3 hours ago
እናት ፓርቲ መምህር ዮሐንስ ሸዋቀናን ፕሬዚዳንት ፤ ወ/ሮ ጥሩማር አባተን ም/ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።
2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በሶራምባ ሆቴል ዛሬ ያካሄደው እናት ፓርቲ፣ የሥራ አስፈጻሚ እና የላዕላይ ምክር ቤት አመራሮች ሹመት አካሂዷል።
በዚህም፥ መ/ር ዮሐንስ ሸዋቀና እና ኢ/ር በለጠ እያዩ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆነው ቀርበው፣ መምህር ዮሐንንስ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ወ/ሮ ጥሩማር አባተ እና ሐብታም ግለጠው ደግሞ በም/ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆነው ቀርበው፣ ወ/ሮ ጥሩማር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
እንዲሁም
- አቶ ጥበቡ ይርጋ (ጠቅላይ ፀሐፊ)
- ወ/ሮ ሊባኖስ ደምሴ (ሕዝብ ግንኙነት)
- አቶ አያሌው ተስፋዬ (አባላት ምልመላ)
- አቶ አንዳርጌ መኹሪያ (የፖለቲካ ትንተና ክፍል)
- አቶ መኮንን ከበደ (የውጭ ግንኙነት ክፍል)
- ወ/ሮ ሐብታም ዳኘው (የመረጃ ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ክፍል)
- አቶ ቴዎድሮስ በየነ (ፋይንስና እና ገቢ ማሰባሰቢያ ክፍል)
-ስመኝ ታደመ (ስልጠና እና አቅም ግንባታ ክፍል)
- አቶ ከፍያለው ዘውዱ (ፖሊሲና ምርምር፣ እቅድ ክፍል)
- ብርሃኑ ታዬ (የአካል ጉዳተኞች ክፍል)
- ወ/ሮ ሰብለወርቅ ፅጌ (ሴቶች እና ወጣቶች ክፍል)
- አቶ ዋለልኝ አስፋው (የሕግ እና ስነስርዓት ኮሚቴ)
- አቶ ሽመልስ ተገኝ (ሒሳብ ክዋኔ ኮሚሽን)
- መምህር መንግስቱ አረጋኸኝን (አርትኦት ኤዲትሪያል ቦርድ ኃላፊ) አድርጎ መርጧል።
ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ጠዋት 2 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራም የተጀመረው ከቀኑ 6 ሰዓት ነው። ከከሰዓት 11 ሰዓት ያልቃል የተባለው ጠቅላላ ጉባዔው የተጠናቀቀው ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሂደቱን ሲታዘብ መዋሉን እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል።
ከነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሲሳይ ነጋሽ፣ ከኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ራሔል ባፌ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ምስጢረስላሴ ታምራት እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
የእናት ፓርቲው ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ ጌትነት ወርቁ በቅርቡ "ይብቃኝ" በሚል ከፖለቲካው ዓለም ማግለላቸው የሚታወስ ነው።
የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ሰይፈሥላሴ አያሌው ደግሞ "ከሀገር ወጥተዋል" የተባለ ሲሆን፣ የፓርቲውን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ ዛሬ በዙም ገለጻ ሲያርጉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

