2 hours ago
በግብር አመቱ ከተፈቀደላቸው ዘርፎች ውጪ የሂሳብ መዝገብ ሳያቀርቡ በሚቀሩ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት ቅጣት በማድረግ ህጉ ተፈጻሚ እንዲሆን መመሪያ ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በህጉ የተቀመጠውን የሂሳብ መዝገብና መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ወደ ጎን በመተው ገቢያቸውን ለመደበቅ በሚሞክሩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥቷል።
ቢሮው የ2018 የግብር ዘመን የማሳወቂያ ጊዜ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ መመሪያ አውጥቷል።
ቢሮው ባወጣው መመሪያ እንዳስታወቀው፣ የሂሳብ መዝገብ አለመያዝ እንደ አማራጭ ሊወሰድ እንደማይችልና አሰራሩን ጥሰው በሚገኙ ከፋዮች ላይ አስተማሪ የህግና የአስተዳደር ቅጣቶች ይጣላሉ።
እንደ ገቢዎች ቢሮ ማብራሪያ፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 3/ሀ፣ 6 እና አንቀጽ 50/ለ እንዲሁም በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 21፣ 33 እና 82 ድንጋጌዎች መሰረት ማንኛውም የደረጃ «ሀ» እና ደረጃ «ለ» ግብር ከፋይ አመታዊ ጠቅላላ ገቢውን በሰነድና በሂሳብ መዝገብ አስደግፎ የማሳወቅ፣ ሰነዶችን የመያዝ እና ግብር የመክፈል ሙሉ ግዴታ አለበት።
ሆኖም መመሪያው በልዩ ሁኔታ ካካተታቸው የተወሰኑ ዘርፎች ውጪ ሆነው ሰነድ ሳያቀርቡ የሚቀሩ አካላት ድርጊት በቀጥታ «ግብርን ለመሰወር የሚደረግ ድርጊት» ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብሏል።
በመሆኑም ይህንን የህግ ጥሰት በፈጸሙ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት የሚከተሉት ቅጣቶች ተፈፃሚ የሚደረጉ መሆኑም ገልጿል፦
- በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ለደረጃ «ሐ» ግብር ከፋዮች የተቀመጠው የትርፋማነት ህዳግ ለእነዚህ አካላት በእጥፍ አድጎ እንዲሰላ ይደረጋል።
- በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 109 እና 110 ድንጋጌዎች መሰረት፣ ታክሱን ባለማሳወቃቸው ምክንያት በሚፈጠረው የታክስ ጉድለት ላይ 40 በመቶ እንዲሁም በዋናው የታክስ መጠን ላይ 200 በመቶ ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል ይደረጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አክሎ እንዳሳሰበው፣ በዚህ መልኩ በቅጣትና በእጥፍ የትርፍ ህዳግ የሚስተናገዱ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ዝርዝር ፋይልና መረጃ ተደራጅቶ ለህግ ተገዥነት ዘርፍ እንዲተላለፍ ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እና አልባሳት ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
አረጋዊ ገ/ህይወት እና ካሳ ተክሌ የተባሉት ተጠርጣሪዎ ች የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ውሀ ልማት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ነው።
ካሳ ተክሌ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ልጅ ት/ቤት የሚያደርስ ሲሆን ት/ቤት ካደረሳት በኋላ የስጋ ዘመዷ ከሆነው አረጋዊ ገብረህይወት ከተባለው አባሪው ጋር በመደዋወል ወንጀሉን ለመፈጸም ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
የግል ተበዳይ ስራ ቦታ መሆኗን ደውለው ካረጋገጡ በኋላ የመኖሪያ ቤቷን መኝታ ቤት መስኮት ገንጥለው ወደ ውስጥ በመግባት 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት 3 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ የዋጋ ግምታቸው 1ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የሚገመቱ ከውጪ የመጡ የተለያዩ የወንድ ጃኬቶች በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ሰርቀው መሰወራቸውን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአድዋ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ጠቁሟል።
የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቁ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ቶፊክ መደድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ አማካኝነት አስቸኳይ ክትትል እና ምርመራ እንዲደረግ ስምሪት ሰጥተዋል።
በመሆኑም የዋና ጠቅላይ መምሪያው የየካ ክ/ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ እና የአድዋ ፖሊስ መምሪያ የክትትል እና የምርመራ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት/INSA የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአፋር ክልል የሚሌ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና የተሰረቀውን ንብረት ለማስ መለስ እልህ አስጨራሽ ርብርብ አድርገዋል።
በተደረገው እልህ አስጨራሽ ማፈላለግ ተጠርጣሪዎች ከላም በረት መናኸሪያ በመሳፈር በአፋር ክልል አድርገው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በአፋር ክልል ሚሌ ከሚባለው ኬላ ላይ በክልሉ ፖሊስ እና በተቀናጀው የጸጥታ ግብረ ኃይል ፍተሻ ከነ ኤግዚቢቱ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

5 hours ago
የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ የሽግግር ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውስጥ ቀደምትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሀገራችን የውጭ ፖሊሲ ከውስጣዊ ደኅንነትና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ውስንነቶች ነበሩበት።
በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የውጭ ፖሊሲው በዋናነት የምዕራባውያንን ድጋፍ በማጠናከርና ሉዓላዊነትን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን ደግሞ የሶቭየት ኅብረትን የርዕዮተ-ዓለም ካምፕ በመከተል በደኅንነትና የወታደራዊ ትስስር ላይ ያተኮረ አካሄድን ይከተል ነበር።
ከ1983 ዓ.ም በኋላ የወጣው ፖሊሲ ደግሞ ድህነትን መዋጋትን ዋና መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲንና የጎረቤቶች ሰላምን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መለወጥ፣ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር መጨመር እና የሀገር ውስጥና የአካባቢው ለውጦች ፖሊሲውን ማሻሻልና ማሳደግ አስፈላጊ አድርገውታል።
በቅርብ ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ተቀባይነት ፍለጋ በመውጣት፣ በክልላዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ንቁ አጀንዳ ሰጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዲፕሎማሲያዊ ሚና ወደ መጫወት ተሸጋግሯል።
ዓለም ከአንድ ወገን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን መሸጋገሯ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎቿን እንድታሰፋና የፖሊሲ አማራጮቿን እንድታበዛ ያስገደዳት ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የኃይል ሽያጭን ጨምሮ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ አቀራረብ ተከትላለች።
በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከነበራት በተወሰኑ ምዕራባውያን ወይም ታላላቅ ኃይሎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት በመውጣት፣ ከሁሉም ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ተግባራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ጀምራለች።
የዚህ የውጭ ፖሊሲ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሀገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ድምጿ እንዲሰማ፣ ከአስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤቶች እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚልና ሩሲያ ጋር ያላትን ትስስር እንድታጠናክርና አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ በር ከፍቷል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ የንጹሕ ኃይል አቅርቦት ማዕከል ያደረጋት ሲሆን፣ ለሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከሩ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አሳድጎታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የተመጣጠነና የብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በመከተል በታላላቅ ኃይሎች ፉክክር ውስጥ ገለልተኝነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት፣ የኢኮኖሚና የኃይል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በቀጣናው የሚደረጉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴዎችም ብሔራዊ ጥቅሟን ከቀጣናዊ ትስስር እና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር አጣጥማ በመጓዝ የጀመረችውን የአጀንዳ ሰጭነት ሚና አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሏት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopianforeignpolicy #brics #gerd #የመደመርመንግሥት

