Logo
Getu Temesgen
የቤተክርስቲያን ትምህርት በኦሮሚኛ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ታግዞ ሊሰጥ ነው #ethiopia | ​የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ (ማኅበረ ፍኖተ አበው) ጋር በመሆን፣ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትን በኦሮሚኛ ቋንቋ በርቀትና በኢ-ለርኒንግ (Online) ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
​
ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ብሉይና ሐዲስ) እና የቤተክርስቲያን ታሪክን ያካተቱ 5 መጻሕፍት በኦሮሚኛ ቋንቋ ተዘጋጅተዋል።
​
ትምህርቱ በመጽሐፍ (ርቀት) እና በቴክኖሎጂ የታገዘ በይነ-መረብ (ኢ-ለርኒንግ) አማራጮች የቀረበ ሲሆን፣ ማንኛውም ምእመን ባለበት ቦታ ሆኖ በኢንተርኔት መማር ይችላል።
​
የርቀት ትምህርቱ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የኢ-ለርኒንግ ትምህርቱ ደግሞ በተማሪው ፍጥነት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊጠናቀቅ ይችላል።
​
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአራት ኪሎ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መሠረተ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ብጹዓን አባቶችና እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይመረቃል።

​ይህ አገልግሎት የቤተክርስቲያንን ትምህርት በቋንቋና በአካባቢ ሳይገደብ ለምእመናን ለማድረስ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ በምርቃቱ ዕለት የሚዲያ አካላት፣ ባለሀብቶችና ምእመናን በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።

​#getu #ethiopia #orthodoxtewahedo #oromiffaministry #elearning #distanceeducation #amdehaymanot #woldadandiaboti #gospelexpansion #addisababa #መንፈሳዊትምህርት #ኦሮሚኛ #ኢለርኒንግ #ተዋሕዶ #ቅዱስገብርኤል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.