🏡
+971527866251
🔥 በ24% ቅድመ ክፍያ ብቻ የራስዎ ቤት ይሁንዎ! ቀሪውን ክፍያ በ5 ዓመት ይክፈሉ።
💰 ቅድመ ክፍያ፦ $98,630.10
📈 የተገመተ ዓመታዊ የኪራይ ገቢ፦ $24,657.50
📩 ለበለጠ መረጃ Brook Real Estateን ያነጋግሩ!
#dubairealestate #dubaiproperty #ethiopiandiaspora #realestateinvestment #brookrealestate #ዱባይ #ሪልኢስቴት
5 hours ago
በግብር አመቱ ከተፈቀደላቸው ዘርፎች ውጪ የሂሳብ መዝገብ ሳያቀርቡ በሚቀሩ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት ቅጣት በማድረግ ህጉ ተፈጻሚ እንዲሆን መመሪያ ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በህጉ የተቀመጠውን የሂሳብ መዝገብና መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ወደ ጎን በመተው ገቢያቸውን ለመደበቅ በሚሞክሩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥቷል።
ቢሮው የ2018 የግብር ዘመን የማሳወቂያ ጊዜ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ መመሪያ አውጥቷል።
ቢሮው ባወጣው መመሪያ እንዳስታወቀው፣ የሂሳብ መዝገብ አለመያዝ እንደ አማራጭ ሊወሰድ እንደማይችልና አሰራሩን ጥሰው በሚገኙ ከፋዮች ላይ አስተማሪ የህግና የአስተዳደር ቅጣቶች ይጣላሉ።
እንደ ገቢዎች ቢሮ ማብራሪያ፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 3/ሀ፣ 6 እና አንቀጽ 50/ለ እንዲሁም በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 21፣ 33 እና 82 ድንጋጌዎች መሰረት ማንኛውም የደረጃ «ሀ» እና ደረጃ «ለ» ግብር ከፋይ አመታዊ ጠቅላላ ገቢውን በሰነድና በሂሳብ መዝገብ አስደግፎ የማሳወቅ፣ ሰነዶችን የመያዝ እና ግብር የመክፈል ሙሉ ግዴታ አለበት።
ሆኖም መመሪያው በልዩ ሁኔታ ካካተታቸው የተወሰኑ ዘርፎች ውጪ ሆነው ሰነድ ሳያቀርቡ የሚቀሩ አካላት ድርጊት በቀጥታ «ግብርን ለመሰወር የሚደረግ ድርጊት» ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብሏል።
በመሆኑም ይህንን የህግ ጥሰት በፈጸሙ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት የሚከተሉት ቅጣቶች ተፈፃሚ የሚደረጉ መሆኑም ገልጿል፦
- በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ለደረጃ «ሐ» ግብር ከፋዮች የተቀመጠው የትርፋማነት ህዳግ ለእነዚህ አካላት በእጥፍ አድጎ እንዲሰላ ይደረጋል።
- በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 109 እና 110 ድንጋጌዎች መሰረት፣ ታክሱን ባለማሳወቃቸው ምክንያት በሚፈጠረው የታክስ ጉድለት ላይ 40 በመቶ እንዲሁም በዋናው የታክስ መጠን ላይ 200 በመቶ ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል ይደረጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አክሎ እንዳሳሰበው፣ በዚህ መልኩ በቅጣትና በእጥፍ የትርፍ ህዳግ የሚስተናገዱ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ዝርዝር ፋይልና መረጃ ተደራጅቶ ለህግ ተገዥነት ዘርፍ እንዲተላለፍ ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት "የኤርትራ ጦር 60 ኪሎ ሜትር ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ ገብቷል" በማለት ያቀረበውን ክስ "የጦርነት አዋጅ" ነው ስትል ውድቅ በማድረግ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብና ወታደራዊ እርምጃን ሊያካትት የሚችለውን የቻፕተር 7 አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ በይፋ ጠይቃለች።
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳላህ ለምክር ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ፣ አዲስ አበባ ያቀረበችው የድንበር ጥሰት ክስ ሌላ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት የታለመ ሰበብ መሆኑን አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለፀጥታው ምክር ቤት አርብ ዕለት በላከችው ደብዳቤ፣ የውጭ ኃይሎች በግዛቷ መገኘት ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳላስቀረላት በማስጠንቀቅ የክሱን ክብደት አጠናክራዋለች።
መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና አጋር ሚሊሻዎች ከኤርትራ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ስትራቴጂካዊቷ የአዲግራት ከተማ መግባታቸውን የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል። በቅርቡ በአካባቢው በነበረው የድሮን ጥቃት እና ከባድ ውጊያ የኤርትራ ኃይሎች ወደ ኋላ ማፈግፈጋቸው የተነገረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከተማዋን ሲቆጣጠሩ የሚያሳይ የቪድዮ መረጃም ወጥቷል። ይህ እንቅስቃሴ ባለፈው ወር በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ዳግም ያገረሸውን ውጊያ ይበልጥ ውስብስብ ወደሆነ ቀጠናዊ ግጭት አሸጋግሮታል።