6 hours ago
#adigrat 📍
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ ዓዲግራት ከተማ መግባታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ወደ ከተማዋ ሲገቡ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንደተቀበላቸው ተናግረዋል።
ከኤርትራ ድንበር 35 ኪ/ሜ የምትርቀው ከተማዋ ላለፉት ቀናት ያለአንዳች የጥበቃ ኃይል ነው የቆየችው።
በተመሳሳይ ሁኔታ እንዳስላሰ ሽረ ከተማ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደገባቸው ታውቋል።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ (ዓዲግራት)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #adigrat 📍 ዓዲግራት ከተማ ዛሬም የሚጠብቃት ኃይል ሳይኖር ውላለች። ነዋሪዎች በየሰፈሩ ተደራጅተው አካባቢያቸውን ከዘራፊዎች እየጠበቁ ይገኛሉ። የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ዛሬ ቀን እንዲሁም አሁን በዚህ ሰዓት (በለሊት) " ተቋማችንን አናስደፍርም " በማለት ከዝርፊያ እየጠበቁ ይገኛሉ። ከሀገር መከላከያ ጋር የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ሰለም ኃይል ወደ ዓዲግራት መቃረቡንና ከተማዋ በከበባ ውስጥ…

Sponsored by
Surafel
16 hours ago
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !
8:30 አርሰናል ከ ሊድስ ዩናይትድ
9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ነገሌ አርሲ
10:00 ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ
11:00 አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ
11:00 ቼልሲ ከ በርንማውዝ
1:00 ኢንተር ሚላን ከ ፓርማ
1:30 ማንችስር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም
1:30 ባርሴሎና ከ ሄታፌ
4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል
@tikvahethsport kidusyoftahe
8:30 አርሰናል ከ ሊድስ ዩናይትድ
9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ነገሌ አርሲ
10:00 ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ
11:00 አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ
11:00 ቼልሲ ከ በርንማውዝ
1:00 ኢንተር ሚላን ከ ፓርማ
1:30 ማንችስር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም
1:30 ባርሴሎና ከ ሄታፌ
4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል
@tikvahethsport kidusyoftahe
17 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤል ወታደራዊ ኃይሎች በደቡባዊ ሶሪያ ቁኔይትራ ገጠር በምትገኘው ራስም አል-ሃይዳራህ መንደር ውስጥ ድንገተኛ ፍተሻ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማካሄዳቸውን የሶሪያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
እንደ ዘገባው መረጃ ከሆነ ይህ እንቅስቃሴ የተካሄደው ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በቁኔይትራ ግዛት በሚገኙ በርካታ መንደሮች ውስጥ በተደጋጋሚ ሲደረጉ በቆዩ ወታደራዊ ቅኝቶች፣ የቤት ለቤት ፍተሻዎች እና የእስር እርምጃዎች መቀጠል ሳቢያ ነው።
በአካባቢው ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ክስተቱ በሶሪያ ደቡባዊ ድንበር አቅራቢያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገው ተዘግቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውስጥ በተደረገ አዲስ ሹመት ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ (Delivery Monitoring Unit) ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ይህ አዲሱ ሹመት መንግስት የጀመራቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች እና ቁልፍ አገራዊ የልማት ውጥኖችን አፈጻጸም በቅርበት ለመከታተልና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ አሰራር በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ ዘመናዊ መንግስታት መዋቅር ውስጥ የተለመደና በስፋት የሚተገበር ነው። የጽንሰ-ሀሳቡ ጀማሪ በ2001 (እ.ኤ.አ) የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ሲሆኑ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቃል የገቡትን ሥራ በተግባር መፈጸማቸውን የሚከታተልና ሪፖርት የሚያደርግ ገለልተኛ አካል በማቋቋም አሰራሩን ወደ ትግበራ አምጥተውታል። ይህንኑ ልምድ በመከተል ማሌዥያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ እንዲሁም በአፍሪካ እንደ ኬንያ እና ሴኔጋል ያሉ ሀገራት የመንግስትን ስራ አፈጻጸም ለማፋጠን ተመሳሳይ ቢሮዎችን በፕሬዝዳንቱ ወይም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ስር አቋቁመው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
የዚህ ዘርፍ ዋና ዓላማ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ወደ ተግባር መቀየር ሲሆን፣ የኃላፊው ዋነኛ ተግባርም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስፈጻሚ ክንድ በመሆን መስራት ነው። በዚህም መሰረት ዲያቆን ዳንኤል መንግስት በግብርና፣ ጤና፣ መሰረተ ልማት እና ሌሎችም ዘርፎች ቅድሚያ የሰጣቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ እና በጀት እየተከናወኑ መሆናቸውን በቅርበት ይከታተላሉ። በተጨማሪም በፕሮጀክቶች ላይ የቢሮክራሲ መጓተት ሲያጋጥም ወይም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የሥራ መደራረብና አለመግባባት ሲፈጠር በፍጥነት ጣልቃ በመግባት ማነቆዎችን የመፍታት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ከዚህ አኳያ የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን እና የተቋማትን አፈጻጸም በመረጃ እና በስታቲስቲክስ እየለካ ትክክለኛውን የመሬት ላይ እውነታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያደርጋል። በአጠቃላይ ይህ ሹመት የተቋማት ኃላፊዎች በወረቀት ላይ ካለው እቅድ ባለፈ ለህዝቡ የሚዳሰስ ውጤት እንዲያመጡ ግፊት የሚያደርግና ሚኒስትሮች የተሰጣቸውን የቤት ስራ ያለምንም ማመካኘት በተግባር ማቅረባቸውን የሚቆጣጠር ቁልፍ የሥራ መደብ ነው።

