Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

የምንገኘው የዓለም ዋነኛ የንግድ ኮሪደር በሆነው ሥፍራ አካባቢ ነው። የቀይ ባሕር አካባቢ የምሥራቁንና የምዕራቡን ዓለም አገናኝ ወሽመጥ ነው። በመሆኑም የአፍሪካና እስያ መገናኛ ድልድይ ነን። ይህንን ግን ለዕድገታችን አላዋልነውም። እንደ ሲንጋፖር ያሉት ሀገራት አካባቢያቸው የሰጣቸውን ትሩፋት ተጠቅመው በልጽገዋል። አካባቢያቸው የሰጣቸውን ተጽዕኖ የመፍጠር ትሩፋት ለዕድገታቸው ግብአት ያደረጉ ሌሎችም በርካታ ሀገራት አሉ። ሀገራችን በአንጻሩ በአፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ለዕድገቷ ግብዐትነት በሚገባ አልተጠቀመችውም።

የመደመር መንግሥት
ገጽ 53

Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc #ቀይባሕር #የባሕርበር

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.