Logo
FBC
በአቶ ሌንጮ ለታ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ሌንጮ ለታ ትግል ህይወቱ’ በሚል ርዕስ በአቶ ሌንጮ ለታ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተጻፈው መጽሐፍ ተመርቋል።

በዙፋን ኡርጋ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈው ይህ መጽሐፍ የአንጋፋውን ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ የግማሽ ምዕተ ዓመት የፖለቲካ እና የትግል ጉዞን በስፋት የዳሰሰ ነው።

የመጽሐፉ ምረቃ ሥነ ሥርዓት የኦሮሞን ባህል፣ እሴት እና ወግ ጠብቆ የተከናወነ ሲሆን፤ አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች መርሐ ግብሩን መርቀው አስጀምረውታል።

ከዚህም በኋላ በአቶ ሌንጮ ለታ የትግል እና የህይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ደራሲያን፣ አርቲስቶች፣ የአቶ ሌንጮ ለታ የትግል አጋሮች እና ቤተሰቦችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በአዲስ ታምራት

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.