11 hours ago
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል - ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ‼️
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡፡
የአየር ኃይሉ የ3ኛ አየር ምድብ ላስመዘገበው የላቀ የግዳጅና የሥራ አፈጻጸም ስኬት በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው የምድቡ ጠቅላይ መምሪያ የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መከላከያ ሠራዊት በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ከፍተኛ ለውጥ እያደረገ ይገኛል፡፡
አሁን የምንገኝበት ዘመን የውጊያ አካሄድና ስልት ለመገመት በሚያዳግት መልኩ በፍጥነት እየተቀያየረ ነው ያሉት አዛዡ፥ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ቀጣናም ያለው የኃይል አሰላለፍ ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይልም ይህንን ታሳቢ በማድረግ የዘመኑን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል በማብቃት፣ በርካታ ፓይለቶችን፣ ቴክኒሽያኖችንና የአስተዳደር ባለሙያዎች እያፈራ መሆኑንና የዘመኑን የውጊያ ቴክኖሎጂዎች እየታጠቀ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
3ኛ አየር ምድብም የሪፎርሙ አካል በመሆን በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ልዩ ታሪክ ያለው መሆኑንም አንስተዋል።
ምድቡ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እና ኮሎኔል ባጫ ሁንዴን የመሳሰሉ በርካታ ጀግኖችን ያፈራ መሆኑን አስታውሰው፥ አሁንም ያንን የጀግንነት ታሪክ እያደሰ በርካታ ተተኪ ወጣት በራሪዎችን በአጭር ጊዜ፣ በጥራትና በብዛት እያፈራ ይገኛል ነው ያሉት።
የሚለወጠውን የውጊያ አውድና የኃይል አሰላለፍ በመገንዘብ አመራሩና ሠራዊቱ ራሱን ከጊዜው ጋር ማዘመን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ጠላቶችን መመከትና ድባቅ መምታት የሚያስችል ጀግና ተቋም መገንባቱን ገልጸው፥ የምድቡ አመራሮችና የሠራዊት አባላት ግዳጃቸውን በጀግንነትና በስኬት በመወጣታቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ታላላቅ ተልዕኮዎች እንደሚጠበቁ በመረዳት በሁሉም ረገድ ዝግጁነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
Seledadotio

1 day ago
የዘመናችን ሉዓላዊነት፡ ከድንበር ጥበቃ እስከ ኢኮኖሚያዊና ዲጂታል ልዕልና
*******************
( የዕለቱ መልዕክት)
ትናንት የሀገር ዳር ድንበር በጀግኖች ደምና አጥንት ይጠበቅ ነበር። ዛሬ ግን የዓለማችን የጂኦ-ፖለቲካ መልክ እና የኃይል አሰላለፍ መሰረታዊ ለውጥ ሲያስተናግድ፣ የሉዓላዊነት ትርጓሜም እጅግ ጥልቅ የሆነ አዲስ ገጽታን ተላብሷል።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የህልውና ዋስትና የሚረጋገጠው ጂኦግራፊያዊ ድንበርን በጦር መሣሪያ በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በስንዴ ማሳዎቻችን ስፋት፣ በፋብሪካዎቻችን የማምረት አቅም እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ብቃታችን ጭምር ነው።
እውነተኛ ነፃነት ማለት የራስን ትርክት በራስ አቅም መጻፍ መቻል፣ የራስን ህዝብ በራስ አቅም መመገብ እና የሀገርን ጉዳይ ያለ አንዳች የውጭ ጫና መወሰን መቻል ማለት ነው።
ይህ ሉዓለዊነት ከእርዳታ ጥገኝነት እና ከተረጂነት አዘቅት ተላቆ በምግብ ራስን መቻልን፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ አቅም ማምረትን እና በከንቱ የሚባክኑ የተፈጥሮ ጸጋዎቻችንን ወደ ሀገራዊ ሀብት መቀየርን ማዕከል ያደረገ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ደሃ አይከበርም፤ እየለመነ የሚኖር ሀገር አይከበርም" ሲሉ የተናገሩት መራር ሀቅ፣ የዘመናችንን የሉዓላዊነት ትግል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ክብራችን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ደምቆ የሚታየው፣ ቃላችንም የሚሰማው ፖሊሲዎቻችንን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ማስፈጸም የሚያስችል የኢኮኖሚ ጡንቻ ስንገነባ ብቻ መሆኑን ይህ አዲስ እሳቤ ያስገነዝበናል።
ይህ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እርስበርስ በተሳሰሩ ጠንካራ ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። የግብርናው ዘርፍ ዜጎችን ከረሃብ ከመታደግ አልፎ፣ ሀገርን በእርዳታ ስም ከሚመጣ የፖለቲካ ተጽዕኖ እና የውጭ ጫና ነጻ የማውጣት አቅም አለው።
ከዚህ ጎን ለጎን አምራች ኢንዱስትሪውና ማዕድን ልማቱ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶቻችንን በራሳችን አቅም እንድንገነባና ኢኮኖሚያችን እንዲጠናከሩ እያደረጉ ይገኛሉ። የቱሪዝም ዘርፉ የብሔራዊ ገጽታችንን ከመገንባት ባሻገር ባህላችንን ለዓለም የምናስተዋውቅበት የሶፍት ፓወር መሣሪያችን ሲሆን የዲጂታል ኢኮኖሚው ደግሞ ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ፍጥነት ጋር እኩል እንድንራመድ የሚያደርገን የህልውናችን ወሳኝ ቁልፍ ሆኗል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሉኣላዊነታችን መከበር ትልቁ ማሳያ ነው። ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁመን ግድቡን ከዳር ማድረሳችን፣ ወደ ብሪክስ (BRICS) አባልነት መቀላቀላችን እና የባህር በር ጥያቄያችንን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማሳካት የምናደርገው ትጋት ሀገራችን በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት እና ሉዓላዊ ክብሯን በተጨባጭ የሚያሳዩም ናቸው።
ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ታላላቅ ሀገራዊ ስኬቶችና የዲፕሎማሲ ድሎች ዘላቂና ሙሉ ትርጉም የሚኖራቸው በውስጣችን ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ሲሰፍን ብቻ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። የልዩነት ግንቦችን አፍርሰን በጠረጴዛ ዙሪያ በሀገራዊ ምክክር ካልተወያየን እንዲሁም የጋራ ጠላታችን በሆነው ድህነት ላይ በአንድነት ካልዘመትን፣ የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ ማሳካትና ሉዓላዊነታችንን ከውስጥም ከውጭም ማስጠበቅ እጅግ ይከብዳል። የኢኮኖሚና የዲጂታል ልዕልናን ለማረጋገጥ መነሻው የውስጥ ሰላምና የአንድነት መንፈስ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ እውን ለማድረግ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝባችንን ሰላም ለማስጠበቅ ሌሊትና ቀን የሚተጋው፣ በቆራጥነትና በጀግንነት የተገነባው መከላከያ ሠራዊታችን ሚና በጉልህ የሚጠቀስ ነዉ፡፡
ሠራዊቱ ለሀገሩና ለህዝቡ ሲል ዛሬም ይፋለማል፣ ይዋደቃል፣ የተከበረ ህይወቱንም ይሰጣል። ይህ ሠራዊት ሀገሩን ከውጭና ከውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በመጠበቅ የሉዓላዊነታችን ጠንካራ ዘብ በመሆን ለልማታችን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
የሠራዊቱን የጀግንነት ፈለግ በመከተል ሕዝብ በአንድነት ሲቆም፣ አገርን ከጠላት መጠበቅና ወደ ብልጽግና ማሻገር ይቻላል። ስለዚህም የሀገርን ድንበርና ሰላም በንቃት መጠበቅ እንዲሁም ለጸጥታ አካላት ጠንካራ ድጋፍና አጋርነት ማሳየት የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው።
ስለሆነም አሁን ጊዜው ታሪካዊ ጀግንነታችንን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምናሸጋግርበት ወቅት ነው። ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ዘላቂ ለማድረግ፣ ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ እንዲሁም ትግላችንን ከጦር ሜዳ ወደ ዲጂታል ፈጠራ፣ ከተረጂነት ወደ አምራችነት እና ወደ ጠንካራ የስራ ባህል የምናሸጋግርበት ወሳኝ የለውጥ ዘመን ላይ እንገኛለን። የትናንት አባቶቻችን በደማቸው ያቆዩልንን ነጻነት፣ ዛሬ በላባችን፣ በእውቀታችን እና በፈጠራ ክህሎታችን ልናደምቀው ግድ ይለናል!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

2 days ago
805.3 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር፤ የኢትዮጵያውያን ተአምራዊ ውሎ
*********************
ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ በመንቀሳቀስ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።
ኢትዮጵያውያን የዕድሜ ልዩነት ሳይበግራቸው ከሕፃናት እስከ አዛውንት ከአካል ጉዳተኞች እስከ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በጋራ በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። ይህ የነቃ ተሳትፎም የማህበረሰቡን አንድነትና ለአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ነው።
ይህ መርሃ ግብር ልጆችን በማሳተፍ ስለ አካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት በተግባር የሚማሩበት ልዩ መድረክ ሆኗል። ህፃናት ከወዲሁ የችግኝ እንክብካቤን እንደ ባህል እንዲለምዱና የነገዋን አረንጓዴ አገር የመረከብ ሃላፊነታቸውን ገና በሕፃንነታቸው እንዲረዱ ያግዛል።
በተጨማሪም ሀገራዊ አንድነትን በተግባር ከመግለጹ በላይ ለአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠትና የኢትዮጵያን የመጻኢ ዘመን ዕጣ ፈንታ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ንቅናቄ ነው።
ይህ የተቀናጀ ሀገራዊ ርብርብ የትናንቱ የአድዋ ድል የነፃነት አርበኝነት በተፈጥሮ ጥበቃ የሚደገምበት የዘመናችን የጀግንነት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።
ቀደምት አባቶች በአድዋ ተራሮች ላይ ልዩነቶቻቸውን አክስመው ለሀገር ነፃነት እንደቆሙ ሁሉ የዛሬው ትውልድም ድህነትንና የተፈጥሮ መራቆትን ለማሸነፍ ዕውቀቱን ጉልበቱንና ፍቅሩን አስተባብሮ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ የአፈር መሸርሸርና የጎርፍ አደጋዎች እንዲቀንሱ እንዲሁም የከርሰ ምድር ውሃ እንዲበለጽግ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ ታበረክታለች።
ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው ባሻገር መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት የሚያነቃቃ ታላቅ ዕድል ፈጥሯል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በችግኝ ማፍላት በጉድጓድ ዝግጅትና በተከላ ሥራዎች በመሰማራት ሰፊ የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆን በተለይም እንደ ቡና፣ አቮካዶና ማንጎ ያሉ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ተክሎች ትኩረት ማግኘታቸው ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት ጥሏል።
በተጨማሪም ይህ ሀገራዊ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት መዛባትን ለመቋቋም የሚረዳና ኢትዮጵያ ለዓለም አረንጓዴ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ውርስ ነው።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቅድመ ዝግጅት ከተያዘው እቅድ በላይ በመፈጸም በዛሬዉ ዕለት ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን 26.2 ሚሊየን ሰዎች ተሳትፈዋል በዚህም 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈን ተችሏል በዚህም ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል።
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው አገራዊ የችግኝ ተከላ ዘመቻ የህዝባችንን የተቀናጀ የተቀናጀ ጥረት እና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ሁነት ሆኖ አልፏል።
በዘንድሮው አመት እስካሁን ባለው ጊዜ ከ6.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን የተያዘውን አጠቃላይ እቅድ ለማጠናቀቅ ቀሪ የሆኑት 1.5 ቢሊዮን ችግኞች ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት ተተክለው የሚጠናቀቁ ይሆናል።
የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ እውነተኛ ስኬት የሚለካው በተከላው ሂደት ብቻ ሳይሆን ከተከላ በኋላ በሚደረግ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤና ጥበቃ በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የተከላቸውን ችግኞች ተንከባክቦ ለፍሬ የማብቃት አደራ አለበት።
በብሌን ደምበሎ