ይህ የዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ፍጥጫ ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት እና የቀጠናውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ማዕከል ያደረገ ነው። በ2010 ዓ.ም የተደረሰውን ታሪካዊ የሰላም ስምምነት እና በትግራይ ጦርነት ወቅት የነበራቸውን ጥምረት ወደ ጎን በመተው፣ ሁለቱ ሀገራት አሁን ላይ በይፋ ወደ ለየለት ጦርነት አፋፍ መድረሳቸውን የቃላት ምልልሶቹ ያሳያሉ። የኤርትራ የተመድ ጣልቃ ገብነት ጥሪም በአፍሪካ ቀንድ እያቆጠቆጠ ያለው አዲሱ ጦርነት ከሁለቱ ሀገራት አቅም በላይ ሆኖ አህጉራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ መጣሉን የሚያመላክት ግልጽ ማሳያ ነው።

ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እና አልባሳት ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
አረጋዊ ገ/ህይወት እና ካሳ ተክሌ የተባሉት ተጠርጣሪዎ ች የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ውሀ ልማት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ነው።
ካሳ ተክሌ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ልጅ ት/ቤት የሚያደርስ ሲሆን ት/ቤት ካደረሳት በኋላ የስጋ ዘመዷ ከሆነው አረጋዊ ገብረህይወት ከተባለው አባሪው ጋር በመደዋወል ወንጀሉን ለመፈጸም ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
የግል ተበዳይ ስራ ቦታ መሆኗን ደውለው ካረጋገጡ በኋላ የመኖሪያ ቤቷን መኝታ ቤት መስኮት ገንጥለው ወደ ውስጥ በመግባት 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት 3 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ የዋጋ ግምታቸው 1ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የሚገመቱ ከውጪ የመጡ የተለያዩ የወንድ ጃኬቶች በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ሰርቀው መሰወራቸውን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአድዋ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ጠቁሟል።
የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቁ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ቶፊክ መደድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ አማካኝነት አስቸኳይ ክትትል እና ምርመራ እንዲደረግ ስምሪት ሰጥተዋል።
በመሆኑም የዋና ጠቅላይ መምሪያው የየካ ክ/ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ እና የአድዋ ፖሊስ መምሪያ የክትትል እና የምርመራ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት/INSA የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአፋር ክልል የሚሌ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና የተሰረቀውን ንብረት ለማስ መለስ እልህ አስጨራሽ ርብርብ አድርገዋል።
በተደረገው እልህ አስጨራሽ ማፈላለግ ተጠርጣሪዎች ከላም በረት መናኸሪያ በመሳፈር በአፋር ክልል አድርገው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በአፋር ክልል ሚሌ ከሚባለው ኬላ ላይ በክልሉ ፖሊስ እና በተቀናጀው የጸጥታ ግብረ ኃይል ፍተሻ ከነ ኤግዚቢቱ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

9 hours ago
የእስራኤል ድሮን በኤርትራ‼️
ዘ- ጆርዳን ታየምስ የተባለው የደህንነት ሚዲያ መነሻውን ከእስራኤል ያደረገ አንድ የስለላ ድሮን በኤርትርራ ላይ የብዙ ሰአት ቅኝት ሲያደርግ ማምሸቱን ዘግቧል።
የሰሜኑ ጦርነት ወደ ኤርትራ መሬት እየተጠጋ ነው ያለው ይህ ጋዜጣ፣ አዲስ አበባ እራስን ለመከላከል በምታደረርገው ውጊያ ላይ እስራኤል አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ የሳተላይት መረጃዎችን በመስጠት ውጊያው የቀይባህር መስመርን ሳያውክ እንዲጠናቀቅ እስራኤል የዶናልድ ትራፕን አመራር እያሳመነች ነው ብሏል።
እስራኤል በአፍሪካ ቀንድ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ሲቃወምና ሲያወግዝ የነበረው የ35 አመቱ የአስመራው አገዛዝ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ስራን እየሰራች መሆኑን የጠቀሰው ይህ ጋዜጣ፣ ግብፅ ኤርትራን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ የረጅም ግዜ ውጊያ እንዲፈጠር አቅዳ እየሰራች ቢሆንም እስራኤል የጦርነቱን ሁኔታ አይታ የሲና በረሀን ለመቆጣጠር አዲስ ውጊያ መክፈት አስፈላጊነቱን እያጤነችበት ነው ሲል ነው የዘገበው።
እስራኤል ዜጎቿ ወደግብፅ መሬት እንዳይሄድ ያሳሰበችው ትናት ነው።
ሱሌማን አብደላ
Seledadotio

