Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

ትዕይንታዊ ሀብቶቻችንም ለብዙ ዘመናት ባህላዊና ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ሲከወኑ የኖሩ የኢትዮጵያ የቱሪስት መስሕቦች ናቸው። የሕዝቦችን ትውውቅና ትሥሥር ለሚያሳድጉ፣ ባህልንና ቅርስን ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ የዘመን መለወጫዎች፤ የጥምቀት፣ የኢሬቻ፥ የአረፋ፤ የአዊ የፈረሰኞች ትርዒት፣ ዓይነቶቹን የያዘ ነው። ከኪነ ጥበባዊ ቅርሶችም አኳያ ሀገራችን የሙዚቃ፣ የሥዕል፣ የቅርጻ ቅርጽ፣ ሀብታም ናት።

ኢትዮጵያ ከዋሻ ላይ ሥዕሎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ሥዕሎች ድረስ ከ5ሺ ዘመን የበለጠ የሥነ ሥዕል ታሪክ አላት። የተቀመረና በኖታ የተገለጠ ዜማ በማዘጋጀት ከዓለም ቀደምቶቹ ተራ የሚያሰልፋት የቅዱስ ያሬድ ዜማ ባለቤት ናት።

በየብሔረሰቡ ዘንድ ልዩ ልዩ የጭፈራ፣ የዜማ ስልትና የሙዚቃ መሣሪያዎች ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በየአርኬዎሎጂው ቦታ ከተገኙት ቅርጻ ቅርጾች አንሥቶ በየብሔረሰቡ እስካሎት የቅርጽ ጥበቦች የተሞላች ናት።

የመደመር መንግስት
ገጽ 263

Ethiopian Broadcasting Corporation #medemer #ethiopia #አረፋ #መደመር #ኢትዮጵያ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.