Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ከሁሉም በላይ በፋብሪካ ምሕንድስናና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የበቃ የሰው ኃይል ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡ ለዘርፉ የሚደረጉ ሥልጠናዎች ከተግባር ጋር የተያያዙ መሆን አለባቸው፡፡ እነርሱም ቴክኖሎጂን የማሸጋገር፣ የማለማመድና የመፍጠር፣ የመተርጎምና የመተግበር ክሂሎት ያለው የሰው ኃይል በማብቃት ላይ ማተኮር ይገባቸዋል።

ቴክኖሎጂ በአምራች ኢንዱስትሪው የነበረውን ምርት ለመተካት ይረዳል። አዲስ ምርት ለማምረት ወይም የነበረውን ለማዘመን ይችላል። በአዲስ የማምረት ሂደት ከፍተኛ ምርታማነት እንዲመዘገብ ያደርጋል። ተለጣጭነትንና የማምረት ሀቅምን በመገንባት የማምረት ወጪን ይቀንሳል። ጥራትና ጊዜን በመቀየር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ የዕሴት ጭማሪ ለማስገኘትና የተወዳደሪነትን ዐቅም ለማጎልበት ያግዛል።

የመደመር መንግስት
ገጽ 208/209

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ebc #መደመር #medemer

19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.