሰፊ የትምህርት ዕድልና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞችን ማመቻቸት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ከእነዚህ የአካዳሚክ እድሎች ባሻገር፣ ስብሰባው የሁለቱን ሀገራት ተቋማዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ሰፊ በር ከፍቷል። በዚህም መሠረት ኮሚሽነር ሳንዶካን እና የቻይናው ልዑካን ቡድን በተለይ በፋይናንሺያል ሞዴሊንግ ልምዶች እና ጠንካራ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት በሚረዱ ስትራቴጂዎች ላይ ዝርዝር ምክክር አድርገዋል።
እነዚህ ምክክሮች ኢትዮጵያ ለጀመረችው የኒውክሊየር ኃይል ዘርፍ ዘላቂ ማዕቀፎችን ለመዘርጋት፣ የቁጥጥር ደረጃዎችን ለማውጣት እና አስተማማኝ የፋይናንስ መንገዶችን ለመቅረጽ ለምታደርገው ብሔራዊ ጥረት እጅግ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ሚና አላቸው።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የቻይና አቶሚክ ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ሊቀመንበር ሊ ጂንግ፣የቻይና ብሔራዊ ኒውክሊየር ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ማ ዌንጁን እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ይህ ግንኙነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ስትራቴጂካዊ ትብብር የሚያንፀባርቅ ሲሆን፤ በአቶሚክ ኃይል ሰላማዊ አጠቃቀም ረገድ ለወደፊት የጋራ ፕሮጀክቶች እና ለዘላቂ የሁለትዮሽ ግንኙነት አዲስና ብሩህ መንገድ የሚከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ የኒውክለር ኃይል ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

“የአዶ ትዝታዎች” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በፕሮፌሰር ታሪክ ወልደሚካኤል እና በአቶ ሙሉጌታ ወልደሚካኤል መጪው ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይመረቃል።
መጽሐፉ፤ የአንድ ቤተሰብን ታሪክ ዋቢ በማድረግ ከጉራጌ ማህበረሰብ ምድር ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የተደረጉ ታሪካዊና ትውልድ ተሻጋሪ የህይወት ጉዞዎችን በስፋት የሚዳስስ ነው። በተለይም ውድ አያት ኑሮን ለማሸነፍ የከፈሉትን ከፍተኛ ተጋድሎ፣ ያጋጠሟቸውን አስገራሚ ክስተቶች በሳቅና በትዝታ ታጅቦ በሚያስነብብ መልኩ እንደተከተበ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ የክቡር አባታችን የአቶ ወልደሚካኤል አንዳግቤ እና የውድ እናታችን የወ/ሮ አስካለ ኃብተማርያም ከጉራጌ ዞን እስከ አዲስ አበባ የዘለቀውን አስደናቂ የህይወት ጉዞ፤ ህይወትን ለመለወጥና ቤተሰብን ለመገንባት ያደረጉትን ተጋድሎ፣ ያፈሩትን ሀብትና ያጋጠሟቸውን ውጣ ውረዶች በግልጽ የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ መጽሐፍ ፈጣሪ የሰጠንን ችሎታና ማስተዋል ለበጎ ነገር ማዋል እንደምንችል የምንማርበት፣ ከየትኛውም ከባድ ውድቀት መነሳት እንደሚቻል የሚያሳይና የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያጸና የታሪክ መዝገብ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከሜክስኮ ወደ መካኒሳ በሚወስደው መንገድ፣ ከሳር ቤት አደባባይ አለፍ ብሎ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቲዎሎጂካል ሴሚናሪ (EGST) አዳራሽ በድምቀት እንደሚካሄድ ታውቋል።