ለአስታጥቃቸው ይሁን ስጦታ ሊበረከት ነው
ጥቅምት 7 2019 ዓ.ም የምስጋና መርሀ- ግብር የሚደረግለት የቴአትር ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን ታሪኩ በዶክመንተሪ ሊሠራ ነው።
ቦሌ ፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች የቴአትርና የሲኒማ ኮምፕሌክስ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የምስጋና መርሀ ግብር ስለ ከያኒው ምስክርነት የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚታደሙ ሲሆን ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶችም ይኖራሉ ተብሏል።
ተመስጋኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን እና ቤተሰቡ የምስጋና መርሀ ግብሩን እንዲያዘጋጅ ይሁንታቸውን በህጋዊ መንገድ ለተወዳጅ ሚድያ የሰጡ ሲሆን በምስጋና መርሀ ግብሩ እለት ለሚታየው ዶክመንተሪም ቃለ ምልልስና መረጃ ሰጥተዋል።
የአስታጥቃቸው ልጆች ወይዘሮ መልካም አስታጥቃቸው እና የኤሌክትሪክ መሀንዲስ ዮርዳኖስ አስታጥቃቸው እንዳሉት አባታቸው እዩኝ እዩኝ የማይል ሥራውን ግን አድምቶ የሚሠራ ለብዙዎች ተምሳሌት የሆነ ሰው መሆኑን ተናግረዋል።
በቀረፃ ሥራው ወቅት ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን 10 የሚጠጉ የአስታጥቃቸው ኦሪጅናል ስክሪፕቶችን የተመለከተ ሲሆን ወደፊትም ሥራዎቹ መታተም እንዳለባቸው ምክረ- ሀሣብ ቀርቧል።
በአስታጥቃቸው እጅ ከሚገኙ የቲያትር ስክሪፕቶች መካከል ተናጋሪው ዲዳ የተሰኘው የሬድዮ ድራማ የሚገኝበት ሲሆን የፃፈበት ጊዜም 1975 እንደሆነ ታውቋል።ሌላው በሚያዝያ 30 1989 የዛሬ 30 አመት የተፃፈው ባለ 11 ገፅ የሬድዮ ድራማ ባለሱሪው የሚል ርዕስ የሰጠው ነው።ሳልሣዊው ባልንጀራ ባለ 3 ገቢር ተውኔት ሲሆን በ1975 ለእይታ የበቃ ነው።ሌሎች ስክሪፕቶቹም ፍፁም ቅጣት፣ ቅሌት በድንኳን፣ፈታኙ አስክሬን 1985(የሬድዮ ድራማ)፣ቀባሪ ያጣ በድን 1974ባለአንድ ገቢር ድራማ፣ በ1983 የተፃፈው ድርሳነ ፀጋ፣ አንቺን አሉ እናትነሽ በእጁ ከሚገኙ ድርሰቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
በኢትዮጵያ የቴአትርና የጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው ሁለገብ ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁንን ለማመስገንና የ69ኛ ዓመት ልደቱን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተወዳጅ ሚድያ ጋር በባህር ማዶና በአገር ቤት የሚኖሩ ወዳጆቹ ከፍተኛ ትብብር ያሳዩ ሲሆን በአሁኑሰዓትም መርሀ ግብሩን እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ታውቋል።
ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በቴአትር ጥበብ የተመረቀ ሲሆን፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ማስተማር ከጀመረበት ሁለተኛው ባች (ምሩቃን) ያደርገዋል።
ከተመረቀበት ዓመት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በሥነ-ፅሁፍና ቋንቋ ኤክስፐርትነት የተቀጠረው ከያኒው፣ ላለፉት 37 ዓመታት በጥበቡ ዓለም ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ሀገሩን ህዝቡን በታማኝነት አገልግሏል።
አስታጥቃቸው አጠቃላይ ከ60 በላይ የተውኔት ፅሁፎችን ያበረከተ ሲሆን፣ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎችን፣ መጣጥፎችን፣ አጫጭር ልቦለዶችንና ግጥሞችን ፅፏል።
አስታጥቃቸው ይሁን ፋንታ ከ1990-1995 ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን በዋናሥራ አስኪያጅነት ያገለገለ ሲሆን በሥነ ምግባሩ እና በትህትናው በብዙዎች የሚወደድ የጥበብ ሰው እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ ታላላቆች የቴአትር ፈርጦች አያልነህ ሙላት፣ ጌትነት እንየው፣ ተስፋዬ ሲማ ፣ ተፈሪ አለሙ እና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚገኙ ተነግሯል ።
በምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ለከያኒው ለየት ያለ ስጦታ እንደሚበረከትለት ታውቋል።

Sponsored by
Surafel
10 hours ago
ኢትዮጵያ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን ማጣራት የሚችል ፋብሪካ ሥራ አስጀመረች
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ጀምሯል ።
በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካው፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከርና የሰለጠነ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ፋብሪካው የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ከመደገፍ ባለፈ፣ በውድ ማዕድናት ማጣራት ዘርፍ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ እንዲሁም ግልጽና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት እንደሚያግዝ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል ።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

11 hours ago
እነማን ተሾሙ ?
በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታነት ከሾሟቸው መካከል የቀድሞ የህወሓት አመራር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ይገኙበታል።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።
ሌላው፥ የኢዜማው መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ፣ ከዛ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ፣ በብሔራዊ መረጃና ደህነትም አመራር ሆነው ያገለገሉት እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
ሌላው በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።
ሌላው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በነበረበት ወቅት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ በረሆ ሀሰን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።
የፋይዳ ቨርስ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታነት ተሹመዋል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ሹመት በዛሬው ዕለት 62 አመራሮችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል። (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል) መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

