15 days ago
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ትንሣኤ፤ ከሦስቱ ያመለጡ አብዮቶች ቁጭት እስከ 4ኛውና 5ኛው የዝላይ ጉዞ
#industrialrevolution #aiinstitute #electricvehicles #digitalethiopia #boeing #ebcworld
22 days ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 2032 ከ100 በላይ አውሮፕላኖችን ይረከባል - አቶ መስፍን ጣሰው
******************
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ታሪካዊ በሆኑ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።
አየር መንገዱ ይህንኑ ታላቅ በዓል አስመልክቶ ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባዘጋጀው የአውሮፕላኖች የማይንቀሳቀስ የአየር ትርኢት ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ተቋሙ ባለፉት ስምንት አስርት ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ ቀዳሚና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆኑን ገልጸዋል።
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች በመታገዝ በዓመት 21 ሚሊዮን መንገደኞችን እና ከ850 ሺህ ቶን በላይ ጭነት በማጓጓዝ ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ተቋሙ የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ከ100 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማዘዙን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ይፋ አድርገዋል።
አየር መንገዱ እነዚህን አውሮፕላኖች እስከ 2032 ዓ.ም ድረስ የሚረከብ ሲሆን፣ ይህም የአየር መንገዱን ዘመናዊ የአውሮፕላን ስብስብ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ የአፍሪካ የልህቀት ተምሳሌት እና ለሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ሞተር ነው ብለዋል፡፡
አየር መንገዱ የተመሰረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተመሰረተ ጥቂት ጊዜያት በኋላ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ይህም በየአህጉራቱ የሚገኙ ሰዎችን፣ ባህሎችን እና ኢኮኖሚዎችን በማገናኘት ረገድ ጥልቅ የሆነ የታሪክ ቅርስ እንዲኖረው ማድረጉን አመልክተዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለስምንት አስርት ዓመታት በአፍሪካ እና በዓለም መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ማገልገሉን አንስተው፤ አየር መንገዱ ተሳፋሪዎችን እና ጭነቶችን ብቻ ሳይሆን ተስፋን፣ ዕድልን፣ ኢንቨስትመንትን እና ዲፕሎማሲንም ጭምር ሲያጓጉዝ ቆይቷል ሲሉ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአምስት አህጉራት በሚገኙ 82 አገሮች ውስጥ ከ140 በላይ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ 80ኛው የምስረታ በዓሉን "ሰዎችንና ባህሎችን ማገናኘት" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopianairlines #aviation #boeing #airbus #80yearsofexcellence #ethiopia

1 month ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ጥንካሬ መገለጫ
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሰባ ዓመታት ከተራ የንግድ ተቋምነት ባለፈ፣ የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሚያስፈጽም ቀዳሚ የዲፕሎማሲ መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል።
ተቋሙ በተለይ የኢትዮጵያን "Soft Power" ወይም ለስላሳ ኃይል በዓለም መድረክ ላይ በማገንነን ረገድ ወደር የለውም።
፩. የፓን-አፍሪካኒዝም ክንፍ
(The Wing of Pan-Africanism)
አየር መንገዱ አፍሪካን እርስ በእርስ በማገናኘት የፓን-አፍሪካኒዝም ርዕዮትን በተግባር ቀይሮታል። ብዙ የአህጉሪቱ ሀገራት የራሳቸው አየር መንገድ በሌላቸው ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክፍተቱን በመሙላት የኢትዮጵያን ስልታዊ ተሰሚነት (Strategic Importance) ከፍ አድርጎታል።
ዛሬም ለ"አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና" (AfCFTA) ስኬት ዋነኛው የሎጂስቲክስ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
፪. ሰብዓዊ ዲፕሎማሲ
(Humanitarian Diplomacy)
የኮቪድ-19 ትዝታ
አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በረራ ባቆሙበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሕክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እንደ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ማዕከል ሆኖ አገልግሏል።
የኢቦላ ወረርሽኝ
በ2014 በምዕራብ አፍሪካ ወረርሽኙ በተከሰተ ጊዜ በረራ ባለማቋረጥ 'የችግር ጊዜ አጋር' መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ይህ የሀገራችንን በጎ ገጽታ በዓለም ፊት ገንብቶታል።
፫. አዲስ አበባ፦ "የአፍሪካ ጄኔቫ"
(The Geneva of Africa)
አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት (AU) እና የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መቀመጫ እንድትሆን ካስቻሏት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የአየር መንገዱ ሰፊ መዳረሻ ነው።
መሪዎችና ዲፕሎማቶች በቀላሉ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግ ከተማዋ የአህጉሪቱ ፖለቲካዊ ርዕሰ መዲና ሆና እንድትቀጥል አድርጓል።
፬. የአሜሪካና ቦይንግ ቁርኝት
(The Boeing Factor)
አየር መንገዱ ከአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ ጋር ያለው የረጅም ዘመን ግንኙነት ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያችን እንደ ምሶሶ ይቆጠራል።
ስትራቴጂካዊ አጋርነት
ኢትዮጵያ በአሜሪካ እይታ የዕርዳታ ፈላጊነት ገጽታዋ ተቀይሮ 'ስትራቴጂካዊ የንግድ አጋር' እንድትሆን አድርጓታል።
የፖለቲካ ማለስለሻ
(Lobbying Power)
በሁለቱ ሀገራት መካከል የፖለቲካ አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት እንኳን፣ እንደ ቦይንግ ያሉ ግዙፍ ተቋማት የንግድ ፍላጎት ግንኙነቱ እንዳይላላ እንደ ዋስትና ሆኖ ያገለግላል።
የ737 MAX ቀውስ
አየር መንገዱ አደጋውን ያስተዳደረበት ሙያዊ ብቃት፣ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ማህበረሰብ ዘንድ 'አስተማማኝ አጋር' የሚል የከበረ ስም አሰጥቶታል።
ባጭሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግን መምረጡ የቴክኖሎጂ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ልዩ ስፍራ እንድታገኝ የሚያስችል ብልኅ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መሣሪያ ነው። ይህ ተቋም የሀገራችን ኩራት ብቻ ሳይሆን የዲፕሎማሲያችን ጋሻም ነው።
ለ Getu Tenesgen ( ጌጡ ተመስገን )
ቀመርቲ ጨንገሬ
#ethiopianairlines #diplomacy #boeing #panafricanism #aviation #economy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa #softpower #ethiopia

