2 months ago
አዲስ አበባ : በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡
የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል 5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡
ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
#addisababa #trafficaccident #ethiopiannews #bole #ethiopiapolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ለማግኘት
ባለጭምብሎቹ : የአምስት ታዳጊዎች መጨረሻ
#ethiopia | በአየርላንድ አውራ ጎዳና ላይ አምስት ታዳጊዎች ሕይወታቸውን ያጡበትና አንድን ቤተሰብ ለከባድ አደጋ የዳረገ አስከፊ የመኪና ግጭት ከመከሰቱ አስቀድሞ ታዳጊዎቹ አደገኛ አሽከርካሪነታቸውን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያሰራጩ እንደነበር ተገለጸ።
በአየርላንድ ኪልዳሬ ግዛት ኤም9 በተባለው አውራ ጎዳና ላይ አምስት ታዳጊዎች የተሳፈሩበት የተሰረቀ ቢኤምደብሊው መኪና ከሌላ የተሽከርካሪ ጋር በደረሰው የፊት ለፊት ግጭት የሁሉም ታዳጊዎች ሕይወት አልፏል።
አደጋው ከመከሰቱ አስቀድሞ ታዳጊዎቹ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በየአካባቢው ቤት በመስበር፣ መኪና በመስረቅ እና ከፖሊስ አሳዳጅነት ለማምለጥ የሻተሩባቸውን አደገኛ እንቅስቃሴዎች በቪዲዮ ቀርጸው በቲክቶክ እና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሲያሰራጩ እንደነበር ተረጋግጧል።
የሞቱት ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 18 ዓመት የሆኑ ሲሆን፣ አደጋው በደረሰበት ወቅት ሁሉም ፊታቸውን በደብቅ ጭንብል ሸፍነው እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።
ታዳጊዎቹ ከተቃራኒ አቅጣጫ በሚመጡ ተሽከርካሪዎች መስመር ላይ በፍጥነት በመንዳት እና ከፖሊስ አሳዳጅነት ሲያመልጡ የሚያሳዩ ምስሎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማሰራጨት እርስ በርስ ለመፎካከር ይሞክሩ እንደነበርም ተጠቅሷል።
በሌላኛው መኪና ውስጥ የነበሩ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ለሰርግ ወደ እንግሊዝ ለመጓዝ ወደ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ በመሄድ ላይ ሳሉ ለዚህ አደጋ ተዳርገዋል።
ተጎጂዎቹ ሦስት እህትማማቾች እና አንድ የሰባት ዓመት ህፃን ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል በከባድ ህክምና ላይ ይገኛሉ።
ድርጊቱ በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ለማግኘት ሲባል የሚደረግ እጅግ አደገኛና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት እና የፖሊስ አዛዦች ገልጸዋል።
የአየርላንድ ፍትህ ሚኒስትር በተቃራኒ አቅጣጫ የሚያሽከረክሩ መጨረሻቸው እስር ቤት ወይም መቃብር እንደሚሆንet በማስጠንቀቅ፣ መሰል ድርጊቶችን የሚያስቀጡ አዳዲስ ህጎችን ለማውጣት እየሰራን ነው ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ireland #kildare#trafficaccident#m9crash #roadsafety #crimenews #socialmedia #getutemesgen #getu#ጌጡ#ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
በአሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ 18 ተጓዦችን አሳፍሮ በጠረጋ ከተማ በኩል ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰዓታት በፊት ከመስመር ውጭ በመውጣት ወደ ገደል ወድቋል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።
በደረሰው አደጋ ምክንያት እናቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና አባቶችን ያካተቱ 11 ተጓዦች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከአሽከርካሪ ጋር ሌላ ሁለት ሰዎች በድምሩ ሦስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
በአንጻሩ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ተጓዦች ከአደጋው ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ለመትረፍ ችለዋል።
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች አስክሬን ከቡታጀራ ሆስፒታል ወደ ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማጓጓዝ ለቤተሰቦቻቸው የማስረከብ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቡታጀራ እና በወራቤ ሆስፒታሎች ተገቢውን የህክምና ክትትል እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል።
#trafficaccident #roadsafe #ethiopianews #wolaita #butajira #worabe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
ባቡርና ሲኖትራክ መካከል አደጋ ተከሰተ!
#ethiopia | ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡55 ሰዓት ላይ በየካ ክፍለ ከተማ ሰዓሊተ ምህረት አካባቢ በሚገኘው የባቡር መስመር ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሷል።
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ንብረት የሆነ ሲኖትራክ (ታርጋ ቁጥር 5-82D11-2) እና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር (ኮድ 111)።
ሲኖትራኩ ከላምበረት ወደ ጃክሮስ በሚጓዝበት ወቅት፣ ከአያት ወደ መገናኛ ይጓዝ ከነበረው ባቡር ጋር ተጋጭቷል።
በባቡሩ ውስጥ ተሳፍረው በነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ እያጣራ ሲሆን፣ በሲኖትራኩ ላይ ያለውን ከባድ ጭነት በማንሳት መንገዱን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን እንዲቆጣጠሩና ለመንገዱ አቀማመጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
#getu #addisababa #trafficaccident #lightrail #yeka #roadsafety #breakingnews #ethiopia #አዲስአበባ #ትራፊክአደጋ #ቀላልባቡር #ሰዓሊተምህረት #ጥንቃቄ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
6 months ago
በአዲስ አበባ ኮተቤ 02 አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ተከሰተ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ "አንቆርጫ" ተብሎ በሚጠራው ቁልቁለት መንገድ ላይ፣ ዛሬ ንጋት 11፡30 አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰው አካል እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ።
አደጋው የተከሰተው ከየረር ወደ አንቆርጫ በሚወስደው ቁልቁለት ላይ ሲሆን፣ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ ታክሲ የመንገድ አካፋይን ጥሶ በመገልበጡ ነው። የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እንዳረጋገጠው፣ ተሽከርካሪው በወቅቱ ከተፈቀደለት የሰው ቁጥር በላይ 19 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ ነበር።
የየካ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክሌ ካሳዬ እንደገለጹት፣ በአደጋው ሳቢያ በተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። የቴክኒክ ባለሙያዎች ባደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ፣ ተሽከርካሪው ከአቅሙ በላይ መጫኑ ለአደጋው መከሰትና ለጉዳቱ ስፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።
በአሁኑ ወቅት የፖሊስ የትራፊክ ምርመራ ክፍል የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ እያጣራ ይገኛል። አሽከርካሪዎች የትርፍ ጭነት የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ ተገንዝበው፣ የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #addisababa #trafficaccident #ethiopianews #yeka #roadsafety #breakingnews #አዲስአበባ #ትራፊክአደጋ #የካ