18 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ይፋ የተደረገው የ2026ቱ የዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውር ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ የሰዎችን ዝውውር ለማስቆም የተቀመጡትን አነስተኛ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ባታሟላም፣ ጉልህ ጥረቶችን በማሳየቷ በደረጃ ሁለት (Tier 2) ላይ መቆየቷን አስታውቋል። መንግስት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን በመለየት፣ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅን በማሻሻል እና ተጎጂዎችን ወደ ሀገር በመመለስ ረገድ መሻሻሎችን ቢያሳይም፣ በህግ ማስከበር እና ወንጀለኞችን በመቅጣት በኩል ግን ክፍተቶች እንደታዩበት ሪፖርቱ አብራርቷል።
ሪፖርቱ በህግ ማስከበር ዘርፍ ያለውን ሁኔታ ሲገመግም፣ የኢትዮጵያ መንግስት በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚያደርገው ምርመራ እና ክስ መቀነሱን አመላክቷል። በ2025 ዓ.ም የተመዘገቡት የምርመራዎች ቁጥር 363 ሲሆን፣ ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት 470 ምርመራዎች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ አሳይቷል። በተመሳሳይ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ አዘዋዋሪዎች ቁጥር ከ340 ወደ 191 ዝቅ ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሙስና እና የባለስልጣናት ተባባሪነት ትልቅ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች ሰራተኞች ዜግነት ለሌላቸው ግለሰቦች ህገ-ወጥ ፓስፖርት በመስጠት ለህገ-ወጥ ዝውውር መጋለጥ ምክንያት ሆነው በመገኘታቸው፣ በምክትል ዳይሬክተሩ ላይ የስምንት ዓመት እስራት እና በሌሎችም ላይ ተመሳሳይ ቅጣቶች መተላለፉን አስታውሷል።
በሌላ በኩል ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ እና የህጻናት ምልመላ አሳሳቢ መረጃን አካቷል። ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ እንዳሰፈረው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ እንዲሁም እንደ ፋኖ፣ ሕወሓት (TPLF) እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ህጻናትን ከህግ ውጪ ለውትድርና እና ለተለያዩ የጦርነት ደጀን ተግባራት መጠቀማቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዚህ ዙሪያ የተወሰኑ ምርመራዎችን ቢያደርግም፣ መንግስት ወንጀለኞቹን በህግ ስለመጠየቁ ሪፖርት አላደረገም ብሏል።
በበጎ ጎኑ መንግስት የተጎጂዎችን ጥበቃ እና መከላከል ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉ ተነስቷል። ባለፈው ዓመት ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተመለሱ ከ142 ሺህ በላይ ተጋላጭ ዜጎችን አጣርቶ ድጋፍ አድርጓል። የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ስርዓት ለማስያዝም አዲስ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1389/2025) በማጽደቅ፣ ኤጀንሲዎች እንደየደረጃቸው ከ50 ሚሊዮን እስከ 250 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የመጠባበቂያ ገንዘብ እንዲያስቀምጡ አድርጓል። ይህ እርምጃ ሰራተኞች የህክምና እና ሌሎች ወጪዎችን ኤጀንሲዎች እንዲሸፍኑ በማድረግ ዜጎች ያለአግባብ እንዳይበዘበዙ ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ሪፖርቱ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አዳዲስ አዝማሚያዎችን የዳሰሰ ሲሆን፣ አዘዋዋሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን እና የውሸት የስራ እድሎችን በመጠቀም ወጣቶችን እያታለሉ መሆኑን አጋልጧል። በተለይም ኢትዮጵያውያን ወንዶች በደቡብ ምስራቅ እስያ (እንደ በርማ፣ ካምቦዲያ እና ላኦስ) በሚገኙ የበይነመረብ (ኦንላይን) ማጭበርበር ስራዎች ላይ በግዳጅ እንዲሰሩ እየተደረጉ መሆኑን፤ እንዲሁም ወጣት ሴቶች ወደ ሩሲያ የድሮን ማምረቻ ጣቢያዎች በተታለለ የስልጠና ስምሪት ተወስደው ብዝበዛ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ሪፖርቱ በስፋት ዘግቧል። በአገር ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ተፈናቃዮች እና ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ለዚህ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸውንም አክሎ አስጠንቅቋል።

19 hours ago
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች
በስፔን ላሊጋ
ማላጋ 1-1 ኤስፓኞል
በጀርመን ቡንደስሊጋ
ዶርትሙንድ 2-2 ወርደር ብሬመን
በፈረንሳይ ሊግ 1
ሌንስ 2-1 ሊዮን
በሳውዲ ፕሮ ሊግ
አል-ናስር 3-0 ድሪያህ
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 0-1 አዳማ ከተማ
ሀላባ ከተማ 1-1 ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ማላጋ 1-1 ኤስፓኞል
ዶርትሙንድ 2-2 ወርደር ብሬመን
ሌንስ 2-1 ሊዮን
አል-ናስር 3-0 ድሪያህ
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 0-1 አዳማ ከተማ
ሀላባ ከተማ 1-1 ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
24 hours ago
አል ነስር ድል አድርጓል !
በሳውዲ አረቢያ ሊግ አል ነስር አል ዲሪያህን 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የአል ነስርን የማሸነፊያ ግብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሳሙ እና ኪንግስሌይ ኮማን ማስቆጠር ችለዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 980 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
አል ነስር በሊጉ የሰበሰባቸውን ነጥቦች አስራ ዘጠኝ በማድረስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በቀጣይ መርሐ ግብር አል ነስር ከአል አህሊ ጋር ይጫወታል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
በሳውዲ አረቢያ ሊግ አል ነስር አል ዲሪያህን 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የአል ነስርን የማሸነፊያ ግብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሳሙ እና ኪንግስሌይ ኮማን ማስቆጠር ችለዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 980 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
አል ነስር በሊጉ የሰበሰባቸውን ነጥቦች አስራ ዘጠኝ በማድረስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በቀጣይ መርሐ ግብር አል ነስር ከአል አህሊ ጋር ይጫወታል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
Sponsored by
Surafel
1 day ago
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ አንዱ አንዱን "የጥቃት ጦርነት" ጀምሮብኛል ሲሉ መወነጃጀል ጀመሩ።
-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ሰላምና ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ለነዋሪዎች በድምፅ ማጉያ ጥሪ ማቅረባቸዉ ተሰማ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ፤ መቀሌ ከተማ የሚያደርገዉን በረራ ጥቅምት 1 እንደሚጀምር ተመልክቷል።
-አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ አህጉራዊ እና ዓለማቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለመፍታት እና ተጨማሪ ጭካኔ የተሞላባቸው ወንጀሎችን ለመከላከል አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን ጠየቁ።
-የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ፤ኢህአፓ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩ እና «መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም» ብለው የቀሩ እስረኛ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ሰዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ላይ «ከፍተኛ ግፍ፣ ጫና እና እንግልት» እየደረሰ ነዉ ሲል አሳሰበ።
-ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ።
Via:- ዶቼቬሌ
@Yenetube Fikerassefa

የአል ናስር ደጋፊዎች ለሮናልዶ ድጋፍ አሳይተዋል !
ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአል ነስር ደጋፊዎች ከፍተኛ ድጋፍ ተሰጥቶታል።
ደጋፊዎቹ በብሔራዊ ቡድኑ የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
በሰባተኛው ደቂቃ ላይ የክለቡ ደጋፊዎች ትልቅ ባነር በማሳየት የሮናልዶን ስም እየጠሩ ድጋፍ ሲያሳዩ ታይተዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው ግብ ያስቆጠረ ሲሆን አል ናስር አል ዲሪያህን 2ለ0 እየመራ ይገኛል።
ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 980 ማድረስ ችሏል።
@tikvahethsport kidusyoftahe አል ነስር ለሮናልዶ ድጋፍ ያሳያል ! የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር በዛሬው ጨዋታ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድጋፍ ለማሳየት ማቀዱ ተነግሯል። አል ነስር ለክርስቲያኖ ሮናልዶ በስታዲየሙ ውስጥ የድጋፍ ባነር ለማሳየት ማቀዱ ተገልጿል። በተጨማሪም በስታዲየሙ ለደጋፊው ለሮናልዶ ድጋፍ የሚያሳዩ ወረቀቶች እንደሚሰራጩ ተዘግቧል። አል ነስር ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ከአል ዲሪያህ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። …

