1 month ago
የሀረሩ ጃፓን!
የአገር ኩራት!
ያንዳንድ ሰው እድል ደሞ ይገርማል፡፡
የሀረሩ ጃፓን እንድል አሰኝቶኛል፡፡
ይህ የእውቁ ቢሊየነር የሮክፌለር መነሻ፤ መናገሻ ነው ኢስት ክሊቭላንድ ከተማ።
ሰውየው ደግሞ እስኪገርመኝ የነካኸው ይስፋ የተባለለት አይነት ነው።
“የአንዳንድ ሰው እድል ደግሞ ጉደኛ ነው፣” ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል።
ግራ ቢገባኝ ነው የሀረሩ #ጃፓን ማለቴ።
በአሜሪካ አገር ከፊት ከሚቆሙ በጣት የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ባለሃብቶች አንዱ ነው፡፡
የአለም ቀን መጀመሪያ የምስራቁ ክፍል መነሻ አገር ጥንቁቅ ወግ እና ባህል ለሚረዱ ነገሩ ይገባል፡፡
የጃፓኖች አመጋገብ ሆነ የምግብ ዝግጅት የተለየ ግምት የሚወስድ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
ለዚህም ነው በጃፓን ምግብ ስራ ለመሰማራት እንኳን ሌላ ጃፓናዊ እራሱ ሁለት ሶስቴ ማሰብ ይጠበቅበታል የሚባለው፡፡
ቢዝነስ እና ድፍረት ግን ያወጣል! እንዲል መርሁ
በምስራቅ አፍሪካ ከምስራቋ ታሪካዊ ከተማ ሀረር የፈለቀው ሰው ወደዚህ ቢዝነስ ሲገባ ውሳኔው የቢዝነስ ድፍረት ነበር፡፡
ጀመረው፤ እናም ብዙዎች ይሆንልኛል ብለው የማያስቡትን የጃፓን ጣእም አመጣው!
ተሳካለት!
የምወደውን ምግብ ለመመገብ ከባልደረቦቼ ጋር ጃፓን ሬስቶራንት ሄድኩኝ አለ ጨዋታው ሲነሳ፡፡
በምኖርበት ክሊቭላንድ ከተማ ወደሚገኝ የጃፓን ቴርያኪ ሬስቶራንት አቀናሁ የተመኘሁትን ለማግኘት ግን እንዳሰብኩት አልቀናኝም ይላል ለማ ጌታቸው፡፡
“ምግብ ልበላ ሄጄ ወረፋ አላስደርስ አለኝ፡፡ ያኔ ወሰንኩ።” የሚለው የተለያዩ ግዙፍ ቢዝነሶች ባለቤት፤ አስቦት በማያውቀው ነገር ግን ገንዘብ እንደሚያመጣ ቀልቡ በነገረው የምግብ ቢዝነስ ለዛውም ትልቅ ግምት በሚሰጠው የጃፓን ማእድ ስራ ሊሰማራ ወሰነ፡፡
እውነቱን ነው!
የሞላ ገበያ መገለጫዋ በሆነችው አገረ አሜሪካ ‘የምን ወረፋ ነው? የምን እጥረት?’
ቀልቡ ነገረው፡፡ እሱም አመነው፡፡ “ቢዝነሱ ተጨማሪ ዘዋሪ ይፈልጋል፣” ሲል ወሰነ በቀዝቃዛማዋ ኦሃዮ ግዛት የሞቀ የንግድ ህይወት የሚዘውረው ለማ፡፡
ቀልጣፋው የሃረር ልጅ ዘየደ። አንድ ወዳጁ ጋር ደወለ።
“ስማ ወዳጄ የፈጀውን ይፍጅ እስቲ ሁነኛ የጃፓን ሼፍ ፈልግልኝ፣” አለ፡፡ ተገኘ፡፡
መኖር ደጉ ጨላውን አወጣ! በሮክፌለር የቢዝነስ መነሻ ሰፈር፤ ኢስት ክሊቭላንድ ሬስቶራንቱ የሚከፈትበትን ቦታ ገዛው፡፡
አቦ ይመቸው!