እየሄዱበት የነበረው መኪና ነዳጅ በመጨረሱ የተሳፈሩበት ሲኖትራክ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት አለፈ
📌በቄለም ወለጋ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ደንታ ወረዳ፣ ነዳጅ በጨረሰ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ምክንያት ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች በደረሰባቸው የመገልበጥ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ላይ ከደንቢ ዶሎ ከተማ ወደ አሺ ሙጌ ወረዳ ከ20 በላይ ተጓዦችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ "ዶልፊን" ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ነዳጅ ይጨርሳል። በዚህም ምክንያት ተጓዦቹ ጉዟቸውን ለመቀጠል አሸዋ ጭኖ ወደ ሙጊ ከተማ ይጓዝ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35460 ኢቲ በሆነ "ሴኖ ትራክ" የጭነት መኪና ላይ ለመሳፈር ተገደዋል።
የጭነት መኪናው ደንታ ቀበሌ "አባ ጃራ ቀረብቾ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ ሲደርስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የሚከተሉት ጉዳቶች ደርሰዋል፦
የ8 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 6 ወንዶች እና 2 ሴቶች (ሁለቱ ሕፃናት ናቸው) ይገኙበታል።
በ12 ሰዎች ላይ (7 ወንዶች እና 5 ሴቶች) ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ተጓዦች በደንቢ ዶሎ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
አደጋውን ያደረሰው የሴኖ ትራኩ አሽከርካሪ ለጊዜው ከአካባቢው ቢሰወርም፣ ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል ሲል የዘገበው ብስራት ኤፍ ኤም ነው።
እንዲህ ያሉ አሳዛኝ አደጋዎች እንዳይደገሙ አሽከርካሪዎች የቴክኒክና የነዳጅ ዝግጅታቸውን አስቀድመው እንዲፈትሹ፣ ተጓዦችም ለጭነት ተብለው በተዘጋጁ መኪኖች ላይ ከመሳፈር እንዲቆጠቡ መልእክት ተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #trafficaccident #wollega #news #safetyfirst #ቄለምወለጋ #ትራፊክአደጋ

