(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሕወሐት ሰሜን ዕዝን ሲመታ አዝዥ የነበሩት የአሁኑ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አዛዥ ጄኔራል ደሪባ መኮንን፣ የክልሉ ፖሊስ ከአፋር፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ መስማማቱን አስታወቁ። ጄኔራሉ ይህንን የገለጹት የፀጥታ ኃይሎቹ የቀጠናውን ደህንነት አስመልክቶ በጋራ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው።
በመንግስት በኩል "ሸኔ" ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) እና የፋኖ ታጣቂዎች የዘመቻው ዋነኛ ኢላማዎች መሆናቸውን ጄኔራሉ በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል። መንግስት እነዚህን ኃይሎች ሥርዓት ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሲል የሚፈርጃቸው ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ በድንበር አካባቢዎች ተጠልለዋል በሚል የሁለቱ ክልሎች ፀጥታ ኃይሎች የክልል ወሰን ሳይገድባቸው ድንበር ተሻግረው እርምጃ ለመውሰድ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ይህ "ድንበር የለሽ" የተባለ የጋራ ዘመቻ በተለይ በከሰም፣ ኮሎ፣ እና አዋሽ ሰባት አካባቢዎች እየሰፋ ነው የተባለውን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል።
አዛዡ አክለውም ታጣቂዎቹን በሎጂስቲክስ፣ በመሳሪያ እና በስንቅ ይደግፋሉ የተባሉ አካላትን ከህብረተሰቡ ነጥሎ ያለምህረት እርምጃ የመውሰድ ስራ መጀመሩን ጠቅሰዋል። ውይይቱ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ ኃይሎች የመረጃ ልውውጥ እንዲያጠናክሩና የጋራ ግብረ ኃይል ፈጥረው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በአፋር ክልል የሚገኙ እና በመንግስት የሚፈለጉ ግለሰቦችንም አሳልፎ ለመስጠት ከስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል። ይህ እንቅስቃሴ የሀገሪቱን ዋና የኢኮኖሚ መስመሮች፣ የባቡር ሀዲዶች እና እንደ አዋሽ ድልድይ ያሉ መሰረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ ገልጿል።
በሌላ በኩል ጄኔራል ደሪባ የሰራዊቱን ሞራል ለመገንባት በሚመስል መልኩ፣ ባለፈው ግንቦት ወር በምስራቅ ጉጂ ዞን አጋዋዩ ወረዳ በተደረገ ውጊያ ሳጅን ዳንኤል ፈይሳ የተባለ የፖሊስ አባል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታጣቂዎች ብቻውን በመቋቋም ህይወቱ ማለፉን በማንሳት፣ ለዚህም የአንደኛ ደረጃ የጀግንነት ሜዳሊያ እና የደረጃ እድገት እንደተሰጠው አውስተዋል።
ይሁን እንጂ የፀጥታ ኃይሎቹ ያቀዱት ይህ ዓይነቱ ድንበር ዘለል እና የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ቀድሞውንም በግጭት የተጎዳውን የቀጠናውን ማህበረሰብ ይበልጥ ወደ ከፋ ቀውስ እንዳያስገባው ስጋት አለ። ህብረተሰቡ ታጣቂዎችን እንዲያጋልጥና የምግብ አቅርቦት እንዲከለክል በመግለጫው ላይ ጥሪ ቢቀርብም፣ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ስለሚገኘው የንፁሀን ዜጎች ደህንነት አጠባበቅ እና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ በመንግስት ባለስልጣናቱ በኩል የተብራራ ነገር የለም።

21 days ago