ቢዝነሱ ተጀመረ። ተከፈተ፡፡ ተሳካ! መሳካት ብቻ አይደለም ሞቀ። በቅርንጫፎች ሰፋ፤ ደመቀ።
እንደ መደበኛ ተመጋቢ ምናልባት በወራት አንዴ ይሄድ እንደሆን እንጂ ዛሬ ቢዝነሱ እሱን አይፈልግም፡፡ ጥሩ ገንዘብ ግን ያመጣል፡፡
“ተመጋቢዎች ለምን እንዳማረን ይቅር?” በሚል የተጀመረው ቢዝነስ ዛሬ የካናዳ ድንበር በምትጋራው የኦሃዮ ክሊቭ ላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች ስራው ሞቋል፡፡
በሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጫና፤ የራስ ሰው በማጣት እና በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ ቦታ አመቺነት ችግር ቢዝነሱ እጅግ ማደግ የሚችልበትን እድል አልተጠቀምም እንጂ በጣም ሊሰፋ ይችል ነበር ይላል ለማ፡፡
ስለ እትዮጵያ ዲያስፖራ እንዲህ አለ፡፡ “እኛ ትንሽ ነን፡፡ የሆነ 10 ሺ ኢትዮጵያዊ ባለበት ከተማ ለምን መቶ የሀበሻ ምግብ ቤት ትከፍታለህ? ሁሉም ላይሰሩ ነው፡፡ ማን ውጤታማ ሊሆን ነው? ስንት ሰው በአንድ የሀበሻ ምግብ ቤት ሊመገብ ነው?” ሲል ይጠይቃል ለማ፡፡
“ሀበሾች መንቃት አለባቸው እርስ በእር ከመነጣጠቅ ይልቅ በርካታ ተመጋቢ ባለባቸው የሌላ አገር የሬስቶራንት ቢዝነሶች ጭምር ስለመሰማራት ማሰብ ይኖርባቸዋል፣” ሲል ሃሳቡን ያጋራል፡፡
ይህ ከለማ በርካታ ተስፈንጣሪ የቢዝነስ መገለጫዎጭ መካከል አንዱ ብቻ ነው፡፡
በርግጥ ሰውየው ብዙ ስራ አለው፡፡ ይህ የጃፓን ቴርያኪ ምግብ አቅራቢ እሱ ከደረሰበት የሀብት ማማ አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው፡፡ የትርፍ ጊዜ ስራ (ሆቢ እንደማለት)፡፡
የብዙ ክህሎት ባለቤት!
በግዛቱ አለ የተባለ የሪል እስቴት ኢንቨስተር ነው ለማ፡፡
በኦሀዮ ክሊቭላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች የሚያከራያቸው በርከታ የንግድ ህንፃ እና ቦታዎች አሉት፡፡
የተለያዩ ቢዝነሶች ጀምሮ ያሳካ፡፡
ለስደተኛ አይታለፍ የሚባሉ መከራዎችን የተሻገረ ጀግና፡፡
አይደለም ተወልዶ ላደገባት ኢትዮጵያ የህዝብ ወገን እና ደራሽ ነው ለማ በሰሜን አሜሪካ፡፡
ሀረር ከተማ አደሬ ጢቆ ነው ተወልዶ ያደገው፡፡
ጨዋታ አዋቂ፣ ወሬ የሚያምርለት፣ ተዝናንቶ የሚያዝናና ነው ይሉታል፡፡
ያደገበትን ያካባቢውን ወግ አልረሳም፡፡ ወደ አገሩ ሲመጣ አብሮ አደግ የሀረር ልጆችን ይዞ ይዞራል፡፡
ወርቃማ የህይወቱን ክፍል ውጭ ነው ያሳለፈው ከማለት ይልቅ እዛው ሀረር ነው የሚኖረው ያስብላል ነገረ ስራው፡፡
ቸርነቱስ ቢባል አሉ። ሰውየው በዚህ ጉዳይ ብዙ መናገር ባይፈቅድም እጁ የደረሰበት ልቡ ያውቀዋል።
መጪው ትውልድ ላይ ደግሞ ወጥሮ መስራት ነው መርሁ፡፡ ትምህርት ላይ ያምናል፡፡
የአገር ኩራት!
ኢትዮጵያውያኖች በደረሳችሁበት ይሁንላችሁ!