3 days ago
ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
· አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፦ የሰዎች ህመም የሚሰማቸው፣ ተስፋን በተግባር የሚተረጉሙት ስራ ፈጣሪ
“Life’s most persistent and urgent question is, 'What are you doing for others?'”
(የህይወት ዘወተር እና አጣዳፊው ጥያቄ፦ ‘ለሌሎች ሰዎች ምን እያደረግክ ነው?’ የሚለው ነው።)
— ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር
በማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን አይቶ ከመቆጨት ይልቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን መነሳት የትልልቅ ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው። በትውልደ ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ዘንድም የሚታየው ይህ ህያው እውነት ነው፤ ጥበብን፣ የበጎ አድራጎት መንፈስን እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን በማስተሳሰር በሀገራችን ልዩ የለውጥ አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
የተድላ አምቡላንስ መወለድ፦
የህይወት አድን አገልግሎት ራዕይ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በሀገራችን በህክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትልቅ ክፍተት በጥናት በመረዳት ነው "ተድላ አምቡላንስን" ወደ ስራ ያስገቡት። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት (ኦቲዝም) ያለባቸው፣ የዳያሊሲስ ህመምተኞች እና አረጋውያን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጋጥማቸውን የእንቅስቃሴ እና የትራንስፖርት እንግልት በመመልከት፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የድንገተኛ እና ድንገተኛ ያልሆነ የህክምና መጓጓዣ አገልግሎት እንዲመሰረት አድርገዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራ በላይ የማህበረሰብ አለኝታነትን መርሁ በማድረግ፦
· ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ፣
· በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ደረጃ አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ የተጋ፣
· ለሁሉ አቀፍ ተደራሽነትና ለዜጎች ክብር የቆመ ተቋም ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
“The best way to find yourself is to lose yourself in the service of others.”
(ራስህን ለማግኘት የሚቻለው የተሻለው መንገድ በሌሎች አገልግሎት ውስጥ ራስህን ስትሰጥ ነው።)
— ማሃትማ ጋንዲ
“ማንም የላት”፦
ጥበብ ለሰብአዊነት እና ለማህበራዊ ንቅናቄ
አቶ ሳሚ ከስራ ፈጣሪነታቸው ባሻገር፣ ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያላትን ትልቅ ሀይል በመረዳት ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ “ማንም የላት” የተሰኘውን ታሪካዊ የኅብረት ዜማ ፕሮዲዩስ አድርገዋል።
ይህ ስራ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ በቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) እንዲሁም በዳይሬክቲንግ ነፃዓለም አብዲ የተቃኘ ሲሆን፤ ድምፃውያን ማስተዋል እያዩ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሀና ግርማ እና አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) ድምፃቸውን ሰጥተውበታል። ከ50 በላይ የሙያ አጋሮች የተሳተፉበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ህብረተሰቡን ስሜታዊ ጉዳት ውስጥ ሳይከት በደማቅ ቅንብር የችግሩን አሳሳቢነትና የለውጥ አስፈላጊነት ያሳያል።
አካል ጉዳተኝነት የችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እና የትራንስፖርት እጥረት ዋናው ክፍተት መሆኑን ማሳወቅ ነው። “ማንም የላት” የሚለውን ስሜት “እኛ አለንላት!”በሚል አዎንታዊ ምላሽ ለመተካት ያለመ ማህበራዊ ንቅናቄ ነው።
አቶ ሳሚ ካህሳይ እና ድርጅታቸው ተድላ አምቡላንስ ቃላቸውን በተግባር በማስመስከር፤ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በተደረገ ስነ-ስርዓት፦የሙዚቃ ቪዲዮውን ገቢ፦ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የዩቲዩብ ቻናል ተለቆ የሚሰበሰበው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንዲሆን አስረክበው ነበር።
በርካታ ዊልቸሮች፣ ዘይት፣ ላርጎ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመቄዶንያ መስራች ለዶ/ር ቢንያም በለጠ በአካል አስረክበዋል።
ተድላ አምቡላንስ ለማንኛውም ሰዓት ለመቄዶንያ ማዕከል ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት በይፋ ቃል ገብተዋል።
የአቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ህልም በዋና ከተማው አዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በክልሎች፣ በገጠራማ አካባቢዎች እና ክፍለ ሀገራት የሚኖሩ፣ አማራጭ ያጡ ዜጎች ዘንድ ይሄው ዘመናዊና የተከበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲደርስ ከመንግስት እና ከተለያዩ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት አቅደዋል።
“No one has ever become poor by giving.”
(መስጠት ማንም ሰው ደሃ አያደርግም።)
— አን ፍራንክ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ በስራ ፈጠራቸው ሀገራዊ ክፍተትን የደፈኑ፣ በጥበብ ስራቸው የማህበረሰብ ህሊናን ያነቁ፣ በበጎ አድራጎታቸው ደግሞ የብዙዎችን እምባ ያበሱ የዘመናችን አርአያ ናቸው።
ተድላ አምቡላንስ “ሕይወትን ለማስቀጠል እየመጣን ነው!” በሚለው መሪ ቃሉ፣ የብዙዎችን ህይወት የመታደግ እና ተስፋ የመንዛት ታላቅ ሀገራዊ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ከ 27 ዓመታት ሰድት በኋላ አገር ቤት መጥተዋል። የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው "እናቴ፤ ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
የሀገር ጥሪን የመለሰ የዲያስፖራ ተሳትፎ፦ ህልምን በሀገር ላይ መተርጎም እንደነሳሚ ነው።
“Ask not what your country can do for you — ask what you can do for your country.”*
(ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን፣ እኔ ለሀገሬ ምን አደረግሁ ብለህ ጠይቅ።)
— ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካ) ያካበቱትን የሙያ ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ይዘው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በህክምናና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩት በምክንያት ነው። መንግስትና የሀገር ጥሪ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያቀረቡትን ጥሪ መሰረት በማድረግ፣ በውጭ ሀገር ያዩትን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥና ህልማቸውን በሀገራቸው ምድር ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።
ይህ እርምጃቸው ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፤ ሌሎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መጥተው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ትልቅ ማነቃቂያና መንገድ ጠራጊ አርአያ የሚሆን ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ ጀግንነት ነው!
ለሥራቸው፤ ለሰበአዊነታቸው እጅ እንነሳለን!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
"ሕይወትን ማዳን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያችን!"
– ተድላ አንቡላንስ
📞 ለአስቸኳይ ጥሪዎች 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት ዝግጁ
☎️ +251 985 585 888
📞 8558
የማኅበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ናቸው - ይከተሉን፦
Facebook: fb.com/Tedlaambulance
Instagram: instagram.com/tedlaambulance
Telegram: t.me/tedlaambulanceservice
TikTok: tiktok.com/tedlaambulance

Sponsored by
Surafel
5 days ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፡-
👉 ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ወታደራዊና የመንግሥት አመራሮች ላይ የተፈጸመው ግድያ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትምምን ውስጥ ጠባሳ ፈጥሯል፡፡
👉 የፖለቲካ መተማመን በጣም እንዲቀዘቅዝ አድርጓል፣ በሰዎች መካከል አብረህ እየኖርክ፤ እየሰራህ፤ እየተሰበሰብክ የመተማመን ዝንባሌው በእጅጉ እንዲቀንስ አደርጓል፡፡
👉 አብረህ ስለ ሀገር ከምትመክረው ሰው አደጋ ያጋጥመኛል ብለህ እያሰብክ መምከር በእጅጉ ትምምንን የሚቀንስ ጉዳይ ስለሆነ እንደ አንድ ጠባሳ የሚታይ ክስተት ነው፡፡
👉 ክስተቱ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል አበላሽቶታል፤ ከንግግር ከውይይት ይልቅ በመሳሪያና በጉልበት ግለሰቦችን በማፈንና በመግደል ስልጣን የመጎናጸፍ ልምምድን የሚያስቀጥል ጠባሳ ሆኗል፡፡
👉 ገዳይንም፣ ሟችንም ሁለቱንም ወገኖች በጀግንነት ያወሳ የፖለቲካ ትርክት የታየበት ክስተት ነው፤ ይህንን አሁንም ቆም ብለን ማየት ይገባናል፡፡
👉 ታሪክን እየመረጥን፣ እያንሻፈፍን እና በፈለግነው መንገድ የማቆየት የትርክት ስብራት ጉዳይ አሁን ላለንበት አጠቃላይ ውጥንቅጥ ዋናው መሰረት ነው፡፡
👉 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስካሁን ከሚስተዋለው ከዚህ ውጥንቅጥ ወጥተን፤ ታሪክን እንዳለ አስቀምጠን ከመልካሙም ከስህተቱም መማር ይገባናል፡፡
👉 አሁን እዚህ እንደ ዋዛ በብሄርተኝነት ስሜት በአውራጃዊነት ስሜት ታሪክን አንሻፍፈን ብንጽፍ፣ ብንናገር ነገ ልጆቻችንን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ማሰብ አለመቻል ደግሞ ያሳዝነኛል፡፡
👉 ይሄ ጉዳይ እንዳለ ታሪኩን አስቀምጠህ ከተቀመጠው ታሪክ ተነስተህ በሚኖረው ትንተና የፈለግከውን ነገር ወደ ቀኝ ወደ ግራ ወስደህ መማር ትችላለህ፡፡
👉 ታሪክን ማዛባት ግን እምብዛም ጠቃሚ አይደለም፤ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ዋጋ ያስከፍላል፣ ትውልድ ዋጋ ይከፍልበታል፡፡
👉 እኛ በህይወት እያለን የምናውቀውን ጉዳይ በተንሸዋረረ የታሪክ አረዳድ የምናስቀምጥ ከሆነ እኛ በማንኖርበት ሰዓት የሚኖረው ትወልድ እንዴት እንደሚወስደው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ታሪክ መመልከት ይቻላል፡፡
👉 አሁን ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ የዚህ የተንሸዋረረ የፖለቲካ ትርክት ውጤት ነው፡፡
👉 ታሪክን እንዳለ ማስቀመጥ ሳይሆን አዛብተን በማስቀመጣችን ምክንያት የሚፈጠር ችግር ነው፤ ከዚያም ሻገር ሲል የፖለቲካ ሴራ ተንታኞች መጠቀሚያም ሆኗል፡፡
👉 ያ ክስተት በተፈጠረበት ወቅት አሚኮን ጠርተን ለሕዝቡ መግለጫ የሰጠነው እዚሁ አዲስ አበባ መሆኑን ታውቃለህ፥ በኋላ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህር ዳር ሆነው መግለጫ ሰጡ በሚል የሴራ ተንታኔ ተቀይሯል፡፡
👉 እንደዚህ ያለ ከእውነት የተፋታ፤ ለዛሬም ለነገም የማይበጅ፤ የሚሸነገል የሚዋሽ ነገር ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጣው፡፡
👉 ክስተቱ እንደ ጥቁር ጠባሳ የሚወሰድ መጥፎ ክስተት ነው፡፡
በአቤል ነዋይ

ዜና እረፍት | ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ – የምሕረት፣ የጀግንነትና የአገር አገልግሎት ተምሳሌት አረፈች
#ethiopia | የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል አንዷ፣ የኮሪያ ጦርነት ዘማች፣ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ እና ዓለም አቀፍ የነርስነት ክብር ተሸላሚ የነበሩት መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በ96 ዓመታቸው አርፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ በአዲስ አበባ ከአቶ ከበደ ዘውገ እና ከወ/ሮ አልመዝ የግሉ ተወለዱ። ወላጆቻቸውን በለጋ ዕድሜያቸው በሞት ካጡ በኋላ፣ በአያታቸው ወ/ሮ ላቀች ጻታ እጅ አደጉ። የአባታቸው የአርበኝነት ታሪክ በመታሰቡ፣ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በነጻ እንዲማሩ እድል አግኝተዋል።
በኋላም በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሆስፒታል (አሁን የካቲት 12 መታሰቢያ ሆስፒታል) በነበረው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነርሶች ትምህርት ቤት ተምረው፣ ከሀገሪቱ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል በክብር ተመርቀዋል።
በ1943 ዓ.ም. ከሦስተኛው ቃኘው ሻለቃ ጋር ወደ ኮሪያ በማቅናት፣ ከሁለት ጥቁር አፍሪካዊ ሴት ነርሶች አንዷ ሆነው ታሪክ ሠርተዋል። ከሲስተር አስቴር አያና ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የቀይ መስቀል ዘማቾች በመሆን በተባበሩት መንግሥታት ሥር በኮሪያ ጦርነት ውስጥ ለወታደሮች ሕክምና እና ሰብዓዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ከሕክምና ሥራቸው በተጨማሪ ለኢትዮጵያውያን ወታደሮች የትርጉም አገልግሎትም አበርክተዋል።
ከኮሪያ በኋላ በጃፓን ወታደራዊ ሆስፒታል እንዲሁም በኢትዮጵያ በክብር ዘበኛ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በድሬዳዋና በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ተቋማት ለብዙ ዓመታት በታማኝነት አገልግለዋል።
ለሰብዓዊ አገልግሎታቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና በማግኘት፣ በነርስነት ሙያ ከፍተኛ ክብር የሆነውን Florence Nightingale Award የተሸለሙ ጥቂት አፍሪካውያን ሴቶች መካከል አንዷ ሆነዋል።
የአገር አገልግሎታቸውን ለማክበር፣ እናት ባንክ በቦሌ ቡልቡላ የሚገኘውን አንድ ቅርንጫፍ በስማቸው ሰይሟል፤ ይህም ለሀገር ያበረከቱትን የማይረሳ አስተዋፅኦ የሚያሳይ የክብር ምልክት ነው።
መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በ96 ዓመታቸው አርፈዋል። ከባለቤታቸው ከጄኔራል ደስታ ገመዳ ጋር ያፈሯቸውን አራት ልጆችና ስምንት የልጅ ልጆች ትተው አልፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በጀግንነታቸው፣ በሰብዓዊነታቸው እና ለሀገራቸው ባበረከቱት አገልግሎት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለዘላለም የሚታወሱ ባለውለታ ሆነው ይኖራሉ።
ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ።
#tizbit Assefa

