Logo
Getu Temesgen
የቃል ፌርማታ
#ethiopia | “መካከለኛው ትውልድ” የሽግግር ቀውስ፣ ተጠራጣሪነት እና የጎርባቾቭ አምሳያ፡- በያ ትውልድ እና በሚሊኒያልስ መካከል የተገኘውን የጄነሬሽን ኤክስ (Generation X) ወይም “መካከለኛው ትውልድ” ሥነ-ልቦናዊ መዋቅር፣ ተጠራጣሪነትና ተግባራዊነት ያሳያል።

ይህ ትውልድ የደርግን ዘመን ቀውስ፣ እርስ በእርስ መፋጀትንና ረሃብን አይቶ ስላደገ ለትልልቅ ርዕዮተ-ዓለሞች ጥላቻ ያለውና ውጤት ተኮር የሆነ ስብስብ ነው።

ለምሳሌ ደራሲ ቤተማርያም ተሾመ “ማይክ አቀባባዮች” ወይም “ቅልጥም ያመለጠው ትውልድ” ቢላቸውም፣ ጽሁፉ እንደሚያመላክተው መካከለኛው ትውልድ በዶክተር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ሥልጣን ይዞ “ማይኩን፣ ባንኩንም ታንኩንም” ተቆጣጥሯል፤ ነገር ግን በፖለቲካው መስክ እንደ ጎርባቾቭ ያለ የግላስኖስትና የፔሬስትሮይካ ሽግግር በመጀመራቸው ሀገሪቱን ግልጽ ፍኖት ወደሌለው መዋቅራዊ መላላትና ቀውስ አጋልጠዋታል።

ሚሊኒየሞቹ፡- ከ1981 እስከ 1996 (እ.ኤ.አ.) ከተወለዱትና “የዲጂታል ድልድይ” ወይም “ጀግና” (Hero) ተብለው ከሚጠሩት የጄነሬሽን ዋይ (Generation Y) “ዘጠናዎቹ” ትውልድ ባህሪ ጋር ይተዋወቃል። ይህ ትውልድ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የተሸጋገረ፣ በቡድን ሥራና በማኅበራዊ ንቃት የሚያምን፣ የኢሕአዴግን የልማታዊ መንግሥት ዘመን የተከታተለና የ2010ሩን የፖለቲካ ለውጥ በዋናነት የመራ ነው።

ለምሳሌ በጽሑፉ እንደተገለጸው፣ “ለውጥ ማምጣት እችላለሁ በሚል ‘ጀግንነት’ ሥርዓቱን ቢገፋና ቢፋለምም፤ ለውጡን አየር ላይ መካከለኞች (የጄነሬሽን ኤክስ) ትውልድ አስቀርቶ ቢቆረጥመውም፤ ቀጥሎም ከለውጡ ማግስት የመጣውን የሀገር መናጋትና ጦርነት ሲያይ ግን ዛሬ ላይ ወደ ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ (Cynicism) እና ሀገር ጥሎ የመሰደድ አባዜ ውስጥ የገባ ስብስብ ነው”። ይለዋል፡፡

ይህ ትውልድ (ሁለቱ ትውልዶች)፡- የአዲሱን የጄነሬሽን ዜድ (Gen Z) እና የአልፋዎችን ዲጂታል ተወላጅነት፣ የቲክቶክ ሥነ-ልቦና፣ እንዲሁም የፖለቲካዊ ፖፑሊዝምና የ“ሲሎቪኪ” (የኃይል ሰዎች) ናፍቆታቸውን ይተነትናል።

ይህ ትውልድ በዲሞክራሲ ስም በሚመጣ ውዥንብርና ተቋማዊ መላላት በመሰልቸቱ (Democratic Fatigue) ምክንያት፣ ሀገርን ሰጥ ለጥ አድርጎ የሚያቆም ጠንካራና አምባገነናዊ መሪን (Authoritarian Pragmatism) ይመኛል፤ ብሎ በምክንያት ኮንኖታል።

ለምሳሌ በጽሑፉ እንደተብራራው፣ ትውልዱ በሁለት ተጣራሽ ህልሞች የቆመ ሲሆን፤ በአንድ በኩል ተስፋ በመቁረጥ የ“ኤርትራን መስመር” (መገንጠል/የብሔር ጠርዝ) ሲያይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ “የባሕር በርን የሚያስመልስ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት በጉልበት የሚያስከብር፣ ወታደራዊና ቴክኖሎጂያዊ የበላይነትን የሚያውጅ ብርቱና ቆራጥ መሪ (ሲሎቪኪ) ይመኛል” ብሎታል።

ከመጣጥፎቹ እኛ ዘጠናዎቹ፣ ደራሲነት ማኅበራዊ መደብና የፈጠራ ሥነ-ልቡና፣ የአክሱምና የላሊበላ ወግ፣ ኢየሱስ ወልደ አብ፣ ጎዶሎው ዓድዋ ሉዓላዊነትና ሰዋዊ ክብር የየራሳቸው ሳፋፊ ጭብጥ ያላቸው ብዙ ሚያነጋግሩ ናቸው፡፡

አጫጭር ልቦለዶቹ ሳልነግስ አልሞትም፣ ሰበራ፣ የበሶው ውል፣ የኮሮናው ሰሞን፣ ለምን አትቆጣም? እና መካደም ወይ መጋደም በቃል ፌርማታ በምሳሌ ብዙ መብራራት ብዙ መተንተን የሚያስችሉ ናቸው፡፡

ወፍ እንደ ሀገሯ ትዘምራለች፤ ደራሲ ቃል ኪዳን ኃይሉ እንደ ዘመኑ ጦምሯል፤ አንብቡትና እንደ ዘመኑ እንወያይበት!!

የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.