ንብ ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን "ንብተራ ደረሰኝ "የተሰኘ ዘመናዊ የክፍያና የዲጂታል ደረሰኝ አገልግሎት አስጀመረ
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፕራይም ኦል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን ሁሉን በአንድ የያዘ "ንብተራ ደረሰኝ " የተሰኘ የዲጂታል ስርዓትን መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አስጀምሯል ።
በዚህ ወቅትም የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ባንኩ ያስጀመረዉ ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ነጋዴዎች ፣በገቢዎች ሚኒስቴር ዕዉቅና የተሰጠዉን የፕራይም ኦል ትሬዲንግ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እና የድርጅት ሀብት አስተዳደር ስርዓትን ከንብተራ ኦንላይን ጋር በማቀናጀት በአንድ ስማርት ፓስ አማካኝነት የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እንዲያወጡ ፣የክፍያ እና የንግድ ስርዓታቸዉን እንዲያዘምኑ ያስችላቸዋል ማለታቸዉ ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
"ንብተራ ደረሰኝ "ነጋዴዎች ለደንበኞቻቸዉ ጊዜ ያለፈባቸዉንና እርስ በእርስ የማይገናኙ ባህላዊ የሽያጭ መመዝገቢያ ካሽ ሬጂስተሮችን በአንድ እጅ ብቻ በሚያዝ ዘመናዊ ስማርት ፖስ በመተካት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላቸዋል ተብሏል ።
የፕራይም ኦል ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዉብሸት አዝመራዉ እንደተናገሩት ይህ አዲስ የክፍያ ስርዓት ነጋዴዎች የተነጣጠሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲሰጡት የነበረዉን ኃላቀር አገልግሎት ያስቀራል ብለዋል ። በንግዱ ዘርፍ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩትንም የአሠራር ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያግዝ ተገልጿል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል

አል ነስር ለሮናልዶ ድጋፍ ያሳያል !
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር በዛሬው ጨዋታ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድጋፍ ለማሳየት ማቀዱ ተነግሯል።
አል ነስር ለክርስቲያኖ ሮናልዶ በስታዲየሙ ውስጥ የድጋፍ ባነር ለማሳየት ማቀዱ ተገልጿል።
በተጨማሪም በስታዲየሙ ለደጋፊው ለሮናልዶ ድጋፍ የሚያሳዩ ወረቀቶች እንደሚሰራጩ ተዘግቧል።
አል ነስር ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ከአል ዲሪያህ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

ሎተሪ ደርሶናል በማለት የማታለል ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ተያዙ
አርሴማ ማስረሻ፣ ታደሰ ነሪ እና ዮሴፍ ተሾመ የተባሉት ተጠርጣሪዎች የማታለል ወንጀሉን ፈፅመው በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቤቴል አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት ቪቲዝ መኪና በመንቀሳቀስ የግል ተበዳይ የቀበሌ መታወቂያ ለማሳደስ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በሚሄዱበት አጋጣሚ ያገኟቸዋል።
ታደሰ ነሪ የተባለው ግለሰብ ቤትና መኪና የሚያስገኝ ሎተሪ ቢደርሰውም በቅርቡ ከክፍለ ሃገር ስለመጣ መታወቂያ እንደሌለውና ጉዳዩን ለማስጨረስ የግል ተበዳይን እርዳታ እንደሚፈልግ በመናገር አታለው መኪና ውስጥ ያስገቧቸዋል።
ግለሰቦቹ ለ3 ሠዓታት ያህል የግል ተበዳይን በተለያዩ ቦታዎች ሲያዞሯቸውና ሲያንገላቷቸው ከቆዩ በኃላ የተለያዩ የማሳመኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጉዳዩ ማስጨረሻ በሚል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና እናት ባንክ 100 ሺህ ብር አውጥተው ይሰጧቸዋል።
በተጨማሪም ቤቴል ወረዳ 6 አካባቢ ከሚገኝ የአንድ ግለሰብ ህንፃ አጠገብ ሲደርሱ ፣ የወርቅ ጌጣጌጥና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይቻል፤ በመግለፅ እስከሚመጡ ድረስ የግል ተበዳይ ንብረት በእነሱ እጅ እንዲቆይ ያደርጋሉ።
የግል ተበዳይም 220 ሺህ ብር የሚያወጣ 11 ግራም የአንገት ሃብልና የጆሮ ጌጥ ወርቅ እንዲሁም 17 ሺህ ብር የሚገመት ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ በአጠቃላይ 337 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ለተጠርጣሪዎቹ አስረክበው ቤትና መኪና የደረሰን ሎተሪ በሚል በትንሽ ካኪ ወረቀት ውስጥ የታሸገ 75 ሺህ ብር የሚል ፅሁፍ ያለው የተፋቀ የፈጣን ሎተሪ ወረቀት ሰጥተዋቸው ከመኪናው እንዲወርዱ ካደረጉ በኃላ የግል ተበዳይን ንብረት ይዘው ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ ተይዘዋል ።

ቤትና መኪና የሚያስገኝ ሎተሪ ደርሶናል በማለት የማታለል ወንጀል የፈፀሙ 3 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ተያዙ።
አርሴማ ማስረሻ፣ ታደሰ ነሪ እና ዮሴፍ ተሾመ የተባሉት ተጠርጣሪዎች የማታለል ወንጀሉን ፈፅመው በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቤቴል አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ለመፈፀም አስበው በተከራዩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ3A-73299 አ.አ የሆነ ቪቲዝ መኪና እየተንቀሳቀሱ እያለ የግል ተበዳይ የቀበሌ መታወቂያ ለማሳደስ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በሚሄዱበት አጋጣሚ ያገኟቸዋል።
ከሦስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል ታደሰ ነሪ የተባለው ግለሰብ ቤትና መኪና የሚያስገኝ ሎተሪ ቢደርሰውም በቅርቡ ከክፍለ ሃገር ስለመጣ የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ እንደሌለውና ጉዳዩን ለማስጨረስ የግል ተበዳይን እርዳታ እንደሚፈልግ በመናገር አታለው መኪና ውስጥ ያስገቧቸዋል።
ግለሰቦቹ ለ3 ሠዓታት ያህል የግል ተበዳይን በተለያዩ ቦታዎች ሲያዞሯቸውና ሲያንገላቷቸው ከቆዩ በኃላ የተለያዩ የማሳመኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጉዳዩ ማስጨረሻ በሚል ማታለያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና እናት ባንክ 100 ሺህ ብር አውጥተው ለተጠርጣሪዎቹ ይሰጧቸዋል።
በዚህ የማታለል ወንጀል ያላበቃው የተጠርጣሪዎቹ ተግባር ቤቴል ወረዳ 6 አካባቢ ከሚገኝ የአንድ ግለሰብ ህንፃ አጠገብ ሲደርሱ በሎተሪ የደረሳቸውን ቤትና መኪና መውሰድ የሚችሉት በዚህ ህንፃ ቢሮ ውስጥ መሆኑንና ገብተው እንዲያስጨርሱላቸው ካሳመኗቸው በኃላ ቢሮ ውስጥ ሲገቡ የወርቅ ጌጣጌጥና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይቻል፤ ጉዳዩን አስጨርሰው እስከሚመጡ ድረስ የግል ተበዳይ ንብረት በእነሱ እጅ እንዲቆይ ያደርጋሉ።
የግል ተበዳይም 220 ሺህ ብር የሚያወጣ 11 ግራም የአንገት ሃብልና የጆሮ ጌጥ ወርቅ እንዲሁም 17 ሺህ ብር የሚገመት ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ በአጠቃላይ 337 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ለተጠርጣሪዎቹ አስረክበው ቤትና መኪና የደረሰን ሎተሪ በሚል በትንሽ ካኪ ወረቀት ውስጥ የታሸገ 75 ሺህ ብር የሚል ፅሁፍ ያለው የተፋቀ የፈጣን ሎተሪ ወረቀት ሰጥተዋቸው ከመኪናው እንዲወርዱ ካደረጉ በኃላ የግል ተበዳይን ንብረት ይዘው ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የቤቴል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም ሴት ተጠርጣሪዋ የማታለል ወንጀሉን ለመፈፀም በአርቴፊሻል ፀጉር እራሷን እንደምትቀያይር የግል ተበዳይ የሰጡት ቃልና የምርመራ መዝገቡ እንደሚያስረዳ ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።
ወንጀል ፈፃሚዎች የተለያዩ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀምና የሰዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል መሰል ወንጀል ሊፈፅሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለፖሊስ ማሳወቅ ተገቢ መሆኑን በመልዕክቱ አስተላልፏል።

