ሀገራዊ ምክክር፡- ኢትዮጵያ የነገ መሠረቷን የምትጥልበት ታሪካዊ ጉዞ
************************
ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከምሁሩ እስከ አርሶ አደር፣ ከሸኽ እስከ ቄስ ከከተማው እስከ ገጠሩ ማኅበረሰብ ድረስ "አጀንዳችሁ ሀገርን ያቀናል፤ ብንመክርበት ለመግባባት መንገዳችን ይበጃል" በሚል እምነት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በመዲናዋ አዲስ አበባ ተመካካሪዎችን በማሰባሰብ የምክክር ጉባኤውን በይፋ ከጀመረ ቀናትን አስቆጥሯል።
የምክክሩ ሂደት ልዩነቶች እንደ ስጋት ሳይሆኑ፣ እንደ ሀገራዊ ፀጋና በረከት የሚታዩበትን አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማጎልበት ያለመ ነው። የተለያዩ ሐሳቦች በመደማመጥ ወደ ጋራ መግባባት የሚያመራ ሂደት እንዲጠናከርም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያን ከጥንት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ያካበቱት ታላቅ ጥበብ ቢኖር አለመግባባቶችን በውይይትና በሽምግልና የመፍታት ባህል ነው። ከዋርካ ሥር በመሰባሰብ ቅራኔዎችን ማለዘብ፣ በባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ስብራቶችን ጠግኖ ግንኙነቶችን ማደስ የዚህች ሀገር የቆየና የማይነጥፍ እሴት ነው።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የጀግንነት ድሎችንና የጥንካሬ ማረጋገጫዎችን እንዳስመዘገበች ሁሉ፣ ፈታኝ የሚባሉ ጊዜያትንም አሳልፋለች።
ያልተፈቱ የፖለቲካ ችግሮች፣ የታሪክ ቅሬታዎች እና የፍትሕ ጉድለቶች በሕዝቦች መካከል እንደ ዘመናት እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። እነዚህ ተግዳሮቶችም አንዳንዴ የግጭትና የመከፋፈል እሳትን እየለኮሱ የአለመግባባት መንፈስ እንዲነግስ አድርገዋል።
ዛሬ ግን ያንን የቁስልና የቅሬታ ምዕራፍ የመዝጊያው ጊዜ ደርሷል። ኢትዮጵያ ከአራቱም ማዕዘን ከተሰባሰቡ በልጆቿ ጥበብ ልዩነቶቿን በጠረጴዛ ዙሪያ ልትፈታ ቁጭ ብላለች።
የዚህ ሀገራዊ ምክክር መዳረሻ ግቡም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት፣ ለመጪው ትውልድ የተረጋጋች፣ ያደገችና የተባበረች ኢትዮጵያን ማስረከብ ነው።
ይህ ምክክር ከላይ የተጫነ ውሳኔ ሳይሆን፣ መነሻውን ከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ያደረገ ሕዝባዊ ሂደት ነው። ከወረዳ ጀምሮ የተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር፣ እያንዳንዱ ዜጋ የችግሩ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውም አካል መሆኑን ያረጋገጠ ነበር።
የብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ ብሶት፣ ጥያቄ እና የነገ ተስፋ በሂደቱ ውስጥ ተንጸባርቋል። እያንዳንዱ ዜጋም በሀገሩ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የራሱን ዐሻራ እንዲያሳርፍ ወርቃማ ዕድል ፈጥሯል።
ውስብስብ ችግሮችን በውይይት የመፍታት፣ ለዘመናት ሥር የሰደዱና ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮችን በመግባባት ለመቋጨት እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት፣ የኢትዮጵያን አዲስ አቅጣጫ ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን፣ ከመከፋፈል ይልቅ መግባባትንና አንድነትን የምትመርጥበት ታሪካዊና አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ይህ ምዕራፍ ደግሞ የነገዋን ሀገር በፅኑ መሠረት ላይ የመገንባት ታላቅ ጉዞ ነው።
በመቅደላዊት ደረጀ
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #nationbuilding #nationaldialogue

12 days ago