ሆ በሸነና
📌ባጋጣሚ ተቀርጾ መነጋገሪያ የሆነው "ሆ በሸነና" የቦረና የባህል ሙዚቃ
#ethiopia | በአጋጣሚ በስልክ ተቀርጾ የተለቀቀው "በሸነና" የተሰኘው ኦሮሚኛ ሙዚቃ ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሆኗል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ 'ቫይራል' በሆነው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ይህን የሕዝብ ዜማ ሲጫወተው የሚታየው ወጣት ሊበን ጃርሶ፤ በሸነናን ሲጫወቱ የሚያሳየው ምስል ከተለቀቀ በኃላ በብዙዎች ተወዳጅነት ማግኘቱን ይገልጻል።
ይህን ዜማ በሰርግ እና በተለያዩ የደስታ ጊዜዎች ማህበረሰቡ የሚጫወተው ሲሆን፤ ይህንኑ ዜማ በራሱ ግጥም እንየዘፈነ እንደነበር ነው ሊበን ጃርሶ ለኢቲቪ የተናገረው።
መልዕክቱም ደስታ እና ሀሴት ለሁሉም ይገባል ነው ሲልም የሙዚቃውን ይዘት ገልጾታል።
ዘፈኑ ስለ ደስታ የሚገልጽ ሲሆን ከተለያየ ቦታዎች የሚመጡ እንግዶች ሰብሰብ ብለው የሚጫወቱት እንደሆነም ነው ያነሳው።
በአጋጣሚ የተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በብዙዎች ተወዳጅነት ማግኘቱም እንዳስደሰተው ይናገራል።
ወጣት ሊበን ጃርሶ ሙዚቀኛ የመሆን ፍላጎት እንዳለውም የገለጸ ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያበረታታኝ እና ድጋፉ እንዳይለየኝ” ስል እጠይቃለሁ ብሏል።
በሜሮን ንብረት

1 year ago