በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ የኤአይ (AI) የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ኤስ.አር.ኢ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ሀገር በቀል ኩባንያ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚችል ''ኤ አይ ሳይበር ጋርድ'' የተሰኘ የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ መተግበሪያ ለህዝብ ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው መተግበሪያው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘና ከግል ስልኮች ጀምሮ የገንዘብ ተቋማትንና የተለያዩ ግዙፍ ተቋማትን ከሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅም ያለው ነው።
አገልግሎቱ ድረ-ገጾችን፣ የተቋማት ኔትወርኮችን፣ የባንክና የገንዘብ ተቋማት ሲስተሞችን እንዲሁም የግል መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ የመጠበቅ አቅም ያለው ሲሆን፣ ዋነኛ ልዩ ባህሪው ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መስራት መቻሉ ነው።
ይህም የኢንተርኔት መቆራረጥ በሚኖርበት ጊዜም እንኳ ጥበቃው ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
በተጨማሪም የጥቃት ምልክቶችን ቀድሞ መለየት፣ አደጋዎችን መከላከል፣ ፈጣን ምላሽ መስጠትና ለወንጀል ምርመራ ስራዎች አስፈላጊውን ዲጂታል መረጃ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
የሳይበር ጥቃት በሚከሰትበት ጊዜም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች በሚገባ ቀላል ቋንቋ የችግሩን ሁኔታ ያስረዳል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፈለኝ በሰጡት ማብሪርያ ተቋማትና ግለሰቦች ወደ ዲጂታል አሰራር በሚሸጋገሩበት በዚህ ወቅት የመረጃ ምንተፋ፣ የማንነት ስርቆትና የድረ-ገጽ ጠለፋ አደጋዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
ይህንን አደጋ ለመግታትም የ24 ሰዓት ንቁ ክትትል የሚያደርግና ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን የሚቆጣጠር ዘመናዊ የኤአይ ጥበቃ አስፈላጊ በመሆኑ መተግበሪያውን ለማልማት መቻላቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቅጅ መብት ህግ መሠረት ሙሉ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ያገኘው ይህ ሀገር በቀል ፈጠራ፣ ተቋማት የደህንነት ስጋታቸውን በአንድ መድረክ ላይ ተከታትለው በጊዜው እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

2 days ago