6 days ago
የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ!
*************
የዘመን ማህደርን ገልጠን ወደ ኋላ ስንመለከት፣ ልክ ከ130 ዓመታት በፊት በ1888 ዓ.ም የኢትዮጵያ ተራሮች በታላቅ የክተት አዋጅ እና በነጋሪት ድምጽ ተንቀጥቅጠው ነበር። ወራሪው የፋሺስት ጦር ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ክብራችንን ሊገፍና ነፃነታችንን ሊቀማ በዘመተ ጊዜ፣ የወቅቱ ንጉሥ አፄ ምኒልክ ያንን ታሪካዊ የክተት ጥሪ አሰሙ።
"ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ እርዳኝ፤ ሀገር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና ተነስ! ይህን ሳታደርግ ቀርተህ ሀገርህ ስትደፈር ዝም ብትል ግን ማርያምን እጣላሃለሁ!" የሚለው የንጉሡ ጥሪ ኢትዮጵያን ከዳር እስከ ዳር አነቃነቃት።
ያኔ ጥሪው የኅልውና ነበር፤ ሀገር የማዳን፣ ድንበር የተጋፋውን የፋሽስት ወራሪ ኃይል በጀግንነት የመመከት ጥሪ ነበር። በዚህ ብሔራዊ ጥሪ የተንቀሳቀሰው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እንደ ማዕበል ተምሞ በዓድዋ ተራሮች ላይ በደሙ የነፃነት ታሪክ ጻፈ። ኢትዮጵያም በልጆቿ አንድነት ዳነች።
ዛሬ ደግሞ ዘመን ተቀይሯል። የትናንቱ ጠላት በጀግኖች አባቶቻችን ተሸንፎ ታሪክ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም በድጋሚ ኢትዮጵያ እየተጣራች ነው።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ጥሪ ግን፣ እንደ ትናንቱ የጦርነት የጠላት ወረራ ክተት አይደለም። የዛሬው ጥሪ ምድሪቱን የማከም፣ እናት ሀገርን አረንጓዴ ካባ የማልበስ እና ልምላሜዋን የመመለስ የብልጽግና ጥሪ ነው። ይህ ጥሪ አባቶቻችን በደም እና በአጥንታቸው ያስከበሯትን ውድ ሀገር፣ እኛ በአረንጓዴ ዐሻራችን አድሰን፣ በላባችን አልብሰን ልዕልናዋን በተግባር የምናረጋግጥበት ታሪካዊ አዋጅ ነው።
ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ዐሻራ ወደ ከፍታ ማማ የማሸጋገር እና የጀመረችውን የተስፋ ጉዞ የማስቀጠል ተከታታይ እና ያልተቋረጠ የክተት ጥሪ ነው።
እነሆ የዘንድሮው የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ ደግሞ ታሪክን በአዲስ መልክ ሊያድስ፣ ተደጋጋሚ ድሎችን ሊያስመዘግብ እና የዓለምን ክብረ ወሰን በድጋሚ ሊሰብር ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጋራ ሀገራዊ ቀጠሮ ይዟል።
በዚህ ታሪካዊ ዕለት፣ አዲሱ የመደመር ትውልድ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ሀገራዊ የክተት አዋጅ ታውጆለታል።
ከማለዳው የንጋት ጮራ ጀምሮ ጀንበር እስክትጠልቅ ድረስ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እጆች፣ የነገዋን ሀገር በምናብ እያዩ በአንድ ልብ ይሰባሰባሉ። በእነዚህ ጥቂት የብርሃን ሰዓታት ውስጥ 800 ሚሊዮን የተስፋ ዘሮችን በኢትዮጵያ ማህፀን ውስጥ ያኖራሉ።
ይህ የሐምሌ 27ቱ ክተት ከዛፍ ተከላ የዘለለ እጅግ ጥልቅ የሆነ ሀገራዊ ትርጉም አለው። ይህ ድንቅ የአንድ ጀንበር ተአምር፣ የተረሱና የተራቆቱ ተራሮቻችን ዳግም ህይወት የሚዘሩበት፣ የነገው ትውልድ ንጹህ አየር የሚተነፍስበት እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በጽኑ መሰረት ላይ የሚገነባበት ህያው ታሪክ ነው።
ትናንት አባቶቻችን በነጋሪት ድምጽ ጥሪዋን ሰምተው ሀገር እንዳዳኑ ሁሉ፣ ዛሬም እኛ ልጆቿ ይህንን የአረንጓዴ ዐሻራ ጥሪ ሰምተን በጋራ ስንሰለፍ ኢትዮጵያ በልጆቿ እጅ ትንቆጠቆጣለች፣ ውበቷ ይደምቃል፣ ሉዓላዊነቷም በምጣኔ ሀብት ይረጋገጣል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ፍቅር ተጣርታለች፤ ምድሪቱን ለማልበስ፣ 800 ሚሊዮን ዐሻራዎችን በአንድ ቀን ለማሳረፍ፣ ክተት ለሐምሌ 27!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #800milliontrees #ethiopiarising #environmentalprotection #ebcdotstream

የኢትዮጵያ ክተት ጥሪ ለአረንጓዴ ዐሻራ!

7 days ago
የ16 ዓመቱ ታዳጊ የ10 ዓመቱን ህጻን አዳነ፤
* በትራምፕ ሊሸለም ነው!
#ethiopia | በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘው የሴንታ ክሩዝ ሲብራይት (Seabright) የባህር ዳርቻ የ16 ዓመቱ ታዳጊ ላይፍጋርድ ራይደር ዊሊያምስ በኃይለኛ ማዕበል ተወስዶ ለሞት የተጋለጠን የ10 ዓመት ህጻን በጀግንነት በማዳኑ በመላው አሜሪካ ትልቅ አድናቆት እያገኘ ነው።
በምስክሮች በተቀረጸው ቪዲዮ መሠረት፣ ህጻኑ በድንገት በተነሳ ኃይለኛ ማዕበል ወደ ባህሩ ከተወሰደ በኋላ ራይደር ሳይዘገይ ወደ ውሃው ዘልቆ በመግባት ህጻኑን አጥብቆ ይዞ ከተደጋጋሚ ከባድ ማዕበሎች ጋር በመታገል እስከ ዳርቻ ድረስ ማድረስ ችሏል። በኋላም ሌላ ላይፍጋርድ በመድረስ ህጻኑ በደህና ወደ ዳርቻ ተወስዶ በሕክምና ከታየ በኋላ ለወላጆቹ ተሰጥቷል።
የማዳኑ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ሚሊዮኖች ተመልካቾች ታዳጊውን "እውነተኛ ጀግና" በማለት ሲያወድሱት ታይቷል።
አባቱም ልጁ ከልጅነቱ ጀምሮ በውሃ ስፖርቶችና በላይፍጋርድ ስልጠና የተዘጋጀ መሆኑን ገልጾ፣ "ልጁን ፈጽሞ አልለቀቀውም" ብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልእክት፣ ራይደርንና ቤተሰቡን እንዲሁም ያዳነውን ህጻን ወደ ነጩ ቤት በመጋበዝ ለታዳጊው "High Civilian Honor" የተባለውን ከፍተኛ የሲቪል ክብር ሽልማት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል።
ራይደር ዊሊያምስ በበኩሉ፣ ይህ በቪዲዮ የተቀረጸው ማዳን ብቻ ሳይሆን በዚያው ቀን ከስራ በኋላ ሌሎች ሁለት ሰዎችንም ከአደገኛ ማዕበል ማዳኑን ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #america #lifeguard #ryderwilliams

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን፣ ሀገራዊ ግዴታቸውን በጦር ግንባር በመወጣት ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈው የጋራ ኃይሉ የኮርዶፋን ቀጠና ዘመቻ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አብዱልአዚዝ እስማኤል አበከር ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
በካርቱም በተካሄደው የሀዘን መግለጫ ሥነ-ሥርዓት ላይ በሚኒ አርኮ ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ/ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የጋራ ኃይሉ የጦር መኮንኖች እና የሟች ቤተሰቦች በአካል ተገኝተዋል።
የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ለሟች ቤተሰቦች እና ለትግል አጋሮቻቸው ጥልቅ ሀዘናቸውን በገለጹበት ወቅት፣ ሜጀር ጄኔራሉ ሀገራቸውን ለመከላከል ያሳዩትን ጀግንነት እና የከፈሉትን መስዋዕትነት አድንቀዋል። አክለውም የሰማዕታቱ መስዋዕትነት የሱዳንን አንድነት፣ ደህንነት እና መረጋጋት ለማስጠበቅ በሚደረገው ትግል ውስጥ ሁሌም በኩራት የሚታወስና የትግሉ መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በበኩላቸው የሟች ቤተሰቦች፣ በሚኒ ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ እና የጋራ ኃይሉ አመራሮች ፕሬዝዳንት አል-ቡርሃን በአካል ተገኝተው ሀዘናቸውን በመግለጻቸው ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ሜጀር ጄኔራል አብዱልአዚዝ የጀግንነት እና የቅንነት ተምሳሌት ሆኖ እንደሚቀጥል አውስተው፣ የትግል አጋሮቹም የእርሱን ፈለግ በመከተል ሱዳንን የመከላከል ሀገራዊ ግዴታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

11 days ago
ክንዱ የማይታጠፈው የጀግኖች አምባ!
****************
እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ፤ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የጸጥታና የሉዓላዊነት ምሽግ ምን ያህል ጠንካራ ነው? የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዛሬ የተረከበውን ሀገራዊ አደራ ታሪክን በሚቀይር የልህቀት ከፍታ ላይ አድርሶታል።
እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት እና በጽኑ ኩራት የሚያስደምመው ይህ ተቋም፣ በጥልቅ ሪፎርም ዳግም የተወለደ የሉዓላዊነታችን ሕያው ምሽግ ነው። ሠራዊታችን ዛሬ በተግባር ያረጋገጠው አቅም የውጊያ ክህሎትን ማሳደግ ብቻ አይደለም።
ከዚያም በዘለለ፤ ጦርነትን ቀድሞ የማስቀረት፣ የጥፋት ሥጋትን ገና በእንጭጩ የማምከን እና በማያዳግም የቅድመ መከላከል (Deterrence) ሳይንሳዊ ስትራቴጂ ጠላትን የማንበርከክ እጅግ የላቀ አቅም ነው።
ጠላት ክፉ አስቦት ወደ ኋላ በድንጋጤ እንዲያፈገፍግ የሚያደርገው ይህ ዘመኑን የሚዋጅ ወታደራዊ ጥበብ፣ ኢትዮጵያን የማትደፈር የብረት አጥር አድርጓታል።
በምድር ላይ ከሚታየው አንበሳ መሰል የውጊያ ጀግንነት፣ በአየር ላይ ካለው ንስራዊ የበላይነት፣ እንዲሁም ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ ዳግም ተቋቁሞ የቀይ ባሕርን ቀጣና በንቃት ከሚቃኘው የባሕር ኃይላችን ልዕልና ጀርባ ያለው ትልቁ ምሥጢር፤ በቴክኖሎጂ የታጀበው ታሪካዊ የተቋም ሪፎርም ነው።
በተለይም ዘመናዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (UAVs)፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን እና ዘመን አመጣሽ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በላቀ የሳይበር አቅም በማዋሃድ የገነባው የኤሮስፔስ ልዕልና፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ቀጣናዊ አስፈሪ ኃይል አድርጓታል።
የዘመኑ ሳይንስ በከፍተኛ ደረጃ ያስታጠቃቸው፣ በሥነ ልቦና የገዘፉት የሠራዊቱ አባላት፣ ኢትዮጵያን በላቀ የውጊያ ጥበብ የሚጠብቁ የብረት ካስማዎች ናቸው።
ይህ ታሪካዊና እጅግ ስኬታማ ሪፎርም "ሀገር አስቀድም፣ ራስ አስቀጣይና ብቃት ያለው ተቋም ፍጠር" በሚል የጠለቀ ፖለቲካዊና ተቋማዊ ፍልስፍና የተመራ ነው። መከላከያችን ዛሬ የጦርነት ጋሻችን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የልማት አቅም፣ የሰላም ኢንጂን እና የሽግግሩ ዘመን ታማኝ ዋልታ ነው።
ሠራዊቱ የፈጠረው ቴክኖሎጂያዊ እና ሳይንሳዊ ብቃት ለሀገር የልማት ጉዞ፣ ለመሠረተ ልማት ደኅንነት እና ለኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችን ጥበቃ ትልቅ ትሩፋት እያበረከተ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የነገዋን፣ በለጽጋና ተከብራ የምትኖረውን ጠንካራ ኢትዮጵያ እውን የሚያደርግ የኩራታችን ምንጭ ነው።
ኢትዮጵያ የቱንም ያህል ውጫዊና ውስጣዊ ፈተና ቢገጥማት፣ ይህ በቴክኖሎጂ የረቀቀ፣ በሳይንስ የላቀ፣ ጦርነትን አስቀድሞ በማምከን ዘላቂ ሰላምን የሚያጸና አሸናፊ ኃይል እስካላት ድረስ፣ የማትበገር የነጻነት አምባ ሆና ለዘላለም ትቀጥላለች! ክብራችን፣ ጋሻችን፣ እና የዘመኑ የቴክኖሎጂ ምሽጋችን ለሆነው ጀግናው ሠራዊታችን ማለቂያ የሌለው ክብር ይገባል!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #endf #sovereignty #militarycapability

