3 months ago
10ኛው የኢትዮ ሄልዝ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ጉባኤ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ ለማዘመንና የሕክምና ግብዓቶችን አቅርቦት ለማሳለጥ ያለመው 10ኛው የኢትዮ ሄልዝ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ጉባኤ፣ እንዲሁም 2ኛው የአገር ውስጥ የሕክምና ግብዓቶች ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ከመጋቢት 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።
በዚህ መድረክ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና በፕራና ኤቨንትስ አዘጋጅነት የሚቀርብ ሲሆን፣ ከስምንት አገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለታዳሚዎች ያቀርባሉ።
በኤግዚቢሽኑ ላይ ከእንግሊዝ፣ ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከታይላንድ፣ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና ከአሜሪካ የመጡ ታዋቂ ድርጅቶች የሚሳተፉ በመሆኑ፣ የውጭውን ቴክኖሎጂ ከአገር ውስጥ አምራቾች ጋር ለማስተሳሰርና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከንግድ ትርኢቱ ጎን ለጎን የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ከ40 በላይ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማሳደጊያ (CPD) ስልጠናዎች የሚሰጡ ሲሆን፣ ከ20 በላይ የሚሆኑ የዘርፉ የሙያ ማህበራትም በዝግጅቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
በተጨማሪም የጤና አመራር ጉባኤ፣ የዲጂታል ሄልዝ ፎረም እና የሳይንሳዊ መድረኮች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በጤናው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን በምርምርና በቴክኖሎጂ ለመፍታት የሚያስችሉ ምክክሮች የሚደረጉባቸው መድረኮች ይሆናሉ።
ይህ ዝግጅት በተለይም የሀገር ውስጥ የሕክምና መሣሪያዎችና የመድኃኒት አምራቾች ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ድርሻ እንዲያሳድጉና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) እና በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት ሙሉ እውቅናና ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ጉባኤ፣ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና ይጫወታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiohealth2026 #healthcareethiopia #medicalexhibition #pranaevents #ahri #digitalhealth #medicalinnovation #ethiopiahealthconference

5 months ago
6ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር፣ ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ ከጥር 19 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው!!
በሀገራችን የፈርኒቸር ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ዘርፍ ትልቅ ድርሻ ያለው “6ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር፣ ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ” ከጥር 19 እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለ 4 ተከታታይ ቀናት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ።
ይህ ታላቅ ኤክስፖ በዋናነት በፈርኒቸር አምራቾች፣ በቤተ-ውበት እና በግንባታ አጨራረስ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሰፊ የገበያ አማራጭ ይዞ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በርካታ አምራቾች እና አስመጪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በኤክስፖው ላይ የሚሳተፉ ዋና ዋና ዘርፎች፦
• የፈርኒቸር (Furniture) እና የቤተ ውበት (Interior design) ውጤቶች፣
• የሴራሚክስ (Ceramics)፣ የወለል ንጣፎች (Flooring) እና የጣራ ክዳን (Roofing) ምርቶች፣
• ቀለሞች (Paint) እና ዘመናዊ የመብራት (Lighting) ስርዓቶች፣
• የመታጠቢያ ቤት ማጠናቀቂያዎች (Bathroom finishing materials) ፣
• የስፖንጅና የፍራሽ (Foam & Mattress) ምርቶች እና ሌሎችም የግንባታ ማጠናቀቂያ ግብዓቶች በስፋት ለእይታ ይቀርባሉ።
እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ፣ ኤክስፖው የመንግስት የግዢ ቢሮዎች፣ አርክቴክቶች፣ ስራ ተቋራጮች፣ የሪል ስቴት አልሚዎች እንዲሁም የሆቴል እና የትምህርት ቤት ግንቢዎች ከአምራቾች ጋር ቀጥተኛ የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ይህንን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ እንደተለመደው ፕራና ኢቨንትስ (Prana Events) ከአፍሪካ ትረስትድ ፓርትነርስ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፣ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ግለሰብ በነፃ መጎብኘት እንደሚችል ታውቋል።
ተጨማሪ መረጃ፡ ኤክስፖውን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ሁሉ በድረ-ገጽ https://pranaevents.net/fi... ቀድመው እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል።

Comments