ዩጋንዳ ዜጎቿ በኬንያ የመራጮች ምዝገባ ላይ እንዳይሳተፉ አገደች
ዩጋንዳ እ.ኤ.አ በ2027 በሚካሄደው የኬንያ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጎረቤት ሀገር የሚሻገሩ ዜጎቿ እንዲታገዱ እና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለጸጥታ አካላት ትእዛዝ አስተላልፋለች።
የዩጋንዳ የመጀመሪያዋ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቤካ ካዳጋ እንደገለጹት የዩጋንዳ ዜጎች በሌላ ሀገር የምርጫ ሂደት ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው ገልጸው በበርካታ የድንበር አካባቢዎች የሚገኙ ባለስልጣናት ወደ ኬንያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት እንዲከታተሉ አዟቸዋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አንዳንድ የዩጋንዳ ዜጎች የኬንያ መታወቂያ ሰነዶችን በማውጣት በመራጭነት እየተመዘገቡ ነው የሚሉ ዘገባዎችን ተከተሎ ነው። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ የተቀናጀ ሕገ-ወጥ የምዝገባ ቅስቀሳ መኖሩን የሚያረጋግጥ ታማኝ የሆነ ማስረጃ እንዳልደረሰው አስታውቋል።
ዩጋንዳ የኬንያን ሉዓላዊነት የምታከብር እና ተመሳሳይ ምላሽ እንደምትጠብቅ የገለጸች ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በጸጥታ እና በዲፕሎማሲያዊ መስመሮች በኩል በቀረቡት ክሶች ላይ ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።
ሰላማዊ ነጋሲ

በ5 ዓመት ህፃን ላይ የጉልበት ብዝበዛና ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
በሸኮ ከተማ አስተዳደር 01 ቀጠና የጉልበት ብዝበዛና አካላዊ ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሏን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታውቋል
የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እንዳስታወቁት በ5 ዓመቷ ህፃን ሳራ ዘማች ላይ ብዝበዛና አካላዊ ጉዳት አድርሳለች ተብላ የተጠረጠረችው ግለሰብ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውላለች።
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በህፃኗ ላይ አካላዊ ጉዳት አድርሳለች ተብላ የተጠረጠረችው ግለሰብ በፈፀመችው ድርጊት ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።በጉዳዩ ላይ ፖሊስ ምንም ዓይነት እርምጃ አልወሰደም በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውንም ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ምርመራውን እያካሄደ መሆኑንም ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም

የምክር ቤት አባላት የዜጎችን ድምፅ በማስተጋባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለፁ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የምክር ቤት አባላት የወከሉትን ማህበረሰብ ችግርና ፍላጎት በማዳመጥ፣ የዜጎችን ድምፅ በምክር ቤት ማስተጋባትና የሚወሰኑ ፖሊሲዎች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ መስራት ይገባቸዋል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናግረዋል ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዘላለም በቀለ የምክር ቤት አባላት የሚወክሉትን ማህበረሰብ ችግርና ፍላጎት በመለየት፣ ለመንግስት በማሳወቅና በውሳኔ ሰጪ መድረኮች የህዝቡ ድምፅ እንዲሰማ በማድረግ ተገቢውን ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል ።
በማህበረሰቡ የሚነሱ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና ተጨባጭ መፍትሄ እንዲያገኙ የመከታተል ሚና እንዳላቸውም ገልጸዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በረኸተስፋ ዜጎች በኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚወጡ ፖሊሲዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ መደረጋቸው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የዜጎች ተጠቃሚነት ከሰላም ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመው የምክር ቤት አባላት ለሀገር ሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
ሙስና የሀገር የኢኮኖሚ ላይ ሙስና ያለውን ተፅዕኖ የገለፁት ባለሙያው ሙስናን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ስርዓቶችን መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የምክር ቤት አባላት የወከሉትን ማህበረሰብ ድምፅ በታማኝነት ማንፀባረቃቸው፣ የዜጎች ችግር በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ የህዝብ ሀብት ለህዝብ ጥቅም እንዲውልና ዜጎች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚረዳ አስረድተዋል ።
በቃልኪዳን ኃይሌ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

ኩባ ከ11ሺ በላይ የዴንጊ ትኩሳት ታማሚዎችን መዘገበች
👉 ዴንጊ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣና በትንኞች ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ ከባድ የትኩሳት በሽታ ነው።
ኩባ እ›አ›አ በ2026 11ሺ 235 በበሽታው የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት መረጃ ላይ ተመስርቶ ከሚጠበቀው አማካይ መጠን ጋር ሲነፃፀር የ 9.2 እጥፍ ብልጫ እንዳለው የኢንፎቤ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡
በቅርብ ወራት ውስጥ የሕመምተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ የተነገረ ሲሆን በመስከረም ወር ብቻ 4,102 ተጠቂዎች ተመዝግበዋል።
የጥቅምት ወር በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የሕመምተኞች ቁጥር ሊጨምር የቻለው በደሴቲቱ ላይ ከከፋው የኃይል እና የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የመብራት መቋረጥ ቤተሰቦች በሞቃታማ ሌሊቶች በሮችንና መስኮቶችን ክፍት አድርገው እንዲተኙ አስገድዷቸዋል፤ ይህም ለትንኞች የመጋለጥ እድልን ሊጨምር ይችላል። የነዳጅ እጥረትም የትንኝ ማጥፋት ስራዎችን የጎዳ ሲሆን የትንኞችን ቁጥር የመቀነስ እና የበሽታውን ስርጭት የመከላከል ስራዎችን ገድቦታል።
አብዛኞቹ ታማሚዎች ያለ ከባድ ችግር የሚያገግሙ ቢሆንም፣ ከባድ የዴንጊ ህመም ግን ደም መፍሰስን፣ ድንገተኛ የደም ግፊት መውደቅን እና የሰውነት ክፍሎች ጉዳትን ሊያስከትል ስለሚችል ሆስፒታል መተኛትን ሊጠይቅ ይችላል ነው የተባለው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ዴንጊ በዓለም አቀፍ ደረጃ በትንኞች አማካኝነት ከሚተላለፉ የቫይረስ በሽታዎች መካከል በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመሩ ካሉት መካከል አንዱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡

ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
👉ራሚስ ባንከ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪከ አዲስ ምዕራፍ የከፈተለትን ታላቅ ስኬት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
በይፋ አብስሯል፡፡
ባንኩ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው የሚገኙ 2 ሚልየን 101ሺ 106 አክስዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) በይፋ መመዝገባቸውና የምዝገባ መግለጫው በመጽደቁ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና ገጽ ላይ ለመመዝገብ ያቀረበው ማመልከቻ ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ በ ESX ዋና ገጽ ለመመዝገብ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙት ከመጀመሪያዎቹ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ አድርጎታል።
የራሚስ ባንከ የዳይሬከተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ራቢ ሼክ ሁሴን፥ ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በፅኑ የሸሪዓ መርሆች፣ በግልጽነት እና በጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደር ላይ በመቆም የህብረተሰቡን እምነት ያተረፈ ሲሆን፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን በመጠቀም በምስራቅ አፍሪካ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዋና ማዕከል የመሆን ታላቅ ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሊ እንደገለጹት ይህ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተሰጠው የምዝገባ ፈቃድ የራሚስ ባንክን የፋይናንስ ጥንካሬ፣ የኮርፖሬት አስተዳደር ብቃት እና ተቋማዊ አስተማማኝነት በግልጽ ያረጋገጠ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ የኤአይ (AI) የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ኤስ.አር.ኢ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ሀገር በቀል ኩባንያ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚችል ''ኤ አይ ሳይበር ጋርድ'' የተሰኘ የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ መተግበሪያ ለህዝብ ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው መተግበሪያው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘና ከግል ስልኮች ጀምሮ የገንዘብ ተቋማትንና የተለያዩ ግዙፍ ተቋማትን ከሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅም ያለው ነው።
አገልግሎቱ ድረ-ገጾችን፣ የተቋማት ኔትወርኮችን፣ የባንክና የገንዘብ ተቋማት ሲስተሞችን እንዲሁም የግል መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ የመጠበቅ አቅም ያለው ሲሆን፣ ዋነኛ ልዩ ባህሪው ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መስራት መቻሉ ነው።
ይህም የኢንተርኔት መቆራረጥ በሚኖርበት ጊዜም እንኳ ጥበቃው ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
በተጨማሪም የጥቃት ምልክቶችን ቀድሞ መለየት፣ አደጋዎችን መከላከል፣ ፈጣን ምላሽ መስጠትና ለወንጀል ምርመራ ስራዎች አስፈላጊውን ዲጂታል መረጃ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
የሳይበር ጥቃት በሚከሰትበት ጊዜም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች በሚገባ ቀላል ቋንቋ የችግሩን ሁኔታ ያስረዳል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፈለኝ በሰጡት ማብሪርያ ተቋማትና ግለሰቦች ወደ ዲጂታል አሰራር በሚሸጋገሩበት በዚህ ወቅት የመረጃ ምንተፋ፣ የማንነት ስርቆትና የድረ-ገጽ ጠለፋ አደጋዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
ይህንን አደጋ ለመግታትም የ24 ሰዓት ንቁ ክትትል የሚያደርግና ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን የሚቆጣጠር ዘመናዊ የኤአይ ጥበቃ አስፈላጊ በመሆኑ መተግበሪያውን ለማልማት መቻላቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቅጅ መብት ህግ መሠረት ሙሉ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ያገኘው ይህ ሀገር በቀል ፈጠራ፣ ተቋማት የደህንነት ስጋታቸውን በአንድ መድረክ ላይ ተከታትለው በጊዜው እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

“ህይወታችንን በምን እንምራ? ችግር ላይ ወድቀናል!” | የሞተረኞች ቅሬታ❗
በአዲስ አበባ የተጣለው የሞተር ብስክሌት እገዳ በርካታ አሽከርካሪዎችን ለቅሬታ ዳርጓል። በሞተር ብስክሌት ሥራ ተሰማርተው የዕለት ገቢያቸውን በማግኘት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ሲደግፉ የነበሩ አሽከርካሪዎች፣ እገዳው በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ገልጸዋል።
አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት፣ በሕጋዊ መንገድ በማህበር ተደራጅተው፣ ዩኒፎርምና መታወቂያ በማዘጋጀት ሥራቸውን ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ድንገተኛው እገዳ ግን የዕለት ገቢያቸውን እንዳሳጣቸውና የቤተሰቦቻቸውን ወጪ ለመሸፈን እንዳስቸገራቸው ተናግረዋል።
አሽከርካሪዎቹ መንግሥት እገዳውን ከመጣሉ በፊት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸውና አማራጭ የሥራ ዕድሎችን ወይም መፍትሔዎችን ሊያመቻችላቸው ይገባ እንደነበር ያምናሉ። ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎትና ከሥራው የሚያገኙት ገቢ ግምት ውስጥ እንዲገባም ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ባወጣው መረጃ፣ ከስርቆትና ወንጀል መከላከል እንዲሁም ከትራፊክ ደህንነት ጋር በተያያዘ፣ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌቶች ውጭ ያሉ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶች እንዳይንቀሳቀሱ መከልከሉ ይታወሳል።
አሁን የአሽከርካሪዎቹ ዋነኛ ጥያቄ እገዳው በኑሯቸው ላይ ያሳደረው ጫና እንዲታይና ፍትሃዊ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ነው።
Seledadotio

2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤደን ፕሪሪ ፖሊስ ባለፈው ሳምንት አርብ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ የተጠረጠረውን የ18 ዓመቱን ወጣት አዳም አብዲሃኪም አዳምን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። የሴንት ሉዊስ ፓርክ ነዋሪ የሆነው ተጠርጣሪው ሐሙስ ከሰዓት በሚኒያፖሊስ ከተማ የተያዘ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሁለተኛ ደረጃ ከባድ ጥቃት ጥርጣሬ በሄነፒን ካውንቲ እስር ቤት ይገኛል።
ፖሊስ እንዳስታወቀው አደጋው የተከሰተው በስታዲየሙ አካባቢ ከተፈጠረ ትልቅ ጸብ በኋላ የተወሰኑ ግለሰቦች ከስፍራው እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ነው። ወዲያውኑ በመኪና ማቆሚያ ስፍራው በተከፈተው ተኩስ የ17 እና 18 ዓመት ወጣቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ጨዋታውም እንዲቋረጥ ሆኗል። የጸጥታ አካላት ይህ የተኩስ ልውውጥ ከሶማሊያ የጋንግ ቡድኖች እንቅስቃሴ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል።
የኤደን ፕሪሪ ፖሊስ አዛዥ ማት ሳኬት ይህ እስራት ለምርመራው ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ ምርመራው አሁንም እንደቀጠለና ተጨማሪ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ፖሊስ ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው በ 911 ወይም 952-949-8477 ደውሎ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
የስፔን ላሊጋ
04:00 | ማላጋ ከ ኤስፓኞል
የጀርመን ቡንደስሊጋ
03:30 | ዶርትሙንድ ከ ወርደር ብሬመን
የፈረንሳይ ሊግ 1
03:45 | ሌንስ ከ ሊዮን
የሳውዲ ፕሮ ሊግ
03:00 | አል-ናስር ከ ድሪያህ
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
09:00 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
10:00 | ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
04:00 | ማላጋ ከ ኤስፓኞል
03:30 | ዶርትሙንድ ከ ወርደር ብሬመን
03:45 | ሌንስ ከ ሊዮን
የሳውዲ ፕሮ ሊግ
03:00 | አል-ናስር ከ ድሪያህ
09:00 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
10:00 | ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
2 days ago
በወተት ምርትና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮችን ለመቆጣጠር አዲስ ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ ነው
#ethiopia | በወተት ምርት፣ አያያዝና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራትና የንፅህና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት ባካሄደው ጥናት ከወተት እርባታ ሼዶች እስከ ችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ድረስ የንፅህና ጉድለቶች መኖራቸውን መለየቱን ገልጿል።
በእርባታ ቦታዎች አላቢዎች ተገቢውን የደንብ ልብስ አለመልበሳቸውና የንፅህና አጠባበቅ ክፍተቶች መኖራቸው በጥናቱ ከተለዩ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም ላሞች ሲታመሙ የሚሰጣቸው መድኃኒት ከሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ ሳይወጣ ወተቱ ለገበያ የሚቀርብበት ሁኔታ መኖሩ ተመልክቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ጸጋ ለማ እንደገለጹት፣ ወተት ለማለብ፣ ለማጠራቀምና ለማጓጓዝ ተገቢውን የምግብ ደህንነት መስፈርት የማያሟሉ የፕላስቲክ ጀሪካኖች በስፋት እየተጠቀሙ ነው። ይህም ለማፅዳት አስቸጋሪ በመሆኑ በወተት ጥራትና ደህንነት ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ወተት ውስጥ ውሃ በመጨመር ተፈጥሯዊ ይዘቱን የማዛባት ሕገወጥ ድርጊት በአንዳንድ አካላት እየተፈጸመ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።
ኮሚሽኑ እነዚህን የምግብ ደህንነትን የሚጎዱ ተግባራት ለመቆጣጠር፣ ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድና በወተት ምርት ሰንሰለት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል አዲስ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለማስጸደቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ረቂቅ ደንቡ ጸድቆ ወደ ተግባር ሲገባ፣ ከእርባታ ጀምሮ እስከ ምርት ማጓጓዝ፣ ማከማቸትና ለሸማቾች ማቅረብ ድረስ ባለው የንግድ ሰንሰለት ውስጥ የጥራትና የንፅህና መስፈርቶችን ለማስጠበቅ አስፈላጊ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
ይህም ለህብረተሰቡ ጤናማ፣ ጥራቱ የተጠበቀና ደህንነቱ የተረጋገጠ ወተት እንዲደርስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
ፋሲል አረጋይ — አሐዱ