በዚህ ታላቅና ታሪካዊ የምረቃ በዓል ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወዳጅ ዘመዶችና የመጽሐፍ አፍቃሪያን ተገኝተው የደስታው ተካፋይ እንዲሆኑ አዘጋጆቹ በአክብሮት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) አቶ ጌታቸው ረዳ በአፍሪካ ሪፖርት ላይ ላቀረቡት ፅሁፍ ህወሀት መልስ ሰጠ፡፡ ህወሀት ‹‹ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብና እውነትን ለሚፈልጉ ሁሉ›› በሚል ርእስ ዛሬ ባሰራጨው ባለ 6 ገፅ ዘለግ ያለ ፅሁፍ አቶ ጌታቸው ረዳ በአፍሪካን ሪፖርት ላይ ላቀረቡት ፅሁፍ መልስ ሰጥቷል፡፡ በፅሁፉ አቶ ጌታቸው ረዳን ‹‹ስነምግባር የጎደለው፣ ሆነ ብሎ የተሳሳተና ህዝብን የዘለፈ›› በሚል የገለፀው ህወሀት ካነሳቸው ነጥቦች መካከል የጦርነቱን አጀማመር የተመለከተው ይገኝበታል፡፡ አቶ ጌታቸው በመፅሄቱ ላይ ‹ጦርነቱ ሊነሳ የቻለው ህወሀት ክልላዊ ምርጫ ማካሄዱን ተከትሎ ነው›› ብለው የፃፉ ሲሆን ህወሀት በመልሱ ላይ ‹‹ይህ ሞኝነት ብቻ ሳይሆን በስነምግባርም ሆነ በፖለቲካ እጅግ አፀያፊ አገላለፅ ነው›› ብሏል፡፡
ሲያስረዳም በትግራይ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት በፌዴራል መንግስቱ ፖለቲካዊ ሴራ፣ የኢኮኖሚ አፈና፣ ወታደራዊ ከበባ፣ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳና የተቀናጀ የጦርነት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አቶ ጌታቸው ረዳ ሆነ ብለው እንደዘለሉት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም በአቶ ጌታቸው ረዳ ፅሁፍ ህወሀት ጦርነቱ ውስጥ የገባው በተሳሳተ ስሌት መሆኑን መግለፁን ‹‹በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነው›› ያለው ህወሀት ጨምሮም ይህ አስተሳሰብ አደገኛ መሆኑን አስረድቷል፡፡
‹‹ትግራይ ወደገደል አፋፍ እየተወሰደች ነው›› የሚለውን የአቶ ጌታቸው ረዳ ገለፃ ደግሞ ህወሀት ‹‹እንደእውነቱ ከሆነ በትግራይ ውስጥ ያሉ ሰዎች በብዛት የሚናገሩት ተቃራኒውን ነው፡፡ ትግራይ በአብይ አህመድ የተቀየሰውን የፖለቲካ ወጥመድ ለማምለጥ ፖለቲካዊና ስትራቴጂያዊ አማራጮችን እየፈለገች ነው›› ብሎታል፡፡ ህወሀት በማስከተልም ‹‹በአቶ ጌታቸው ረዳ በፅሁፋቸው በመቶ ሺዎች መገደላቸውንና በሚሊዮኖች መፈናቀላቸውን እንዲሁም ትግራይ መውደሟን አምነዋል፡፡ ይሁንና የዚህን ግፍ ዋና አርክቴክ አብይ አህመድን ስም ከመጥቀስ ግን ተቆጥበዋል›› ያለ ሲሆን በፅሁፉ ውስጥ በአብዛኛው ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን መውቀሱን ተቃውሟል፡፡
ረዘም ያሉ ሀተታዎችን የያዘው ይህ የህወሀት ፅሁፍ ‹‹ትግራይ አሁን ጦርነት ሳይሆን አማራጭ በመፈለግ ላይ ናት›› ብሏል፡፡ የአቶ ጌታቸውን ፅሁፍ በአብዛኛው የአብይ አህመድን መንግስት ፍላጎቶችና ስትራቴጂያዊ ስሌቶች የያዘ ነው ሲልም አጣጥሎታል፡፡

በአቶ ሌንጮ ለታ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፍ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ሌንጮ ለታ ትግል ህይወቱ’ በሚል ርዕስ በአቶ ሌንጮ ለታ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተጻፈው መጽሐፍ ተመርቋል።