12 days ago
ጀግንነት በሰላማዊ ግንባር | የቀድሞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ #nationaldialogue #peacefuldialogue #nationbuilding #ethiopianunity #peaceandconsensus
12 days ago
ሀገራዊ ምክክር፡- ኢትዮጵያ የነገ መሠረቷን የምትጥልበት ታሪካዊ ጉዞ
************************
ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከምሁሩ እስከ አርሶ አደር፣ ከሸኽ እስከ ቄስ ከከተማው እስከ ገጠሩ ማኅበረሰብ ድረስ "አጀንዳችሁ ሀገርን ያቀናል፤ ብንመክርበት ለመግባባት መንገዳችን ይበጃል" በሚል እምነት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በመዲናዋ አዲስ አበባ ተመካካሪዎችን በማሰባሰብ የምክክር ጉባኤውን በይፋ ከጀመረ ቀናትን አስቆጥሯል።
የምክክሩ ሂደት ልዩነቶች እንደ ስጋት ሳይሆኑ፣ እንደ ሀገራዊ ፀጋና በረከት የሚታዩበትን አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማጎልበት ያለመ ነው። የተለያዩ ሐሳቦች በመደማመጥ ወደ ጋራ መግባባት የሚያመራ ሂደት እንዲጠናከርም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያን ከጥንት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ያካበቱት ታላቅ ጥበብ ቢኖር አለመግባባቶችን በውይይትና በሽምግልና የመፍታት ባህል ነው። ከዋርካ ሥር በመሰባሰብ ቅራኔዎችን ማለዘብ፣ በባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ስብራቶችን ጠግኖ ግንኙነቶችን ማደስ የዚህች ሀገር የቆየና የማይነጥፍ እሴት ነው።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የጀግንነት ድሎችንና የጥንካሬ ማረጋገጫዎችን እንዳስመዘገበች ሁሉ፣ ፈታኝ የሚባሉ ጊዜያትንም አሳልፋለች።
ያልተፈቱ የፖለቲካ ችግሮች፣ የታሪክ ቅሬታዎች እና የፍትሕ ጉድለቶች በሕዝቦች መካከል እንደ ዘመናት እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። እነዚህ ተግዳሮቶችም አንዳንዴ የግጭትና የመከፋፈል እሳትን እየለኮሱ የአለመግባባት መንፈስ እንዲነግስ አድርገዋል።
ዛሬ ግን ያንን የቁስልና የቅሬታ ምዕራፍ የመዝጊያው ጊዜ ደርሷል። ኢትዮጵያ ከአራቱም ማዕዘን ከተሰባሰቡ በልጆቿ ጥበብ ልዩነቶቿን በጠረጴዛ ዙሪያ ልትፈታ ቁጭ ብላለች።
የዚህ ሀገራዊ ምክክር መዳረሻ ግቡም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት፣ ለመጪው ትውልድ የተረጋጋች፣ ያደገችና የተባበረች ኢትዮጵያን ማስረከብ ነው።
ይህ ምክክር ከላይ የተጫነ ውሳኔ ሳይሆን፣ መነሻውን ከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ያደረገ ሕዝባዊ ሂደት ነው። ከወረዳ ጀምሮ የተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር፣ እያንዳንዱ ዜጋ የችግሩ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውም አካል መሆኑን ያረጋገጠ ነበር።
የብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ ብሶት፣ ጥያቄ እና የነገ ተስፋ በሂደቱ ውስጥ ተንጸባርቋል። እያንዳንዱ ዜጋም በሀገሩ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የራሱን ዐሻራ እንዲያሳርፍ ወርቃማ ዕድል ፈጥሯል።
ውስብስብ ችግሮችን በውይይት የመፍታት፣ ለዘመናት ሥር የሰደዱና ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮችን በመግባባት ለመቋጨት እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት፣ የኢትዮጵያን አዲስ አቅጣጫ ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን፣ ከመከፋፈል ይልቅ መግባባትንና አንድነትን የምትመርጥበት ታሪካዊና አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ይህ ምዕራፍ ደግሞ የነገዋን ሀገር በፅኑ መሠረት ላይ የመገንባት ታላቅ ጉዞ ነው።
በመቅደላዊት ደረጀ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationbuilding #nationaldialogue

16 days ago
የ4 ሺህ ድምፆች ውክልና፡- ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ሲያድስ
*********************
የጥይት ቋንቋን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የጦር ሜዳ ጀግንነትን ደግሞ በሐሳብ ልዕልና ለመተካት የሚያስችለው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ተከፍቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 4 ሺህ ተመካካሪዎች ያካተተውን ሰፊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት ሀገራችን ከጦርነት አዙሪት ወጥታ ወደ ዘላቂ ሰላምና የሀገር ግንባታ የምትሸጋገርበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ገዳ እና የሽምግልና ሥርዓቶች ያሉ የዳበረ የውይይትና የችግር አፈታት ባህል ቢኖርም፣ የፖለቲካው ማኅበረሰብ ግን ከዚህ እሴት ባለመቅዳቱ "አሸናፊ ወደ ቤተመንግሥት፣ ተሸናፊ ወደ ግዞት" የሚል አጥፊ የፖለቲካ ባህል ስር ሰዶ ቆይቷል።
ይሁንና አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ይህንን የተዛባ የፖለቲካ ትርክት በማረም ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ሂደት ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ትንታኔያቸውን የሰጡት የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት ተሾመ ኢትዮጵያ ጠንካራ የመንግሥት ምስረታ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በውስጣዊ ክፍፍሎች እና የውጭ ኃይሎች የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ምክንያት በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሏን ይገልጻሉ።
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በከተማ ልማት እና በዲፕሎማሲ እያስመዘገበች ያለችውን አበረታች ዕድገት ለማስቀጠል፣ ሀገራዊ ምክክሩ ወቅታዊ እና ወሳኝ መድኃኒት መሆኑን አስምረውበታል።
በየትኛውም የዓለም ክፍል ጦርነት ትርፍ አምጥቶ እንደማያውቅና ይልቁንም አምራች ኃይልን እና ሀገራዊ ኢኮኖሚን እንደሚያወድም ያነሱት ምሁሩ፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሚዲያ አካላት እና የሃይማኖት አባቶች አጀንዳዎቻቸውን ኦዲት በማድረግ ለትውልድ የሚሻገር ሀገር ለመገንባት በጋራ ሊቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡
በየትኛውም ስሌት የምክክር መድረኩን መጀመር በራሱ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት ለሚሹ ኃይሎች ታላቅ ድል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁን የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት ዘላቂ የሀገር ግንባታ ነው።
ሀገረ-መንግሥት የመመስረቱ ሂደት ቀደም ብሎ ቢጠናቀቅም በእኩልነትና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ አንድነትን ለመፍጠር መመካከር የግድ ይላል።
ባለፈው ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ ቁርሾዎችንና ህመሞችን በዛሬው ዘመን የሰብአዊ መብት መነጽር ከመመዘን ይልቅ፣ ያለፈውን እንደ መማሪያ በመውሰድ ለጋራ የወደፊት ራዕይ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ዘመን እውነተኛ ጀግንነት የሚለካው በጦር ሜዳ ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የሰለጠነ ድርድር መሆኑንም ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
ባለፉት አራት ዓመታት ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከ1 ሺህ 200 በላይ ወረዳዎችን በማዳረስና የኅብረተሰቡን አንገብጋቢ አጀንዳዎች በማሰባሰብ የሁሉንም ድምፅ ያካተተ ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያስኬደ ይገኛል።
መላው ማኅበረሰብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተሳተፈበት የሚገኘው ይህ መድረክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ሁለት ዓመት ከመዋጋት፣ 20 ዓመት መወያየት ይሻላል" በማለት ያስቀመጡትን መርህ በተግባር የሚተረጉም ነው።
በመሆኑም፣ ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ አዳራሽ የተሰባሰቡበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ፣ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በማንሸራሸር ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉበት ወርቃማ እድል ነው፡፡
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogue #nationbuilding #ebcdotstream

