ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት ለሕፃናት የሚሰጥ የነጻ ቀዶ ጥገና ዘመቻ ተጀመረ
#ethiopia | የአራዳ ጊዮርጊስ የአንገት በላይ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻላይዝድ ሕክምና ማዕከል በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ በቀዶ ጥገና መጠባበቂያ ዝርዝር ውስጥ ይገኙ ለነበሩ ሕፃናት ነጻ ሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳወቀ።
በዳግማዊ ምኒሊክ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በአራዳ ጊዮርጊስ ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል ትብብር ለሦስት ቀናት በሚቆየው የበጎ አድራጎት ዘመቻ፣ በሕክምና ወረፋ ላይ የሚገኙ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ አጣዳፊ የጤና ችግር ያለባቸውን ሕፃናት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ በጠቅላላው ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት ተገልጿል።
በአራዳ ጊዮርጊስ ማዕከል የአንገት በላይ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ኃይለማርያም ታፈሰ እንደገለጹት፤ በሕፃናት ላይ የሚከሰተው የቶንሲል እና ከአፍንጫ ጀርባ የሚወጣ የሥጋ እብጠት (አዴኖይድ) የአየር መተላለፊያን በማጥበብ በሌሊት የመታፈን፣ የማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ማጣት ችግሮችን ያስከትላል።
አክለውም ሕመሙ ሳይታከም ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ለልብ ቫልቭ ጉዳት እና ለልብ ድካም የመጋለጥ ዕድልን እንደሚጨምር ጠቁመው፣ ቀዶ ጥገናው እነዚህን ከባድ የጤና ችግሮች አስቀድሞ ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።
በመንግሥት ሆስፒታሎች ያለውን የአልጋ፣ የቁሳቁስ እና የሰው ኃይል እጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀው ይህ ዘመቻ፤ ሕፃናቱ የክረምት የእረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው ታክመው እንዲያገግሙ እና ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ዶክተር ኃይለማርያም ጨምረው ገልጸዋል።
የአራዳ ጊዮርጊስ የአንገት በላይ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻላይዝድ ሕክምና ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብይ ደስታ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ይህ የበጎ አድራጎት ሥራ የግል እና የመንግሥት ዘርፍ አጋርነትን የሚያጠናክር ሲሆን፣ ማዕከሉ ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎችን እና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመመደብ የመንግሥት ሆስፒታሎችን ጫና ለመቀነስ እየሰራ ይገኛል።
የነጻ ቀዶ ጥገና መርሃ ግብሩ የመጀመሪያ ዙር በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ዙር ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
በጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#healthcareethiopia #publicprivatepartnership
#aradagorgorismedicalcenter #addisababa
#menelikhospital #tonsillectomy
#adenoidectomy #childhealthcare

2 months ago