በዙፋን ኡርጋ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈው ይህ መጽሐፍ የአንጋፋውን ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ የግማሽ ምዕተ ዓመት የፖለቲካ እና የትግል ጉዞን በስፋት የዳሰሰ ነው።
የመጽሐፉ ምረቃ ሥነ ሥርዓት የኦሮሞን ባህል፣ እሴት እና ወግ ጠብቆ የተከናወነ ሲሆን፤ አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች መርሐ ግብሩን መርቀው አስጀምረውታል።
ከዚህም በኋላ በአቶ ሌንጮ ለታ የትግል እና የህይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ደራሲያን፣ አርቲስቶች፣ የአቶ ሌንጮ ለታ የትግል አጋሮች እና ቤተሰቦችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በአዲስ ታምራት

የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲና የፕሮግራም ክርክር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ
#fastmereja I በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጥናት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት፣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ያተኮረ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲና የፕሮግራም ክርክር ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ። በመድረኩ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በልማት ፖሊሲዎች፣ በሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎቶች ዙሪያ የየራሳቸውን አማራጭ ሃሳቦች አቅርበዋል።
በዩኒቨርሲቲው የፕሬዚዳንት ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ወቅት መድረኩ ሙሉ በሙሉ አካዳሚያዊ፣ ገለልተኛና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደሚመራ አረጋግጠዋል። ዜጎች ሉዓላዊ ፍቃዳቸውን ተጠቅመው መፃኢ እድላቸውን የሚወስኑበት ወቅት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስራት፣ ታዳሚው የቀረቡትን ሃሳቦች በሂሳዊ መንገድ እንዲመረምር አሳስበዋል።
የስትራቴጂና ወቅታዊ ጉዳዮች ጥናት ክፍል አስተባባሪ አቶ ሀቢብ ሰይድ በበኩላቸው፣ ዳይሬክቶሬቱ ሀገራዊ ጉዳዮችን በገለልተኝነት የመመርመርና ስትራቴጂካዊ አማራጮችን የማመንጨት ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት "የውይይት ባህል ለሀገር ግንባታ" እና "የውክልና ዲሞክራሲና የምርጫ ስርዓት" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራዊ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በአቶ ጀምበሩ አረጋ አወያይነት በተመራው የፓርቲዎች ክርክር፣ ተወካዮቹ ከታዳሚዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩም መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና የሚዲያ አካላት በተገኙበት በሰላም ተጠናቋል።

በባህር ዳር ከተማ በደቡባዊ የጣና ሐይቅ ዳርቻ የተገነባው እና ዛሬ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመረቀው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ምንምን ይዟል?
