4 months ago
በአሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ 18 ተጓዦችን አሳፍሮ በጠረጋ ከተማ በኩል ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰዓታት በፊት ከመስመር ውጭ በመውጣት ወደ ገደል ወድቋል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።
በደረሰው አደጋ ምክንያት እናቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና አባቶችን ያካተቱ 11 ተጓዦች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከአሽከርካሪ ጋር ሌላ ሁለት ሰዎች በድምሩ ሦስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
በአንጻሩ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ተጓዦች ከአደጋው ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ለመትረፍ ችለዋል።
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች አስክሬን ከቡታጀራ ሆስፒታል ወደ ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማጓጓዝ ለቤተሰቦቻቸው የማስረከብ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቡታጀራ እና በወራቤ ሆስፒታሎች ተገቢውን የህክምና ክትትል እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል።
#trafficaccident #roadsafe #ethiopianews #wolaita #butajira #worabe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
በቡታጅራ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቁ
***************************
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ በአጭር ጊዜ በጥራት ግንባታቸው የተጠናቀቁ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት እነዚህ ፕሮጀክቶች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን፣ ለቀጣይ ሥራዎች ውጤታማነት ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ፣ የከተማዋን ልማትና ዕድገት እንዲሁም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸው ተገልጿል።
በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁት የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የ 8 ነጥብ 35 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት፣ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የማኅበረሰብ አቀፍ የሕዝብ መድኃኒት መደብር፣ የልጆች መዝናኛ ማዕከል፣ ሴራና ባህል ቤት፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት፣ የዋናው መንገድ ስማርት ፖል እንዲሁም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ በከተማዋ በቀጣይ ለሚገነቡ የጤና ጣቢያ እና የስታዲየም ግንባታ ማስጀመሪያ የሚሆን የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የቡታጅራ ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው።
ከተማዋን አሁን በተጀመረው ፍጥነት ማሳደግ ከተቻለ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል እንደምትሆን ጽኑ እምነታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ቡታጅራ በብዝሃነት የደመቀች ከተማ መሆኗን ተከትሎ የሰላም ተምሳሌት በማድረግ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ እንድትሆን መሥራትና የከተማውን ገቢ አሟጦ በመጠቀም የልማት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሐሰን፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የከተማና የወረዳ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
#ethiopia #butajira #development #centralethiopia #regionalnews

Comments