13 hours ago
ምባፔ እና ቪንሰስ ሜዳ ላይ እንደሚፎካከሩ ተነገረ !
የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ኪሊያን ምባፔ እና ቪንሰስ ጁኒየር ከሜዳ ውጪ ያላቸው ግንኙነት ጥሩ መሆኑ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ሁለቱ ተጨዋቾች ሜዳ ውስጥ ያላቸው መተባበር አሁንም ጥሩ እንዳልሆነ ተነግሯል።
ሁለቱ ተጨዋቾች ሜዳ ውስጥ ሲገቡ ራሳቸውን በሁሉም ነገሮች ማወዳደር እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
አንዱ ተጨዋች መከላከል ሲያቆም ሌላኛውም ተጨዋች መከላከል እንደሚያቆም ሁለቱን ተጨዋቾች በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድ ለምባፔ የባሎን ዶር ዘመቻ እገዛ ማድረጉ ሳያበሳጨው እንዳልቀረ ተሰምቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሪያል ማድሪድ መልበሻ ቤት ውስጥ ያለው መንፈስ ካለፈው አመት የተሻለ መሆኑ ተገልጿል።
መረጃው የተገኘው ከ ዘ አትሌቲክ ነው።
@tikvahethsport kidusyoftahe

"ቤቱን ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል እመሰገናለሁም ይላል እግዚአብሔር::" ሐጌ 1፥8
የታላቅ በረከት እና የቅዱስ ሕንፃ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ!
የተጀመረውን የመሪ አያት መካነ ሕይወ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ፍጻሜ ለማድረስ የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ መርሐ ግብር! በገዳሙ እናቶችና መነኮሳት በጸሎት የተዘጋጀው ቅዱስ ዳቤ እና ንፍሮ ለቤትዎ በረከት፣ ለሰውነትዎ ፈውስ ሊሆን ቀርቧል።
የዕለቱ መርሐ ግብር፦
ቀን፦ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም
ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፦ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር
🎤 ትምህርተ ወንጌል፦ በሊቀ ማእምራን ፕሮፌሰር ዘበነ ለማ
መንፈሳዊ መዝሙራት፦ ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ እና ዘማሪት ሲስተር ሕይወት
“እኔም ለእግዚአብሔር ቤት አሻራ አለኝ” በማለት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን፦ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000321686854አባይ ባንክ (አጭር ቁጥር)፦ 0505
ለበለጠ መረጃ፦ +251947980166 | +251912609000 |+251921786452
"በሰማይ መዝገብ ለራሳችሁ ሰብስቡ..." ማቴ 6፥20
አድራሻ ፡- በመሪ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ከ 40 በ 60 ኮንዶሚኒየም በታች እና በአያት መኖሪያ በዞን 2 ቤቶች ….

14 hours ago
የትግራይ ክልል የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተገለጸ።
በክልሉ አዲስ አስተዳደራዊ መዋቅር እየተዘረጋ ነው
በትግራይ ክልል መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ክልሉን ወደ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ የሚደረጉ አጠቃላይ የመልሶ ግንባታና የአስተዳደር መዋቅር ዘረጋ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ።
ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የአካባቢ አስተዳደሮችን የማጠናከርና ክፍተቶችን የመድፈን ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በከተሞች አዳዲስ ከንቲባዎች፣ በወረዳዎች አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የዞን አመራሮች እየተሰየሙና እየተመረጡ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል የብዙዎችን ትኩረት የሳበው አቢይ ዜና፣ ህውሃት ለክልሉ ላለፉት 30 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውና በይዘቱ ግጭት ቀስቃሽ እንደነበር የሚነገረው የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ መሰማቱ ነው።
እንደ መረጃው ከሆነ የመዝሙሩን ግጥም አስተካክሎና ዜማውን አሻሽሎ በአዲስ መልክ የማዘጋጀት ስራ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን፣ ይህም ክልሉን ወደ አዲስ የሰላም፣ የእድገትና የመልካም አስተዳደር ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተደረጉ ካሉ ዋና ዋና እርምጃዎች አንዱ እንደሆነ ተመልክቷል።
@Yenetube Fikerassefa

15 hours ago
#moe
#tigray
የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊ ምደባ ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ አጠናቆ ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል።
ተማሪዎቹ በዚህ ማስፈንጠሪያ https://student.ethernet.e... በመግባት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የምደባ መረጃው በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተማሪዎች ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ ግብር መሠረት በመሄድ ትምህርታቸውን መቀጠል ይችላሉ።
ሚኒስቴሩ የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ከመሄዳቸው በፊት የምደባ መረጃቸውን በዚህ ገብተው https://student.ethernet.e... እንዲያረጋግጡ አሳስቧል።
በተጨማሪም አዲስ ተማሪዎች የተመደቡበትን ተቋም በዚህ ማስፈንጠሪያ https://student.ethernet.e...
ማየት እንደሚችሉ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ፤ አሁን ላይ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ በመሆናቸው በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ተማሪዎች (ጊዜያዊ ምደባ የተሰጣቸውን ጨምሮ) የዩኒቨርሲቲዎቹን የጥሪ ማስታወቂያዎች በመከታተል ትምህርታቸውን በነበሩበት ተቋም መቀጠል ይችላሉ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ምደባ ይፋ ሆነ። በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ። በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን…

16 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው ይፋዊ መረጃ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን በሚኒስትር ማዕረግ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አድርገው በድጋሚ ሾመዋቸዋል።
ሹመቱ ይፋ በሆነበት እና የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል በሚባልበት በዚህ ሰዓት፣ በድጋሚ የተሾሙት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው የአስመራን መንግስት ኢላማ ያደረገ አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል። አቶ ጌታቸው "አስመራ የስሌት ስህተትን አራቅቃ ወደ ጥበብነት ቀይራዋለች" በማለት የኤርትራ መንግስት ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት የወሰደው እርምጃ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ክሽፈት እና መዘዙ የከፋ ስህተት መሆኑን አመላክተዋል።
ይህ ሹመት እና ተያይዞ የመጣው ጠንካራ የቃላት ጦርነት፣ በቀጣይ በኢትዮ-ኤርትራ ቀውስ ላይ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ሊከፍት እንደሚችል ይጠበቃል።
ሹመቱን በተመለከተ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? ኮመንት ላይ ያጋሩን!