#ዘመናዊ እና ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያዎች፣
#የመዝናኛ ሥፍራዎች፣
#ሱቆች ፣
#አምፊ ቴአትር እና መሰል መሠረተ ልማቶችን፣
#እስከ 12 ጀልባዎች የሚያስተናግድ ዘመናዊ ወደብ
#እያንዳንዳቸው 30 ሰው የሚይዙ አምስት ዘመናዊ ጀልባዎች
#በማን ተገነባ? #በአቶ ካሳሁን ምስጋናው (የቤአኢካ ንግድና ኢንቨስትመንት መሥራች)
#ስንት ብር ወጪ ሆነበት? #4 .5 ቢሊዮን ብር
#ግንባታው ምን ያህል ጊዜ ፈጀ? ሁለት ዓመት ከስድስት ወር
#በማን ይተዳደራል? ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ይህን አዲስ ሪዞርት እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን በአንድ ላይ በማስተዳደር የቀጣናውን የሆስፒታሊቲ አገልግሎት ይመራል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት መሠረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት የታለመ ነው።

የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 1፡00 ድረስ በሀዋሳ ሃይል ቁ 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን በሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ፣ በቻይና ዳታ ማይኒግ፣ በፒያሳ ክብሩ ሆቴል፣ሀዋሳ ከተማ በከፊል፣ በሴንትራል ሆቴል፣በአሮጌ የገበያ ማዕከል፣ በሞቢል፣ በአልያንስ ጀርባ፣ በቅዱስ ገብርኤል፣ በጤና ቢሮ፣ በቲቲሲና ሪፈራል ሆስፒታል፣ በመካነ ኢየሱስ፣ በአዲሱ መናህሪያ፣ በታቦር፣ መዘጋጃ፣ በአቶቴ፣ በሎቄ፣ በማረሚያ፣ በችፑድ ፋብሪካ፣ በኢንዱስትሪ ዞን፣ በቱላ፣ በዋጅግራ፣ በኬኔራ፣ በአበሌ፣ በጨፌ፣በሞርቾ፣ በገብረ ክርስቶስ፣ በይርባ፣ በዶሬ እና በሻመና አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል
ስለሆነም የጥገና ሥራው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

4 months ago
ምሉዕ ፋውንዴሽን 'እራት በምክንያት' በሚል ሀሣብ ፕሮግራም ሊያደርግ ነው
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ የሚሠራው ምሉዕ ፋውንዴሽን ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ሜ በሸራተን አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫና 'ራት በምክንያት' በሚል ስያሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ- ግብር ሊያደርግ ነው።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ትዕግሥት ኃይሉ የአለም የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በሚደረገው ልዩ ዝግጅት ትላልቅ ተቋማት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይታደማሉ ስትል በላከችው መግለጫ አስታውቃለች።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የምናከብራት ድምፃዊት ቤቲ ጂ ከስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች ታጅባ ሥራዋን ታቀርባለች።
አብረዋት የሚያጅቡትም የፒያሳ ትሪዬ ባንድ አባላት አንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ዳዊት አደራ ናቸው።
በወግ መፅሐፎቿ የምትታወቀው የሥነ- ፅሑፍ ባለሙያ ህይወት እምሻው ሥራዎቿን የምታቀርብ ሲሆን የመድረኩ አጋፋሪም መቲሸዋዬ ይልማ እንደሆነችም ታውቋል።
ምሉዕ ፋውንዴሽን፣ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ባላቸው ወላጆች በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና በአቶ ክንፈ ፅጌ ተመስርቶ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ነው።