19 days ago
የቃል ፌርማታ
#ethiopia | “መካከለኛው ትውልድ” የሽግግር ቀውስ፣ ተጠራጣሪነት እና የጎርባቾቭ አምሳያ፡- በያ ትውልድ እና በሚሊኒያልስ መካከል የተገኘውን የጄነሬሽን ኤክስ (Generation X) ወይም “መካከለኛው ትውልድ” ሥነ-ልቦናዊ መዋቅር፣ ተጠራጣሪነትና ተግባራዊነት ያሳያል።
ይህ ትውልድ የደርግን ዘመን ቀውስ፣ እርስ በእርስ መፋጀትንና ረሃብን አይቶ ስላደገ ለትልልቅ ርዕዮተ-ዓለሞች ጥላቻ ያለውና ውጤት ተኮር የሆነ ስብስብ ነው።
ለምሳሌ ደራሲ ቤተማርያም ተሾመ “ማይክ አቀባባዮች” ወይም “ቅልጥም ያመለጠው ትውልድ” ቢላቸውም፣ ጽሁፉ እንደሚያመላክተው መካከለኛው ትውልድ በዶክተር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ሥልጣን ይዞ “ማይኩን፣ ባንኩንም ታንኩንም” ተቆጣጥሯል፤ ነገር ግን በፖለቲካው መስክ እንደ ጎርባቾቭ ያለ የግላስኖስትና የፔሬስትሮይካ ሽግግር በመጀመራቸው ሀገሪቱን ግልጽ ፍኖት ወደሌለው መዋቅራዊ መላላትና ቀውስ አጋልጠዋታል።
ሚሊኒየሞቹ፡- ከ1981 እስከ 1996 (እ.ኤ.አ.) ከተወለዱትና “የዲጂታል ድልድይ” ወይም “ጀግና” (Hero) ተብለው ከሚጠሩት የጄነሬሽን ዋይ (Generation Y) “ዘጠናዎቹ” ትውልድ ባህሪ ጋር ይተዋወቃል። ይህ ትውልድ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የተሸጋገረ፣ በቡድን ሥራና በማኅበራዊ ንቃት የሚያምን፣ የኢሕአዴግን የልማታዊ መንግሥት ዘመን የተከታተለና የ2010ሩን የፖለቲካ ለውጥ በዋናነት የመራ ነው።
ለምሳሌ በጽሑፉ እንደተገለጸው፣ “ለውጥ ማምጣት እችላለሁ በሚል ‘ጀግንነት’ ሥርዓቱን ቢገፋና ቢፋለምም፤ ለውጡን አየር ላይ መካከለኞች (የጄነሬሽን ኤክስ) ትውልድ አስቀርቶ ቢቆረጥመውም፤ ቀጥሎም ከለውጡ ማግስት የመጣውን የሀገር መናጋትና ጦርነት ሲያይ ግን ዛሬ ላይ ወደ ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ (Cynicism) እና ሀገር ጥሎ የመሰደድ አባዜ ውስጥ የገባ ስብስብ ነው”። ይለዋል፡፡
ይህ ትውልድ (ሁለቱ ትውልዶች)፡- የአዲሱን የጄነሬሽን ዜድ (Gen Z) እና የአልፋዎችን ዲጂታል ተወላጅነት፣ የቲክቶክ ሥነ-ልቦና፣ እንዲሁም የፖለቲካዊ ፖፑሊዝምና የ“ሲሎቪኪ” (የኃይል ሰዎች) ናፍቆታቸውን ይተነትናል።
ይህ ትውልድ በዲሞክራሲ ስም በሚመጣ ውዥንብርና ተቋማዊ መላላት በመሰልቸቱ (Democratic Fatigue) ምክንያት፣ ሀገርን ሰጥ ለጥ አድርጎ የሚያቆም ጠንካራና አምባገነናዊ መሪን (Authoritarian Pragmatism) ይመኛል፤ ብሎ በምክንያት ኮንኖታል።
ለምሳሌ በጽሑፉ እንደተብራራው፣ ትውልዱ በሁለት ተጣራሽ ህልሞች የቆመ ሲሆን፤ በአንድ በኩል ተስፋ በመቁረጥ የ“ኤርትራን መስመር” (መገንጠል/የብሔር ጠርዝ) ሲያይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ “የባሕር በርን የሚያስመልስ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት በጉልበት የሚያስከብር፣ ወታደራዊና ቴክኖሎጂያዊ የበላይነትን የሚያውጅ ብርቱና ቆራጥ መሪ (ሲሎቪኪ) ይመኛል” ብሎታል።
ከመጣጥፎቹ እኛ ዘጠናዎቹ፣ ደራሲነት ማኅበራዊ መደብና የፈጠራ ሥነ-ልቡና፣ የአክሱምና የላሊበላ ወግ፣ ኢየሱስ ወልደ አብ፣ ጎዶሎው ዓድዋ ሉዓላዊነትና ሰዋዊ ክብር የየራሳቸው ሳፋፊ ጭብጥ ያላቸው ብዙ ሚያነጋግሩ ናቸው፡፡
አጫጭር ልቦለዶቹ ሳልነግስ አልሞትም፣ ሰበራ፣ የበሶው ውል፣ የኮሮናው ሰሞን፣ ለምን አትቆጣም? እና መካደም ወይ መጋደም በቃል ፌርማታ በምሳሌ ብዙ መብራራት ብዙ መተንተን የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ወፍ እንደ ሀገሯ ትዘምራለች፤ ደራሲ ቃል ኪዳን ኃይሉ እንደ ዘመኑ ጦምሯል፤ አንብቡትና እንደ ዘመኑ እንወያይበት!!
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን

20 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሕወሐት ሰሜን ዕዝን ሲመታ አዝዥ የነበሩት የአሁኑ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አዛዥ ጄኔራል ደሪባ መኮንን፣ የክልሉ ፖሊስ ከአፋር፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ መስማማቱን አስታወቁ። ጄኔራሉ ይህንን የገለጹት የፀጥታ ኃይሎቹ የቀጠናውን ደህንነት አስመልክቶ በጋራ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው።
በመንግስት በኩል "ሸኔ" ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) እና የፋኖ ታጣቂዎች የዘመቻው ዋነኛ ኢላማዎች መሆናቸውን ጄኔራሉ በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል። መንግስት እነዚህን ኃይሎች ሥርዓት ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሲል የሚፈርጃቸው ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ በድንበር አካባቢዎች ተጠልለዋል በሚል የሁለቱ ክልሎች ፀጥታ ኃይሎች የክልል ወሰን ሳይገድባቸው ድንበር ተሻግረው እርምጃ ለመውሰድ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ይህ "ድንበር የለሽ" የተባለ የጋራ ዘመቻ በተለይ በከሰም፣ ኮሎ፣ እና አዋሽ ሰባት አካባቢዎች እየሰፋ ነው የተባለውን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል።
አዛዡ አክለውም ታጣቂዎቹን በሎጂስቲክስ፣ በመሳሪያ እና በስንቅ ይደግፋሉ የተባሉ አካላትን ከህብረተሰቡ ነጥሎ ያለምህረት እርምጃ የመውሰድ ስራ መጀመሩን ጠቅሰዋል። ውይይቱ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ ኃይሎች የመረጃ ልውውጥ እንዲያጠናክሩና የጋራ ግብረ ኃይል ፈጥረው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በአፋር ክልል የሚገኙ እና በመንግስት የሚፈለጉ ግለሰቦችንም አሳልፎ ለመስጠት ከስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል። ይህ እንቅስቃሴ የሀገሪቱን ዋና የኢኮኖሚ መስመሮች፣ የባቡር ሀዲዶች እና እንደ አዋሽ ድልድይ ያሉ መሰረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ ገልጿል።
በሌላ በኩል ጄኔራል ደሪባ የሰራዊቱን ሞራል ለመገንባት በሚመስል መልኩ፣ ባለፈው ግንቦት ወር በምስራቅ ጉጂ ዞን አጋዋዩ ወረዳ በተደረገ ውጊያ ሳጅን ዳንኤል ፈይሳ የተባለ የፖሊስ አባል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታጣቂዎች ብቻውን በመቋቋም ህይወቱ ማለፉን በማንሳት፣ ለዚህም የአንደኛ ደረጃ የጀግንነት ሜዳሊያ እና የደረጃ እድገት እንደተሰጠው አውስተዋል።
ይሁን እንጂ የፀጥታ ኃይሎቹ ያቀዱት ይህ ዓይነቱ ድንበር ዘለል እና የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ቀድሞውንም በግጭት የተጎዳውን የቀጠናውን ማህበረሰብ ይበልጥ ወደ ከፋ ቀውስ እንዳያስገባው ስጋት አለ። ህብረተሰቡ ታጣቂዎችን እንዲያጋልጥና የምግብ አቅርቦት እንዲከለክል በመግለጫው ላይ ጥሪ ቢቀርብም፣ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ስለሚገኘው የንፁሀን ዜጎች ደህንነት አጠባበቅ እና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ በመንግስት ባለስልጣናቱ በኩል የተብራራ ነገር የለም።

21 days ago
"እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ የተሻለው ቡድን ድሉን ወስዷል! በዚህ ጉዳይ ላይ ሀቁን አፍርጠን መናገር እና ታማኝ መሆን አለብን። አርጀንቲናዎች ሜዳ ላይ የሰጡት ምላሽ እጅግ አስደናቂ ነበር፤ ኳስን ከግቡ ቋሚ ጋር በተደጋጋሚ ሲያጋጩ እንግሊዝ በእድል ነው የተረፈችው።
"ምንም እንኳን ሳይደናገጡ፣ በያዙት የጨዋታ ስልት ላይ ጸንተው መቀጠላቸው፣ በሚያደርጉት ነገር ላይ የነበራቸው ጽኑ እምነት... እና በመጨረሻም ያን አስገራሚ ነገር አሳኩት!
"ያደረጓቸው የተጫዋች ቅያሬዎች በሚገባ ሰርተውላቸዋል፤ ከሽንፈት ተነስተው ወደ ጨዋታው የተመለሱበትን አስገራሚ የጀግንነት መንገድ በእውነት ልናከብረው ግድ ይለናል። ይሄን መናገር ለእኛ ልብን የሚሰብርና በእጅጉ የሚያም ቢሆንም... እሁድ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ማለፍን በርግጥም ይገባቸዋል!"
አላን ሺረር
(የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ)