17 hours ago
#moe
ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩ ነባር ተማሪዎች ካደረገው ጊዜያዊ ምደባ ጋር በተያያዘ ለቀረቡ ቅሬታዎች የማጣራት ሥራ አጠናቆ ምላሽ ሰጥቷል።
በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ ለመመልከት 👇 https://student.ethernet.e...
የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሐግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሔድ ትምህርታችሁን መቀጠል እንደምትችሉ ተገልጿል።
በምደባው ላይ የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሔዳቹህ በፊት https://student.ethernet.e... ላይ በመግባት እንድታረጋግጡ ተብሏል።
አዲስ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ተቋም https://student.ethernet.e... ላይ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
🔔 ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ)ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ ተገልጿል።
@tikvahuniversity

20 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤል ወታደራዊ ኃይሎች በደቡባዊ ሶሪያ ቁኔይትራ ገጠር በምትገኘው ራስም አል-ሃይዳራህ መንደር ውስጥ ድንገተኛ ፍተሻ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማካሄዳቸውን የሶሪያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
እንደ ዘገባው መረጃ ከሆነ ይህ እንቅስቃሴ የተካሄደው ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በቁኔይትራ ግዛት በሚገኙ በርካታ መንደሮች ውስጥ በተደጋጋሚ ሲደረጉ በቆዩ ወታደራዊ ቅኝቶች፣ የቤት ለቤት ፍተሻዎች እና የእስር እርምጃዎች መቀጠል ሳቢያ ነው።
በአካባቢው ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ክስተቱ በሶሪያ ደቡባዊ ድንበር አቅራቢያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገው ተዘግቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውስጥ በተደረገ አዲስ ሹመት ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ (Delivery Monitoring Unit) ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ይህ አዲሱ ሹመት መንግስት የጀመራቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች እና ቁልፍ አገራዊ የልማት ውጥኖችን አፈጻጸም በቅርበት ለመከታተልና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ አሰራር በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ ዘመናዊ መንግስታት መዋቅር ውስጥ የተለመደና በስፋት የሚተገበር ነው። የጽንሰ-ሀሳቡ ጀማሪ በ2001 (እ.ኤ.አ) የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ሲሆኑ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቃል የገቡትን ሥራ በተግባር መፈጸማቸውን የሚከታተልና ሪፖርት የሚያደርግ ገለልተኛ አካል በማቋቋም አሰራሩን ወደ ትግበራ አምጥተውታል። ይህንኑ ልምድ በመከተል ማሌዥያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ እንዲሁም በአፍሪካ እንደ ኬንያ እና ሴኔጋል ያሉ ሀገራት የመንግስትን ስራ አፈጻጸም ለማፋጠን ተመሳሳይ ቢሮዎችን በፕሬዝዳንቱ ወይም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ስር አቋቁመው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
የዚህ ዘርፍ ዋና ዓላማ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ወደ ተግባር መቀየር ሲሆን፣ የኃላፊው ዋነኛ ተግባርም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስፈጻሚ ክንድ በመሆን መስራት ነው። በዚህም መሰረት ዲያቆን ዳንኤል መንግስት በግብርና፣ ጤና፣ መሰረተ ልማት እና ሌሎችም ዘርፎች ቅድሚያ የሰጣቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ እና በጀት እየተከናወኑ መሆናቸውን በቅርበት ይከታተላሉ። በተጨማሪም በፕሮጀክቶች ላይ የቢሮክራሲ መጓተት ሲያጋጥም ወይም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የሥራ መደራረብና አለመግባባት ሲፈጠር በፍጥነት ጣልቃ በመግባት ማነቆዎችን የመፍታት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ከዚህ አኳያ የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን እና የተቋማትን አፈጻጸም በመረጃ እና በስታቲስቲክስ እየለካ ትክክለኛውን የመሬት ላይ እውነታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያደርጋል። በአጠቃላይ ይህ ሹመት የተቋማት ኃላፊዎች በወረቀት ላይ ካለው እቅድ ባለፈ ለህዝቡ የሚዳሰስ ውጤት እንዲያመጡ ግፊት የሚያደርግና ሚኒስትሮች የተሰጣቸውን የቤት ስራ ያለምንም ማመካኘት በተግባር ማቅረባቸውን የሚቆጣጠር ቁልፍ የሥራ መደብ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ይፋ የተደረገው የ2026ቱ የዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውር ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ የሰዎችን ዝውውር ለማስቆም የተቀመጡትን አነስተኛ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ባታሟላም፣ ጉልህ ጥረቶችን በማሳየቷ በደረጃ ሁለት (Tier 2) ላይ መቆየቷን አስታውቋል። መንግስት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን በመለየት፣ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅን በማሻሻል እና ተጎጂዎችን ወደ ሀገር በመመለስ ረገድ መሻሻሎችን ቢያሳይም፣ በህግ ማስከበር እና ወንጀለኞችን በመቅጣት በኩል ግን ክፍተቶች እንደታዩበት ሪፖርቱ አብራርቷል።
ሪፖርቱ በህግ ማስከበር ዘርፍ ያለውን ሁኔታ ሲገመግም፣ የኢትዮጵያ መንግስት በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚያደርገው ምርመራ እና ክስ መቀነሱን አመላክቷል። በ2025 ዓ.ም የተመዘገቡት የምርመራዎች ቁጥር 363 ሲሆን፣ ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት 470 ምርመራዎች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ አሳይቷል። በተመሳሳይ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ አዘዋዋሪዎች ቁጥር ከ340 ወደ 191 ዝቅ ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሙስና እና የባለስልጣናት ተባባሪነት ትልቅ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች ሰራተኞች ዜግነት ለሌላቸው ግለሰቦች ህገ-ወጥ ፓስፖርት በመስጠት ለህገ-ወጥ ዝውውር መጋለጥ ምክንያት ሆነው በመገኘታቸው፣ በምክትል ዳይሬክተሩ ላይ የስምንት ዓመት እስራት እና በሌሎችም ላይ ተመሳሳይ ቅጣቶች መተላለፉን አስታውሷል።
በሌላ በኩል ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ እና የህጻናት ምልመላ አሳሳቢ መረጃን አካቷል። ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ እንዳሰፈረው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ እንዲሁም እንደ ፋኖ፣ ሕወሓት (TPLF) እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ህጻናትን ከህግ ውጪ ለውትድርና እና ለተለያዩ የጦርነት ደጀን ተግባራት መጠቀማቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዚህ ዙሪያ የተወሰኑ ምርመራዎችን ቢያደርግም፣ መንግስት ወንጀለኞቹን በህግ ስለመጠየቁ ሪፖርት አላደረገም ብሏል።
በበጎ ጎኑ መንግስት የተጎጂዎችን ጥበቃ እና መከላከል ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉ ተነስቷል። ባለፈው ዓመት ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተመለሱ ከ142 ሺህ በላይ ተጋላጭ ዜጎችን አጣርቶ ድጋፍ አድርጓል። የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ስርዓት ለማስያዝም አዲስ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1389/2025) በማጽደቅ፣ ኤጀንሲዎች እንደየደረጃቸው ከ50 ሚሊዮን እስከ 250 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የመጠባበቂያ ገንዘብ እንዲያስቀምጡ አድርጓል። ይህ እርምጃ ሰራተኞች የህክምና እና ሌሎች ወጪዎችን ኤጀንሲዎች እንዲሸፍኑ በማድረግ ዜጎች ያለአግባብ እንዳይበዘበዙ ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ሪፖርቱ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አዳዲስ አዝማሚያዎችን የዳሰሰ ሲሆን፣ አዘዋዋሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን እና የውሸት የስራ እድሎችን በመጠቀም ወጣቶችን እያታለሉ መሆኑን አጋልጧል። በተለይም ኢትዮጵያውያን ወንዶች በደቡብ ምስራቅ እስያ (እንደ በርማ፣ ካምቦዲያ እና ላኦስ) በሚገኙ የበይነመረብ (ኦንላይን) ማጭበርበር ስራዎች ላይ በግዳጅ እንዲሰሩ እየተደረጉ መሆኑን፤ እንዲሁም ወጣት ሴቶች ወደ ሩሲያ የድሮን ማምረቻ ጣቢያዎች በተታለለ የስልጠና ስምሪት ተወስደው ብዝበዛ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ሪፖርቱ በስፋት ዘግቧል። በአገር ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ተፈናቃዮች እና ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ለዚህ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸውንም አክሎ አስጠንቅቋል።