8 months ago
በምዕራብ አርሲ ዞን የደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ
#ethiopia | በምዕራብ አርሲ ዞን ነሲቦ ወረዳ "አመሽቃ" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በ35 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
የአደጋው ዝርዝር፦
* ቀን፦ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ከሰዓት በኋላ)
* መነሻና መድረሻ፦ ከደላ ከተማ ወደ ወረቃ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ
* የተሽከርካሪ ዓይነት፦ 40 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ
* ምክንያት፦ ተሽከርካሪው በገጠመው ድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መገልበጡ ተገልጿል።
የተጎጂዎች ሁኔታ፦
በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 35 ተጓዦች በአሁኑ ወቅት በሻሸመኔ እና በነሲቦ ሆስፒታሎች አስፈላጊው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች መሰል አደጋዎችን ለመከላከል የቴክኒክ ምርመራን በወቅቱ እንዲያደርጉና ጥንቃቄ እንዲጨምሩ መልዕክት ተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ብስራትሬዲዮ #ኢትዮጵያ #ትራፊክአደጋ #ምዕራብአርሲ #ነሲቦ #ዜና #ethiopia #trafficaccident

9 months ago
💔 በሐዋሳ የሁለት ሙሽሮችን ህይወት የቀጠፈው አሰቃቂ አደጋ
#ethiopia | ዛሬ ንጋት ላይ በሐዋሳ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ፣ ገና የጫጉላ ጊዜያቸውን እያሳለፉ የነበሩ ሁለት ሙሽሮችን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ተሰማ።
🏠 የሞት ግብዣ በመኝታ ቤት
አደጋው የተከሰተው ከሐዋሳ ወደ ሰደ ቦረ ዕቃ ጭኖ ይጓዝ የነበረ አንድ "አይሱዙ" የጭነት መኪና መንገድ ስቶ አጥር በመጣስ የሙሽሮቹን መኝታ ቤት ሰብሮ በመግባቱ ነው። ጥንዶቹ በሰላም ተኝተው በነበረበት ወቅት መኪናው ቤቱን ሰብሮ በመግባቱ በቅጽበት ህይወታቸው አልፏል።
በአደጋው የሟቾች ዝርዝር፦
* ሁለቱ ሙሽሮች፦ በጫጉላ ጊዜያቸው የነበሩት ጥንዶች በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ።
* ሁለቱ በመኪናው ውስጥ የነበሩ፦ የጭነት መኪናው አሽከርካሪ እና ረዳቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
⚠️ መንስኤውና የነዋሪዎች ቅሬታ
የዓይን እማኞች እንደሚሉት አደጋው የደረሰው መኪናው በከፍተኛ ፍጥነት ይጓዝ ስለነበር አሽከርካሪው መቆጣጠር በማቃቱ ነው።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት፣ መንገዱ ለመኖሪያ ቤቶች እጅግ ቅርብ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ፍጥነት እንዲቀንሱ የሚያስገድድ የፍጥነት ገደብ ምልክት ወይም የፍጥነት መቆጣጠሪያ (Bumps) እንዲደረግ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቢቆዩም ምላሽ አለማግኘታቸውን በምሬት ይናገራሉ።
ይህ አደጋ የፍጥነት ወሰን ማክበር እና የመንገድ ደህንነት ጥንቃቄ ምን ያህል የሰው ህይወትን ለመታደግ ወሳኝ መሆኑን ዳግም ያሳሰበ ክስተት ሆኗል።
ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ሐዋሳ #የትራፊክአደጋ #ሀዘን #ኢትዮጵያ #የመንገድደህንነት #hawassa #trafficaccident #ethiopia

⚫️ እጅግ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ዜና! 😭
#ethiopia ከከሚሴ ወደ ደብረ ብርሀን በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የሰው ህይወት አልፏል።
የአደጋው ዝርዝር፡-
መነሻና መድረሻ፡ ከከሚሴ - ደብረ ብርሀን
የታርጋ ቁጥር፡ ኮድ 3 - 11026 አማ
የአደጋው ቦታ፡ በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ፣ ጨረቲ ከተማ
በዚህ አሳዛኝ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፤ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
ህይወታቸው ላለፈው ወገን ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአት ይሙትልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን። ጉዳት ለደረሰባቸውም ፈጣሪ ፈውስን ይስጥልን።
አሽከርካሪዎች እባካችሁ በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ ለህይወት ክብር በመስጠት በጥንቃቄ አሽከርክሩ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#trafficaccident #kemise #debrebirhan #artumafursi #ethiopia

Comments