23 days ago
"ገላ ገላ" አስቱካን እካችሁ
የሰው ልጅ ነፍስ የምትተነፍስበት ጥልቅ ውቅያኖስ "ሙዚቃ"
"ሙዚቃ" እና "ፍቅር" ደግሞ ተነጣጥለው የማይታዩ፣ አንዱ ለአንዱ የተፈጠሩ፣ የሰማይ እና የምድር ያህል የተሳሰሩ የነፍስ ቋንቋዎች ናቸው።
ከትላንት እስከ ዛሬ... ከካሴት ክር እስከ ዲጂታል ዘመን፣ ቴክኖሎጂው ቢለዋወጥም፣ ትውልድ ቢተካካም እነዚህን ሁለት መለኮታዊ ጸጋዎች በአንድ ልብ አዋህዳ፣ ስሜትን በዜማ ሸምና ያቀረበችልን የዘመናቶች ፈርጥ—እሷ አስቴር አወቀ ናት!
የትውልድን ልብ ያንኳኳች፣ ማዕበል እና ጸጥታን በድምጿ ያስማማች የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጸጋ! አስቴር የ"ሶል" (Soul)
የፍቅር ንግሥት በድምጿ ጅረት ውስጥ የሰውን ልጅ ጥልቅ የልብ ጓዳ የምትፈትሽ፣ ስንከፋ አባባይ፣ ስንደሰት አጀብ ባይ የሆነች የዘመን ሀብት ናት።
ትዝታን ብቻ አይቀሰቅሱም፤ ገና ሳንኖረው የናፈቀንን፣ በቃላት የማይገለጸውን ያንን ጥልቅ ናፍቆት (መናፍቅነት) በውስጣችን ይፈጥራሉ። "ፍቅር" የሚለውን ቃል ስታዜመው፣ የፍቅርን ፊደል ያልቆጠረው እንኳ በፍቅር ይነድፋል፤ ገና ያላየነውን የፍቅር ብስራት በሙዚቃዋ እንድንኖረው፣ ያላጣጣመነውን ስሜት በምናባችን እንድንስለው ታደርገናለች። ድምጿ ሲሰማ የሌለብን ትዝታ ይጭንብናል፣ የሌለ ስንብት ያስለቅሰናል፣ ገና ያልመጣ ተስፋ ያስፈነድቀናል።
ትላንት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያደመጧትን፣ ዛሬ እኛ በፍቅር እንሰማታለን፤ ነገም ልጆቻችን ይወርሷታል። ጊዜ የማይሽራት፣ ዘመን የማያልፍባት ተወዳጅ አርቲስት!
እስኪ አንድ ሁለቲቱን እንምልክት
"ለመድክ ወይ" የተሰኘውን ይህን ልብ ሰባሪ እና ስሜት አንጀት ሰርስሮ የሚገባ የሙዚቃ ስራ ስናዳምጥ፣ የሰውን ልጅ የፍቅር ስነ-ልቦና፣ የልብ ስብራትን (Heartbreak) እና የመለየትን መራር እውነት በሚያስገርም ጥልቀት ስትፈትሸው እናገኛለን።
ይህ ዘፈን ተራ የሙዚቃ ዜማ አይደለም፤ ይልቁንም አንዲት በፍቅር የተከዳች፣ ማመን ያቃታት እና በትዝታ እስር ቤት ውስጥ የቀረች ነፍስ የምታሰማው የውስጥ ጩኸት ነው።
የዚህን ድንቅ ዘፈን ጥልቅ መልእክት በበሰለ የኪነ-ጥበብ መነጽር ስንተነትነው የሚከተሉትን ህያው እውነታዎች እናገኛለን
1. "ለመድክ ወይ?" ይህ ጥያቄ ተራ መጠይቅ አይደለም። የድንጋጤ እና የመገረም ጩኸት
ያለኔ መኖርን ቻልከው? እኔ ገና የትላንቱን አብሮነታችንን መርሳት አቅቶኝ በትዝታ እሳት እየነደድኩ፣ አንተ ግን እንዴት ያለምንም ህመም የክህደት እና የመገረም ስሜት ነው አንድ ሰው የነፍሱን ግማሽ አድርጎ ያሰበው አካል አዲስ ህይወት በአንድ ጀንበር የሚፈጠረውን የአእምሮ ንዝረት ያሳያል
አስቴር ይህንን ሚዛን የሳተ ፍቅር በጉልህ ታሳያለች።
በፍቅር መለያየት ውስጥ እጅግ አሳማሚው ነገር የህመሙ አለመመጣጠን ነው።
ለአንዱ (ለአፍቃሪዋ) ፍቅር የህይወት መሰረት፣ እስትንፋስ እና አለም ሲሆን፤ ለሌላኛው (ለተፈቃሪው) ግን ፍቅር ጊዜያዊ ማረፊያ፣ በቀላሉ ሊተካ እና ሊረሳ የሚችል ተራ ክስተት ሆኖ እናገኘዋለን። "እኔ እንዲህ ሆኜ፣ አንተ እንዴት ሆንክ?" የሚለው የዘፈኑ የጀርባ አጥንት ይህንን የስሜት መራራቅ ያጋልጣል።ያ የለመደችው ድምፅ፣ ያ የለመደችው መዓዛ በድንገት ሲቋረጥ ነፍስ ባዶ ትቀራለች። አስቴር በዚህ ዘፈኗ፣ መለየቱን አምና ለመቀበል የሚደረገውን የውስጥ ትግል እና የትዝታን አረመኔነት በቃላቷ ትስላለች። "ልመዳ" እንዴት ከባድ እንደሆነና ያንን ማቋረጥ ደግሞ ሞት መሆኑን ልክ አንዲት ሴት ብቻዋን ክፍሏ ውስጥ ሆና የምታነባውን፣ የምታቃስተውን እና ከራሷ ጋር የምታደርገውን ሙግት በዜማ ልክ ሰፍታ ታለብሰናለች።
የናፍቆትን እሳት እና የልብን መታለል ያለምንም ማለዘቢያ ፊት ለፊት
ለመድክ ወይ" የፍቅርን የጨለመ ገፅ ሚያዳምጣት ሁሉ የተወሳሰበ የሰው ልጅ ስሜት ወስዳ
የቆሰለ ልብ ያለው ሁሉ፣ በዚህ ዘፈን ውስጥ የራሱን እንባ ያገኛል!
"ገላ ገላ" በረቂቅ ቃላት የተሳለበት የፍቅር ጸሎት ።
ይህ ዘፈን ተራ የቃላት ድርደራ ሳይሆን፣ አንዲት የሰው ልጅ ነፍስ በፍቅር ስትገዛ፣ ስትማረክ እና ራሷን አሳልፋ ስትሰጥ የሚኖራትን ጥልቅ ስነ-ልቦናዊ እና ስጋዊ ውህደት የሚያሳይ ህያው ማሳያ ነው።
ገላ—የነፍስ ማረፊያ፣ የስሜት መግለጫ እና የፍቅር ቤተ-መቅደስ ነው።
አስቴር "ገላ" ስትል፣ መነካካትን ብቻ ሳይሆን፣ ሁለት ነፍሶች አንድ የሚሆኑበትን፣ መለያየት የሌለበትን ያንን የመጨረሻውን የፍቅር ልዕልና (Intimacy) እየጠራች ነው። ለእሷ ህይወት የሚዘራ፣ ግን ደግሞ ናፍቆትን የሚያባብስ ጣፋጭ እስር ቤት ነው።
አንድ የምታውቀው ፍጹም እውነት ቢኖር የራሷን የልብ ትርታ ነው።
የሷ "ሆድ" (ውስጧ/ነፍሷ) ለእሱ መገዛቱን አምና መቀበሏ፣ በፍቅር ውስጥ ያለውን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ራስን አሳልፎ የመስጠት ጀግንነት ያሳያል።ፍቅር ከስሜት አልፎ ወደ "መኖር እና አለመኖር" ትርጉም ይሸጋገራል። ፍቅር የልብ ምት ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሳንባ ገብቶ የሚያኖራት ኦክስጅኗ ሆኗል።
የነፍስ ኑዛዜ ነው ገና ያላፈቀረውን "እንዲህ ያለ ጥልቅ ፍቅር ባገኘሁ" ብሎ እንዲመኝ ሲያደርግ፤ ያፈቀረውን ደግሞ የልቡን ቋንቋ አግኝቶለታል።የሰውን ልጅ ድብቅ እና ጥልቅ የልብ ጓዳ ገብታ፣ ትበረብራልች
በሥራ መክበርን" በተግባር በማሳየቷ እንጂ! 40የልማሳ ዓመታት ሙሉ በመድረክ ላይ መቆየት፣ 28 አልበሞችን ማበርከት... ይህ ቁጥር ብቻ አይደለም፤ የትጋት፣ ለጥበብ የመገዛት እና የተሰጥኦ ጥግ ነው። አስቴር ጥበብን ከትጋት ጋር አጣምራ፣ የሰራችው ስራ ሁሉ ወርቅ ሆኖላት፣ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም የነገሰች የጥበብ ጀግና ናት። "ሙዚቃ" ፍቅር ነው፤ "ፍቅርም" ሙዚቃ ነው። ሁለቱም ደግሞ በአንድነት ሲጣመሩ "አስቴር አወቀ" የሚል ትርጉም ይሰጡናል።
ክብር በሥራዋ ለከበረችው...
ክብር ጥበብን አክብራ ላስከበረችን...
ክብር ትውልድን በዜማ እና በፍቅር ላዋሃደችው...ክብርም በስራሽ ሁሉ እድንወድሽ ላደረጉት በስራዎችሽ አሻራቸውን ላኖሩ ከቴዎድሮስ መኩሪያ ላስቱካ

25 days ago
ከፖለቲካ ሽኩቻ የላቀው የጋራ ተቋማችንን እናክብር
****************
የአንድ ሀገር ጥንካሬ ከሚገለጽባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ዜጎች በጋራ የሚግባቡባቸው እና በኩራት የሚጠሯቸው ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚውን እና የክብር ማማውን ስፍራ ይይዛል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንመለከት፣ በሠለጠኑ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የሠራዊት አባላትን ማክበር ከፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የላቀ ብሔራዊ መግባባት የተገነባበት ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ በፓርቲዎች መካከል የጎላ ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነት ቢኖርም፣ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ፉክክር ውጪ የማድረግ ብሔራዊ ስምምነት አለ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በሚተቹበት ወቅት እንኳ በጦር ግንባር የተሰማሩትን ወታደሮች እንደ ጀግና በመቁጠር ውዳሴ እና ክብር ያቀርባሉ።
በዩናይትድ ኪንግደም "የጦር ኃይሎች ቃል ኪዳን" (Armed Forces Covenant) የተሰኘው ብሔራዊ ሰነድ የሠራዊት አባላት ልዩ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋል።
ካናዳ ለአርበኞች ልዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ስታቋቁም፣ ፈረንሳይ ደግሞ ሠራዊቷን የሀገሯ የክብር እና የአጋርነት ብሔራዊ ተምሳሌት በማድረግ በትልቅ ማዕረግ ትዘክራለች።
ወደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በባሕርይው እጅግ ሕዝባዊ የሆነ፣ ከሀገር አልፎ ለዓለም የሰላም ዘብ በመሆን ደሙን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር በኮሪያ ልሳነ ምድር በቃኘው ሻለቃ አማካኝነት "አንድም ወታደር አልተማረከም፤ የሞተ ጓዱንም ጥሎ አልመጣም" የሚል የዓለምን አስደናቂ ሪከርድ ያስመዘገበ ጀግና ነው።
በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በአብዬ፣ በዳርፉር እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት አፍሪካውያን ወንድሞቹን ከእልቂት የታደገ፣ የራሱን ሬሽን እያካፈለ የውጭ ሀገር ዜጎችን ያኖረ የሰብአዊነት ተምሳሌት ነው።
ይህ ሠራዊት በሀገር ውስጥም ቢሆን ጦር መሣሪያውን አስቀምጦ በክረምት የገበሬውን ማሳ ሲያርስ እና በመኸር ሲያጭድ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ከነፍስ አድን ሥራ እስከ አንበጣ መንጋ ማባረር ድረስ ከሕዝቡ ጎን የቆመ ታላቅ አለኝታ ነው።
ነገር ግን አለመታደል ሆኖ፣ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል በሚደረጉ ፍልሚያዎች ውስጥ የከፉ ምኞቶች ሰለባ ሲሆን ይስተዋላል።
አንዳንዴም የፖለቲካ ልዩነትን እና የሀገርን የፀጥታ ምሰሶ መለየት ያቃታቸው አካላት ሠራዊቱን የማንቋሸሽ አዝማሚያ ያሳያሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ማክበር እና ለሀገር ሕልውና የሚከፍለውን ዋጋ ማወቅ የአንድ ማኅበረሰብ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገርን ጠብቆ የሚያኖርን ኃይል እንደ "ገዳይ" መፈረጅ እና ተቋማዊ ክብሩን አለማወቅ የሲቪል-ወታደራዊ ግንኙነትን አለመረዳት እና ያለመሠልጠን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት እና ፖሊሲ አውጪዎችን በጥብቅ መተቸት የዴሞክራሲ አካል ነው። ነገር ግን ለሀገር ሕልውና አጥንቱን የሚከሰክሰውን ሠራዊት ከተቋማዊ ትችት ነፃ አድርጎ በጀግንነት መዘከር ይገባል።
በመሠረቱ ሠራዊቱ ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት የመካስ የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት አድርጋ ከሠራችባቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል የፀጥታ ተቋማት ግንባታ ዋነኛው የሆነውም ለዚሁ ነው።
ሠራዊታችን ከፖለቲካ ልዩነቶቻችን በላይ የሆነ የጋራ የብረት አጥራችን እና የሕልውናችን ምሰሶ በመሆኑ ዘወትር ክብር እና ሞገስ ይገባዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #endf #nationalpride #standwithourtroops

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) እንግሊዝ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ምርጡን ብቃቷን በማሳየት፣ በስሜት እና በደጋፊዎች ጩኸት በተሞላው ታሪካዊው የአዝቴካ ስታዲየም ሜክሲኮን በአስደናቂ ሁኔታ አሸንፋለች። በዚህም ከኖርዌይ ጋር ለምታደርገው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቀጠሮ ይዛለች።
በከባድ ማዕበል ምክንያት ከአንድ ሰዓት መዘግየት በኋላ በተጀመረው እና የትያትር ያህል በሚመስለው በዚህ የስፖርት ምሽት፣ የቶማስ ቱኸል ስብስብ በርካታ ፈተናዎችን አልፏል። በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ጃሬል ኳንሳህ በቀይ ካርድ ከሜዳ ቢወጣበትም፣ ቡድኑ ጫናውን ተቋቁሞ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ካስመዘገባቸው ታላላቅ ድሎች አንዱን አሳክቷል።
ሜክሲኮ በገዛ ሜዳዋ፣ "ምሽጌ" በምትለው አዝቴካ ባደረገቻቸው 89 ተወዳዳሪ ጨዋታዎች የተሸነፈችው በሁለቱ ብቻ ነበር። ነገር ግን የእንግሊዝ የተረጋጋ አቀራረብ ጨዋታውን ቶሎ እንዲቆጣጠሩ አስችሏቸዋል። በተለይም ድንቁ ጁድ ቤሊንግሃም ከእረፍት በፊት በ98 ሰከንዶች ልዩነት ውስጥ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር እንግሊዝን መሪ አድርጓል።
የእንግሊዙ ግብ ጠባቂ ጆርዳን ፒክፎርድ ራውል ሂሜኔዝ ያደረጋቸውን ሁለት አስቆጣሪ ሙከራዎች በሚያስደንቅ ሁኔታ በማዳን ብቃቱን አሳይቷል። ሆኖም ከእረፍት ሶስት ደቂቃዎች በፊት ጁሊያን ኪኖኔስ በኃይለኛ ምት አንድ ግብ ለሜክሲኮ ማስቆጠሩ አልቀረም።
በደጋፊዎቿ ጩኸት ታጅባ ወደ ፊት የተገፋችው ሜክሲኮ፣ ኳንሳህ በሄሱስ ጋላርዶ ላይ በሰራው አደገኛ ጥፋት ቀይ ካርድ አይቶ ሲወጣ ይበልጥ ተነቃቃች። ነገር ግን አንቶኒ ጎርደን በሜክሲኮው ግብ ጠባቂ ራውል ራንጄል የተሰራበትን ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሃሪ ኬን ወደ ግብ በመቀየር የእንግሊዝን መሪነት አሳደገው።
እንግሊዝ ጨዋታውን ያረጋጋችው ሲመስል፣ ሃሪ ኬን በራሱ የቅጣት ክልል ውስጥ የብራያን ጉቴሬዝን እግር በመምታቱ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ራውል ሂሜኔዝ ለሜክሲኮ አስቆጠረ። በከፍተኛ ጫና እና አስጨናቂ ድባብ ውስጥ ቶማስ ቱኸል፣ ዳን በርን እና ጄድ ስፔንስን ቀይረው በማስገባት አምስት ተከላካዮችን ወደ መጠቀም ተመለሱ። በዚህም ለ11 ደቂቃዎች የተሰጠውን የባከነ ሰዓት ጀግንነት በተሞላበት መከላከል አሳልፈው ይህን ድንቅ ድል አስመዝግበዋል።
በሜክሲኮ የእግር ኳስ ታሪክ ትልቁ ተብሎ በተጠራው በዚህ ጨዋታ ላይ፣ እንግሊዞች ምን እንደሚጠብቃቸው ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። ከባህር ወለል በላይ ከ7,000 ጫማ በላይ ከፍታ ባለው እና እጅግ ፈታኝ በሆነው በዚህ ስታዲየም፣ የቱኸል ቡድን ያሳየው ብስለት እና ጽናት ትልቅ በራስ መተማመንን የሚሰጠው ነው።
የቡድኑ ኮከቦች ለታላቅ ጨዋታ ታላቅ ብቃት አሳይተዋል። በተለይም ጁድ ቤሊንግሃም ሁለት ግቦችን ከማስቆጠሩም ባሻገር፣ ከእረፍት በፊት የሜክሲኮው ተከላካይ ሴዛር ሞንቴስ አቻ የሚያደርጋትን ግብ ሊያስቆጥር ሲል ያደረገው ወሳኝ ሸርተቴ የግሉን ብቃት ከፍ አድርጎታል። የሜክሲኮን የኃይል አጨዋወት ለማቀዝቀዝ እንግሊዝ ወደ ኋላ እንድታፈገፍግ ያደረጉት ቱኸልም ለታክቲክ ብቃታቸው ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።
በአንዳንድ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ማመንታት ታይቶበት የነበረው ጆርዳን ፒክፎርድ (በተለይ በ32ቱ ጥሎ ማለፍ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር በነበረው ጨዋታ ፣ በአዝቴካው ከፍተኛ ጫና ውስጥ በብሔራዊ ቡድን ታሪኩ ምርጡን ብቃት አሳይቷል።
ለ17ኛ ጊዜ በዓለም ዋንጫው የተሰለፈው እና የፒተር ሺልተንን ክብረ ወሰን የተጋራው ፒክፎርድ፣ ለምን የእንግሊዝ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ እንደሆነ በተግባር አሳይቷል። የሂሜኔዝን ኃይለኛ የጭንቅላት ኳሶች ግራ እና ቀኝ እየበረረ ሲያድን፣ በስታዲየሙ ውስጥ የተፈጠረውን ማዕበል ሁሉ ተቆጣጥሮት አምሽቷል። ይህ ለፒክፎርድም ሆነ ለእንግሊዝ የማይረሳ ምሽት ነበር!