1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባሳለፉት አዲስ የሹመት ውሳኔ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ አድርገው ሾመዋል። ይህ ሹመት መንግስት በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ እያደረገ ያለው ሰፋ ያለ ሽግሽግ አካል ነው።
እንደሚታወሰው ዘ-ሐበሻ ከሳምንት በፊት የውስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ፣ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ በቅርቡ ወደ ከፍተኛ የመንግስት ሹመት እንደሚመጡ ቀድሞ ለተከታታዮቹ አድርሶ ነበር። ተሿሚው ከዚህ ቀደም በመቄት ምርጫ ክልል 1 ለክልል ምክር ቤት በብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው ቀርበው እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊም::
አዲሱ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪነት የሥራ መደብ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት፣ የተቋማትን አሰራር የማሻሻል እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሒደቶችን በበላይነት የማስተባበር ቁልፍ ኃላፊነት የሚወስድ ይሆናል። አቶ ፍሰሃ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ መንግስት የጀመራቸውን የፖለቲካ ሪፎርሞች በቅርበት እንደሚከታተሉ ይጠበቃል።
____
ወቅታዊ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ቀድመው ለማግኘት የዘ-ሐበሻ ገጽን ፎሎው ማድረጋችሁን አትርሱ!

የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተደረገውን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተከትሎ በርካታ ተማሪዎችና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ባወጣው አዲስ የክፍያ ተመን፣ ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። በተጨማሪም በድህረ-ምረቃ መግቢያ፣ በ12ኛ ክፍል ፈተና እና በሌሎች የማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ተመሳሳይ የክፍያ ጭማሪ ተደርጓል።
በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፣ አዲሱ የክፍያ ተመን በተለይ ለሥራ አጥና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎችና ቤተሰቦች ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
በ2017 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስዳ እንዳልተሳካላት የገለጸች አንዲት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ፣ ለ16 ዓመታት የለፋችበት ትምህርት ውጤት አልባ ሆኖ እንዳይቀር በድጋሚ 750 ብር እየከፈለች ፈተናውን መውሰዷን ተናግራለች። አሁንም ስላልተሳካላት ለሦስተኛ ጊዜ ለመሞከር እያሰበች ቢሆንም፣ አዲሱ የክፍያ ተመን እንዳስደነገጣት ገልጻለች።
" 2,000 ብር መክፈል በጣም ከባድ ነው። ሥራ አጥ ነኝ፣ በጣም የሚያስጨንቅ ውሳኔ ነው። ለሦስተኛ ጊዜ ለመፈተን እያሰብኩ ነበር። አሁን ግን 2 ሺህ ከፍዬ ከመፈተን ይልቅ አለመፈተንን መርጫለሁ " ብላለች።
የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመጀመር እየሞከሩ ያሉ ተማሪዎችም የአገልግሎቱ አዲስ የክፍያ መጠን " ተስፋችንን የበለጠ አጨልሞታል፣ በትምህርት የሚያምኑ ሰዎችን ተስፋ የሚነጥቅ ነው " ብለዋል።
አንድ ተማሪ ለአገልግሎቱ 3,500 ብር እንዲከፈል መጠየቅ ምን ማለት ነው ? ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎቹ ትምህርት የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን ራስን ለማሳደግና ለማሻሻል የሚደረግ ነው። ታዲያ የተጋነነ ዋጋ እንድንከፍል የምንደረገው ለምንድን ነው ? " ብለዋል።
" የፈተናው ይዘት በራሱ የተማሪዎችን ችሎታ ለመመዘን አይመስልም " ያሉት ተማሪዎቹ ከ750 ብር ወደ 3,500 ብር ማሳደጉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዳይወስዱ እንቅፋት እንደሚሆን ገልጸዋል።
" አንዳንዴ ገቢ መሰብሰብ ብቻ የሚመስሉ አጋጣሚዎች አሉ " ሲሉ ወቅሰዋል።
ለጤና ባለሙያዎች አሁን ያለው ጊዜ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጸ ተማሪ ደግሞ " በኑሮ ውድነቱ ከዘርፉ እየወጣን ነበር፣ አሁን ጭራሽ በሙያው ላይ የበለጠ ተስፋ እንድንቆርጥ እያደረጉን ነው " ብሏል።
ሌላው ተማሪ ደግሞ፣ " 3,500 ብር ከፍሎ መፈተን በጣም ያስፈራል " ሲል፣ ለትምህርት የሚወጡ ወጪዎች ቢያንስ ሁሉንም ያማከሉ መሆን እንዳለባቸው ገልጿል።
" በፈተና መውደቅ አለመውደቅ የተፈታኙ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል። ቢያንስ ለመሞከር ግን እንደዚህ በሩ መጥበብ የለበትም " ብሏል።
ሌላ ተማሪ ደግሞ ሰዎች ትምህርት መማር እየፈለጉ ባላቸው ገቢና በኑሮ ውድነት ምክንያት መማር ካልቻሉ፣ ይህ ለሚመጣው ትውልድ የመማር ፍላጎትን ሊያወርድ እንደሚችል ገልጿል።
" ሰዎች እንዳይማሩ በዚህ ልክ ክፍያ መጠየቅ እንዴት ሊብራራ እንደሚችል አላውቅም! " ሲል ተናግሯል።
" ክፍያ የተጨመረበት ዓላማ ራሱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ተማሪ መሆን የሚፈልግ ነው ሁለተኛ ዲግሪውን የሚማረው፣ ስለዚህ ክፍያው ሁሉን ያማከለ ቢሆን ጥሩ ነው " ሲልም ሌላ ተማሪ ገልጿል።
የፈተናዎች ኤጀንሲ ያወጣውን አዲሱን የአገልግሎት ክፍያ መረጃ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ እንዳየ የገለጸ አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ፣ መረጃውን በተመለከተበት ወቅት " እውነት ለመናገር ደንግጫለሁ፣ የማዘን ስሜትም ተሰምቶኝ ነበር፤ ያልጠበኩት ውሳኔ ነው " ብሏል።
ተማሪው ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 950 ብር መጠየቁን አግባብነት የሌለው እንደሆነ ገልጿል።
" የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሥራው ትምህርት ነው፣ ክፍያ የለውም፣ ገቢ ወደሚያስገኝ ሥራ አልገባም፣ በቤተሰብ ላይ ጥገኞች ነን። ለፈተና ይሄን ያህል ክፈሉ ብሎ ሌላ ጫና መፍጠር፣ መክፈል በማይችሉት ላይ ችግር መፍጠር ነው " ብሏል።
አክሎም፣ " ተማሪዎችን የሚያገል ደንብ ነው። ፍትሐዊና ሁሉን ያማከለ አይደለም። ትምህርት የመማር መብት አለን፣ እንዳንማር የሚያደርጉ ውሳኔዎች ሊኖሩ አይገባም። አሁን ላይ ትምህርት ከመሠረታዊ መብትነት ይልቅ የተወሰኑ ገንዘብ ያላቸው የሀብታም ልጆች ብቻ እንዲማሩ እየተደረገ ነው " ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም የስም ስህተትን ጨምሮ እንደዚህ ያሉ ስህተቶችን ለማስተካከል የሚጠየቁ ክፍያዎች ሙሉ በሙሉ መቅረት እንዳለባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።
" በተቋማት በኩል በሚፈጠሩ ስህተቶች ተማሪዎች ልንጨነቅ አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ የአገልግሎቱ ምላሽ በዚህ ዘገባ ውስጥ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#tikvahethiopia
@tikvahethiopia የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች…

የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ እና ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት ያሟላ እንደሆነ ተገለጸ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ፣ ደህንነት እና ሚስጥራዊነት ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት እንደሚያሟላ በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል።
በተጨማሪም፤ ሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የታካሚዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓቶች እንደምትከተል አብራርተዋል።
የመጀመሪያው "ዲ ኤች አይ ኤስ ቱ" የተባለው ሥርዓት ሲሆን፣ በጤና ተቋማት የታካሚዎችን ጠቅላላ መረጃ የሚሰበስብና በሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚጋራ ነው።
ሁለተኛው "ኤሌክትሮኒክ ኮሚኒቲ ኸልዝ ኢንፎርሜሽን ሲስተም" ደግሞ በገጠር ጤና ኬላዎች የሚያገለግል ሲሆን፣ እስከ አሁን የ31 ሚሊዮን ሰዎችን የግል መረጃ መመዝገቡ ተጠቅሷል።
የታካሚዎችን የግል የጤና መረጃ ባለሙያዎች ብቻ እንዲመለከቱት ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ በብሔራዊ ደረጃ ቁጥራዊ መረጃዎችን ብቻ የሚያሳየው ይህ አሠራር፣ የዓለም ጤና ድርጅት የታካሚዎች መረጃ ደኅንነት ጥበቃ መስፈርትን እንደሚያሟላ ተገልጿል።
ሥርዓቱ የታካሚዎች የግል የጤና መረጃ ከጤና ተቋሙ ውጪ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በቪፒኤን በተሰኘ ኢንተርኔት በሌለባቸው አካባቢዎች ኢንተርኔት ለመጠቀም በሚያስችል ኔትወርክ እንዲሠራ መደረጉንም አቶ ገመቺስ አብራርተዋል።
በመሰረት ሙሉ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3

