Logo
Getu Temesgen
10 ሺህ ዜጎችን ተደራሽ የሚያደርገው ነጻ የሕክምና አገልግሎት
#ethiopia | በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ1 ሳምንት የሚቆይ የነጻ ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡

ነጻ የሕክምና አገልግሎቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል ሲሆን ለ10 ሺህ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን የሆስፒታሉ የጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ወኪል ወልዴ ገልጸዋል፡፡

ሆስፒታሉ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በተዘጋጀበት ወቅት ባለፈው ወር ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከሰቱን ያስታወሱት ዶ/ር ወኪል ፤ በፈተናም ውስጥ ቢሆን ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ነው የተናገሩት።

በጎ ፈቃደነኛ ሐኪሞችን ጨምሮ መደበኛ ሐኪሞች ከሥራ ሰዓት ውጪ ይህንን ሥራ እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።

አገልግሎቱን ከበጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች ጋር በቅንጅት መስጠት መቻሉ የዘንድሮውን መርሐ-ግብር ለየት እንደሚያደርገውም ነው አክለው የገለጹት።

የራዲዮ ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት መስራች ዶ/ር ልሳነወርቅ ሆንሴቦ በበኩላቸው ይህ ሥራ 14ኛ የዘመቻ ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ በአንድ ሳምንት ቆይታ ለ10 ሺህ ሰዎች ነጻ ምርመራና የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ስፔሻሊስቶችን ጨምሮ 15 የሕክምና ባለሙያዎች በነጻ አገልግሎቱ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት ሕክምናው ወጪ እና ጊዜ የሚቆጥብ ከመሆኑ ባሻገር፣ የጤና ሁኔታቸውን ለይተው እንዲያውቁ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

በተመስገን ተስፋዬ
#ebc #freemedicalservice #wolaita

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.