የመደመር አንቀጽ
የሀገር ደኅንነትና የመገናኛ ሥርዓቶችም በከፍተኛ ደረጃ ተቆራኝተዋል። ማኅበራዊ መገናኛ በሀገራት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖም ከፍተኛ ሆኗል። የፈጠራና የሐሰት ወሬዎች ከየትኛውም የዓለም ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በሰከንዶች እስከ ማስተላለፍ ተደርሷል። የዲጂታል ቴክኖሎጂና የማኅበራዊ መገናኛ ዕድገት እውነትን ከሐሰት አምታትቶታል። የጥልቅ ማመሳሰል (Deepfake) ዘመን እውነትና ሐሰት ልዩነቱ ጠፍቶ፤ የትርክት ፉክክር የሀገራትን ፖለቲካ መረጋጋት ነሥቶታል።
ቴክኖሎጂና ማኅበራዊ መገናኛ በሀገራት ፖለቲካ ውስጥ ተዋንያኑ ብዙ እንዲሆኑ አድርገዋል። አለመረጋጋትን መፍጠር ለሚፈልጉ ኃይሎች ድንበር ሳይሻገሩና ጦር ሳያዘምቱ የሀገራትን ፖለቲካ እንዲንጡ ዐቅም ሰጥቷቸዋል። ሀገራትን ለማውደምና ለማንበርከክ የሚደረግ ጦርነትም ሕንጻንና ከተማን ከማፍረስ ጭንቅላትን ወደ መስለብና ወደ ማፍረስ ማዕከሉን ቀይሯል። ጥይት ሳይተኩሱና ሕንጻ ሳያወድሙ፣ በማኅበራዊ መገናኛ የሚለቀቁ የሐሰት ወሬዎች፣ ሀገር ወደ ማፍረስ ተሸጋግረዋል።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 16
Ethiopian Broadcasting Corporation #abiyahmed #ethiopia #medemer #ebc #fakenews #deepfakes

27 days ago