3 months ago
"ሶስት ልጆች አሉኝ፤ ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጅ አሉኝ። አያትም ሆኛለሁ። የመጀመሪያዋ ሴት ልጄ ሁለት ቆንጆ ወንድ ልጆችን ወልዳለች። ወንድ ልጄም ተምሮ አሁን ሁለተኛ ዲግሪውን አጠናቅቆ በግል ስራው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ሁለቱም ተምረው የጨረሱት ልጆች በጣም ጎበዞች ናቸው። አሁን እኔን ይረዱኛል። እኔ (ጊዜ በማጣት ምክንያት) ማንበብ ያልቻልኩትን መጽሐፍ፣ እነሱ አንብበው ማጠቃለያውን በመጻፍ 'ይህ መረጃ እንደ አመራር ይጠቅምሻል፣ አንብቢው' ይሉኛል። እንዲህ ያለ ቤተሰብ አለኝ። ባለቤቴም በጣም ጥሩ እና የሚደግፈኝ ሰው ነው። ሶስተኛዋ ልጄ የአምስት ዓመት ልጅ ናት። እሷም አሁን በፈጣሪ እርዳታ እየደረሰች ነው።"
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢቢሲ ኦሮሚኛ ጋር ባደረጉት ቃለምልል

5 months ago
የቤተክርስቲያን ትምህርት በኦሮሚኛ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ታግዞ ሊሰጥ ነው #ethiopia | የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ (ማኅበረ ፍኖተ አበው) ጋር በመሆን፣ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትን በኦሮሚኛ ቋንቋ በርቀትና በኢ-ለርኒንግ (Online) ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ብሉይና ሐዲስ) እና የቤተክርስቲያን ታሪክን ያካተቱ 5 መጻሕፍት በኦሮሚኛ ቋንቋ ተዘጋጅተዋል።
ትምህርቱ በመጽሐፍ (ርቀት) እና በቴክኖሎጂ የታገዘ በይነ-መረብ (ኢ-ለርኒንግ) አማራጮች የቀረበ ሲሆን፣ ማንኛውም ምእመን ባለበት ቦታ ሆኖ በኢንተርኔት መማር ይችላል።
የርቀት ትምህርቱ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የኢ-ለርኒንግ ትምህርቱ ደግሞ በተማሪው ፍጥነት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊጠናቀቅ ይችላል።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአራት ኪሎ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መሠረተ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ብጹዓን አባቶችና እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይመረቃል።
ይህ አገልግሎት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በቋንቋና በአካባቢ ሳይገደብ ለምእመናን ለማድረስ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ በምርቃቱ ዕለት የሚዲያ አካላት፣ ባለሀብቶችና ምእመናን በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #ethiopia #orthodoxtewahedo #oromiffaministry #elearning #distanceeducation #amdehaymanot #woldadandiaboti #gospelexpansion #addisababa #መንፈሳዊትምህርት #ኦሮሚኛ #ኢለርኒንግ #ተዋሕዶ #ቅዱስገብርኤል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

11 months ago
የፋናው ጋዜጠኛ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን ላይ ያስተላለፈው መልዕክት በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ቅሬታን ፈጠረ።