መሉቀን የወንደወሰን
ከአሜሪካ 🇺🇸
#harar #ጃፓን #ሀረር #teriyaki #clevelandohio #cleveland #teriyaki_express #lemmagetachew #lemma_getachew #ohio #japanesefood #ጃፓን #ethiopianfood #ethiopia #realestate #addisababarealestate #clevelandclinic #clevelandclinicabudhabi #clevelandsddisview #addisview #harar #japan #teriyaki #cleveland #ohio #success #business #diaspora #realestate #entrepreneur #ethiopian #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ኢራን ለምን አሜሪካን በቀጥታ መምታት አትችልም? የኢራን የሚሳይል ስትራቴጂ እና የአሜሪካ የአየር የበላይነት"
የኔታ ሚዲያ
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ ወደ ለየለት ጦርነት ተቀይሯል። ምንም እንኳን የኢራን ጀነራሎች ያልታዩ መሳሪያዎች አሉን ቢሉም ተጨባጩ ወታደራዊ ሳይንስ ግን የኃይል ሚዛኑ ወደ አሜሪካ ያጋደለ መሆኑን ያሳያል።
ኢራን በቀጥታ አሜሪካን መምታት የማትችልባቸው ምክንያቶች
ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ትልቅ የሚሳይል ኃይል ቢኖራትም የሰሜን አሜሪካን ምድር ለመምታት የሚከተሉት እንቅፋቶች አሉባት፦
* የአህጉር አቋራጭ ሚሳይል (ICBM) እጥረት
አሜሪካን ለመምታት ቢያንስ ከ10,000 ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ የሚችል ሚሳይል ያስፈልጋል የኢራን እጅግ ዘመናዊ የሚባሉ ሚሳይሎች (እንደ Khorramshahr-4) የሚጓዙት እስከ 2,500 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው ይህም አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅን እንጂ ዋሽንግተንን አይደርስም።
* የአየር ክልል ዳግም መግቢያ ቴክኖሎጂ (Re-entry Vehicle)
አንድ ሚሳይል አሜሪካ ለመድረስ ወደ ጠፈር ወጥቶ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ መሬት መመለስ አለበት በዚህ ጊዜ የሚፈጠረውን እጅግ ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም የሚችል "Heat Shield" ቴክኖሎጂ ኢራን እስካሁን በተግባር አላሳየችም።
* የአሜሪካ የባህር እና የየብስ መከላከያ ጋሻ
አሜሪካ በፓስፊክ እና አትላንቲክ ውቅያኖሶች ላይ የዘረጋችው Aegis የተሰኘ የሚሳይል መከላከያ እና በአላስካ የሚገኘው GMD መከላከያ ማንኛውም ከኢራን የሚነሳ ሚሳይል ግቡን ሳይመታ በአየር ላይ እንዲጋይ ያደርገዋል።
አሜሪካ ኢራንን በቀጥታ የመምታት ብቃትና ብልጫ
ከኢራን በተቃራኒ አሜሪካ ከገዛ ምድሯ ተነስታ ወይም በአቅራቢያ ካሉ የጦር ሰፈሮቿ ኢራንን የማድቀቅ ሙሉ ብቃት አላት
* የረጅም ርቀት ስትራቴጂካዊ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች (B-21 Raider & B-2):
እነዚህ አውሮፕላኖች ከራዳር ውጭ በመሆን ከአሜሪካ ተነስተው በዓለም ዙሪያ ነዳጅ እየቀዱ ኢራን ውስጥ የሚገኙ የኒውክሌር እና የሚሳይል ማዕከላትን መደመሰስ ይችላሉ።
* በኒውክሌር የሚሰሩ ሰርጓጅ መርከቦች (Ohio-class Submarines):
አሜሪካ በህንድ ውቅያኖስ እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ ስር ባሏት ሰርጓጅ መርከቦች በመቶዎች የሚቆጠሩ Tomahawk ሚሳይሎችን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ቴህራን ማስወንጨፍ ትችላለች።
* የጠፈር ኃይል እና ሳተላይቶች፦
አሜሪካ የኢራንን ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሰከንድ ልዩነት በሳተላይት ትከታተላለች ይህም ኢራን ሚሳይል ለመተኮስ ስትዘጋጅ ቀድሞ ለመምታት (Pre-emptive Strike) ዕድል ይሰጣታል።
* የአየር ላይ የበላይነት
አሜሪካ ያሏት F-22 እና F-35 የተሰኙ አምስተኛ ትውልድ ተዋጊ አውሮፕላኖች የኢራንን የአየር መከላከያ ሰብረው በመግባት የጦር መሪዎችን እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የማውደም አቅም አላቸው።
የኢራን ዛቻ በአብዛኛው የሚያተኩረው በመካከለኛው ምስራቅ ባሉ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እና አጋሮች ላይ እንጂ በአሜሪካ ምድር ላይ አይደለም አሜሪካ ግን በቴክኖሎጂ፣ በበጀት እና በስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ኢራንን በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ የመምታት ፍጹም ብልጫ አላት።