ምሉዕ ፣ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የተቀናጀ ቴራፒ አገልግሎት፣ ተግባር ተኮር ስልጠና፣ የወላጆች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም ሁሉን አካታች ትምህርት ላይ በትኩረት የሚሠራ ፋውንዴሽን ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም በምሉዕ የተቀናጀ የቴራፒ ማዕከል 50 ልጆች የመሠረታዊ ቴራፒ አገልግሎት እንዲሁም እድሜያቸው ከ13-19 ላሉ ታዳጊዎች ደግሞ የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸውን በሥነልቦና እና በተግባር ተኮር ዕውቀት የማብቃት ሥራ እየሰራ ይገኛል፣ ከ300 በላይ የሚሆኑ ልጆች ደግሞ በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሰል ተግባርም ምሉዕ ፋውንዴሽን በስልጠና መርሃግብሩ ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም በትምህረት ቤቶች፣ በሕፃናት ማሳደጊያዎች፣ በሆስፒታሎች እና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ በዕውቀት የተደገፈ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በምሉዕ ቤተ-መጻሕፍት በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገለገሉበት ከ3ሺ 6መቶ በላይ ዘርፈብዙ መጻሕፍት ያሉ ሲሆን ከዚህም ጋር በማያያዝ የቤተ-መጻሕፍት አባልነትን ከአረንጓዴ ልማትና አካባቢን ከማስዋብ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ይህን በጎ አላማ ለማስቀጠል አብራችሁን እንድትቆሙ ሲል ፋውንዴሽኑ በገቢ ማሰባሰብ ሥራው ላይ እንዲሳተፉ፣ ለድርጅቶችም ሆነ በግል ቲኬቶችን ለሚገዙ ጥሪ አቅርቧል።
የዚህ መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባዎች አስተባባሪ ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

በኦቲዝም ጥላ ስር በሚኖሩ ልጆች ላይ የሚሠራው ምሉዕ ፋውንዴሽን ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ሜ በሸራተን አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫና 'ራት በምክንያት' በሚል ስያሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ- ግብር ሊያደርግ ነው።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ትዕግሥት ኃይሉ የአለም የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በሚደረገው ልዩ ዝግጅት ትላልቅ ተቋማት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይታደማሉ ስትል በላከችው መግለጫ አስታውቃለች።
በመርሀ -ግብሩ ላይ የምናከብራት ድምፃዊት ቤቲ ጂ ከስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች ታጅባ ሥራዋን ታቀርባለች።አብረዋት የሚያጅቡትም የፒያሳ ትሪዬ ባንድ አባላት አንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ዳዊት አደራ ናቸው ።በወግ መፅሐፎቿ የምትታወቀው የሥነ- ፅሑፍ ባለሙያ ህይወት እምሻው ሥራዎቿን የምታቀርብ ሲሆን የመድረኩ አጋፋሪም መቲሸዋዬ ይልማ እንደሆነችም ታውቋል።
ምሉዕ ፋውንዴሽን፣ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ባላቸው ወላጆች በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና በአቶ ክንፈ ፅጌ ተመስርቶ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ነው።
ምሉዕ ፣ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት ለሚያስፈልጋቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ የተቀናጀ ቴራፒ አገልግሎት፣ ተግባር ተኮር ስልጠና፣ የወላጆች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሁም ሁሉን አካታች ትምህርት ላይ በትኩረት የሚሠራ ፋውንዴሽን ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም በምሉዕ የተቀናጀ የቴራፒ ማዕከል 50 ልጆች የመሠረታዊ ቴራፒ አገልግሎት እንዲሁም እድሜያቸው ከ13-19 ላሉ ታዳጊዎች ደግሞ የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸውን በሥነልቦና እና በተግባር ተኮር ዕውቀት የማብቃት ሥራ እየሰራ ይገኛል፣ ከ300 በላይ የሚሆኑ ልጆች ደግሞ በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሰል ተግባርም ምሉዕ ፋውንዴሽን በስልጠና መርሃግብሩ ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ለልዩ ፍላጎት ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም በትምህረት ቤቶች፣ በሕፃናት ማሳደጊያዎች፣ በሆስፒታሎች እና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ በዕውቀት የተደገፈ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በምሉዕ ቤተ-መጻሕፍት በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገለገሉበት ከ3ሺ 6መቶ በላይ ዘርፈብዙ መጻሕፍት ያሉ ሲሆን ከዚህም ጋር በማያያዝ የቤተ-መጻሕፍት አባልነትን ከአረንጓዴ ልማትና አካባቢን ከማስዋብ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ይህን በጎ አላማ ለማስቀጠል አብራችሁን እንድትቆሙ ሲል ፋውንዴሽኑ በገቢ ማሰባሰብ ሥራው ላይ እንዲሳተፉ፣ ለድርጅቶችም ሆነ በግል ቲኬቶችን ለሚገዙ ጥሪ አቅርቧል።
የዚህ መርሀ ግብር የሚድያ ዘገባዎች አስተባባሪ ተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
5 months ago
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ ታዬ ደንደአ ላይ ተላልፎ የነበረውን የ7 ዓመት እስራት ወደ 4 ዓመት ዝቅ አደረገ
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ ተላልፎ የነበረውን የ7 ዓመት የጽኑ እስራት ቅጣት ወደ 4 ዓመት ዝቅ ማድረጉን አስታወቀ።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ግለሰቡ ያለፈቃድ የጦር መሣሪያ በመያዝ ወንጀል ተከሰው የቀረበባቸውን የቅጣት ቅነሳ ይግባኝ መርምሮ ሲሆን፤ ለውሳኔውም የተከሳሹን የጤና ሁኔታ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪነትና ቀደም ሲል ለሕዝብ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ ማስገባቱን ገልጿል።
በክስ ሂደቱ ወቅት የታዬ ጠበቆች እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያሉ የመከላከያ ምስክሮች በችሎት ባለመቅረባቸው የተከሳሹ የመከላከያ ምስክር የማሰማት መብት መጣሱን በመጥቀስ ሲከራከሩ ቢቆዩም፣ ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ ባለሥልጣናቱ ያልቀረቡት በሥራ መደራረብ ምክንያት መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።
seledadotio

ለአባታችን አቶ ሲሳይ አማረ አስቸኳይ የህይወት አድን እርዳታ ጥሪ
#ethiopia | አባታችን አቶ ሲሳይ አማረ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ኩላሊቶቻቸው ሥራ በማቆማቸው፣ ባለፉት 8 ወራት በየረር ሆስፒታል በሳምንት ሁለት ቀን የኩላሊት እጥበት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ለአንድ እጥበት ብቻ ከመድኃኒት ውጭ 5,200 ብር እየከፈሉ ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ አሁን ግን በሀገር ውስጥ ያለው ህክምና በቂ ባለመሆኑ በአስቸኳይ ውጭ ሀገር ሄደው መታከም እንዳለባቸው በሐኪሞች ተነግሯቸዋል።
ለአቶ ሲሳይ የውጭ ሀገር ህክምና ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ተጠይቋል። ይህ የገንዘብ መጠን በአቶ ሲሳይና በቤተሰባቸው አቅም የሚሸፈን ባለመሆኑ፣ የሁላችሁንም ደግ ኢትዮጵያውያን እገዛ ይሻሉ።
ሁላችሁም በምትችሉት መጠን በገንዘብም ሆነ በጸሎት ከጎናቸው እንድትቆሙ ቤተሰቦቻቸው በትህትና ይጠይቃሉ።
እርዳታ ለማድረግ የሚከተለውን የባንክ አካውንት መጠቀም ትችላላችሁ፦
የባንክ ስም፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የአካውንት ቁጥር፦ 1000043600738
የአካውንቱ ስም፦ ሲሳይ አማረ አራጋው
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0910563850 ደውላችሁ ቤተሰቦቻቸውን ማነጋገር ትችላላችሁ።
ዛሬ ለአቶ ሲሳይ የምናደርገው እገዛ ለአንድ አባት ህይወት መትረፍ ትልቅ ተስፋ ነው። ለወገን ደራሽ ወገን ነውና አቅማችን የፈቀደውን እናድርግ።
#አቶሲሳይአማረ #ለወገንደራሽ #የህይወትአድንጥሪ #ኢትዮጵያ #እርዳታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ስምረት ፓርቲ በአወዛጋቢ ቦታዎች ላይ የሚካሄድ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን ክስ ለምን አነሳ?
