እንኳን ደስ አላችሁ - ከለቡ ገብርኤል የምሥራች ተሠማ
ከ100,000,000.00 - ከአንድ መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ በድል ተጠናቀቀ
የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ለማጠናቀቅ ሰኔ 27 እና 28 በተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በቃል ኪዳን ሰነድ ተሰብስቧል ።
ከ13 ዓመታት በፊት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ወደ ግንባታ የገባው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና መርጡለ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም በውስጡ የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እና ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን የያዘ ነው።
በደብሩ የሚገኘው የቅድስት አርሴማ ሕንጻ ቤተመቅደስ በአቶ ሰማቸው ከበደን እና ቤተሰቦቻቸው ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ቤተክርስቲያኑ ለአገልግሎት መብቃቱን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ አስጠፋኖስ ይርጋ አስተታውሰዋል።
አስተዳዳሪው እዚያው ግቢ ውስጥ ከቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ቀድሞ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ከቅድስት አርሴማ በኋላም እንኳ ማለቅ ያልቻለው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተክርስቲያንን ለማጠናቀቅ ሰኔ 27 እና 28 በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ሕንጻውን ለማጠናቀቅ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና በቃል ኪዳን ሰነድ ተሰብስቦ በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ቸሩ በግላቸው 9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው ፣ በደብሩ አስተዳዳሪ አስተባባሪነት ወልደጊዮርጊስ ተብሎ በጥምቀት ስሙ የተገለጸ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ 10 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለመርጡለ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የክርስትና ቤት ለመሥራት ቃል መግባቱን ገልጸዋል።
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ አስጢፋኖስ በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ አቶ ሰማቸው ከበደን እና ባለቤታቸውን ወ/ሮ ሀናን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትና በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናን ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በተለይም አቶ ስማቸው ከበደ በሆቴላቸው መርሐ ግብሩ በነጻ እንዲከናወን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነጻ አገልግሎት መስጠታቸው እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው ለሌሎች ባለሀብቶችም አርአያነታቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ደብሩ ገቢ የተደረገውን እና በቃል ኪዳን ሰነድ ቃል የተገባውን ገንዘብ በመሰብሰብ በአጭር ጊዜ ቀሪውን የማጠናቀቂያ ሥራ ፈጽሞ ሕንጻ ቤተመቅደሱን ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው በሥራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል ።
የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና መርጡለ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም በ1986 ዓ.ም የተመሠረተ ደብር ነው።
ኹነቱን በበጎ አድራጎት ያስተባበረው ሎዛ ኹነቶች አዘጋጅ መኾኑን የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ተናግረው ለሚዲያዎች፣ ለአገልጋዮች እና ለምእመናን ምስጋናቸውን አቅርበዋል

1 month ago