ጋዜጠኛ ኡጋሳ ፉፋ የተባለው የፋና ጋዜጠኛ በፌስቡክ ገጹ የመስቀል በዓልን አስታኮ በኦሮሚኛ ያስተላለፈው መልዕክት "እኛ የእስራኤል እና ለአረብ አምላክ..." በማለት የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን የዘለፈበት መንገድ አንድ ትልቅ የሀገሪቱ ሚዲያ ውስጥ ከሚሰራ ጋዜጠኛ የሚጠበቅ አመለካከት አይደለም እንደዚህ አይነት ነውር ይዞ እንዴት በተቋሙ ሊሰራ ቻለ ያስባለ ሆኗል።
ከፍተኛ ተቋሞ ሲገጥመው የለቀቀውን ፖስት አንስቶታል።
ፋና ትናንት የመስቀል ደመራ በዓል በሚከበርበት እለት በፌስቡክ ገጹ የለቀቀውን የኢሬቻ ፖስተር ከደረሰበት ተቋሞ በኋላ አንስቶታል።

ዓይኖቻችን በቀይ ባህር ላይ፣ ልባችን ደግሞ በአሰብ ላይ ነው። ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ከባድ ፈተናዎችን እንዳለፍነው ሁሉ፣ ህጋዊ የባህር መብታችንንም እናስመልሳለን።
የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከቀይ ባህር ጋር የተቆራኘ ነው፤ ሉዓላዊነቱን እና ብልጽግናውን ለማረጋገጥ የቆረጠን የተባበረ ህዝብ ፍላጎት ሊሰብረው የሚችል ምንም ኃይል የለም።"
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ፣ ከፕራይም ሚዲያ ጋር በኦሮሚኛ ቋንቋ ካደረጉት ቃለምልልስ።
Seledadotio

1 year ago
ወንጌላዊ ኦኔስሞስ ነሲብና ዳግማዊ ምኒልክ፣
(ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በእንግሊዝኛ እንደጻፉት፣ ሲሣይ ተፈራ መኮንን ወደ አማርኛ እንደተረጎመው)
#ethiopia | እንደ ልጅ ልጃቸው አቶ ኢዶሳ ገመቺስ ከሆነ ኦኔስሞስ ነሲብ የተወለዱት በኢሉባቦር ሁርሙ በሚባለው አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 1842 ዓ.ም ነው፡፡ የኦኔስሞስ ነሲብ የልጅነት ስማቸው ሂቃ ሲሆን ሂቃ ማለትም በኦሮምኛ ፈቺው ወይም ተርጓሚው እንደማለት ነው፡፡ ወላጆቻቸው እንደትንቢት ሂቃ ብለው የሰየሟቸው ኦኔስመስ፣ ልክ እንደስማቸው የመጀመሪያውን የመጽሀፍ ቅዱስ የኦሮሚኛ ትርጉም በማዘጋጀታቸው ታረክ ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡
የሂቃ የልጅነት ጊዜ አሳዛኝ ነበር፡፡ አባታቸው በ4 አመት እድሜያቸው እንደሞቱ ሂቃ በባሪያ ፈንጋዮች ታፍነው ተወሰዱ፡፡ ጠረፍ እስከሚደርሱ ድረስም በተለያዩ ጌቶች ስር በባርነት አድረዋል፡፡ አንዳንዶች ሂቃ ነጻ ከመውጣታቸው በፊት 4 ጊዜ በባርነት እንደተሸጡ ሲጽፉ ሌሎች ደግሞ የተሸጡበትን ጊዜ 8 ያደርሱታል፡፡ በመጨረሻም ምጽዋ ላይ በነበረው የፈረንሳይ ቆንሲል ዌርነር ሙዚንገር አማካኝነት ሂቃ ከባርነት ነጻ ወጥተዋል፡፡
ዌርነር ሙዚንገር በጥቅምት ወር 1863 ዓ.ም ከባርነት ነጻ የወጡትን ሂቃ ለስዊድናውያን ሚሲዮኖች ያስረከቡ ሲሆን የሂቃም ህይወት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዘላቂነት መለወጥ ጀመረ፡፡ በመጋቢት ወር 1864 ዓ.ም የፋሲካ ቀን ዋና ጠባቂ ሆነው በተመደቡላቸው ሉንድሃል አማካኝነት ሂቃ ኦኔስሞስ በሚል አዲስ ስም እንዲጠመቁ ተደረገ፡፡
ኦኔስሞስ ነሲብ በ1868 ዓ.ም ወደ ስዊድን የተላኩ ሲሆን በዛም ለ5 አመት ያህል ሃይማኖታዊ ትምርት ተከታትለዋል፡፡ ከስዊድን እንደተመለሱም የአጼ ቴዎድሮስ የቀድሞ ጸሀፊና የስዊድን ሚሽን ት/ቤት መምህር የነበሩትን የጎጃሙን አለቃ ኃይሉ ልጅ ምህረት ሐይሉን አገቡ፡፡ ከዚህ በኋላም ከንቲባ ገብሩ አቅደው ከፍጻሜ ያላደረሱትን መጽሀፍ ቅዱስን ለኦሮሞ ህዝብ የማስተማር እቅድ በትውልድ አካባቢያቸው ለመፈጸም ሂቃ ወደዛው ለመጓዝ ወሰኑ፡፡