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ "አወዛጋቢ" ቦታዎችን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ በመቃወም ምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበውን ክስ ማንሳቱን አስታውቋል።
ፓርቲው ረቡዕ መጋቢት 2/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ "የሕግ መሠረት በሌለው ሰነድ ላይ ተመሥርቶ ክርክሩን መቀጠል የክቡር ፍርድ ቤቱን ውድ ጊዜ እና የሕዝብን ሀብት ያለአግባብ ማባከን ሆኖ አግኝተነዋል" ብሏል።
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየበት ገለልተኛ እና ሕጋዊ አካሄድ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ያለውን "እምነት የሚያጠናክር" መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ "በአሁኑ ወቅት ክሳችንን መቀጠል አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘነው በፍትሃ ብሔር ሥርዓት ሕግ ቁጥር 278(1) መሠረት ክሳችንን ሙሉ በሙሉ አንስተናል" ሲል ገልጿል።
ስለጉዳዩ ለቢቢሲ ምላሽ የሰጡት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ነጋ አሰፋ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ "አጠቃላይ የፌዴሬሽን ም/ቤቱን ምልዓተ ጉባዔ ሳያሟላ አፈ ጉባዔው ብቻ የወሰኑት ነው" በሚል ክሳቸውን ማንሳታቸውን እና "ጉዳዩ ፖለቲካዊ ውሳኔ ስለሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ" እንደሚፈልጉለት ተናግረዋል።
ቢቢሲ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ምላሽ አላገኝም።
ስምረት ፓርቲ መጀመሪያ ላይ ክሱን ሲያቀርብ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ከሥልጣኑ ውጪ የሆነ እና "ሌላ ግጭት የሚቀሰቅስ፣ በሕገመንግሥት የተሰጠውን ሥልጣን የጣሰ ስለሆነ ትክክል አይደለም" በሚል እንደነበር አብራርተዋል።
አቶ ነጋ ፓርቲው ክሱን መሥርቶ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲታገድ ካደረገ በኋላ "ወደ ማጣራት ስንሄድ ውሳኔውን ምክር ቤቱ አለመወሰኑን ነው ያጣራነው" ብለዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ አካሄድ አለው ያሉት አቶ ነጋ "አባላቱ ተጠርተው፤ ሁሉም ተገኝተው ተወያይተውበት የሚወስኑት፣ ስህተትም ቢሆን ትክክል በምልዓተ ጉባዔ መጽደቅ ነበረበት" ብለዋል።
"አሁን ስናረጋግጥ አፈ ጉባዔው ለብቻቸው የወሰኑት ውሳኔ በመሆኑ እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ ደግሞ የሕግ መሠረት ስለሌለው" በማለት ክሳቸውን ማቋረጣቸውን አስረድረተዋል።
"ይህ ፖለቲካዊ ጉዳይ ነው፤ ከአሁን በኋላ መታየት እና መመለስ ያለበት በፖለቲካዊ መልኩ ነው" በሚል ክሳቸውን ማቋረጣቸውን ጨምረው አስረድተዋል።
ስምረት ፓርቲ መጀመሪያ ውሳኔውን ያሳለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለምን በቀጥታ እንዳልከሰሰ የተጠየቁት አቶ ነጋ፣ የመጀመሪያ ክሳቸው "ምክር ቤቱ ያለ ሥልጣኑ ነው የወሰነው" ብለውን ክስ መመሥረታቸውን አብራርተዋል።
"ክሱ ምርጫ ቦርድ ተሳስተሃል ሳይሆን ውሳኔውን ያቀረበው አካል ፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው።. . . [የምክር ቤቱ] ውሳኔ ስህተት ነው። በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን ሥልጣን ተላልፎ . . . ሌላ ክልል የማዋቀር ሥራ ነው የሠራው እና ያ የሠራው ሥራ ትክክል ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ ይህንን እንዲያግድልን. . . ነበር ክስ ያቀረብነው" ብለዋል።