ከቤት ደጃፍ እስከ አፍሪካ ክብር፤ የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ ከፍታ
****************
“ኑ ቡና ጠጡ፣ ቡና ፈልቷል” የሚለው ጥሪ በኢትዮጵያውያን የዘወትር ሕይወት ውስጥ ትልቅ የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነት ግብዣ ነው።
በዚሁ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ወቅት ማኅበራዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፤ ጥልቅ ትስስር ይፈጠራል።
የኢትዮጵያዊነት አንዱ መገለጫ የሆነው የቡና ስነ ስርዓት ከእርሻ ማሳዎች እስከ ሲኒያችን ድረስ የአርሶ አደሩ እጅ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን የሚደግፍ ታላቅ እሴት ነው።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ የቡና ባህል በቤትና በማኅበረሰብ ደረጃ ብቻ ተወሰኖ አልቀረም።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና ሌላ አዲስ የክብር ገጽታውን ለአፍሪካና ለዓለም አሳይቷል።
በአንድ ቀን 10 ሺህ ሲኒ ቡና በአንድ ሥፍራ በማቅረብ፣ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥርዓቱ በአፍሪካ የድንቃድንቅ መዝገብ ውስጥ ዕውቅና አግኝቷል።
በመሆኑም “ኑ ቡና ጠጡ” የሚለው ጥሪ ከቤት ደጃፍ አልፎ በአህጉራዊ የክብር መዝገብ ውስጥ በመግባት፣ ከ“ኑ ቡና ጠጡ” ወደ “የኢትዮጵያን ባህልና አብሮነት ይዩ” ወደሚል ሰፊ አህጉራዊ ጥሪ ተሸጋግሯል።
ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ እና የአፍሪካ ቀዳሚ ቡና አምራች ሀገር ስትሆን፣ የመጀመሪያው የቡና ፍሬ ተለቅሞና ተሰብስቦ ለዓለም የተበረከተው እዚሁ በኢትዮጵያ ምድር ነው።
ሀገራችን በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ኢትዮጵያ ባለፉት 17 ዓመታት በአጠቃላይ ካገኘችው 3.3 ቢሊዮን ዶላር የገቢ መጠን ጋር የሚቀራረብ ነው።
በተጨማሪም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች በሚተከሉበት የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚይዙት የቡና ችግኞች ናቸው።
ይህም ደኖችን መልሶ ለማቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን ለመጠበቅ እና የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስፈልገውን አየር ንብረት ለመፍጠር አስችሏል።
ከዚህ ዕድገት ጎን ለጎን ኢትዮጵያ የቡና በሽታን ለመለየትና ለማከም የሚያስችሉ አዳዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን እና ምርምሮችን በማሳደግ ላይ ትገኛለች።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #ethiopiancoffee #coffeeculture

🚨 «"መላውን የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ብቻ ቀርተዋል" — ጃዋር መሐመድ»
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል መላውን ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ብቻ እንደቀሯቸው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ገለጹ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የቀሩ ከተሞች፦ ሠራዊቱ ክልሉን ሙሉ በሙሉ በእጁ ለማስገባት የቀሩት አክሱም፣ ዓድዋ እና ዓዲግራት ከተሞች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።
የኃይሎች ማፈግፈግ፦ የህወሓትና የኤርትራ ኃይሎች በድንበር አካባቢ ኃይላቸውን መልሰው ለማደራጀት ወደ ኋላ እያፈገፈጉ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
የቀጣይ ሂደት አቅጣጫ፦ ከዚህ በኋላ ያለው ሂደት የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ውሳኔ የሚጠይቅ እንደሚሆን የጠቆሙት ጃዋር መሐመድ፣ ጄነራሎቹና ወታደሮቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት እንዳላቸው በተግባር ማሳየታቸውን አብራርተዋል።

