3 months ago
የቤተክርስቲያን ትምህርት በኦሮሚኛ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ታግዞ ሊሰጥ ነው #ethiopia | የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ (ማኅበረ ፍኖተ አበው) ጋር በመሆን፣ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትን በኦሮሚኛ ቋንቋ በርቀትና በኢ-ለርኒንግ (Online) ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ብሉይና ሐዲስ) እና የቤተክርስቲያን ታሪክን ያካተቱ 5 መጻሕፍት በኦሮሚኛ ቋንቋ ተዘጋጅተዋል።
ትምህርቱ በመጽሐፍ (ርቀት) እና በቴክኖሎጂ የታገዘ በይነ-መረብ (ኢ-ለርኒንግ) አማራጮች የቀረበ ሲሆን፣ ማንኛውም ምእመን ባለበት ቦታ ሆኖ በኢንተርኔት መማር ይችላል።
የርቀት ትምህርቱ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የኢ-ለርኒንግ ትምህርቱ ደግሞ በተማሪው ፍጥነት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊጠናቀቅ ይችላል።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአራት ኪሎ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መሠረተ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ብጹዓን አባቶችና እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይመረቃል።
ይህ አገልግሎት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በቋንቋና በአካባቢ ሳይገደብ ለምእመናን ለማድረስ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ በምርቃቱ ዕለት የሚዲያ አካላት፣ ባለሀብቶችና ምእመናን በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #ethiopia #orthodoxtewahedo #oromiffaministry #elearning #distanceeducation #amdehaymanot #woldadandiaboti #gospelexpansion #addisababa #መንፈሳዊትምህርት #ኦሮሚኛ #ኢለርኒንግ #ተዋሕዶ #ቅዱስገብርኤል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments