Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

"የኢንዱስትሪ ጉዟችን የውስጥ ዐቅምን አሟጦ መጠቀምና አስፈላጊ ዐቅሞችን መገንባትን ማዕከል ያደረገ ነው። በዚህም የመጀመሪያው ጥቅል ግባችን በገቢ ንግድ (Import) ወደ ሀገራችን የሚጎርፉ ሸቀጦችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት አካሄድ ነው። የብዙ ጥሬ ዕቃዎች አምራች ብንሆንም፣ እነዚህን ግብዓቶች ተጠቅመው የሚሠሩ ምርቶችን መልሰን በውድ ዋጋ ከውጭ ሀገራት የምናስገባ ሀገር ነን።

ይህንን እውነታ ሥርዓት በያዘ መልኩ መቀየር እስካልቻልን ድረስ፣ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪ መገንባት አንችልም። ሁለተኛው ጥቅል ግብ ደግሞ የወጪ ንግድ (Export) ቀጥታ ጥሬ ዕቃ ከመሸጥ አልፎ፣ ዕሴት የታከለባቸው ምርቶችን ማቅረብን፣ ከዚያም ሲያልፍ ያለቀላቸው ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለተጠቃሚዎች ማቅረብን ዓላማ ያደረገ ነው።"

የመደመር መንግሥት
ገፅ 215

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ebc #መደመር #medemer #ኢንዱስትሪ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.