አንድን ሹፌር በሰደፍ ሲመታ እና ሲደበድብ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶችን ያስቆጣ አንድ ቪድዮ እየተዘዋወረ ይገኛል።
ይህ ቪድዮ ሁለት የጭነት መኪናዎች በቆሙበት ለዜጎች የሕግ ከለላና ሰላም መስጠት የነበረበት አንድ የፖሊስ አባል አንድ ግለሰብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እና ድብደባ ሲፈጽም የሚያሳይ ነው።
በርካታ ሰዎች የተፈጸመውን ድርጊት " ከህግ የወጣ እና ኢሰብዓዊ ፤ በየቦታው በሹፌሮች ላይ የሚፈጸመውን በደል ጭምር በገሃድ የሚያሳይ " ሲሉ ኮንነውታል።
" አልተቀረጸ እንጂ ሹፌሮች በየቦታው ይህን መሰል ተግባር ነው የሚገጽማቸው " ሲሉም ገልጸዋል።
ድርጊቱ መቼ እና የት ተፈጸመ ?
ብዙሃንን ያስቆጣው ድርጊት የተፈጸመው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ " ጠንጠሌ " ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር አብረሃም አየለን አነጋግሯቸዋል።
አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ነው።
" በወረዳው ጠንጠሌ አከባቢ ' ዮ ሆልዲንግ ' ከተሰኘ የድንጋይ ከሰል አቅራቢ ድርጅት ሳይት ከሰል ጭነው በመውጣት ላይ የነበሩ የዳንጎቴ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች በአከባቢው ከነበሩ የፖሊስ አባላት ጋር ያለመግባባት ተፈጥሮ ነበር " ብለዋል።
" የፖሊስ አባሉ ፍጹም ተገቢ ባልሆነ መንገድ አሽከርካሪውን ሲመታው የሚያሳይ ምስል በዚያው ቅፅበት በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ መረጃው በስልክ ነው የደረሰኝ " ሲሉ ገልጸዋል።
" መረጃው እንደደረሰን በዕለቱ ድርጊቱ በተፈፀመ 30 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው አባሉን በቁጥጥር ስር ያዋልነው " ያሉት አዛዡ " በአሁኑ ወቅት ምርመራ ተጀምሯል የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ እየተጠበቀ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ድርጊቱ በየትኛውም አይነት መመዘኛ ትክክል አይደለም " ያሉ ሲሆን " የተፈጸመው ድርጊት ግለሰቡን እንጂ የወረዳውን ፣ የዞኑንና የክልሉን ፖሊስ የማይወክል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሳራጩት አንዳንድ ማብራሪያና ፍረጃዎች ተገቢነት የላቸውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከዳንጎቴ ተቋም በኩል መረጃ ለማግኘት ሙከራ አድርጎ አልተሳካም።
አንድ በተቋሙ ለዞኑ የተፃፈ ደብዳቤን ግን ተመልክቷል።
" ይህ የአሁኑን ጨምሮ በሌሎችም ጊዜያት የተለያዩ ክፍያዎችን እየከፈሉ ቢሆንም የድርጅቱን አሽከርካሪዎች እና መኪኖች ላይ ያለአግባብ የማንገላታት ሁኔታዎች አሉ " ይላል።
ድርጅቱ " ለልማት ማህበር፣ ለፋይናንስ ቢሮ፣ ለከተማ ልማት እንዲሁም ያለደረሰኝ 'የተራ እና ሽራ አሰራ' በሚል በድምሩ እስከ 27,100 ብር ህጋዊና ህገ-ወጥ ክፍያዎችን እየከፈለ " መሆኑን ጠቁሟል።
በተጨማሪም "ፓርኪንግ" በሚል ያልቆሙበትን ክፍያ ለመጠየቅ ሲባል ወጣቶች በመደራጀት ሾፌሮቹን ከ3 እስከ 4 ቀናት በማስቆም ከፍተኛ እንግልት እንደሚያደርሱባቸው ገልጿል።
" በመንገድ ላይ የተመደቡ ፖሊሶች ያለአግባብ ከሾፌሮች ከ200 እስከ 500 ብር ይጠይቃሉ " የሚለው የድርጅቱ ደብዳቤ " ክፍያውን ያልፈጸሙ አሽከርካሪዎችን በማንገላታትና በመደብደብ ጉዳት መድረሱን " አመልክቷል።
አንድ አሽከርካሪ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ምክንያት ደብዳቤ እንደተፃፈለትም ጠቅሷል።
እነዚህ አሰራሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ አሽከርካሪዎች ያለስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ እና ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ህገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም!
*******************
ከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር የግዛቷ አካል ሆኖ መርከቦቿ ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ጥንታዊት ኢትዮጵያን በአለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ሀይሎች አንዷ እንድትሆን ያደረጓት በወቅቱ ታስተዳድራቸው የነበሩት ወደቦቿ፣ የንግድ ትስስሮቿ እና "ባህረ ነጋሽ" የሚለው የማእረግ መጠሪያ ስያሜ እንደነበሩ ይታወቃል።
ሆኖም ሀገራችን በታሪክ አጋጣሚዎች እና በተደረጉባት እኩይ ሴራዎች ምክንያት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና በመቆየቷ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ የጂኦ ፖለቲካ እና የብሄራዊ ደህንነት ማነቆዎች ተዳርጋ ኖራለች።
በተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ መረጃ መሰረትም የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከአለም አማካይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ለማውጣት የሚገደዱ በመሆኑ ይህ ተፅእኖ በዜጎች እለታዊ የሸመታ አቅም፣ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዲጂታል መረጃ በሚያስተላልፉት ከባህር በታች ያሉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት አጥብቀን እንሰራለን ያሉም ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት እና የትውልድ ቁጭት ለመቅረፍ "የመደመር መንግስት" የባህር በር ጥያቄን ከወቅታዊ ፖለቲካ እና ከፓርቲ ወገንተኝነት በላይ በሆነ ትውልድ ተሻጋሪ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የመደመር መንግስት በያዘዉ ጠንካራ አቋም የኢትዮጵያ ስልጣኔና እድገት ያለ ባህር በር እውን ሊሆን ስለማይችል ሀገራችን በሰጥቶ መቀበል በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ መርህ ወደ አለም የምትወጣበትን መስመር የማረጋገጥ ጉዞዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እውነተኛ ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት የሚረጋገጠው ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶች ያለ ምንም የውጭ ጫና እገዳ ወይም የጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ሲችሉ እንደመሆኑ መጠን ቀጥተኛ የባህር በር ማግኘት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመክፈት የወጣቶችን ስራ አጥነት ከመቅረፉ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በስትራቴጂካዊ የውሃ አካላት ቀጠናዊ ውሳኔዎች ላይ ያላትን የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ አካል እንጂ ከሩቅ የመጣች እንግዳ እንዳልሆነችና በጂኦ ፖለቲካዊ ሴራዎች የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓን ለአለም እያስረዳች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ እግሯን እንዳትተክል የሚደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ የዲፕሎማሲ እና የፕሮፓጋንዳ ሸፍጦች አልቆሙም እነዚህን ሸፍጦች ሲጠነስሱ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ አካላት መፍጨርጨራቸው ባይገታም ኢትዮጵያን በዘላቂነት ሊያግዷት አይችሉም።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና የአካባቢያዊ ትስስር ዋና ምሰሶ እንደመሆኗ የባህር በር ማግኘቷ ለአካባቢው ሀገራትም ቢሆን ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በቅርብም በሩቅም ያሉ ሀገራት ለኢትዮጵያ ቀና ምላሽ በመስጠት በጋራ መስራትን ተመራጭ ያደርጋሉ።
ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው ኢኮኖሚና ትልቅ ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗም ይህን ግስጋሴ የሚያስተናግድ የባህር በር የማግኘት ትልሟን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናታል።
በአጠቃላይ የታሪክ እውነታ የህግ መብት እና የህልውና ጥያቄ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ አይቀሬ ያደርጉታል።
ይህንን አገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማፅናትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሃሳብ ፖለቲካን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ወሳኝ መፍትሄ ነው።
በአለም አቀፍ የባህር ህግጋት እና በዲፕሎማሲያዊ አማራጮች የታገዘው ይህ ጥረት የመጪውን ትውልድ መብትና እድል የማስከበር የታሪክ ጥሪም ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ለዘላቂ ብልፅግና የሚያሸጋግር ጨዋታ ቀያሪ ምእራፍ ነው።
ዛሬ ብርቱዋ ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት አመታት ካቀረቀረችበት ቀና ብላለች የቀይ ባህር ተጋሪነቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማናቸውም ሸፍጦች ጊዜያዊ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የህዝቧን የታሪክ እና የተፈጥሮ መብት ሊያጠፉ አይችሉም።
ኢትዮጵያ አትቆምም የጂኦ-ፖለቲካ ሴራዎችን ሁሉ በጣጥሳ ከባህሩ ትደርሳለች ባህር ሀይሏና መርከቦቿም በቀይ ባህር ዳግም ይጓዛሉ።
በብሌን ደምበሎ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #seaaccess #redsea #diplomacy

Comments