"አንድን ሀገር በእጆቹ የተሸከመው ጀግና!" 🇨🇻
#ethiopia | የኬፕ ቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ (Vozinha) በዓለም ዋንጫው ላይ ባሳየው አስደናቂ ብቃት የእግር ኳስ ዓለምን አስደምሟል።
በሻምፒዮኗ አርጀንቲና ፊት በርካታ ወሳኝ ኳሶችን በማዳን ቡድኑን እስከ ተጨማሪ ሰዓት ድረስ በጨዋታው ውስጥ አቆይቷል።
ቢያንስ የኬፕ ቨርዴ የታሪካዊ ድል ሕልም ባይሳካም፣ ቮዚንሃ ባሳየው ጀግንነትና ቁርጠኝነት የውድድሩ አንዱ ታላቅ ጀግና ሆኖ ተወድሷል።
የስፖርት አፍቃሪዎችም በማህበራዊ ሚዲያ፣ "አንድን ሀገር በእጆቹ ተሸክሞ ተጫውቷል" በሚል መልዕክት ለግብ ጠባቂው ክብር እየሰጡት ነው።
አንዳንድ ሽንፈቶች እንኳን ጀግንነትን ይወልዳሉ። ቮዚንሃ ለኬፕ ቨርዴ ዘላለማዊ ጀግና ሆኖ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከ35 በላይ የተዘረፉ ቅርሶቿን ማስመለሷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባከናወነችው ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተለያዩ ጊዜያት ተዘርፈውና ተሰርቀው ከአገር ወጥተው የነበሩ ከ35 በላይ ውድና ታሪካዊ ቅርሶቿን ማስመለስ መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” በሚል በቱሪዝም ዙሪያ ባደረጉት ቆይታ፤ይህ ስኬት መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ ከሰጠው ትኩረት ጎን ለጎን የሀገሪቱን ክብርና የታሪክ ባለቤትነት ለማረጋገጥ የወሰደው ቁርጠኛ እርምጃ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ከተመለሱት ታዋቂ ቅርሶች መካከል በታሪክ የመጀመሪያዋ በኢትዮጵያውያን የተሠራችው የ"ፀሐይ" አውሮፕላን ከጣሊያን መመለሷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያውያንን የጀግንነት ታሪክ የሚዘክረው የአፄ ቴዎድሮስ የራስ ፀጉር እንዲሁም በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ መስቀሎችና ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል።
የቅርሶች የማስመለስ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአሁኑ ወቅትም የአፄ ኃይለ ሥላሴን የዙፋን መቀመጫ ጨምሮ ሌሎች ቀሪ ውድ ቅርሶችን ለማስመለስ ከተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ጋር የዲፕሎማሲ ንግግር እየተደረገ መሆኑንጠቁመዋል።
ይህም በቅርቡ ውጤት እንደሚገኝበትና ተጨማሪ የታሪክ ጸጋዎች ወደ ሀገር እንደሚገቡ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
በቅርሶች አያያዝ ላይ በአንዳንድ ወገኖች የሚነሱ ሥጋቶችን በተመለከተም፣ መንግሥት ቅርስን የሚያጠፋ ሳይሆን የጠፋውን የሚመልስና የፈረሰውን የሚያድስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ቀደም ሲል እንደ እዳ ታይተው ተዘግተውና ተረስተው የነበሩጥንታዊ ቤተመንግሥቶች ዛሬ ላይ ታድሰው ለትውልድ ዕውቀትና ለሀገር ገቢ ምንጭ እየሆኑ መሆናቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።
ይህም ለወደፊቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ አዲስ ተስፋን ከመፍጠሩም በላይ፤ትውልዱ የሀገሩን ጥልቅ ታሪክ በቅርበት እንዲያውቅና እንዲያከብር ትልቅ ዕድል የሚከፍት መሆኑን አመላክተዋል።
Ethio Fm

ይህ ፍልሚያ የሩብ ፍጻሜ ወይንም የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ቢሆን እንዴት ባማረ ነበር ትሉ ይሆናል! ያም ሆኖ ግን ይህን ፈታኝ ጨዋታ መጫወት ግድ ይላል። ሳይባሪ ያቺን ኳስ ይስታታል ብዬ ቅንጣት ታክል አልተጠራጠርኩም። በከፍተኛ የራስ መተማመን የተሞላ፣ እጅግ ማራኪ የፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በእርግጥ በሽንፈታቸው ለኔዘርላንድስ ተጫዋቾች ልባቸው እንደሚሰበር አያጠራጥርም፤ ይሁን እንጂ ሞሮኮዎች ላሳዩት ድንቅ ጀግንነት ታላቅ ክብር እና አድናቆት ሊሰጣቸው ይገባል!
ሊሊ ሞግስ የዘ-ሐበሻ ስፖርት አዘጋጅ
ሊሊ ሞግስ የዘ-ሐበሻ ስፖርት አዘጋጅ
1 month ago
ባለውለታዋን እናት
ከ12 ዓመታት በኋላ የተገለጠ የደግነት ታሪክ
ብሩክታይት ሽመልስ ባለውለታዋን እናት አገኘች፤ የእንባና የምስጋና አፍታ
#ethiopia | አንዳንድ የሰው መልካምነት ከጊዜ ጋር አይረሳም፤ ዓመታት ቢያልፉም በሰው ልብ ውስጥ እንደ ብርሃን ይኖራል። በ"ሰይፉ በኢቢኤስ" ፕሮግራም ላይ የታየው የብሩክታይት ሽመልስ (ብርክቲ) እና የወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል መገናኘት የዚህ እውነት ሕያው ማሳያ ነው።
ያልተረሳ ውለታ
ከ12 ዓመታት በፊት፣ የ15 ዓመት ታዳጊ የነበረችው ብሩክታይት ከሐዋሳ ወጥታ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳለች ጭንቀትና ፍርሃት ውስጥ ገብታ ነበር። በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ሕይወቷን የቀየረች አንዲት ሴት አገኘቻት፤ ዛሬ የምትጠራት "ባለውለታዬ" ብላ ነው።
"ማን እንደላካት አላውቅም፤ እኔ ግን እግዚአብሔር የላከልኝ ሰው ነበረች ብዬ አምናለሁ" ስትል ብሩክታይት የዚያን ቀን ትዝታ በእንባ አስታወሰች።
አንዲት እናት... አንድ የሰብአዊነት ውሳኔ
ወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል በዚያ ዕለት ብሩክታይትን በአውቶቡስ ላይ አገኘቻት። የታዳጊዋ ጭንቀትና ፍርሃት በፊቷ ይነበብ ነበር።
ምሳ እንድትበላ ብትጋብዛትም እንባዋን ማቆም አልቻለችም። ወይዘሮ አዜብም ጉዳዩን በእርጋታ ለማወቅ ሞከረች፤ ከዚያም ወደ ቤቷ ወስዳ አሳረፈቻት፣ አረጋጋቻት፣ ከቤተሰቦቿም ጋር እንድትገናኝ አደረገች።
"እናትሽና አባትሽ በጣም ይጨነቃሉ፤ የምትፈልጊው ቦታ በሰላም ትደርሻለሽ" ብላ በፍቅር ያረጋጋቻትን ቀን ዛሬም በግልጽ ታስታውሳለች።
"ይህ የኢትዮጵያዊነት ባህል ነው"
ወይዘሮ አዜብ ያደረገችውን እንደ ልዩ ጀግንነት አትቆጥረውም። ይልቁንም እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ትገልጻለች።
"እኔ ልጅ ያለችኝ እናት ነኝ። ያንን ልጅ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢያገኛት እንደዚያው ያደርግላት ነበር። ይህ የባህላችንና የማንነታችን መገለጫ ነው" ብላለች።
የደግነት ዋጋ
በፕሮግራሙ ላይ የተፈጠረው መገናኘት የተመልካቾችን ልብ ነክቷል። ብሩክታይት ባለውለታዋን እናት አቅፋ ስታለቅስ፣ ወይዘሮ አዜብም በደስታ እንባ ታጠበች።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ የሰው መልካምነት አይጠፋም፣ አይረሳም። በአንድ አስቸጋሪ ወቅት የተዘራ የደግነት ዘር፣ ከዓመታት በኋላም በምስጋና፣ በክብርና በፍቅር ፍሬውን ያፈራል።
ወይዘሮ አዜብ የተናገረችው አንድ ሐረግ ደግሞ የዚህን ታሪክ ሙሉ ትርጉም ይገልጻል፦
"ለሰው ብትኖር ምንም አትጎዳም፤ በምድርም በሰማይም ዋጋውን ታገኛለህ።"

