23 days ago
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ አድጓል
**********************
የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት መጠኑ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ ማደጉን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው ከ7ኛ ስብሰባው በኋላ በሰጠው መግለጫ እንዳብራራው፥ በሐምሌ ወር 2016 ተግባራዊ ከተደረገው ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማግስት ሀገራችን በአጠቃላይ የውጭ ኢኮኖሚ ሚዛን ትርፍ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው ጉድለት አንፃር ሲታይ ዘርፉ ከፍተኛ መሻሻል ላይ መሆኑን ያመላክታል።
አጠቃላይ የማሻሻያ እርምጃዎቹ የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነትን እና የውጭ ምንዛሪ ገቢን በማሳደግ የውጭ ኢኮኖሚ ዘርፉን ዘላቂነት እያረጋገጡ መሆኑ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የሸቀጦች ወጪ ንግድ ገቢ በሶስት እጥፍ ማደግ፣ እንዲሁም በግለሰቦች እና በመንግሥት የሃዋላ ፍሰት ላይ የታየው አበረታች መሻሻል የሸቀጦች ገቢ ንግድ መጨመርን በከፊል እንዲያካክስ ረድቶታል።
በዚህም የተነሳ በ2016 በጀት ዓመት 6.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሶ የነበረው የሂሳብ ሚዛን ጉድለት በ2018 በጀት ዓመት ወደ 1.8 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ መቻሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የካፒታል ሂሳብ ትርፍ ለአጠቃላይ የክፍያ ሚዛኑ መሻሻል የጎላ አስተዋፅዖ ማበርከቱ ተገልጿል።
ኮሚቴው የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) የሐምሌ 2018 ትንበያ ዋቢ በማድረግ እንደገመገመው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት ቀደም ሲል ሲጠበቅ የነበረው የተረጋጋ የዓለም ኢኮኖሚ አቅጣጫ እንዲዛባ አድርጓል።
በመሆኑም ዓለም አቀፍ ዕድገት በ2026 ወደ 3.0 በመቶ እንደሚቀንስ እና በ2027 ደግሞ መጠነኛ መሻሻል በማሳየት 3.4 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዮአል።
በተመሳሳይ፣ አጠቃላይ የዓለም የዋጋ ግሽበት በ2026 ወደ 4.7 በመቶ ጭማሪ ካሳየ በኋላ በ2027 ወደ 3.9 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአለመረጋጋት ስጋቶች አሁንም ድረስ መቀጠላቸውን ኮሚቴው አስገንዝቧል።
#ethiopia #ebc #nationalbankofethiopia #foreignexchange #economicreform #macroeconomics #exportgrowth #imf #globaleconomy

2 months ago
Comments