Logo
Getu Temesgen
"አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት"
በጎ አድራጎት ማህበር የተፈናቀሉ እናቶችን ማዕድ አጋራ

​• ከ200,000 ብር በላይ በሆነ ወጪ ድጋፍ ተደረገ
#ethiopia | ​"አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት" በጎ አድራጎት ማህበር፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ሰፍረው ለሚገኙ አቅመ ደካማ እናቶች እስከ መኖሪያ ስፍራቸው ድረስ በመጓዝ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

​ማህበሩ ከ201,000 (ሁለት መቶ አንድ ሺህ) ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገዛውን ዘይት እና ዱቄት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስረክቧል።

​የኃላፊዎች መልዕክት፡-

​👤 ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ (የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር)፦

በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ "እንደዚህ ዓይነት በጎ ተግባራት በዞኑ ውስጥ በሚሰሩ ማህበራትና ግለሰቦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የመንግስት ድጋፍና ክትትል አይለያቸውም" ብለዋል።

​👤 ወጣት ስንታየሁ ሾላቶ (የማህበሩ ሰብሳቢ)፦

ማህበሩ ድንበር የሌለው እና ሰብዓዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል። "ከትንሽ የበጎ ተግባራት ተነስቶ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት እያተረፈ ወደዚህ ደረጃ ደርሷል" ያሉት ሰብሳቢው፤ በቀጣይም ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ሰፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ስራዎችን ለመስራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።

​በጎነት ለራስ ነው!

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#wolaita #charity #andenjeraleanditenat #humanity #abelaabaya #ethiopia

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.