በ5 ዓመት ህፃን ላይ የጉልበት ብዝበዛና ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
በሸኮ ከተማ አስተዳደር 01 ቀጠና የጉልበት ብዝበዛና አካላዊ ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሏን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታውቋል
የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እንዳስታወቁት በ5 ዓመቷ ህፃን ሳራ ዘማች ላይ ብዝበዛና አካላዊ ጉዳት አድርሳለች ተብላ የተጠረጠረችው ግለሰብ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውላለች።
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በህፃኗ ላይ አካላዊ ጉዳት አድርሳለች ተብላ የተጠረጠረችው ግለሰብ በፈፀመችው ድርጊት ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።በጉዳዩ ላይ ፖሊስ ምንም ዓይነት እርምጃ አልወሰደም በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውንም ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ምርመራውን እያካሄደ መሆኑንም ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

ኩባ ከ11ሺ በላይ የዴንጊ ትኩሳት ታማሚዎችን መዘገበች
👉 ዴንጊ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣና በትንኞች ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ ከባድ የትኩሳት በሽታ ነው።
ኩባ እ›አ›አ በ2026 11ሺ 235 በበሽታው የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት መረጃ ላይ ተመስርቶ ከሚጠበቀው አማካይ መጠን ጋር ሲነፃፀር የ 9.2 እጥፍ ብልጫ እንዳለው የኢንፎቤ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡
በቅርብ ወራት ውስጥ የሕመምተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ የተነገረ ሲሆን በመስከረም ወር ብቻ 4,102 ተጠቂዎች ተመዝግበዋል።
የጥቅምት ወር በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የሕመምተኞች ቁጥር ሊጨምር የቻለው በደሴቲቱ ላይ ከከፋው የኃይል እና የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የመብራት መቋረጥ ቤተሰቦች በሞቃታማ ሌሊቶች በሮችንና መስኮቶችን ክፍት አድርገው እንዲተኙ አስገድዷቸዋል፤ ይህም ለትንኞች የመጋለጥ እድልን ሊጨምር ይችላል። የነዳጅ እጥረትም የትንኝ ማጥፋት ስራዎችን የጎዳ ሲሆን የትንኞችን ቁጥር የመቀነስ እና የበሽታውን ስርጭት የመከላከል ስራዎችን ገድቦታል።
አብዛኞቹ ታማሚዎች ያለ ከባድ ችግር የሚያገግሙ ቢሆንም፣ ከባድ የዴንጊ ህመም ግን ደም መፍሰስን፣ ድንገተኛ የደም ግፊት መውደቅን እና የሰውነት ክፍሎች ጉዳትን ሊያስከትል ስለሚችል ሆስፒታል መተኛትን ሊጠይቅ ይችላል ነው የተባለው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ዴንጊ በዓለም አቀፍ ደረጃ በትንኞች አማካኝነት ከሚተላለፉ የቫይረስ በሽታዎች መካከል በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመሩ ካሉት መካከል አንዱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡
ሰላማዊ ነጋሲ

የትምባሆ ኢንዱስትሪዎችን ጣልቃ-ገብነት ለመከላከል አዲስ ረቂቅ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
የትምባሆ ቁጥጥር ስራ በአንድ ተቋም ብቻ እንደማይሳካና የኢንዱስትሪዎችን ያልተገባ ጣልቃ-ገብነት ለመከላከል የተቀናጀ የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ ከማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ባካሄደው የ1ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ ከተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የኮሚቴ አባላት የቁጥጥር ሥራውን በተቋማቸው ዕቅድ ውስጥ አካተው እንዲመሩ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም ቁጥጥሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ክፍተቶችን ለመሙላት በተዘጋጀው አዲስ ብሔራዊ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደርጎ ግብዓት ተሰብስቧል።
ፋውንዴሽኑ በበኩሉ ከትንባሆ ነፃ የሆነች ሀገር ለመፍጠር የጀመረውን ተጋድሎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጹን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@Yenetube FikerAssefa

💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት የሽያጭ መረጃ;
የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው
👉ሌሎች ሳይቶች፦ በሳርቤት፣ አዋሬ፣ ቡልጋሪያ፣ ፒያሳ የመኖሪያና የንግድ ሱቆች/ቢሮዎች ይገኛሉ
💥💥💥(ባለ 2መኝታ)
💥99ካሬ*115,000ብር=11,385,000
20%ቅድመ ክፍያ =2,277,000
100%ስትከፍሉ35%ቅናሽ ከቅናሽ በኋላ =7,400,250ሙሉ ዋጋ ይሆናል
💥103ካሬ*125,000ብር =12,875,000ብር
ቅድመ ክፍያ 20%=2,575,000
100%ስትከፍሉ 35%ቅናሽ =8,368,750ብር
💥💥💥 (ባለ3መኝታ)
💥123ካሬ*125,000ብር=15,375,000ብር ሙሉ ክፍያ
ቅድመ ክፍያ 20%=3,075,000ብር
100%ለከፈለ ከሙሉ ክፍያ 35% ቅናሽ
ያማለት =9,993,750ብር ሙሉ ክፍያ ይሆናል
💥145ካሬ*125,000ብር =17,750,000ብር
ቅድመ ክፍያ 20% 3,550,000ብር
100%ለከፈለ 35% ቅናሽ ከቅናሽ በኋላ 11,537,000 ብር ይሆናል
🌟🌟ፔንታውስ ለምትፈልጉ🌟🌟
👇
💥 235*115,000=27,025,000ብር ይሆናል ።
ቅድመ ክፍያ 20%=5,405,000ብር
100%ለሚከፍል 18,917,500ብር ይሆናል
💥302ካሬ*115,000ብር =34,730,000birr
ቅድመ ክፍያ 20%=6,946,000ብር
100%ለሚከፍል 35% ቅናሽ ተደርጎ 24,311,000ብር ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ +251978791342

2 days ago
ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ይከበራል
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመጪው ሰኞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በድምቀት ይከበራል፡፡
ቀኑ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድምቀት እንደሚከበር የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

Comments