4 months ago
በኒጀር ጉዳት የደረሰባቸው የአስካይ አውሮፕላኖች ተጠግነው ወደ ስራ ሊመለሱ ነው
#ethiopia | ባለፈው ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በደረሰ ጥቃት ጉዳት አስተናግደው የነበሩት ሁለት የአስካይ (Asky) አየር መንገድ አውሮፕላኖች ጥገና ተደርጎላቸው በቅርቡ በረራ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።
ስለ ጥቃቱና ስለ አውሮፕላኖቹ ሁኔታ ቁልፍ መረጃዎች፡
* የጉዳቱ መጠን፦ ወደ ስፍራው የተላከው የቴክኒክ ቡድን ባደረገው ፍተሻ በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
* የአውሮፕላኑ አይነት፦ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ አውሮፕላኖች ቦይንግ 737 (Boeing 737) ሞዴሎች ናቸው።
* ባለቤትነትና ምዝገባ፦ አውሮፕላኖቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው አስካይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የተከራያቸው ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ስር የተመዘገቡ ናቸው።
አየር መንገዱ አክሎ እንደገለጸው፣ አስፈላጊው የጥገና ስራ ተጠናቆ አውሮፕላኖቹ በቅርቡ መደበኛ የንግድ አገልግሎታቸውን እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianairlines #askyairlines #aviationnews #niamey #ethiopia #niger

መልካም ዜና‼️
ወደ መቀሌ በረራ ተጀመረ‼️
ዛሬ ጠዋት ጥር 26/2018 ዓ.ም አንድ Boeing 737 Max-8 አውሮፕላን ወደ መቀሌ እያመራ እንደሚገኝ ከፍላይት ራዳር ማረጋገጥ ችለናል።
በትግራይ ክልል ከሰሞኑ የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ከባለፈው አርብ ጀምሮ ወደ ትግራይ ሙሉ ለሙሉ በረራ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።
seledadotio

7 months ago
በመጨረሻም Air India የ43 ዓመት እድሜ ያለውን አውሮፕላኑን አገኘ
Air India የ43 አመት እድሜ ያለው አውሮፕላን በዛሬው በኮልኩታ አየር መንገድ አግኝቷል
Boeing 737-200 ኮልኩታ አየር ማረፊያ ለ13 ዓመት ተቀምጦ ባለቤት አልባ ሆኖ ቆይቷል::
The aircraft, በምዝገባ ቁጥር VT-EHH, በ1982 ነበር ተመርቶ ለair india የተላለፈው::
የሀገር ውስጥ በረራ ለረጅም አመታት ሲሰጥ የቆየው ከዛም የካርጎ አገልግሎት ለረጅም አገልግሎት ላይ የነበረው በመጨረሻም በ2012 ምንነቱ ባልታወቅ ምክንያት ነበር በ2012 በኮልኩታ አየር ማረፊያ የቆመው
ከአመታታ ብሃላ አየር ማረፊያ ለair india በፃፈው ደብዳቤ ነበር አውሮፕላን እንዳላቸው ያወቁት
በተደረገ ምርመራ ምንም አይነት የወረቀት ምዝገባ ኢንሹራንስ የባለቤትነት ምዝገባ አልተገኘም ከአሮፕላኑ ላይ የጠፋ የተቀነሰ እቃ በምርመራ የለም
Via tewodros s Girma

Comments