ነገር ግን አጼ ዮሀንስ የሚሲዮናውያንን እንቅስቃሴ አግደው ስለነበር፣ ኦኔስሞስ ወደ ወለጋ ለመጓዝ በቅድሚያ በቀይ ባህር ቀዝፈው ሱአኪን ወደምትባለው የሱዳን ወደብ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ ከሱዳን ግዛት ወደ በርበር ካቋረጡ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጠረፍ ወደ ሚያደርሰው አባይ በመጓዝ በታህሳስ ወር 1875 ዓ.ም ፋማካ ተብላ ወደምትጠራው የጠረፍ ከተማ ደረሱ፡፡ ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ ጠረፍ ማቋረጥ ከጀመሩ በኋላ ችግር እንዳለ በመስማታቸው ለመመለስ ተገደዱ፡፡
የመጀመሪያው ሙከራ ከከሸፈ ከ3 አመት በኋላ በ1878 ዓ.ም ኦኔስሞስ በታጁራና ሸዋ አድርገው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ለመጓዝ ያደረጉት ጥረትም ንጉሥ ምኒልክ አስቀድመው የሰጡትን ተስፋ በሚጻረር መልኩ የሸዋ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ማቴዎስ ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ውጤት አልባ ሆነ፡፡ በትውልድ አካባቢያቸው በአካል በመገኘት የወንጌልን ት/ት ለማስፋፋት በተደጋጋሚ ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ያዘኑት ኦኔስሞስ ነሲብ መጽሀፍ ቅዱስን የትውልድ አካባቢያቸው ህዝብ በሚገባው የኦሮምኛ ቋንቋ ለመተርጎም ወሰኑ፡፡
የ4 አመት ህጻን ሆኖ የትውልድ አካባቢውን ለለቀቀ ሰው መጽሀፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ መተርጎም ቀላል ባይሆንም፣ ኦኔስሞስ አስቴር ጋኖ በተባሉ የሊሙ ኦሮሞ ወዳጃቸው እየታገዙ የትርጉም ስራቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም ኦኔስሞስ አዲስ ኪዳንን እና ብሉይ ኪዳንን በቅደም ተከተል በ1885 ዓ.ም እና በ1891 ዓ.ም ወደ ኦሮምኛ በመተርጎም የትርጉም ስራቸውን አጠናቀቁ፡፡ የትርጉም ስራቸውን ለማከናወን በዋነኛነት የተጠቀሙት የአማርኛውን መጽሀፍ ቅዱስ ሲሆን በስዊድን ቋንቋ የተዘጋጀውን መጽሀፍ ቅዱስ ደግሞ ለማመሳከሪያነት ተጠቅመዋል፡፡
የመጀመሪያ ሚስታቸው ወ/ሮ ምህረት ከሞቱ ጥቂት አመታት በኋላ ኦኔስሞስ ሊዲያ ዲምቦ የተባሉትን የወለጋ ሲዮ አካባቢ ተወላጅ አገቡ፡፡ በአስመራ ከተማ ይገኙ ለነበሩ ወደ 500 የሚጠጉ የኦሮሞ ኮሚኒቲ አባላትም የወንጌል ትምህርትን ማስተማር ጀመሩ፡፡ ይህም የትውልድ አካባቢያቸውን ህዝብ በአካል በማስተማር ውጤታማ ስራ ከመስራታቸው በፊት በመፈጸሙ በጎ መንደርደሪያ ሆነላቸው፡፡
በ1885 ዓ.ም ኦኔስሞስ ሚስታቸውን፣ 3 ልጆቻቸውንና አዲስ ሰራተኞቻቸውን በመያዝ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ተጓዙ፡፡ በአዲስ አበባም በከንቲባ ገብሩ አማካኝነት ኦኔስሞስ ከዳግማዊ ምኒልክና ከአቡነ ማታዎስ ጋር ተገናኙ፡፡ ኦኔስሞስም ለዳግማዊ ምኒልክ የተረጎሙትን የኦሮምኛ መጽሀፍ ቅዱስ ኮፒ በስጦታ አበረከቱ፡፡ በመጨረሻም ኦኔስሞስ በሚጓዙበት ሁሉ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚያዘውን የዳግማዊ ምኒልክ ደብዳቤ ታጥቀው ወደ ወለጋ ተጓዙ፡፡
