(ዘ-ሐበሻ ዜና) — በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደ ልዩ የዕውቅና እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ ጸደይ ባንክ አዲሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌውን ከተቀበለ በኋላ የፋይናንስ እና የአሰራር ለውጦችን ማስመዝገብ መቻሉን ገለጸ። ባንኩ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ይገጥመው የነበረውን የኪሳራ ታሪክ በመቀልበስ፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4.3 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት መቻሉ ተገልጿል።
በባንክ ኢንዱስትሪው ትልቅ ማነቆ የሆነውን የተበላሸ ብድር (Non-Performing Loans - NPL) መጠን በመቀነስ ረገድ ጸደይ ባንክ የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገብም ተነግሯል። ባለፈው በጀት ዓመት ከፍተኛ አደጋ በሚያመለክተው የ21 በመቶ ደረጃ ላይ የነበረው የተበላሸ ብድር ምጣኔ፣ በስድስት ወራት ውስጥ ወደ 6 በመቶ ዝቅ ብሎ የነበረ ሲሆን፤ አሁን በጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው አስገዳጅ የ5 በመቶ ጣሪያ በታች ማውረድ መቻሉ ተብራርቷል። ይህ ስኬት አዲሱ አመራር የብድር አመላለስ ሥርዓቱን ውጤታማ እና ጥብቅ በሆነ መንገድ በማሻሻሉ ነው ተብሏል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንኩን አጠቃላይ ግብ እና የሥራ ዕቅድ በማሳካት የላቀ ውጤት ላመጡ የሥራ ኃላፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም ተካሂዷል። ከእነዚህም መካከል የፍኖተሰላም ዲስትሪክት ማናጀር የሆኑት አቶ ደሳለኝ ወንዳለ ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ደሳለኝ በሁሉም ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች (KPIs) ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ልዩ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።
በዕለቱ የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን የለውወሰንም የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸዋል። ለባንኩ ባለፉት 30 ዓመታት አበረከቱት ለተባለው አገልግሎት "ዕውቅና ለመስጠት" ቶዮታ RAV4 Hybrid 2026 ሞዴል መኪና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችም ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩላቸው መደረጉን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ የውስጥ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ባንኩ በዚሁ መድረክ ላይ የረዥም ጊዜ የስትራቴጂክ ዕቅዱን እና ራዕዩንም ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት የባንኩ ቀጣይ ትልልቅ ግቦቼ የሚከተሉት ናቸው ብሏል፦
በአውሮፓውያኑ 2030 በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግዙፍ 4 የንግድ ባንኮች አንዱ መሆን።
በአውሮፓውያኑ 2040 ደግሞ የሀገር ውስጥ ገበያን አልፎ በመላው አፍሪካ ከሚገኙ 40 ምርጥ የንግድ ባንኮች ተርታ መሰለፍ።

3 days ago