ጎል!... ሞሮኮ 0 - 1 ሄይቲ 12ኛ ደቂቃ | ኮሜንታተሩ ሲናገር... "ይህ ስታዲየም ከዚህ በፊት ሰምቼው በማላውቀው ሁኔታ በጩኸት እና በደስታ ተናውጧል። ለሌኒ ጆሴፍ እንዴት ያለች ድንቅ ግብ ናት! ለሄይቲም ቢሆን ምን አይነት ታሪካዊ ቅጽበት ነው! እዚህ አትላንታ ውስጥ ያልተገመተው ቡድን የጀግንነት ታሪክ እየተጻፈ ነው። ምነው በማያሚም ሁኔታው ተመሳሳይ በሆነ ኖሮ..."
በማያሚ ብራዚል ስኮትላንድን 1ለ0 እየመራች ነው።
በማያሚ ብራዚል ስኮትላንድን 1ለ0 እየመራች ነው።
1 month ago
የዓለም ትልቁ የጎል ማሽን ሃሪ ኬንን ከዜሮ ሜትር አድንዝዞት ያመሸው ጠንቋይ !
ከሁለት ቀናት በፊት ጋናዊው ጠንቋይ ናና ክዋኩ ቦንሳም "በሃሪ ኬን ላይ እየሰራሁ ነው። ከዚህ በፊት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሳይቻለሁ ስለዚህ እሱን ለማስቆም ምን አይነት ስራ መስራት እንዳለብኝ አውቃለሁ። ጋናን ለመርዳት ስራዬን እሰራለሁ።"ብሎ መናገሩን ግዮን ማለዳ ከቀናት በፊት አሳውቀን ነበር
የጋና "ጁጁ" ሰርቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም እጣኑም ፣ ጭሱም፣ አመዱም፣ ዱቄቱም፣ ጨሌውም… ምኑም አልቀረም፤ የዓለም ትልቁ የጎል ማሽን ሃሪ ኬንን ከዜሮ ሜትር ላይ አደንዝዞታል።
ጥቋቁሮቹ ክዋክብት (Black Stars) ግልፅ ፔናሊቲ ጭምር እየተከለከሉ፣ የእንpግሊዝን ክንድ ገትረው በመያዝ ነጥብ ተጋርተዋል።
ጋናዎች ግልፅ ፔናሊቲም ተከልክለዋል ። ካርሎስ ኬሮዥ የቀድሞው የፈርጊ ምክትል አንጋፋው አሰልጣኝ በቅርብ ግዜ የአቢዲ ፔሌ አንቶኒ የቦሃ ማይክል ኤሲየን ሱሊ ሙንታሪ ቶማስ ፓርቴ ሀገር ጋናን ይዘው በዓለም ዋንጫው ድንቅ አጀማመር አድርገዋል ።
ሃሪ ኬን በትናንትናው እለት አንድ ግልጽ የጎል እድል አግኝቶ በማይታመን ሁኔታ ሳይጠቀምበት ቀረ። ሃሪ ኬን በጨዋታው ላይ ጠፍቶ ነበር፤ በሚያስገርም ሁኔታ 19 ጊዜ ብቻ ኳስ ሲነካ የጋና ግብ ጠባቂ ቤንጃሚን አሳሬ ከሀሪ ኬን የበለጠ 31 ኳሶችን ነክቷል።
Black stars ከአሳማሆ ጂያን የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ የድል መንፈስ ማስታወሻ ጋር በጀግንነት በህብረት እንደ ቡድን የሚዋደቅ ሁኖ አምሽቷል ። የጋናዎች አፍዝ አደንግዝ ጁጁ ካገኘ የማይስተው ኮኮቡ ሃሪ ኬንን ከጎሉ አፋፍ ጫፍ አደንዝዟል ። Via፦ ጋዜጠኛ ኤፍሬም የማነ

ቁጥሮች ምን ያወራሉ?
***********
ቁጥሮች ዝም ብለው በወረቀት ላይ የሰፈሩ ደረቅ ሂሳቦች አይደሉም። ቁጥሮች ዝም አይሉም፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ያወራሉ! የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ቁጥሮች የኢትዮጵያን የልብ ትርታ፣ የሕዝቧን የነፃነት አየር ወደ ውስጥ የመሳብ ጉጉት እና የዲሞክራሲን ፅንሰት የሚያበስሩ ሕያው ምስክሮች ናቸው። ቁጥሮቹ የትናንቱን ፈተና አልፎ ለነገው ብሩህ ተስፋ የተነሳውን ሕዝብ የድል ጉዞ በትረካ መልክ አፍ አውጥተው ይናገራሉ።
እውነት ቁጥሮች ምን ያወራሉ? "ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወሰዱ" የሚለው አኃዝ፣ አንድ ታላቅና ጀግና ህዝብ የሀገሩን እጣ ፈንታ በገዛ እጁ ለመወሰን ያደረገውን ጽኑ የዜግነት ቃል ኪዳን በከፍተኛ ድምጽ ያወራል።
"ከ96.2 በመቶ በላይ የሚሆኑት መራጮች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን ሰጡ" ሲባል ደግሞ፣ ተስፋ ሳይቆርጥ፣ በፀሐይ ንዳድና በዝናብ ካፊያ ሳይበገር፣ በ1 ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች እና በ52 ሺህ ገደማ የምርጫ ጣቢያዎች በረጅም ሰልፍ ተሰልፎ ሀገሩን ያፀናውን ጀግና ሕዝብ ታሪክ ይተርካል።
ይህ ቁጥር የኢትዮጵያውያንን ፅኑዕ ፍላጎት፣ የማይበገር አገራዊ ፍቅር እና ሰላማዊ የትግል አውድማ ላይ የተቀዳጁትን አንጸባራቂ ድል የሚያንጸባርቅ የጀግንነት ሐውልት ነው። የህዝቡ ድምጽ የሀገርን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ ማህተም ሆኗል።
ቁጥሮች የመንግሥትን እጅግ ታላቅ የፖለቲካ ቁርጠኝነትም በጉልህ ይናገራሉ። 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 10,438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች የተወዳደሩበት አውድማ መፈጠሩ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ በሩን ወለል አድርጎ መክፈቱንና የዲሞክራሲ በር መገንጠሉን ያሳያል።
ከእነዚህ ውስጥ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 8 የግል ዕጩዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫን ማሸነፍ መቻላቸው፣ ከቃላት ያለፈ የተግባር ጀግንነት ማሳያ ነው። ብልጽግና ፓርቲ 438 መቀመጫዎችን ሲያገኝ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች 37 ወንበሮችን ማሸነፋቸው፣ ከመሸናነፍ የጠባብ ፖለቲካ ትርክት ወጥቶ በጋራ አብሮ ማሸነፍን የሰበከ፣ የብዙኃን ድምፅ የተከበረበት እውነተኛ የዲሞክራሲ ድል ነው።
ይህ የቁጥር ድምር መንግሥት ለብዝኃነት ያሳየውን ወደር የለሽ ክብርና ለሀገር ግንባታ የከፈለውን ፅኑ የተግባር ቁርጠኝነት በትክክል ይተርካል።
ወደ ታችኛው የሥልጣን እርከን ስንወርድም ቁጥሮቹ የድል ዜማቸውን በህብረ-ዜማ ያሰማሉ። በሐረሪ 99 በመቶ፣ በኦሮሚያ እና ሲዳማ 97 በመቶ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ 96 በመቶ፣ እንዲሁም በአማራ 95 በመቶ እና በሶማሌ 94 በመቶ የታየው ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ፣ ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከ ዳር በዲሞክራሲ ጎዳና ላይ በአንድ ልብ መቆማቸውን ያረጋግጣል።
በአዲስ አበባ 10 የተለያዩ ፓርቲዎች፣ በአማራ ክልል 9፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ 7 ፓርቲዎች በምክር ቤት መወከላቸው፣ ሀገራችን የብዝኃነት ውበት የደመቀባት፣ የተለያዩ ሀሳቦች አብረው የሚኖሩባት የጋራ ቤት መሆኗን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ስለዚህ፣ የዘንድሮው ምርጫ ቁጥሮች ዝም አይሉም፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ያወራሉ! ስለ ኢትዮጵያ የፀናች ሀገረ መንግሥትነት፣ ስለ መንግሥት ልባዊና ጥልቅ ቁርጠኝነት፣ እና ስለ ሕዝቡ ወደር የለሽ ሰላማዊ ጀግንነት በኩራት ይዘምራሉ። እነዚህ ቁጥሮች የህዝብን ድምፅ ወደ ውብ የዲሞክራሲ ዜማ የቀየሩ፣ የልዩነትን ግድግዳ አፍርሰው የአንድነትን ድልድይ የገነቡ ታሪካዊ ዐሻራዎች ናቸው።
በእርግጥም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ካርዱ ያጻፈው ይህ የቁጥር ትርክት፣ ለትውልድ የሚተላለፍ የድልና የጀግንነት ተውኔት ነው!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ዴሞክራሲ

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለውድድሩ ካለፉ ሀገራት ሁሉ እጅግ ትንሿ ሀገር የሆነችው ኩራሳዎ፣ ጠንካራዋን ኢኳዶርን ገድባ አቻ ማቆየት ችላለች። ግብ ጠባቂው ኢሎይ ሩም አክብሮታችን ይድረስህ! በጨዋታው ያዳናቸው የኳስ መጠኖች በእውነት እጅግ አስገራሚ ነበሩ። ይህ ታሪካዊ እና ትልቅ ውጤት ለኩራሳዎ ይገባታል።
በአንጻሩ ለኢኳዶር ይሄ ውጤት ልክ እንደ ትልቅ አደጋ ነው። የዛሬው ምሽት ሙሉ በሙሉ ስለ ኩራሳዎ ጀግንነት እና ስለተጎናጸፉት አስደናቂ ውጤት ብቻ የሚወራበት ነው። ኢኳዶር በቀጣይ ጨዋታዋ የምትገጥመው ሀያሏን ጀርመንን በመሆኑ፣ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ እጅግ ግድ ይላት ነበር። አሁን ከምድቡ ማለፍ ለእነሱ እጅግ ፈታኝ ሆኗል!
በእውነት የኩራሳዎው ግብ ጠባቂ ከዚህ በላይ ድካም እንዳይበዛበት አረፍ እንዲል ልመኝለት ወይስ የዓለም ዋንጫውን ኳስ የማዳን ክብረ ወሰን እንዲሰብር ልመኝለት? ግራ ገብቶኛል! አስቡት... በጨዋታው አስራ አምስት የተሞከሩበትን ኳሶች አድኗል፤ ክብረ ወሰኑን ለመስበር የሚቀረው አንድ ኳስ ማዳን ብቻ ነበር! ኢኳዶሮች ሙሉ ጨዋታውን በበላይነት ተጭነው ቢጫወቱም፣ የኩራሳዎን ድንቅ የተከላካይ መስመር እና ብርቱውን ግብ ጠባቂ ግን ሊያልፉት ፈጽሞ አልቻሉም። መገረም የሚችለው መገረም ብቻ ነው!
ኮራሳኦ በቀጣይ ጨዋታ አይቮሪ ኮስትን ታሸንፍ ይሆን?
ሊሊ ሞገስ የዘ-ሐበሻ ስፖርት አዘጋጅ

ዘመናትን የተሻገረ የታሪክ ባለቤትነቱ ዛሬም የቀጠለው አየር ኃይላችን
********************
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ለሕዝባዊ ኩራት ዋስትና ሆኖ የቆመ፣ ዘመናትን የተሻገረ የታሪክ እና የጀግንነት ማማ ነው።
"ሰማዩ የኛ ነው" የሚለው የአየር ኃይሉ መሪ ቃል መፈክር ብቻ ሳይሆን፣ በጀግኖች አብራሪዎች ደም እና አጥንት፣ በላቀ የአየር ላይ የበላይነት እንዲሁም ጥልቅ በሆነ የሀገር ፍቅር የተጻፈ እውነት ነው።
አንድ ክፍለ ዘመን የተጠጋ ዕድሜ ያለው የሰማዩ ንስር በአፍሪካ ሰማይ ሥር ያስመዘገበው ደማቅ ታሪክ፣ ሀገራችን ያጋጠሟትን የሕልውና አደጋዎች ሁሉ በድል እንድትወጣ አድርጓል።
በተለያዬ ጊዜ አኩሪ ገድል የፈጸመው አየር ኃይላችን፣ ዛሬ ላይ ዘመኑን የሚመጥን የላቀ አደረጃጀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ደርሷል።
አየር ኃይል የ1969 ዓ.ም ወረራ በቁጥር እና በዘመናዊነት የማይመጣጠን ትጥቅ ይዞ፣ በF-5E ተዋጊ ጄቶች የጠላትን 25 የጦር አውሮፕላኖች (MiG-17 እና MiG-21) በአየር ላይ በማስቀረት ፍጹም የበላይነትን ተቀዳጅቷል።
በዚህ ውጊያ እንደእነ ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ፣ ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ እና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ያሉ ጀግኖች ታሪክ ሠርተዋል።
የ1991-1993 ዓ.ም ጦርነት፦ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ Su-27 እና MiG-29 ፊት ለፊት በተፋለሙበት ውጊያ፣ የኢትዮጵያ Su-27 ተዋጊ ጄቶች የጠላትን አውሮፕላኖች እንደ ጉም በማትነን ሀገራችን የማትደፈር መሆኗን ዳግም አረጋግጠዋል።
"ኢትዮጵያ አሁን ሉዓላዊነቷ ላይ ትንኮሳ የሚሰነዝሩ ኃይሎችን በሰማይም ሆነ በምድር አሳድዳ የምትቀጣ ኃይል ሆናለች!" በሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ልክ፣ አየር ኃይሉ የተዋጊ ጄቶቹን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ ወደ 5ኛ ትውልድ (5th Gen) ቴክኖሎጂ ለመሸጋገር በትኩረት እየሠራ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #airforce

Comments