በወለጋ እንደደረሱም በደጃዝማች ገብረ እግዚአብሔር ሞሮዳ/ኩምሳ ሞሮዳ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ኦኔስሞስ ለመጓዝ ያሰቡት ወደ ትውልድ አካባቢቸው ኢሉባቦር የነበረ ቢሆንም በዳ/ምኒልክና በደጃ/ኩምሳ ሞረዳ በተደረላቸው የክብር አቀባበል ምክንያት ወንጌላዊ ስራቸውን በወለጋ ጀመሩ፡፡ ነጆ አካባቢ በምትገኘው ቦጂ ለኦኔስሞስ መሬት የተሰጣቸው ሲሆን በዛም የማስተማር ስራቸውን ጀመሩ፡፡
የኦኔስሞስን ሃይማኖታዊ ትምህርት በአደጋነት የተመለከቱ የኦርቶዶክስ አባቶች ባቀረቡት ክስ ምክንያት ኦኔስሞስ ወደ አዲስ አበባ ከተጠሩ በኋላ በአቡነ ማቴዎስ የእስራት ፍርድ ተፈረደባቸው፡፡ ነገር ግን ዳግማዊ ምኒልክ የአቡኑን ፍርድ ባለመቀበል ጉዳዩ በድጋሚ በአፈ ንጉሥ ኢስጢፋኖስ እንዲመረመር አዘዙ፡፡ በዚሁ መሰረት አፈ ንጉሡ ጉዳዩን በድጋሚ መርምረው ኦኔስሞስን ከቀረበባቸው ክስ በነጻ አሰናበቱ፡፡
ዳግማዊ ምኒልክ ከዚህም አልፈው ለኦኔስሞስ በንግድ ሚኒስቴር ስራ እንዲሰጣቸው አዘው የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩት ሹማምንት ኦኔስሞስ በንግድ ጉዳይ ለመስራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት የላቸውም በሚል የምኒልክን ትዕዛዝ ሳይፈጽሙ ቀርተዋል፡፡ ኦኔስሞስ ነሲብ ወደ ወለጋ ተመልሰው በተለይም ከልጅ ኢያሱ ዘመን ጀምሮ በነጻነት ሲያስተምሩ ከቆዩ በኋላ በሰኔ ወር 1923 ዓ.ም በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ነፍስ ይማር!
ምንጭ፣ Pioneers of Change in Ethiopia: The Reformist Intellectuals of the Early 20th Century, Prof Bahru Zewde, PP.46-49
ምስል፦ ኦኔስሞስ ነሲብ ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ኤርትራ ውስጥ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው፡፡ ፎቶው የመቼ እንደሆነ አልተገለጸም። #jemal_abdulaziz

ሆ በሸነና
📌ባጋጣሚ ተቀርጾ መነጋገሪያ የሆነው "ሆ በሸነና" የቦረና የባህል ሙዚቃ
#ethiopia | በአጋጣሚ በስልክ ተቀርጾ የተለቀቀው "በሸነና" የተሰኘው ኦሮሚኛ ሙዚቃ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሆኗል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ 'ቫይራል' በሆነው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ይህን የሕዝብ ዜማ ሲጫወተው የሚታየው ወጣት ሊበን ጃርሶ፤ በሸነናን ሲጫወቱ የሚያሳየው ምስል ከተለቀቀ በኃላ በብዙዎች ተወዳጅነት ማግኘቱን ይገልጻል።
ይህን ዜማ በሰርግ እና በተለያዩ የደስታ ጊዜዎች ማህበረሰቡ የሚጫወተው ሲሆን፤ ይህንኑ ዜማ በራሱ ግጥም እንየዘፈነ እንደነበር ነው ሊበን ጃርሶ ለኢቲቪ የተናገረው።
መልዕክቱም ደስታ እና ሀሴት ለሁሉም ይገባል ነው ሲልም የሙዚቃውን ይዘት ገልጾታል።
ዘፈኑ ስለ ደስታ የሚገልጽ ሲሆን ከተለያየ ቦታዎች የሚመጡ እንግዶች ሰብሰብ ብለው የሚጫወቱት እንደሆነም ነው ያነሳው።
በአጋጣሚ የተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በብዙዎች ተወዳጅነት ማግኘቱም እንዳስደሰተው ይናገራል።
ወጣት ሊበን ጃርሶ ሙዚቀኛ የመሆን ፍላጎት እንዳለውም የገለጸ ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያበረታታኝ እና ድጋፉ እንዳይለየኝ” ስል እጠይቃለሁ ብሏል።
በሜሮን ንብረት

Sponsored by
Surafel
Comments