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ተጠሪ ያላደረጉበት ምክንያት ሲያብራሩ ውሳኔው የወጣው በምርጫ ቦርድ በኩል በመሆኑ እንደሆነ አክለው ተናግረዋል።
"ምርጫ ቦርድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህንን ውሳኔ ሰጥቶኛል ብሎ ስላቀረበ እርሱን ጠይቀናል" ያሉት አቶ ነጋ "ውሳኔውን አሁን ስናጣራ ግን ምክር ቤቱም አልወሰነም" ብለዋል።
አቶ ነጋ በመጀመሪያም ምክር ቤቱ ውስጥ የትግራይ ውክልና የለም ያሉ ሲሆን፣ ውሳኔውንም የወሰነው በሕገ መንግሥት የተሰጠውን ሥልጣን ተጠቅሞ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
ከሥልጣኑ ውጪ ወስኗል ብለን እያሰብን ሳለ አሁን አጣርተን እንዳደረስንበት ምክር ቤቱ ሳይሆን "በግለሰብ ደረጃ" የተወሰነ መሆኑን ነው ብለዋል።
ውሳኔው በግለሰብ ደረጃ ለመወሰን የሕጋዊ መሠረት የለውም ያሉት አቶ ነጋ፣ በጉዳዩ ላይ ጊዜ ማጥፋት እንደማያስፈልግ እና "ይህ ፖለቲካዊ ጉዳይ ስለሆነ በፖለቲካዊ ውሳኔ ነው መመለስ ያለበት ብለን ክሳችንን አንስተናል" ሲሉ አስረድተዋል።
ስምረት ፓርቲ ክሱን ማንሳቱን ተከትሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቶት የነበረው ዕግድ ከተነሳ ምርጫ አወዛጋቢ በሆኑት በአምስቱ የምርጫ ክልሎች ይካሄድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ነጋ "አይካሄድም" ብለዋል።
"ውሳኔው የግለሰብ ውሳኔ ስለሆነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። የሕግ መሠረት ያለው ውሳኔ አይደለም፤ የሕግ መሠረት ያለው ቢሆን በሕግ ተከራክረን እንድናሸንፍ ነበር ሃሳባችን፤ ኋላ ስናየው ግን የሕግ መሠረት የለውም የግለሰብ ውሳኔ ነው።"
ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለሆነ በፖለቲካዊ ንግግር እና ድርድር ጥያቄያቸው ምላሽ እንደዲያገኝ እንደሚያደርጉ የስምረት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ነጋ ተናግረዋል።
ምርጫ ቦርድ ምርጫን የሚያካሄደው "አንድ ሰው በወሰነው ውሳኔ መሠረት ሳይሆን በሕገመንግሥቱ ነው" ያሉት አቶ ነጋ "ሕገ መንግሥቱ ደግሞ እነዚያ ስፍራዎች እስካሁን ባለው የትግራይ ሉዓላዊ ግዛቶች ናቸው" ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በተካሄዱት ስድስት ምርጫዎች በእነዚህ አካባቢዎች ምርጫ የተካሄደው በትግራይ ክልል ውስጥ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ነጋ "አሁን እንደ አዲስ በግለሰብ ደረጃ አዲስ የምርጫ ክልል ማዋቀር ስለማይቻል ወደነበረበት ይመለሳል የሚል እምነት ነው ያለን" ብለዋል።
ስምረት ፓርቲ የእነዚህ አወዛጋቢ የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ሕገመንግሥቱን እና የፕሪቶሪያው ስምምነትን መሠረት በማድረግ "እንወያያለን፣ እንከራከራለን አናስመልሰዋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ እንዲሁም አብንን ጨምሮ ሌሎች አካላት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአከራካሪ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንዲያካሄድ ባሳለፈው ጊዜያዊ ዕግድ ውስጥ ገብቶ ለመከራከር አቤቱታ አቀረበው ነበር።
ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአወዛጋቢ የምርጫ ክልሎች ላይ የሰጠው ውሳኔ የማይስተካከል ከሆነ በምርጫ እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰማቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫም የቦርዱ ውሳኔ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር እና ግጭትን የሚቀሰቅስ ነው በማለት ተቃውሞታል።
በተቃራኒው የአማራ ክልል ፖለቲከኞች የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመደገፍ መግለጫዎች አውጥተዋል።
BBC

Comments