ዩጋንዳ ዜጎቿ በኬንያ የመራጮች ምዝገባ ላይ እንዳይሳተፉ አገደች
ዩጋንዳ እ.ኤ.አ በ2027 በሚካሄደው የኬንያ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጎረቤት ሀገር የሚሻገሩ ዜጎቿ እንዲታገዱ እና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለጸጥታ አካላት ትእዛዝ አስተላልፋለች።
የዩጋንዳ የመጀመሪያዋ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቤካ ካዳጋ እንደገለጹት የዩጋንዳ ዜጎች በሌላ ሀገር የምርጫ ሂደት ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው ገልጸው በበርካታ የድንበር አካባቢዎች የሚገኙ ባለስልጣናት ወደ ኬንያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት እንዲከታተሉ አዟቸዋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አንዳንድ የዩጋንዳ ዜጎች የኬንያ መታወቂያ ሰነዶችን በማውጣት በመራጭነት እየተመዘገቡ ነው የሚሉ ዘገባዎችን ተከተሎ ነው። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ የተቀናጀ ሕገ-ወጥ የምዝገባ ቅስቀሳ መኖሩን የሚያረጋግጥ ታማኝ የሆነ ማስረጃ እንዳልደረሰው አስታውቋል።
ዩጋንዳ የኬንያን ሉዓላዊነት የምታከብር እና ተመሳሳይ ምላሽ እንደምትጠብቅ የገለጸች ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በጸጥታ እና በዲፕሎማሲያዊ መስመሮች በኩል በቀረቡት ክሶች ላይ ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

1 day ago